No summary available.
ሐምል 22 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ማስረሻ ገሰሱ ተጠሪ፡- የፋ/ዐ/ሕግ ወይን ገ/እግዚአብሓር መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ አመልካች ላይ በፋ/ከፍ/ፍ/ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው። የክሱ ይዘት በክስ 1. ተከሳሽ የወ/ህ/አ 543(3) የተመለከተውን በመተላለፍ ሲያሽከረክሩት የነበረው ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና የመጫን አቅሙ 132 ኩንታል ሆኖ እያለ 200 ኩንታል ሲሚንቶ ጭኖበት ከአዱሱ ገበያ ወደ ሰሜን ሆቴል አቅጣጫ ያለጥንቃቄ በቂ ርቀት ሳይጠበቅ ሲያሽከረክር ከፉት ለፉቱ በተመሳሳይ አቅጣጫ ሲሽከረከር የነበረውን ኤፍ ኤስ አር መኪና በሃይል ከፉት ለፉት አካለ በመግጨት ወደ ቀኝ ከመንገድ ውጪ እንዱወጣ ካደረገ በኋላ አልፍ በመሄድ ሚኒባስ መኪና ገጭቶ መንገድ ዲር ላይ ቆመው ከነበሩ ላዲዎች ጋር በማጋጨት ሟች ጥሩ ደምሴ፣ ገነት ጽጌን እና ቄስ በቀለ ደምሴ ሕይወታቸው እንዱያልፍ በማድረጉ በፈጸመው በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ተከሷል።
በክስ 2. የወ/ሕ/ቁ. 559(2) የተመለከተውን በመተላለፍ በክስ 1. በተጠቀሰው አኳኋን ተከሳሽ መኪኖችን ገጭቶ በማገጫጨት በእግረኛ መንገድ ላይ የነበረችውን ወ/ሪት ሄለን አበባን በፉት ለፉት አካለ በመግጨት ከላይኛው መንጋጋዋ ላይ 2 ጥርሶችንና ከታችኛው መንጋጋዋ አንድ ጥርስ እንዱወልቅ በማድረጉ፤
በክስ 3. የወ/ሕ/ቁ. 559(2) የተመለከተውን በመተላለፍ በክስ 1. በተጠቀሰው አኳኋን ተከሳሽ መኪኖችን ገጭቶ በመገጫጨት የሰ/ቁ. 3-12333 ኦሮ ሚኒባስ መኪና ውስጥ ተሳፊሪ የነበረችውን ወ/ሪት አስቴር ከፉት የዲላ አጥንት ስብራት እንዱደርስባት ያደረገ በመሆኑ በፈጸመው በቸልተኝነት የአካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ተከሷል።
በክስ 4. የወ/ሕ/ቁ. 572(1) የተመለከተውን በመተላለፍ በክስ 1. በተጠቀሰው አኳኋን ኤፍ.ኤስ.አር መኪና ገጭቶ ከመንገድ ወጥቶ ከላላ መኪና እና ሱቅ ጋር በማጋጨት ብር 45,000 የሚገመት ጉዲት እንዱደርስ ያደረገ በመሆኑ በፈጸመው የትራፉክ ደንብ በመጣስ በንብረት ላይ ጉዲት ማድረስ ወንጀል ተከሷል የሚል ነው። ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) በአራቱም ክሶች ላይ የተመለከቱትን የወንጀል ድርጊቶችን መፈጸማቸውንና ጥፊተኛ መሆናቸውን በማመናቸው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 134(1) መሰረት ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ በአራቱም ክሶች የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል። በመቀጠልም የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት መዝገብ በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 መሰረት በማስላት በየክሶቹ አራት የማቅለያ ምክንያቶችን ወስድ በክስ 1.
ተከሳሽ በ 3 አመት ከ 3 ወር እስራት እና በብር 2000 የገንዘብ ቅጣት በክስ 2 ተከሳሽ በ 2 ወር እስራት እና በብር 1000 የገንዘብ ቅጣት በክስ 3 ተከሳሽ በ 3 ወር እስራት እና በብር 1000 የገንዘብ ቅጣት በክስ 4 አፈጻጸሙን ዝቅተኛ በማድረግ በ 3 አመት ከ 10 ወር እስራት አና በብር 500 የገንዘብ መቀጮ በድምሩ በ 3 አመት ከ 10 ወር እስራት እና በብር 5000 የገንዘብ ቅጣት ተከሳሽ እንዱቀጡ ወስኗል። ቅጣቱም በገደብ እንዱቆይ ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ የቅጣት ውሳኔ ላይ ቅሬታውን ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱ ግራቀኙን አከራክሮ የተደራራቢ ወንጀልች ቅጣት አወሳሰንን በተመለከተ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 184(1)(ለ) ለእያንዲንደ በተደራራቢነት ለተፈጸመ ወንጀል ተገቢ ቅጣት ተወስኖ እንደሚደመር ያስረዲል።
የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 አንቀጽ 22 (1(ሀ) እና 23(5) የተደራራቢ ወንጀልች ቅጣት አወሳሰን የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 184(1)(ለ) የተከተለ ሆኖ ወደ ቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያዎች ከመግባቱ በፉት የእያንዲንደ ወንጀል መነሻ ቅጣት ተደምሮ ድምሩ የሚያርፍበት ዝቅተኛው የእስራት ቅጣት እርከን ተለይቶ መያዝ እንዲለበት ይገልጻል። የስር ፍ/ቤት በዚህ አግባብ ሳይሆን በእያንዲንደ ወንጀል የእስራት ቅጣት እርከን ላይ የቅጣት ማቅለያዎችን በመጠቀም በተናጠል በየክሱ ቅጣቱን በማቅለል የወሰነው ከህጉ ውጭና መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ክስ 1. ደረጃ 2 እርከን 21 የገንዘብ መቀጮ ደግሞ እርከን 6 ይሆናል። መ/ሰጪ የ 3 ሰዎች ሕይወት እንዱጠፊ ስላደረገ መነሻ ቅጣት 6 ዓመት ጽኑ እስራት በክስ 2 በወንጀለ ድርጊት የግል ተበዲይ 3 ጥርሶች የወለቁ በመሆኑ ወንጀለ ደረጃ 3 እርከን 9 የገንዘብ መቀጫ እርከን 3 ይሆናል። 1 አመት ከ 6 ወር እስራት ወደ ጽኑ እስራት ሲለወጥ በ 9 ወር ጽኑ እስራት መነሻ ቅጣት በክስ 3 መነሻ ቅጣት ደረጃ 1 እርከን 7 ላይ የእስራት ቅጣቱን ወደ ጽኑ እስራት በመለወጥ በ 7 ወር ጽኑ እስራት በክስ 4 የእስራት ቅጣቱን ወደ ጽኑ እስራት በመለወጥ በ 3 ወር ጽኑ እስራት መነሻ ቅጣት በመወሰን የአራቱንም ተደራራቢ ወንጀልችን መነሻ ቅጣት በመደመር 7 አመት ከ 7 ወር ጽኑ እስራት መነሻ ቅጣት ይዞ በአራት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች መነሻ ቅጣቱ ካረፈበት እርከን 24 ወደ እርከን 20 ዝቅ በማድረግ መ/ሰጪ (የስር ተከሳሽ) ለፈጸመው ወንጀል በ 5 አመት ከ 4 ወር ጽኑ እስራት እና በብር 7,000 የገንዘብ ቅጣት እንዱቀጣ በመወሰን የስር ፍ/ቤትን የቅጣት ገደብ ውሳኔ በማንሳት መ/ሰጪ የጽኑ እስራት ቅጣቱን እንዱፈጽም የስር ፍ/ቤትን የቅጣት ውሳኔ በማሻሻል ወስኗል።
አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በዚህ ውሳኔ ላይ ተፈጸመ ያለትን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ለማሳረም ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮ የጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ገደብን አስመልክቶ ይግባኝ ባልተባለበት ቅጣት ማቅለያዎችን ከተቀበለ በኋላ የመጨረሻውን 5 አመት ከ 4 ወር በማሳደግ መወሰኑ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194(2)(ሐ) እና ከቅጣት አወሳሰን መርህ አንጻር ለመመርመር ሲባል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል። አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ አቤቱታው እንዱመረመር ከተያዘው ጭብጥ አንጻር የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመ መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪ አመልካች ላይ በፋ/ከፍ/ፍ/ቤት አራት የወንጀል ክሶችን ያቀረበ ሲሆን አመልካች የተከሰሱባቸውን አራቱም ክሶች ላይ የተመለከተውን ወንጀል መፈጸማቸውን በማመናቸው ፍ/ቤቱ በአራቱም ክሶች ላይ የጥፊተኝነት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ቅጣት ሲወሰን በወ/ሕ/አንቀጽ 184(1(ለ) እና በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 አንቀጽ 21(1)(ሀ) መሰረት ለእያንዲንደ ወንጀል መነሻ ቅጣት በመወሰን እና መነሻ ቅጣቶቹን በመደመር ድምሩ የቅጣት መጠን የሚያርፍበትን ዝቅተኛ የቅጣት እርከን በመምረጥ ለይቶ በመቀጠል ወደ ቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ምክንያቶችን በማገናዘብ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት ተገቢ ነው የሚለው ቅጣት መወሰን ሲገባው አመልካች ላይ የጥፊተኝነት ውሳኔ በተሰጠባቸው አራት ወንጀልች በእያንዲንደ ወንጀል በተናጠል አራት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን በመውሰድ ቅጣት ወስኗል። የአሁን ተጠሪ በዚህ የስር ፍ/ቤት ቅጣት አወሳሰን ቅሬታውን ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ የስር ከፍ/ፍ/ቤት የቅጣት አወሳሰን የወንጀል ሕጉን እና የቅጣት አወሳሰን መመሪያውን የተከተለ ባለመሆኑ በማረም በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 መሰረት ለአራቱ ወንጀልች በተናጠል መነሻ ቅጣት ወስኖ በመደመር ድምሩ የሚያርፍበትን ዝቅተኛ እርከን ከለየ በኋላ ለአመልካች ለስር ፍ/ቤት የተያዘላቸውን 4 ማቅለያ ምክንያቶች ወስድ በእርከን 20 ከተመለከተው የቅጣት ፍቅድ ስልጣን በ 5 አመት ከ 4 ወር ጽኑ እስራት እና በብር 7,000 የገንዘብ ቅጣት እንዱቀጡ እና የተሻሻለው የቅጣት ውሳኔ ከ 5 አመት በላይ ጽኑ እስራት በመሆኑ አመልካች የቅጣት ውሳኔውን በማ/ቤት ሆነው እንዱከታተለ የሰጠው ውሳኔ የወ/ሕጉን አንቀጽ 184(1(ለ) ፣ 194(1)ለ) እና የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 አንቀጽ 21 (1(ሀ) እና 23(5) መሰረት ያደረገ ነው። አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ተጠሪ ለስር ፍ/ቤት ባቀረበው ይግባኝ የስር ፍ/ቤት ቅጣት አሰላል ላይ የተፈጸመው ግድፈት ይታረምልኝ አለ እንጂ ቅጣቱ ከፍ ተደርጎ ይወሰንልኝ አላለም ያለ ቢሆንም ተጠሪ ለስር ፍ/ቤት ባቀረበው አቤቱታ የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት 4 ማቅለያ ምክንያቶችን ከወንጀል ሕጉ እና ከቅጣት አወሳሰን መመሪያው ውጭ በመደጋገም ለእያንዲንደ ወንጀል በመጠቀም ቅጣት መወሰኑ ተገቢ አይደለም። በክስ 2 ደረጃ እና እርከን አለአግባብ ተይዟል በአራቱም ክሶች ላይ የተፈጸመው የቅጣት አሰላል ግድፈት ይስተካከልን በማለት ያቀረበውን ቅሬታ ተከትል ከፍ ሲል እንደተገለጸው በወንጀል ህጉ እና በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት የፋ/ጠ/ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት የፋ/ከፍ/ፍ/ቤትን የቅጣት ውሳኔ በማረም መወሰኑ በይግባኝ ከተጠየቀው ዲኝነት ውጭ ወስኗል የሚያስብል ሆኖ አላገኘነውም።
ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ይግባኝ አቤቱታ ግራቀኙን አከራክሮ የስር ፋ/ከፍ/ፍ/ቤትን የቅጣት አወሳሰን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 184(1)(ለ) እና በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ. 2/2006 አንቀጽ 21(1) (ሀ) እና 23(5) መሰረት በማረም መወሰኑ እና አመልካች ላይ የተወሰነው ቅጣት ከ 5 አመት ጽኑ እስራት በላይ በመሆኑ በወ/ሕጉ አንቀጽ 194(1)(ለ) መሰረት የስር ፍ/ቤትን የቅጣት ገደብ ውሳኔ በማንሳት አመልካች የተወሰነባቸውን 5 አመት ከ 4 ወር ጽኑ እስራት በማ/ቤት ሆነው እንዱፈጸሙ የሰጠው የቅጣት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ባለመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
የፋ/ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 107679 በቀን 19/10/2007 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 195(2)(መ) መሰረት ጸንቷል።
መዝገቡ ተዘጋ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.