በእምነት ማጉደል ወንጀል ላይ የተቀመጠው ያልተገባ ጥቅም የማዋል ሒሳብ መርሕ ፤ ለከባድ እምነት ማጉደል ወንጀልም ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ ፤ ወ/ሕ/ቁ 675(3) እና 676 (2) (ሀ) XXVIII
No summary available.
ሐምል 21 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ንጉሴ አሉ አስፊው -ጠበቃ አወል ሰይድ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ -ሰላማዊት ወንድሙ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተከሰሱት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 676 (2) (ሀ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል አድርገዋል ተብለው ነው።የወንጀለ አፈጻጸምም አመልካቹ በን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ በቀበላ 15 የላፍቶ ቁጥር 1 ኮንድሚኒየም ባለቤቶች ኃላፉነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ውስጥ በዋና ገንዘብ ያዥነት በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ተመርጠው ሲሰሩ ከአባላቱ ከተሰበሰበው ገንዘብ ብር 823,617.00 ውስጥ ብር 749,997.00 ብቻ በማህበሩ ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ገቢ አድርገው ልዩነቱን ብር 73,620.00 ገቢ ሳያደርጉ አጉድለው ተገኝተዋል ተብለው ሲሆን ያቀረቡት መቃወሚያ በብይን ታልፍ የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ ወንጀለን አላደረኩም በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ሶስት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ከሰማ እና የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኃላ አመልካቹ መከላከያቸውን ማሰማት እንዱጀምሩ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 142 (1) በሰጠው ብይን መሰረት ሶስት የመከላከያ ምስክሮችን አሰምተዋል። የተለያዩ ሰነድችን በማስረጃነት አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በተጠሪ ማስረጃ የተመሰከረባቸውን ፍሬ ነገር በመከላከያቸው አላስተባበለም በማለት በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር በመዝገብ በ24/06/2007 ዓ.ም. የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል።ቀጥልም የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት መዝግቦ ቅጣቱን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 መሰረት በማስላት የጥፊተኛነት ውሳኔው በተመሰረተበት ድንጋጌ ስር ከተመለከተው የቀላል እና የጽኑ እስራት ቅጣት አማራጭ መካከል ተገቢ ሆኖ የተገኘው የጽኑ እስራት ቅጣት መሆኑን፣ወንጀለ በመካከለኛ ደረጃ የተመደበ መሆኑን፣መነሻ ተደርጎ የተያዘው አራት ዓመት ሆኖ ይህ የቅጣት መጠን የሚወድቀው በአባሪ አንድ በእርከን 19 ስር መሆኑን፣የአመልካቹ የቀድሞ የዘወትር ፀባይ መልካምነት፣የቤተሰብ አስተዲዲሪነት እና የጤና ችግር በሶስት የማቅለያ ምክንያትነት ሲያዙ ቅጣቱ በስድስት እርከን ዝቅ ብል በእርከን 13 ስር የሚሸፈን መሆኑን ገልጾ አመልካቹ በሁለት ዓመት ከሶስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጡ በ01/07/2007 ዓ.ም. ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካቹ አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን በመዝገብ በ16/10/2007 ዓ.ም. ዘግቶ በማሰናበቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ ዐቃቤ ሕግ ተፈጻሚነት ያለው አዋጅ የህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/1991 ስለሆነ በወንጀል ሕጉ ክስ መቅረብ የለበትም፣ክሴን አንስቻለሁ እያለ ፍርድ ቤቱ በክርክሩ ቀጥል ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም፣ይህ ቢታለፍ የእምነት ማጉደል ወንጀል ስለማድረጌ አንድም ኦዱተር ቀርቦ አላረጋገጠም በማለት በአመልካች የቀረበውን አቤቱታ ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዲዩ ከተያዘው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የስር ፍርድ ቤት አቤቱታ የቀረበበትን የጥፊተኝነት ውሳኔ የሰጠው አመልካች ወንጀለን አላደረኩም ቢለም ከአባላት የሰበሰቡት እና ባንክ ያስገቡት የገንዘብ መጠን ሲቀናነስ መጠኑ በክሱ የተጠቀሰው ገንዘብ በጉድለት የተገኘባቸው መሆኑ በተጠሪው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠ ሆኖ ሳለ አመልካቹ ያቀረቡት መከላከያ የተጠሪውን ማስረጃ ለማስተባበል ያልቻለ መሆኑን በመግለጽ ሲሆን ፍሬ ነገርን በማጣራት እና ማስረጃን በመመዘን ረገድ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተደረሰበት ድምዲሜ ተመሳሳይ ስልጣን ባለው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ተቀባይነት አግኝቷል።አመልካች በሰበር አቤቱታቸውም ቢሆን የህብረት ስራ ማህበራት የሂሳብ ምርመራ አዋጅ ቁጥር 147/1991 ‛ን“ በሚያስፈጽመው አካል ካልሆነ በቀር በማህበሩ በራሱም ሆነ በልላ አካል ኦዱት ላደረግ አይችልም ከማለት በቀር የተገኘባቸው ጉድለት ስላለመኖሩ ያቀረቡት ክርክር የለም።አዋጁ አመልካቹ የሚለት ዓይነት ትርጉም ያለው ስለመሆኑ አመልካች ጠቅሰው የሚከራከሩባቸው የአዋጁ ድንጋጌዎች አያመለክቱም።በማህበሩ የውስጥ ኦዱተርም ሆነ ሂሳቡን እንደገና ባጣራው ገለልተኛ ኦዱተር የተገኘው ጉድለት ተመሳሳይ ስለመሆኑም የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
ተከሳሹ ሲጠየቅ በእምነት ወይም በአደራ የተሰጠውን ዕቃ ወይም ጥሬ ገንዘብ ለመመለስ ወይም ለመክፈል ወይም ዕቃው ያለበትን ሁኔታ ለማሳየት ወይም ለተገቢው አገልግልት ያዋለው መሆኑን ለማስረዲት ካልቻለ ንብረቱን ለራሱ ወይም ለላላ ሰው ያልተገባ ጥቅም የማዋል ሃሳብ እንዲለው የሚቆጠር ስለመሆኑ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 675 (3) የተመለከተው መርህ አመልካቹ ጥፊተኛ ለተባለበት ድንጋጌም ተፈጻሚነት ያለው ነው።አመልካች በእጃቸው እንደገባ በተጠሪ ማስረጃ የተረጋገጠውን ገንዘብ በዚህ ድንጋጌ አነጋገር መሰረት ለመመለስ ወይም ለመክፈል ወይም ዕቃው ያለበትን ሁኔታ ለማሳየት ወይም ለተገቢው አገልግልት ያዋለ መሆኑን ለማስረዲት እንዲልቻለ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ በተከከሱበት ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ መባላቸው የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
በልላ በኩል ተጠሪ ክሱን አንስቶ እያለ ፍርድ ቤቱ በራሱ ክርክሩን ቀጥል ውሳኔ ሰጥቶብኛል በማለት አመልካች በሰበር አቤቱታቸው የተከራከሩ ቢሆንም ይህ ስለመሆኑ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም።ይልቁንም መዝገቡ የሚያረጋግጠው ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ክሱ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የቅጣት ውሳኔ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ የክርክሩ አካል የነበረ መሆኑን ነው።በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ክሴን አንስቻለሁ በማለት የገለጸበት ጊዜ እንዲልነበረም ተጠሪው አሁን በሰበር መልሱ አረጋግጧል። በመሆኑም ተጠሪው በስር ፍርድ ቤት ክሱ ቢነሳ አልቃወምም ብሎል በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።አመልካች በጥፊተኝነት ውሳኔው ላይ ካልሆነ በቀር በቅጣት ውሳኔው ላይ ያቀረቡት የቅሬታ ነጥብ ካለመኖሩም በላይ የቅጣት ውሳኔውም የተሰላው አና የተወሰነው ሕጉን እና አግባብነት ያለውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በማድረግ በመሆኑ የቅጣት ውሳኔው የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
እና በ01/07/2007 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ16/10/2007 ዓ.ም. የጸናው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 195 (2) (ለ) (2) መሰረት ፀንቷል።
እንዱያውቁት የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች እና አመልካቹ ለሚገኙበት አዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ይላክ።ለአመልካቹም በዚያው በኩል ይድረስ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.