ከአንድ የወንጀል ድርጊት በኃላ ተከታትል የተፈፀመ ድርጊት ፤አንድን ወንጀል ከግብ ለማድረስ ሲል ተከታትል የተደረገ ድርጊት ከቀድሞ አሳቡና ሉደርስበት ከቀደው ግብ ጋር የተያያዘ በዋናው ወንጀል የሚጠቃለል ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ የሚጣራበት አግባብ፤ ዓ/ሕግ ባስከፈተው የይግባኝ መዝገብ ላይ መ/ሰጭ ሕግን መሰረት አድርጎ የሚቀርበው ክርክር ተቀባይት ሉያጣ የማይገባው ሰለመሆኑ፤ ወ/ሕ/ቁ 88(3)
No summary available.
ሐምል 20 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ደጀኔ መኮንን ሀብተማርያም - ጠበቃ በሬሳ በየነ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከሰሱት ከላልች ተከሳሾች ጋር በመሆን በ1ኛ ክስ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) እና 453 (1) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ሀሰተኛ ምስክርነት የመስጠት ወንጀል አድርገዋል፤በ2ኛ ክስ ደግሞ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) እና 375 (ሀ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ሀሰተኛ ሰነድ የመፍጠር ወንጀል አድርገዋል ተብለው ነው።
የወንጀልቹ አፈጻጸምም በ1ኛ ክስ ሟች አቶ ተፈሪ በቀለ ምንም ዓይነት ኑዛዜ ሳያደርጉ አመልካቹ በ16/04/1999 ዓ.ም. አዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው ሟች ለስር 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ዕፀገነት ተፈራ ጥቅም በ27/11/1998 ዓ.ም. ኑዛዜ አድርገዋል፣ኑዛዜው ሟች እየተናገሩ በልላ ሰው የተጻፈ ነው፣ለሟችም ሆነ ለምስክሮች ተነቧል፣ኑዛዜ ሲያደርጉ አንደበታቸውም ሆነ ሕሉናቸው ትክክል ነበር በማለት ሀሰተኛ ምስክርነት ሰጥተዋል የሚል ሲሆን በ2ኛ ክስ ደግሞ ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ሳይኖር ያለ አስመስለው ላልች ተከሳሾች ባዘጋጁት የኑዛዜ ሰነድ ላይ በምስክርነት በመፈረማቸው ሀሰተኛ ሰነድ ፈጥረዋል የሚል መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካቹ ያቀረቡት መቃወሚያ በብይን ታልፍ የእምነት ክደት ቃል ሲጠየቁ ድርጊቶቹን መፈጸማቸውን፣ይሁን እንጂ የፈጸሙት ሀሰተኛ ምስክርነት ለመስጠት አስበው ሳይሆን የኑዛዜው ተጠቃሚ ናቸው ከተባለት የስር 1ኛ ተከሳሽ ባለቤት ጋር በአንድ መስሪያ ቤት ስለሚሰሩ በእኒሁ የስራ ባልደረባቸው የተነገራቸውን ነገር እውነት እንደሆነ አድርገው በመቀበል ነው የሚል ቃል በማስመዝገባቸው ፍርድ ቤቱ አመልካቹ ክደው እንደተከራከሩ መዝገቦ የዐቃቤ ሕግን አንድ ምስክር ከሰማ እና የሰነድ ማስረጃ ከተቀበለ በኃላ ተጠሪው በክሱ መሰረት ያስረዲባቸው መሆኑን ገልጾ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 142 (1) መሰረት መከላከያቸውን ማሰማት እንዱጀምሩ ብይን የሰጠ ቢሆንም የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደማይችለ በመግለጻቸው በስር 1ኛ ተከሳሽ በኩል የቀረበውን የሰው እና የሰነድ የመከላከያ ማስረጃ ከተቀበለ በኃላ በተከሳሾቹ ላይ በሁለቱም ክሶች በክሱ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች ስር በመዝገብ በ17/08/2006 ዓ.ም. የጥፊተኛነት ውሳኔ ሰጥቷል።
ቀጥልም የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት መዝግቦ ቅጣቱን በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማስላት የጥፊተኛነት ውሳኔው በተመሰረተባቸው ድንጋጌዎች ስር ከተመለከተው የቀላል እና የጽኑ እስራት ቅጣት አማራጭ መካከል ተገቢ ሆኖ የተገኘው የጽኑ እስራት ቅጣቱ መሆኑን፣የወንጀልቹ ደረጃ በዝቅተኛ ደረጃ የተመደበ መሆኑን፣በ1ኛ ክስ ለተመለከተው ወንጀል መነሻ ተደርጎ የተያዘው አንድ ዓመት ከስድስት ወር መሆኑን፣በ2ኛ ክስ ለተመለከተው ወንጀል መነሻ ተደርጎ የተያዘው ሁለት ዓመት መሆኑን፣ይህ የቅጣት መጠን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 184 (1) (ለ) መሰረት ሲደመር ሶስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት ሆኖ በእርከን 16 ስር የሚወድቅ መሆኑን፣ወንጀለ ተደራራቢ በመሆኑ በመመሪያው አንቀጽ 22 (1) (ሀ) መሰረት በአንድ ማክበጃ ወደ እርከን 17 ከፍ የሚል መሆኑን፣ወንጀለ የተደረገው በግብረአበርነት በመሆኑ ቅጣቱ በአንቀጽ 84 (1) (መ) መሰረት እንዱከብድ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የላለው መሆኑን፣የአመልካቹ የዘወትር ፀባይ መልካምነት፣ የቤተሰብ አስተዲዲሪነት እና በመንግስት እና በማህበራዊ ተቋማት የሰጡት ረዥም አገልግልት እንደቅደም ተከተላቸው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 82 (1) (ሀ)፣82 (1) (ሰ) እና 86 ድንጋጌዎች መሰረት በሶስት የማቅለያ ምክንያትነት ሲያዙ እርከኑ ወደ 14 ዝቅ የሚል መሆኑን ገልጾ አመልካቹ በሁለት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ሆኖ ነገር ግን የቤተሰብ ኃላፉ እና የልጆች አባት መሆናቸውን፣በርካታ አገልግልት ፈጽመው በጡረታ ላይ የሚገኙ እና ዕድሜአቸውም ከ70 ዓመት በላይ መሆኑን በምክንያትነት በማስፈር የተወሰነባቸው የእስራት ቅጣት በአንቀጽ 192 ድንጋጌ መሰረት በሁለት ዓመት የፈተና ጊዜ ከመፈጸም ታግድ እንዱቆይ በ15/09/2006 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት በስር 1ኛ ተከሳሽ እና በአመልካች ላይ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ ሳቢያ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ከክብደቱ እና ከአፈጻጸሙ አንጻር የወንጀለ ደረጃ ሉመደብ የሚገባው በመካከለኛ ደረጃ ሆኖ ሳለ በስር ፍርድ ቤት በዝቅተኛ ደረጃ የተመደበው አላግባብ መሆኑን፣በ1ኛ ክስ ለተመለከተው ወንጀል መነሻ ተደርጎ የተያዘው ሁለት ዓመት ከሁለት ወር መሆኑን፣በ2ኛ ክስ ለተመለከተው ወንጀል መነሻ ተደርጎ የተያዘው አራት ዓመት መሆኑን፣ይህ የቅጣት መጠን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 184 (1) (ለ) መሰረት ሲደመር ስድስት ዓመት ከሁለት ወር ጽኑ እስራት ሆኖ በእርከን 22 ስር የሚወድቅ መሆኑን፣ወንጀለ ተደራራቢ ነው በሚል የስር ፍርድ ቤት የመመሪያውን አንቀጽ 22 (1) (ሀ) ጠቅሶ ቅጣቱን ማክበደ ሕጋዊ መሰረት የላለው መሆኑን፣የስር ፍርድ ቤት አንድ የማቅለያ ምክንያት የሚያስቀንሰው አንድ እርከን ብቻ እንደሆነ አድርጎ የወሰነ በመሆኑ ምክንያት አመልካች ለእያንዲንደ የማቅለያ ምክንያት ሁለት እርከን እንዱቀነስላቸው በዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ላይ ያቀረቡት ጥያቄ ስነ ስርዓታዊ አለመሆኑን፣በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ባገኙት ሶስት የማቅለያ ምክንያቶች ቅጣቱ ከእርከን 22 ወደ እርከን 19 ዝቅ የሚል መሆኑን እና የቅጣት ገደብን አስመልክቶ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 197 (1) ከተመለከቱት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ለግል ተበዲይ ከፍለዋል የተባለ ካሳ ባለመኖሩ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው የገደብ ውሳኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ገልጾ ውሳኔውን በማሻሻል አመልካች በአራት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጡ እና ቅጣቱንም በማረሚያ ቤት ሆነው እንዱፈጽሙ በመዝገብ በ01/02/2008 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች በሁለቱ ክሶች ጥፊተኛ የመባላቸውን አግባብነት ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 61 (3) ድንጋጌ አንጻር፣እንዱሁም ለቅጣቱ አወሳሰን መሰረት ተደርጎ መያዝ የሚገባው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ነው ወይስ ቁጥር 2/2006 ነው? የሚለትን ነጥቦች ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም፡-
አመልካቹ በሁለቱም የወንጀል ክሶች ጥፊተኛ የተባለት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም?
ቅጣቱ ሉሻሻል ይገባል ወይስ አይገባም?
የሚለትን ነጥቦች መሰረት በማድረግ ጉዲዩን መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ አመልካቹ ወንጀልቹን ማድረጋቸውን ያልካደ ከመሆኑም በላይ ሟች አቶ ተፈሪ በቀለ ከመሞታቸው በፉት በነበረባቸው ሕመም ምክንያት መናገርም ሆነ መጻፍ የማይችለ የነበረ መሆኑ፣ሟች ያደረጉት ነው በተባለው ኑዛዜ ላይ ከስማቸው ትይዩ የተመለከተው ፊርማም የእርሳቸው አለመሆኑ በፍረንሲክ ምርመራ የተረጋገጠ መሆኑ፣የስር 1ኛ ተከሳሽ ይህንኑ ኑዛዜ ለፍርድ ቤት አቅርበው በአመልካች ምስክርነት ጭምር በሀሰት ተናዛዡ አባታቸው እንደሆኑ በመግለጽ የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ ከወሰደ በኃላ የሟች ንብረት የነበረውን ቤት የሸጡ መሆኑ፣የግል ተበዲይ ናቸው በተባለት የዐቃቤ ሕግ ምስክር አቤቱታ አቅራቢነት ኑዛዜውም ሆነ የኑዛዜ የወራሽነት ማስረጃው በፍርድ ቤት እንዱሰረዝ የተደረገ መሆኑ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን እና ይህንኑ ማሰረጃ ለማስተባበል አመልካቹ የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ ያልቻለ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 61 (3) ድንጋጌ ተጠቅሶ የተያዘውን ጭብጥ በተመለከተ ድንጋጌው ለአንድ ጥፊት አንድ ቅጣት መሆኑን የሚደነግግ ሆኖ የንዐስ ቁጥር (3) ድንጋጌም አድራጊው የተወሰነ ወንጀል ለማድረግ አሳብ አለው ተብል በሚገመትበት ጊዜ በተለይም የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት በንብረት ላይ ወንጀል አድርጎ እንደሆነ ወይም የሐሰት ገንዘብ ሰርቶ እንደሆነ ወይም ይህንኑ ገንዘብ እንዱዘዋወር አድርጎ እንደሆነ ወይም ሀሰተኛ ሰነድ ሰርቶ ተጠቅሞበት እንደሆነ የመጀመሪያውን የጥፊት ዓላማውን ከግቡ ለማድረስ ሲል መሰረታዊ ከሆነው ወንጀል በኃላ አከታትል ያደረገው ድርጊት ከቀድሞ ሃሳቡና ሉደርስበት ካቀደው ግቡ ጋር የተያያዘ ሆኖ በዋናው ወንጀል እንደሚጠቃለል የሚደነግግ ነው።የዚህ ንዐስ ቁጥር ድንጋጌ ዓላማ እና ይዘት የሀሰት ገንዘብ የሰራ አንድ ሰው ገንዘቡ እንዱዘዋወር ካላደረገ በቀር ወይም ሀሰተኛ ሰነድ የሰራ ሰው ካልተጠቀመበት በቀር በወንጀለ ያቀደውን ዓላማ ከግቡ ሉያደርስ የማይችል በመሆኑ ምክንያት ተከታትለው የተፈጸሙት አድራጎቶች በአንድ የወንጀል ማድረግ ሀሳብ እንደተፈጸሙ ተቆጥረው በዋናው ወንጀል እንደሚጠቃለለ እና አድራጊው የሚጠየቀው በአንድ ወንጀል መሆኑን የሚያመለክት ነው።በተያዘው ጉዲይ ሐሰተኛ ሰነድ የመፍጠሩ ወንጀል አስቀድሞ ከተጠናቀቀ እና ፍጻሜ ካገኘ በኃላ አመልካች በፍርድ ቤት ቀርበው ሟች ኑዛዜ ሲያደርጉ በምስክርነት ተገኝተው ማየታቸውን እና መስማታቸውን በማረጋገጥ የሀሰት ምስክርነት መስጠታቸው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 63 ድንጋጌ አነጋገር መሰረት በሁለቱ ወንጀልች ተጠያቂነትን የሚያስከትል ከሚሆን በስተቀር በአንቀጽ 61 (3) ድንጋጌ አነጋገር መሰረት በአንድ ወንጀል የሚጠቃለል ነው ልባል የሚችል ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም አመልካቹን በሁለቱም የወንጀል ክሶች ጥፊተኛ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ አመልካቹ ወንጀልቹን ያደረጉት በ16/04/1999 ዓ.ም. ሲሆን የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ የተሰጠባቸው ደግሞ እንደቅደም ተከተለ በ17/08/2006 ዓ.ም.
እና በ15/09/2006 ዓ.ም. ነው።ይህንኑ ጊዜ መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች ቅጣቱ የተሰላውም ከጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በስራ ላይ የዋለውን የተሻሻለውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በማድረግ ነው።የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በተሰጠበት ጊዜ በስራ ላይ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ይልቅ ለተከሳሽ ወገን ቅጣቱን የሚያቀለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ከሆነ ለቅጣቱ አወሳሰን መሰረት ተደርጎ መያዝ የሚገባው ይኸው መመሪያ ስለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ እና በላልችም መዝገቦች በሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ለቅጣቱ አወሳሰን መሰረት ተደርጎ መያዝ የሚገባው የቀድሞው መመሪያ መሆኑን ተገንዝበናል።ይግባኙን የተመለከተው ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡትን ክርክር ሳይቀበል የቀረው አመልካቹ የዚህ ዓይነት ክርክር ዐቃቤ ሕግ ባስከፈተው መዝገብ ላይ ማቅረብ አይችለም በማለት ነው። በመሰረቱ አመልካች በስር የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በተሰጠባቸው የጥፊተኝነት፣የቅጣት እና የገደብ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ካልነበራቸው ይግባኝ የሚለበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖራቸውም። ክርክሩ የወንጀል እንደመሆኑ መጠን ዐቃቤ ሕግ ባስከፈተው የይግባኝ መዝገብ ላይ ሕጉ የሚሰጣቸውን መብት መሰረት አድርገው የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የሚያጣበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ፍርድ ቤቱ እጅግ ቀላል ከሆነው ቅጣት አንስቶ እስከ ከባደ ድረስ ያለውን በጥንቃቄ በመመርመር ለእያንዲንደ ጉዲይ ተገቢ የሆነውን ቅጣት እንደሚወስን በወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 88 (3) የተመለከተው ድንጋጌም ሆነ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው በቅጣት አወሳሰን መመሪያ የተካተቱት ድንጋጌዎች ይህንኑ የሚያመለክቱ ናቸው።በመሆኑም ዐቃቤ ሕግ ባስከፈተው የይግባኝ መዝገብ ላይ ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ አስመልክቶ አመልካች ያቀረቡት ክርክር ስነ ስርዓታዊ አይደለም በማለት በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተያዘው አቋም ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ከላይ በተገለጸው ሁኔታ ለሁለቱ ወንጀልች መነሻ ተደርጎ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተያዘው ቅጣት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 184 (1) (ለ) መሰረት ሲደመር ስድስት ዓመት ከሁለት ወር ጽኑ እስራት ሆኖ በእርከን 22 ስር የሚወድቅ ሲሆን ይህ የቅጣት መጠን በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ባገኙት ሶስት የማቅለያ ምክንያቶች በቀድሞው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በእያንዲንደ የማቅለያ ምክንያት በሁለት እርከን ዝቅ ሲደረግ ከእርከን 22 ወደ እርከን 16 ዝቅ የሚል በመሆኑ በአመልካቹ ላይ ለሚጣለው ቅጣት መነሻ ተደርጎ መያዝ የሚገባው በእርከን 16 ስር የተመለከተው የቅጣት ፍቅድ ስልጣን ነው።
ሲጠቃለል በአመልካቹ ላይ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ያልተቻለ በመሆኑ እና ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች በአመልካቹ ላይ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጥል የነበረው የቅጣት መጠን ግን ሉሻሻል የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በአመልካቹ ላይ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱም ክሶች በመዝገብ በ17/08/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ01/02/2008 ዓ.ም. በፍርድ የጸናው የጥፊተኝነት ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 195 (2) (ለ) (2) መሰረት ፀንቷል።
በአመልካቹ ላይ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ01/02/2008 ዓ.ም. የተሰጠውን የአራት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 195 (2) (ለ) (2) መሰረት በማሻሻል አመልካቹ በዚህ ጉዲይ የታሰሩበት ጊዜ ሁለ ታስቦላቸው በሶስት ዓመት ከሶስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ወስነናል።
በተሻሻለው የጽኑ እስራት ቅጣት ውሳኔ መሰረት እንዱያስፈጽም የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ከመሸኛ ትዕዛዝ ጋር አመልካቹ ለሚገኙበት የአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ይላክ።
ለአመልካቹም በዚያው በኩል ይድረስ።
እንዱያውቁት የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይላክ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።