የወንጀል ጉዲዮችን በመጀመሪያ ደረጃ ይሁን በይግባኝ ደረጃ የሚመለከት ፍ/ቤት ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ የማስረጃውን አጭር መግለጫ፣ ማስረጃውን የተቀበለበትን የአ/ብ/ክ/መ/ፍትህ ቢሮ እና እነ አቶ ሕሉና ሀይላ XXVII ያልተቀበለበትን ምክንያቶች በፍርድ ላይ ማስፈር የሚገባው ስለመሆኑ፣ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 149/1/ (ሦስት ሰዎች)
No summary available.
መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- የሐረሪ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትሕ ቢሮ ዐቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም ተጠሪዎች፡-
በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው የሐረሪ ክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሶስቱም ተጠሪዎች ላይ በወንጀል ሕግ ቁጥር 555 (ሐ) ስር በመዝገብ እንደቅደም ተከተለ በ24/11/2006 ዓ.ም. እና በ29/11/2006 ዓ.ም. የሰጠባቸውን የጥፊተኛነት እና የእስራት ቅጣት ውሳኔ በከፉል ሽሮ እና በከፉል ደግሞ አሻሽል 1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎችን በነጻ በማሰናበት እና 2ኛ ተጠሪን በተመለከተ ደግሞ ድንጋጌውን ወደ 557 (1) (ሐ) ለውጦ በብር 2,000 እንዱቀጡ በማለት የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ13/05/2007 ዓ.ም የሰጠው እና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ24/08/2007 ዓ.ም በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
አመልካች በክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪዎቹ ላይ ያቀረበው ክስ ይዘት ባጭሩ፡ተከሳሾቹ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና 555 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በሰው አካል ላይ ጉዲት ለማድረስ አስበው በ19/03/2006 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ በሐረር ከተማ ቀበላ 10 ክልል ልዩ ስሙ ሥላሴ ሐይቴክ ትምህርት ቤት አካባቢ ገ/መስቀል ገ/ሥላሴ የተባለውን የግል ተበዲይ ተባብረው ፉቱን እና አፍንጫውን በቦክስ በመምታት፣መላ ሰውነቱን በመደብደብ፣በአፍንጫው ላይ የአጥንት ስብራት ጉዲት፣በግራና በቀኝ ፉቱ ላይ የእብጠት፣በቀኝ አይኑ እና በቀኝ ጆሮው መካከል እብጠትና የመላላጥ ጉዲት እንዱደርስ በማድረጋቸው በሰው አካል ላይ ከባድ ጉዲት የማድረስ ወንጀል አድርገዋል የሚል ሲሆን ተጠሪዎቹ ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ ተደርጎ የእምነት ክደት ቃል ሲጠየቁ ወንጀለን አላደረግንም በማለታቸው አመልካች እንደክሱ ያስረደልኛል በማለት ከቆጠራቸው ሰባት ምስክሮች መካከል የግል ተበዲይን ጨምሮ ስድስቱን አቅርቦ ያሰማ መሆኑን እና አንደ ምስክር በአድራሻቸው አልተገኙም በመባለ በምርመራ ጊዜ ለፖሉስ የሰጡት ምስክርነት ከመዝገቡ ጋር እንዱያያዝ የተደረገ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።ፍርድ ቤቱ የምስክሮቹን ቃል እና አመልካቹ በሰነድ ማስረጃነት ያቀረበውን የሀኪም ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በተጠሪዎቹ ላይ አመልካች በክሱ መሰረት ያስረዲባቸው መሆኑን ገልጾ መከላከያቸውን ማሰማት እንዱጀምሩ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 142 መሰረት ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎቹ ከቆጠሯቸው 11 የመከላከያ ምስክሮች መካከል እራሳቸውን ጨምሮ በድምሩ ሰባት የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበው አሰምተዋል።
ከዚህ በኃላ ፍርድ ቤቱ በሁለቱ ወገኖች የቀረበውን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪዎቹ ባሰሟቸው የመከላከያ ምስክሮች በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተመሰረተባቸውን ፍሬ ነገር ለማስተባበል አልቻለም በማለት በሶስቱም ተጠሪዎች ላይ በክሱ በተጠቀሰባቸው ድንጋጌ ስር የጥፊተኝነት ውሳኔ በማስተላለፍ ግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየታቸውን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት እንዱያቀርቡ አድርጓል። በመቀጠልም በአመልካቹ በኩል የቀረበ የማክበጃ ምክንያት አለመኖሩን፣በተጠሪዎቹ በኩል የቀረቡት የማቅለያ ምክንያቶች ተቀባይነት የላላቸው መሆኑን፣ወንጀለ ደረጃ የወጣለትና የሚመደበውም በደረጃ አንድ መሆኑን እና በድንጋጌው ስር በደረጃ አንድ ለተመደበ ወንጀል በመመሪያው የተመለከተው ፍቅድ ስልጣን በአባሪ አንድ በእርከን 16 የተመለከተው መሆኑን ገልጾ በመመሪያው በእርከን 16 በተመለከተው ፍቅድ ስልጣን መሰረት 1ኛ ተጠሪ በሶስት ዓመት ከአራት ወር ጽኑ እስራት፣2ኛ ተጠሪ በሶስት ዓመት ከሁለት ወር ጽኑ እስራት፣ሶስተኛ ተጠሪ በሶስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጡ በመወሰን እና ተጠሪዎቹ ያቀረቡትን የቅጣት ገደብ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሰጥቷል።
ይግባኙን የተመለከተው የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በከፉል ለመሻር እና በከፉል ደግሞ ለማሻሻል የሰጠው ምክንያት የግራ ቀኙ ማስረጃ በማገናዘብ ሲመረመር በግል ተበዲይ ላይ ለደረሰው ጉዲት መንስኤ የሆነው እራሱ የግል ተበዲይ መሆኑን እና ጉዲቱም የደረሰበት ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ተያይዘው በኮብልስቶን ድንጋይ ላይ በመውደቃቸው መሆኑን የሚያስገነዝብ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔውን የሰጠው የግራ ቀኙን ማስረጃ በአግባቡ መዝኖ ነው ለማለት አልተቻለም የሚል መሆኑን የውሳኔው ይዘት ያመለክታል።
አመልካች ለዚህ ችልት ያቀረበው አቤቱታ ተመርመሮ የአመልካች የዓይን ምስክሮች ቃል በሁለቱ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውድቅ የተደረገበትን አግባብነት ተጠሪዎቹ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመከለተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት ተጠሪዎቹ ተጠይቀው ወንጀለን አላደረግንም በማለታቸው አመልካች አቅርቦ ካሰማቸው ስድስት ምስክሮች መካከል፡- የግል ተበዲይ የሆኑት 1ኛ ምስክር በክሱ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በመንገድ ላይ በመሄድ ላይ እያለ 2ኛ ተጠሪ የግል ተበዲይን ‛ይህም የአጽብሃ ወንድም ነው“ ብል አንቆ ከያዘው በኃላ ትፈለጋለህ በማለት በቦክስ ከፉቱ ላይ እንደመታው፣ 1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በአካባቢው ከነበረ መኪና ውስጥ ወርደው ወደ ግል ተበዲይ በማምራት 1ኛ ተጠሪ በእጁ ይዞት በነበረው ጠፍጣፊ ነገር አፍንጫው ላይ ሲመታው 3ኛ ተጠሪ ደግሞ በጠረባ መቶት ከመሬት ላይ እንደጣለው እና በወደቀበትም ሶስቱም ተጠሪዎች እየረገጡ እንደደበደቡት፣በደረሰበት ድብደባ ምክንያትም የመስማት ችግር እንዲጋጠመው እና በአፍንጫው ስብራት እና ቁስል ምክንያት ማሽተት እንደሚቸግረው በመግለጽ ምስክርነት መስጠቱን፤
3ኛ እና 4ኛ ምስክሮች በአካባቢው ከሚገኝ ግቢ ውስጥ የአናጺነት ስራ በመስራት ላይ እያለ ‛ገደለው“ የሚል ጩኸት ሰምተው ሲወጡ ተጠሪዎቹ የግል ተበዲይን አሸባሪ ነው አያለ ሲናገሩ እንደሰሙ፣ተበዲይ ደምቶ እንደነበረ እና ተጠሪዎቹ ቀበቶውን አውልቀው ሲፈትሹት እንደነበረ እና ጠቡን ግን ከጅምሩ እንዲላዩ በመግለጽ ምስክርነት መስጠታቸውን፤
5ኛ ምስክር በቦታው በደረሰበት ሰዓት ተበዲይ አፍንጫው ላይ ደምቶ ማየቱን፣የግል ተበዲይ ሽጉጥ ጥሎል በማለት 1ኛ ተጠሪ ቆርቆሮ ስር ሲፈልግ እንደነበረ እና 3ኛ ተጠሪን ከቦታው እንዲላየው በመግለጽ ምስክርነት መስጠቱን፤
6ኛ ምስክር በቦታው በደረሰበት ሰዓት ተበዲይን 1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እጁን ግራና ቀን ይዘው ማየቱን፣የተበዲይ ፉት ደም በደም ሆኖ እንደነበረ፣ምስክሩ ሲጠይቃቸው አሸባሪ ነው በማለት እንደመለሱለት፣ሽጉጥ ይዟል በማለት ሲፈትሹት እንደነበረ፣ምስክሩ የአካባቢው ሰዎች ውሃ እንዱያመጡ አድርጎ ፉቱን ሲያጥቡለት 2ኛ ተጠሪ ደግሞ ያዙኝ ልቀቁኝ ይል እንደነበረ በመግለጽ ምስክርነት መስጠቱን፤
የግል ተበዲይ ወንድም መሆኑን የገለጸው 7ኛ ምስክር ከ1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጋር የቆየ ቂም እንደነበረው፣በዚሁ ዕለት ከምሽቱ 12፡30 ላይ ሁለት የፖሉስ አባላትን ይዘው በመምጣት ምስክሩን ወደ ፖሉስ ጣቢያ እንደወሰደት፣እዚያ እያለ የግል ተበዲይ አፈና አፍንጫው ደምቶ እንዲየውና ተጠሪዎቹ የደበደቡት መሆኑን እንደነገረው በመግለጽ ምስክርነት መስጠቱን፤በመግለጽ የመሰከሩ መሆኑን እና የሀኪም ማስረጃውም በግል ተበዲይ የግራ እና የቀኝ ፉት ላይ እብጠትና የሰንበር ምልክት መታየቱን፣በአፍንጫው ላይ እብጠት፣በቀኝ አይኑና በቀኝ ጆሮው መካከል እብጠትና የመላላጥ ምልክት መታየቱን እና በተደረገለት የራጅ ምርመራም የአፍንጫ አጥንት ስብራት መታየቱን የሚያረጋግጥ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል። ሶስቱን ተጠሪዎች ጨምሮ በተጠሪዎቹ በኩል የተሰሙት ሰባት የመከላከያ ምስክሮች አመሰካከር ተጠቃል ሲታይ በዕለቱ የግል ተበዲይ ሽጉጥ ይዞ ማንነቱ ከማይታወቅ ሰው ጋር በመሆን በ2ኛ ተጠሪ ላይ ጸብ ማንሳታቸውን፣በዚህ ጸብም የግል ተበዲይና 2ኛ ተጠሪ ተያይዘው ከኮብልስቶን ድንጋይ ላይ መውደቃቸውን፣በግል ተበዲይ ላይ ጉዲቱ የደረሰውም በኮብልስቶን ድንጋይ ላይ በመውደቁ መሆኑን፣1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በቦታው የነበሩ ቢሆንም በግል ተበዲይ ላይ የፈጸሙት ነገር አለመኖሩን የሚያመለክት ነው።ተጠሪዎቹ በጠበቃቸው አማካይነት በሰጡት የሰበር መልስ ላይ የአመልካች የሰበር አቤቱታ የግራ ቀኙን ማስረጃ የመመዘን ጉዲይን የሚመለከት እንጂ የመሰረታዊ የሕግ ስህተት ጥያቄን የሚያስነሳ ባለመሆኑ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀት 10 ድንጋጌ አንጻር ሰበር ችልቱ ጉዲዩን የመመርመር ስልጣን የለውም በማለት መከራከራቸውን ተገንዝበናል። እንደተባለው የዚህ ሰበር ችልት ስልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ መርምሮ በማረም የተገደበ በመሆኑ በሕግ ስልጣን የተሰጣቸው የመጀመሪያ ደረጃ እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፍሬ ነገርን በማጣራት እና ማስረጃን በመመዘን ረገድ የደረሱበትን ድምዲሜ አግባብነት የመመርመር እና የማቃናት ስልጣን የለውም።ይህ ማለት ግን የማስረጃ ምዘናው በሕግ ተቀባይነት ያላቸውን መሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርሆዎች በጣሰ መልኩ በተከናወነ ጊዜ ጭምር ጉዲዩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ጥያቄን አያስነሳም ወደሚል ድምዲሜ ለማምራት የሚያስችል አይደለም።በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ እና በውሳኔው ላይ የቀረበው የሰበር አቤቱታ የማስረጃ ምዘና ጉዲይን የሚመለከት እንጂ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ጥያቄን የሚያስነሳ ስላልሆነ ሰበር ችልቱ አቤቱታውን የማስተናገድ ስልጣን የለውም በማለት ተጠሪዎቹ ያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ለማለት የሚቻል አይደለም።
በመሰረቱ የወንጀል ጉዲዮችን በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከት ፍርድ ቤት ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ የማስረጃውን አጭር መግለጫ፣ማስረጃውን የተቀበለበትን እና ያልተቀበለበትን ምክንያቶች በፍርደ ላይ ማስፈር እንደሚገባው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ በቁጥር 149 (1) ስር ተመልክቷል።በልላ በኩል የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ የማጽናት፣የማሻሻል ወይም የመሻር ስልጣን እንዲለው በዚሁ ሕግ ቁጥር 195 ስር የተደነገገ ቢሆንም በተለይ ውሳኔውን የሚሽረው ከሆነ እና የሚሽረውም በማስረጃ ምዘና ምክንያት ከሆነ በጉዲዩ ከቀረበው እያንዲንደ ማስረጃ አንፃር በስር ፍርድ ቤት የተከናወነው የማስረጃ ምዘና ተቀባይነት የለውም የሚልበትን ምክንያት እና በስር ፍርድ ቤት የቀረበውን እያንዲንደን ማስረጃ የተቀበለበትን እና ያልተቀበለበትን ምክንያቶች በፍርደ ላይ ማስፈር የሚጠበቅበት በመሆኑ የማስረጃ ምዘናን አስመልክቶ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 149 (1) ስር የተመለከተው መስፈርት ተፈጻሚነት የሚኖረው ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ጭምር መሆኑን ከሁለቱ ድንጋጌዎች አጠቃላይ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ አያዲግትም።በተያዘው ጉዲይ ተጠሪዎቹ ጸብ በማንሳት የደበደቡት እና ጉዲት ያደረሱበት መሆኑን የግል ተበዲይ የሆነው ግለሰብ ቀርቦ ምስክርነቱን ሰጥቷል።የግል ተበዲይ ሽጉጥ ይዞ እንደነበረ በተጠሪዎቹ መከላከያ የተነገረ ቢሆንም ይህ የተባለው ሽጉጥ አልተያዘም።ድርጊቱ የተፈጸመው ቀን ላይ በመሆኑ የግል ተበዲይ ሽጉጥ ይዞ ነበር የሚለ ከሆነ ተጠሪዎቹ የግል ተበዲይን ከደበደቡት በኃላ ወደ ፖሉስ ጽ/ቤት እንደወሰደት ሁለ የግል ተበዲይ ይዞት ነበር የተባለውን ሽጉጥ ወይም የግል ተበዲይ ሽጉጡን አቀብልታል የተባለውን እና ማንነቱ አልታወቀም የተባለውን ግለሰብ ጭምር ይዘው ለፖሉስ ማድረስ ያልቻለበት ምክንያት ስለመኖሩ በመከላከያ ምስክሮች የተገለጸ ነገር የለም።ይህም የግል ተበዲይ ሽጉጥ ይዞ እንደነበረ እና ጠብ ቀስቃሽም እንደነበረ በማስመሰል ተጠሪዎቹ እንደዋነኛ የመከላከያ ጭብጥ አድርገው በመከላከያ ምስክሮቻቸው ያስነገሩት ፍሬ ነገር የላለ እና በማስረጃ ያልተረጋገጠ መሆኑን በግልጽ መገንዘብ የሚያስችል ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጠሪዎቹ የአመልካችን ማስረጃ አስተባብለዋል ከሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰውም ይህንን በማስረጃ ያልተረጋገጠ ፍሬ ነገር እንደዋነኛ የመከላከያ ማስረጃ በመውሰድ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተከተለው የማሰረጃ ምዘና መርህ ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።በግል ተበዲይ ሰውነት ላይ መድረሱ በሕክምና ማስረጃ የተረጋገጠው የጉዲት ዓይነትም ቢሆን የሚያረጋግጠው እና የሚደግፈው በአመልካች ምስክሮች ከተመሰከረው ፍሬ ነገር ጋር እንጂ በተጠሪዎቹ የመከላከያ ምስክሮች ከተነገረው ፍሬ ነገር ጋር እንዲልሆነ ከግራ ቀኙ ምስክሮች ቃልና ከህክምና ማስረጃው ይዘት በግልጽ መገንዘብ የሚቻል ሆኖ እያለ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በግል ተበዲይ ላይ በህክምና ማስረጃው ላይ የተመለከተው ጉዲት ሉደርስ የቻለው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ተያይዞ በወደቀበት ጊዜ በኮብልስቶን ድንጋይ ጠርዝ በመመታቱ ነው በማለት የደረሰበት መደምደሚያ በግል ተበዲይ ላይ ስለደረሰው የጉዲት ዓይነት በህክምና ማስረጃው የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል ይግባኝ ሰሚው የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በከፉል በመሻር እና በከፉል ደግሞ በማሻሻል የሰጠው እና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኘው ውሳኔ በሕግ ተቀባይነት ያለውን የማስረጃ ምዘና መርህን የጣሰ በመሆኑ ምክንያት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉታረም የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።በልላ በኩል ተጠሪዎቹ በማቅለያ ምክንያትነት እንዱያዙላቸው የተለያዩ ምክንቶችን በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርበው ውድቅ የተደረጉባቸው ቢሆንም የቀደመ የወንጀል ሪከርድ ያለባቸው ስለመሆኑ በአመልካች በኩል የቀረበ ክርክር ባለመኖሩ እና የቤተሰብ አስተዲዲሪዎች ሳላለመሆናቸውም በአመልካች በኩል የቀረበ ተቃራኒ ክርክር እና ማስረጃ ባለመኖሩ የቀደመ የዘወትር ጸባያቸው መልካምነት እና የቤተሰብ አስተዲዲሪነታቸው በሁለት የማቅለያ ምክንያቶች ተይዘው የክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለቅጣቱ መነሻ አድርጎ ከያዘው እርከን 16 በሁለት እርከኖች ዝቅ ተደርጎ በእርከን 14 በተመለከተው ፍቅድ ስልጣን መሰረት በቅጣቱ ረገድ ተገቢው መሻሻል ላደረግበት የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የሰጠው እና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ24/08/2007 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 195 (2) (ሀ) መሰረት ተሽሯል።
ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተመለከተው ውሳኔ በሕግ ተቀባይነት ያለውን የማስረጃ ምዘና መርህ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስነናል።
የሐረሪ ክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጠው ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 195 (2) (ለ) (2) መሰረት ተሻሽልአል።
በተራ ቁጥር ሶስት ከተጠቀሰው ውሳኔ ውስጥ በሶስቱም ተጠሪዎች ላይ በወንጀል ሕግ ቁጥር 555 (ሐ) ስር በ24/11/2006 ዓ.ም. የተሰጠው የጥፊተኝነት የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
በተራ ቁጥር ሶስት ከተጠቀሰው ውሳኔ ውስጥ በሶስቱም ተጠሪዎች ላይ በ29/11/2006 ዓ.ም.
የተሰጠው የቅጣት ውሳኔ ተሻሽል በዚህ ጉዲይ ከአሁን በፉት የታሰሩት የሚታሰብላቸው ሆኖ 1ኛ ተጠሪ አቶ ሕሉና ኃይላ በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ጽኑ እስራት፣2ኛ ተጠሪ አቶ ፊሲካ አዕምሮ በሁለት ዓመት ከሰባት ወር ጽኑ እስራት፣3ኛ ተጠሪ አቶ መላኩ ደምሴ በሁለት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ወስነናል።
የክልለ ፖሉስ ኮሚሽን ከፋዳራል ፖሉስ ኮሚሽን ጋር በመሆን ተጠሪዎቹን ተከታትል በመያዝ ለክልለ ማረሚያ ቤት እንዱያስረክባቸው እና ማረሚያ ቤቱም ተጠሪዎቹ ተይዘው ሲቀርቡለት ተረክቦ በቅጣት ውሳኔው መሰረት እንዱያስፈጽም ለሶስቱም አካላት ትዕዛዝ ይተላለፍ።
በክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት 2ኛ ተጠሪ የተወሰነባቸውን መቀጮ ብር 2,000 (ሁለት ሺህ) ከፍለው ከሆነ በሚያቀርቡት ደረሰኝ መሰረት እንዱመለስላቸው ተጠሪው ለሚጠይቁት አካል ይጻፍ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.