ፍ/ቤቶች የገንዘብ መቀጫን ሲወስኑ ከግምት እና ግንዛቤ ውሰጥ ሉያስገቡዋቸው የሚገቡ የተከሳሽ ግላዊና የወንጀለን ሁኔታዋችን በማገናዘብና ፤ በወንጅል ህጉ እና በቅጣት መመሪያው ላይ የተቀመጡ መሰፈርቶችን መሰረት በማድረግ መወሰን ያለባቸው እንጂ በደፈናው የገንዘብ መቀጮ መወሰን ተገቢ ሰላለመሆኑ ፤ የወ/ሕ/ቁ 88 /2/ እ 90 90 (2)፤ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2000 88542 አቶ ቢሆነኝ ደምሴ እና የት/ብ/ክ/መ/ዓቃቤ ሕግ 17/11/ 2005ዓ.ም 338 72. በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ሥርዓት ህግ መሰረት ክስ እንዱሻሻል መፍቀድ የተፊጠነ ፍትህ የማግኘት መብትን የሚያጣብብ ነው የሚባል ስላለመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 188፣119 ኢፋድሪ ሕግ መንግስት አንቀጽ 20(1)
No summary available.
መጋቢት 2 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- የኦሮሚያ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ህግ - ጉዲኔ ፈቃደ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ቴዎድሮስ አብርሃ ቀለቲ - ጠበቃ አማላዩ ፀጋዬ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ የወንጀል ክስ ማሻሻልን የሚመለከት ነው። በስር 1ኛ ተከሳሽ ደርበው ሻንቆ እና 2ኛ ተከሳሽ በሆነው የአሁን ተጠሪ ላይ አመልካች የመሰረተውን ክስ ለማሻሻል ያቀረበው አቤቱታ ጉዲዩን ሲመለከት በነበረው የፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 11311 በ23/4/2007 በዋለው ችልት በትእዛዝ ውድቅ የተደረገ ሲሆን ትእዛዝ ላይ አመልካች ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ በመ/ቁ/192830 በ3/6/2007 በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ትእዛዝ በመሻር ክሱ እንዱሻሻል ወስኗል። የአሁን ተጠሪ ክስ እንዱሻሻል መፈቀደን በመቃወም የሰበር አቤቱታ ለክልለ ሰበር ችልት አቅርበው ችልቱ በመ/ቁ/ 203090 በ1/10/2007 የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የክስ ማሻሻል ጥያቄ የቀረበው መዝገቡ ለምርመራ ከተቀጠረ በኋላ በመሆኑ፣ በዚህ ሁኔታ ክሱ ይሻሻል ቢባል ክርክሩ እንደ አዱስ የሚጀምር በመሆኑ፣ይህ ደግሞ በኢፋዳሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 20/1/ የተጠበቀውን አፊጣኝ ውሳኔ የማግኘት መብት የሚፃረር በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያሳለፈው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት ሽሮ የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ትእዛዝ አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው። አመልካች ያቀረቡት የሰበር ማመልከቻ ተመርምሮ አመልካች ምክንያቶችን በመዘርዘር በጉዲዩ ላይ ውሳኔ ከመስጠቱ በፉት በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው የክስ ላሻሽል ጥያቄ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተቀባይነት ማግኘቱ የኢፋዳሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 20 /1/ የሚጥስ ነው ተብል ውድቅ የመደረጉን አግባብ ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህ መሰረት ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ ተለዋውጠዋል።
ከላይ ባጭሩ የገለጽነው የጉዲዩን አመጣጥ ሲሆን ቅሬታ ያስነሳውን ውሳኔ እና የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር ችልት ከተያዘው ጭብጥ እና ከህጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደመረመርነው አመልካች መስርቶት በነበረው ክስ የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ድርጅት የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኃላፉ የነበረው 1ኛ ተከሳሽ ከመንግስት የግዥ ወይም የጨረታ አወጣጥ ደንብና ከድርጅቱ መመሪያ ውጭ ስልጣኑን ያላግባብ በመገልገል ንብረትነቱ የመንግስት የሆነ የሰላዲ ቁጥር ኢት 4-07074 ገልባጭ መኪና ያለምንም ጨረታና የበላይ ኃላፉ ውሳኔ ለአሁን ተጠሪ በጥገና ሰበብ በ21/07/2007 ዓ/ም እንዱሰጥ በማድረግ መንግስት ከሁለት ሚሉዮን ብር በላይ እንዱያጣ በማድረጋቸው ክስ ቀርቦባቸው የዓቃቤ ህግ ማስረጃዎች ተሰምተው እንዱከላከለ ተፈቅድላቸው መከላከያ ተሰምቶ መዝገቡ ለምርመራ ተቀጥሮ ነበር።
ይህ በእንዱህ እያለ አመልካች ለክሱ ምክንያት የሆነው መኪና ለላላ 3ኛ ወገን የተሸጠ መሆኑን፤
የገዛው ሰውም የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ የሰላዲ ቁጥር በዚህ መኪና ላይ በመለጠፍ ከአዱስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር በህገ ወጥ መንገድ የሻንሲ፤
የሞተር ቁጥርና ላልች መረጃዎችን ከላዩ በመፊቅ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በማስመሰል ከትራንስፖርት ባለስልጣን እውቅና ላልች መረጃዎችን ከላዩ በመፊቅ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በማስመሰል ከትራንስፖርት ባለስልጣን እውቅና ደንብና መመሪያ ውጭ በላዩ ላይ እንዱመታ በማድረግ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ሉብሬ/ በመውሰድ በሽያጭ ለላላ ግለሰብ አስተላልፍ መኪናው በአዱስ አበባ ከተማ ውስጥ በመስራት ላይ እንዲለ ከ6 ዓመታት ፍለጋ በኋላ ያላግባብ በተጠሪ ተወስድ የተሰወረ መኪና እና በወንጀለ ውስጥ ተካፊይ የሆኑ ሰዎች የተያዙና የስር ተከሳሾች የሙስና ወንጀል ድርጊት አፈፃጸምና የተገኘው ጥቅም በአግባቡ በግልጽ በመታወቁ፤ እንዱሁም በወንጀለ ተካፊይ የሆኑ ሰዎች ላይ እንደተሳትፎቸው በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/ 118 እና 119/1/ መሰረት ክስ አሻሽለን ብናቀርብ ፍርድ ቤቱ ትክክለኛ እና ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት ይረዲዋል በማለት ክሱን አሻሽለው ለማቅረብ እንዱፈቀድ ጠይቀዋል።
የተጠሪ ጠበቃ በበኩላቸው ጉዲዩ 1 አመት ከ6 ወር የቆየ መሆኑን፤ መዝገቡም ክርክሩ ተጠናቆ ለምርመራ መቀጠሩን ፤ ምንአልባት ዓቃቤ ህግ ላልች ሰዎች ላይ ክስ መመስረት ከፈለገ የሚገድበው ነገር አለመኖሩንና የተጠቀሰው ምክንያት ክሱን አሻሽል ለማቅረብ የህግ ድጋፍ ያለው አለመሆኑን በማንሳት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በየደረጃው የተመለከቱት የክልለ ፍርድ ቤቶች ከፍ ሲል የተመለከቱትን ውሳኔዎች ሰጥተዋል። በተለይ የክልለ ሰበር ችልት ትክክለኛ እና ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት ሲባል ክሱ ሉሻሻል ይችላል በማለት በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል ቢቀበለውም የክሱ መሻሻል አስቀድሞ በእስር ሆነው ጉዲዩን ሲከታተለ የነበሩ ተከሳሾች አፊጣኝ ውሳኔ የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት የሚያጣብብ በመሆኑ የክስ ላሻሽል ጥያቄው ተቀባይነት እንደላለው ወስኗል።
በመሰረቱ ውሳኔ ከመስጠቱ በፉት በማንኛውም ጊዜ ክሱ እንዱሻሻል ፍርድ ቤቱ ሉፈቅድ የሚችል ሲሆን በዚህ መልኩ ክሱ እንዱሻሻል ፈቃድ ሲሰጥ ወይም የክሱ መሻሻል ሲከለከል ፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ያለው ህጋዊ ምክንያት እንዱሰጥ ይጠበቃል። በተያዘው ጉዲይ የክልለ ሰበር ችልት ክሱ እንዱሻሻል በመፈቀደ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚል መደምደሚያ ላይ የደረሰው ጉዲዩ ለምርመራ ያደረ በመሆኑ እና ክሱ ተሻሽል እንደ አዱስ ቢጀመር አፊጣኝ ውሳኔ የማግኘት መብትን ይጋፊል በማለት ነው። ነገር ግን ከላይ እንደተገለጸው የክሱ መሻሻል ፍርድ ቤቱ ትክክለኛ እና ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችለው መሆኑ ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ፤ ጉዲዩን የሚመለከተው ፍርድ ቤት ውሳኔ ከመስጠቱ በፉት በማንኛውም ጊዜ ክሱ እንዱሻሻል መፍቀድ እንደሚቻል በህጉ የተመለከተ በመሆኑ፤ እንዱሁም የተፊጠነ ፍትህ የማግኘት መብት የሚረጋገጠው በህግ የተዘረጋን ስነ ስርዓት ተከትል ጉዲዩን ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ በመምራት እንጂ በህግ የተዘረጋን ስነ-ስርዓት ወደጎን በማለት ባለመሆኑ የክልለ ሰበር ችልት የክሱ መሻሻል ለትክክለኛ ውሳኔ አሰጣጥ ተገቢ መሆኑን ተቀብል ነገር ግን ክርክሩ የደረሰበትን ደረጃ ብቻ ግምት ውስጥ በማስገባትና አፊጣኝ ፍትህ የማግኘት መብትን ህጋዊ አፈፃጸም ባልተከተለ መልኩ ክሱ እንዱሻሻል ሉፈቀድ አይገባም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ እና ያሳለፈው ውሳኔ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። የተፊጠነ ፍትህ የሚገኘው ጉዲዩ የወንጀል ክርክር በሚመራበት የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ ስርዓት ድንጋጌዎች አግባብ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ በመምራት በመሆኑ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/ 118 እና 119 እንዱሁም ተያያዥ ድንጋጌዎች መሰረት ተቀባይነት ባለው ምክንያት ክስ እንዱሻሻል መፈቀደ የተፊጠነ ፍትህ የማግኘት መብትን የሚያጣብብ ነው የሚባል አይሆንም ብለናል። ስለሆነም የክልለ ሰበር ችልት ክሱ እንዱሻሻል ሉፈቀድ አይገባም በማለት የይግባኝ ሰሚውን ፍርድ ቤት ውሳኔ መሻሩ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። ተከታዩም ተወስኗል።
የኦሮሚያ ልዩ ዞን ፍንፍኔ ዙሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 11311 በ23/4/2007 በዋለው ችልት ያሳለፈው ትእዛዝ እንዱሁም የኦሮሚያ ክልል ሰበር ችልት በመ/ቁ/ 203090 በ1/10/2007 የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸው ስለሆኑ በወ/መ/ህ/ስ/ስ/ቁ/ 195/2/ መሰረት ተሸረዋል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 192830 በ3/6/2007 ያሳለፈው ውሳኔ ፀንቷል።
በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 11311 እየተካሄደ የነበረው ክርክር ታግድ እንዱቆይ በዚህ ፍርድ ቤት ጥቅምት 15/2008 ዓ/ም የተሰጠው ትእዛዝ ተነስቷል።
አመልካች የተሻሻለውን ክስ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዱያቀርብ፤ የስር ፍርድ ቤትም የተሸሻለውን ክስ ተቀብል አከራክሮ እንዱወሰን ብለናል። ይፃፍ።
No topics extracted.