ለአንድ ንብረት የሚከፈለው የኢንሹራንስ ገንዘብ የመያዣ መብት ላላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ይሰጣል የሚለው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ኢንሹራንስ ሰጪው ላልተከፈለ የአርቦን ክፍያ ኢንሹራንስ ገቢውን ከመጠየቅ ውጪ የመያዣ መብት ያለውን አካል መጠየቅ የማይችል ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁ.684(1) XXVI
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 17 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ረታ ቶልሳ አዲነ ንጉሴ ሙስጠፊ አህመድ አመልካች፡- አቶ ቢሆነኝ ደምላ - ጉዲይ ተከታታይ መንበሩ ተስፊው - ቀረቡ ተጠሪ፡- የት/ብ/ክ/መንግስት ዐቃቤ ሕግ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ ንግድ ፈቃድ ሳይኖረው የንግድ ሥራን በህገ ወጥ መንገድ ማከናወን ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው በት/ብ/ክ/መንግስት አላማጣ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ አመልካች ላይ ባቀረበው የወንጀል ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ይዘትም አመልካች ንግድ ፈቃድ ሳይኖረው በ17/11/2004 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ በአላማጣ ከተማ 02 ቀበላ ልዩ ቦታው ወደ ዋጃ መውጫ ተብል በሚጠራ አካባቢ አንድ ኩንታል ስኳር በመኪና ላይ ጭኖ ወደ ቆቦ ወረዲ ሲጓዝ ስለተያዘ አዋጅ ቁ 686/2002 አንቀፅ 60/1/ ተላልፍ በፈፀመው ሕጋዊ ያልሆነ ንግድ ሥራ በማካሄድ ተከሷል የሚል ሲሆን ተከሳሹም ቀርቦ ስኳሩን ወደ ቆቦ ከተማ ወስድ ለመሸጥ በመኪና እየተጓዘ ሳለ መያዙን ጠቅሶ ንግድ ፈቃድ ሳይኖረው ይሄንን የንግድ ሥራ መፈፀሙ ጥፊት መሆኑን በማመን የእምነት ክህደት ቃለን ሰጥቷል።
ጉዲዩን የተመለከተው ወረዲ ፍ/ቤትም ተከሳሹ የሰጠውን የእምነት ክህደት መነሻ በማድረግ ተከሳሹን በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ ካደረገ በኃላ በሁለት ዓመት ፅኑ እስራትና ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ወስኖበታል።
አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወሙ ቅሬታውን ለዞኑ ከፍ/ፍ/ቤትና ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ደረጃውን ጠብቆ ቢያቀርብም በሁለቱም ደረጃ ተቀባይነት አላገኘም አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም አንደን ኩንታል ስኳር ገዝቼ ወደ ቆቦ ከተማ ስንጓዝ የነበረው ለንግድ ወይም ለሽያጭ ሳይሆን ወላጅ አባቴና ሴት አያቴ በሞት በመለየታቸው ምክንያት ለሃዘን ለሚመጡ ሰዎች ሻይና ቡና ማስተናገጃ ሆኖ ሳለ ጥፊተኛ መባላ አላግባብ መሆኑን ለንግድ ነው ቢባል እንኳ የቀረበብኝን ክስ ሙለ በሙለ በማመን የእምነት ክህደት ቃልን መስጠቴ የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆኔን የወንጀል ሪከርድ የላለብኝ መሆኔ የግል ሁኔታዬና የገቢ ምንጭ በወንጀል ህግ ቁ 88/2/፤ 90/2/ እና እንዱሁም በወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በአግባቡ ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ቅጣቱ መጣል ሲገባ ያላግባብ በሁለት ዓመት ፀኑ እስራትና 150,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንድቀጣ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ውሳኔው ተሻሽል የጥፊተኝነት ደረጃዬን ባገናዘበና የገንዘብ መቀጮውንም በተመለከተ የመክፈል አቅሜን ባገናዘበ መልኩ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
አቤቱታውም ተመርምሮ ለሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ ላታይ ይገባል መባለ ተጠሪም ቀርቦ የበኩለን መልስ የሰጠበት ሲሆን አመልካችም የመልስ መልሱን ሰጥቶበታል።
የጉዲዩ አመጣጥና ይዘት ከላይ ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር አቤቱታ በቀረበበት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት ይዘን ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምረናል:: እንደመረመርነውም የጥፊተኝነት ውሳኔን በተመለከተ አመልካቹ የቀረበበትን የወንጀል ክስ መፈፀሙን በዝርዝርና ሙለ በሙለ በማመን የእምነት ክደት ቃለን መስጠቱና ፍ/ቤቱም ይህንኑ የአመልካችን የእምነት ቃል መነሻ በማድረግ የጥፊተኝነት ውሣኔ በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ.134 /1/ ድንጋጌ አንፃር መሰጠቱን መገንዘብ ተችሎል ሆኖም ግን አንድ ሰው በተሰጠበት የጥፊተኝነት የቅጣት ውሳኔ ላይ ደረጃውን ጠብቆ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ይግባኝ ለማለት የሚችል ቢሆንም የጥፊተኝነት ውሳኔው የተሰጠው በወ/መ/ህ/ስ/ስ/ቁ134/1/ ስር እንደተመለከተው የተከሳሹን የእምነት ቃል መነሻ በማድረግ ከሆነ በቅጣቱ ላይ ካልሆነ በጥፊተኝነቱ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ እንደማይቻል በወ/መ/ህ/ስ/ስ/ቁ 185/1/ ስር ተመልክቷል። በመሆኑም በአንድ በኩል አመልካች ወንጀለን በህጉ አግባብ ሙለ በሙለ መፈፀሙን አምኖ የእምነት ክህደት ቃለን ሰጥቶና የጥፊተኝነት ውሳኔም ይህንኑ መነሻ በማድርግ ተሰጥቶ እያለ በልላ በኩል ደግሞ በበታች ፍ/ቤት ከሰጠው እምነት ቃል በተቃራኒ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ እርስ በራሱ የሚጋጭ በመሆኑ ተቀባይት ያለው አይደለም ብለናል።
የቅጣት ውሳኔን በተመለከተ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የህጉ ድንጋጌ ከብር 150,000- 300,000 የገንዘብ መቀጮና እንዱሁም ከ7-15 ዓመት ፅኑ እስራት እንደሚያስቀጣ የደነገገ ሲሆን ከዚህ አኳያ የእስራት ቅጣቱን በተመለከተ የበታች ፍ/ቤቶች የወንጀለን ክብደት የአመልካቹን የግል ሁኔታና ላልች የቅጣት ማቅለያዎች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በድንጋጌው ስር ከተመለከተው መነሻ የእስራት ቅጣት (7 ዓመት ፅኑ እስራት) በመውረድ አመልካቹ በሁለት ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጣ የተወሰነበት ሲሆን ይህ ደግሞ ሉነቀፍ የሚችልበት የህግ አግባብ ባለመኖሩ በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታም አልተቀበልነውም።
በልላ በኩል የገንዘብ መቀጮውን በተመለከተ በወ/ህ/ቁ 90/2/ ስር እንደተመለከተው ፍ/ቤቶች ይህንን የገንዘብ መቀጮ ሲወስኑ የወንጀለ ክብደት የአጥፉውን አደገኛነት መጠን የሀብቱን ሁኔታ የገቢ ምንጩን ዕድሜውንና የጤንነቱን ሁኔታ ከቤተሰብ አስተዲዲሪነት አኳያ ያለንበትን ሸክም የሙያ ስራውንና ከስራው የሚያገኘውን ገቢ መጠን ከግምትና ግንዛቤ ውስጥ ባስገባ ሁኔታ መቀጮው ሉጣል እንደሚገባ በግልፅ ተደንግጓል። ይሁን እንጂ በተያዘው ጉዲይ በአመልካች ላይ የተጣለው የብር 150,000 የገንዘብ መቀጮ እነዚህ ከፍ ሲል የተጠቀሱትን የህጉን መስፈርቶች ግንዛቤ ውስጥ ባስገባ አግባብ መሆን አለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ አያሳይም የመቀጮ ቅጣቱ እነዚህ መስፈርቶችን ባላገናዘበ ሁኔታ የሚጣል ሆኖ ከተገኘም የወንጀል ህጉ ካሰበው ዓላማ ውጭም በመውጣት አጥፉውንና ላልቹን ከማስተማር እና ከማስጠንቀቅ አልፍ አላስፈላጊ ጫናና ችግር በተከሳሹና በቤተሰቡ ላይ እንዲይፈጥር ጭምር ጥንቃቄ ላደረግ ይገባል በተለይም አመልካቹ አርሶ አደርና የቤተሰብ አስተዲዲሪ ከመሆኑ አኳያ የሀብቱ ሁኔታ የገቢ ምንጩ አደገኛነቱና የወንጀለ ክብደትም በተገቢ ሁኔታ ተመዝኖ መታየት ከነበረበት ባጠቃላይ በህጉ እስካልተከለከለ ድረስ በህጉ ከተመለከተው መነሻ መቀጮውም በመውረድ (አጠቃላይ የገንዘብ መቀጮው መነሻ እንደተጠበቀ ሆኖ) መቀጮው በወንጀል ህጉ አግባብና በተለይም በወ/ህ/ቁ88/2/ ፤ 90/2/ እና በፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በወጣው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ 1/2002 አኳያ መጣል ሲገባ በደፈናው አመልካቹ በብር 150,000 እንዱቀጣ መወሰኑና ይኼውም በዞኑ ከፍ/ፍ/ቤት እና ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት መታረም ሲገባ መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፤
በአላማጣ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት መ. በ15/2/2005 ዓ.ም ተወስኖ በከፍተኛ ፍ/ቤቱና ክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የፀናው የጥፊተኝነትና የእስራት ቅጣቱ ውሳኔ ክፍል በወ/መ/ህ/ስ/ስ/ቁ.195/2/ /ለ/ /2/ መሰረት ፀንቷል፤
ሆኖም ግን አመልካች በብር 150,000 (መቶ ሃምሳ ሺህ) ገንዘብ መቀጮ ይቀጣ በማለት የተሰጠው የቅጣቱ ውሳኔ ክፍል ብቻ በወ/መ/ህ/ስ/ስ/ቁ 195/2/ /ለ/ /2/ መሰረት ተሸሯል፤
የአላማጣ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት የራሱን መዝገብ በማንቀሳቀስና ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ ከዚህ በላይ በፍርደ ሐተታ ክፍል በተገለፀው አኳኋን የገንዘብ መቀጮውን ከወንጀል ህጉ ቁ 90/2/፤ 88 /2/ እና ከጉዲዩ ጋር አግባብነት ካላቸው ላልች ድንጋጌዎችና እንዱሁም በፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በወጣው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ 1/2002 አኳያ የገንዘብ ቅጣቱን በማገናዘብ ከመረመረ በኃላ ተገቢውን አስልቶ እንዱወስን ዘንድ ጉዲዩን መልሰንለታል። ይፃፍ።
No topics extracted.