ለአንድ ንብረት የሚከፈለው የኢንሹራንስ ገንዘብ የመያዣ መብት ላላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ይሰጣል የሚለው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ኢንሹራንስ ሰጪው ላልተከፈለ የአርቦን ክፍያ ኢንሹራንስ ገቢውን ከመጠየቅ ውጪ የመያዣ መብት ያለውን አካል መጠየቅ የማይችል ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁ.684(1) XXVI
No summary available.
የሰ/መ/ ቀን 09/02/2009 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል ቀነዓ ቂጣታ ክፍለጽዮን ማሞ ጳውልስ ኦርሲሾ አመልካች፡- ብሓራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንሽ ኩባንያ አ.ማ ጌታቸው ገዲሙ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትዕግስት ገ/እግዚአብሓር ነገረ ፈጅ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው አመልካች የስር ከሳሽ በመሆን በአሁን ተጠሪ (1ኛ ተከሳሽ) እና በዛጌ አግሮ ኢንደስትሪ ኃላ/የተ/የግል ማህበር (2ኛ ተከሳሽ) ላይ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችልት በቀን 19/02/2006 ዓ/ም በመሰረተው ክስ ነው።
2ኛ ተከሳሽ ልዩ ልዩ ተሸከርካሪዎችን በዋስትና በማስያዝ ከ1ኛው ተከሳሽ ብድር የወሰደ ሲሆን አመልካች ለተሸከርካሪዎቹ የመድን ሽፊን ሰጥቷል ክሱንም ሉመሰርት የቻለው በሰጠሁት የመድን ሽፊን መሰረት ያልተከፈለኝ ቀሪ የኦርቦን ክፍያ ስላለ ሁለቱም (የስር) ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ ባለ ዕዲ ናቸው በሚል ነው።
2ኛ ተከሳሽ የወሰደውን የባንክ ዕዲ እንደውለ አጠናቆ ሉከፍል ባለመቻለ 1ኛው ተከሳሽ በመያዣ ውለ መሰረት ንብረቶቹን ካስቆጠረ በኋላ በሐራጅ በመሸጥ በብድር የሰጠውን ገንዘብ ሰብስቧል ቀጥል ለአመልካች በላከው ማስታወሻ የመድን ውለ እንዱቋረጥ አሳስቧል።
2ኛ ተከሳሽ በመክሰሩ ምክንያት ከ1ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) ጋር የነበረው ውል በመቋረጡና የመድን ፖሉሲውም እንዱሰረዝ በመደረጉ አመልካች ገቢ ያላደረገው ብር 42,037.15 እንዱከፈለው በሁለቱ ተከሳሾች ላይ ክስ መስርቷል የክሱ አመሰራረት ተጠሪን 1ኛ ተከሳሽ በማድረግ ሲሆን ይዘቱም በመድን ፖሉሲው ላይ ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሳሽ እንደጣምራ መድን ገቢዎች ሆነው የተጻፈ ኦርቦኑንም እንደ 2ኛ ተከሳሽ በመሆን 1ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) ሲከፍል የነበረ ፖሉሲው እንዱታይለም ተጠሪ ሲፈቅድም ሲስማማ የነበረ የመድን ሽፊን የነበራቸው ተሸከርካሪዎች በመሸጥ ተጠሪ እዲውን የሰበሰበና በዚህም ተጠቃሚ የሆነ በመሆኑ 2ኛ ተከሳሽ መክሰሩን ተከትል ተጠሪ የማረውን አርቦን ልከፍል አይገባም ማለቱ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
አመልካች በበኩለ በሰጠው መልስ ከአመልካች ጋር ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ግንኙነት አለመመስረቱን አመልካች የመድን ውለን የፈረመው ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር እንጂ ከተጠሪ (1ኛ ተከሳሽ) ጋር አለመሆኑን ተጠሪ የመድን ግዳታ ውል ፈጽሞ አለመግባቱን እንዱሁም የመድን ውለ እንዱታደስ መስማማቱ የውለ ተጠቃሚ በመሆኑ እንጂ ባለእዲ ጌዳታ ያለበት መሆኑን አያመለክትም ብሎል።
2ኛ ተከሳሽ መጥሪያ ደርሶት ሳይቀርብ በመቅረቱ ፍ/ቤቱ የአመልካች (ከሳሽ) እና ተጠሪ (1ኛ ተከሳሽ) ክርክሮችንና ማስረጃዎችን ከመረመረ በኋላ ጉዲዩን መርመሯል እንደመረመረውም 1ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) አርቦኑን ሲከፍል እንደነበረ በመድን ውለ ላይም ሁለቱም ተከሳሾች መድን ገቢዎች ለመሆናቸው ‛እና ‛ በሚል ቃል የተጠቀሱ መሆኑ መድን ውለ እንዲይቋረጥ ሲከታተል ና እንዱታደስ ሲፈቅድ የነበረው 1ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) በመሆኑ የሰጠውን ብድር ከሰበሰቡ በኋላ የተጠራቀመውን ኦረቦን አልከፍልም የሚልበት አግባብ ባለመኖሩ 1ኛው ተከሳሽ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር በአንድነትና በነጠላ ሃላፉነት አለባቸው ሲል ስር ፍ/ቤት ወስኗል። ፣ ተጠሪ የስር ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቅሬታውን አቅርቧል ተጠሪ ቅሬታውን ሲያቀርብ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተመሰረቱ የውል ግንኙነት ሳይኖር በአመልካችና በ2ኛው ተከሳሽ መካከል የመድን ውለ ከተመሰረተ በኋላ በተደረጉ በአመልካችና በተበዲሪው በ2ኛ ተከሳሽ መካከል ከነበሩ የብድር ውል ግዳታዎች አፈፃፀም ላይ ተመስርቶ አመልካችን እንደመድን ገቢ በመቁጠር የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ሉሻር ይገባዋል ብሎል። አመልካችም በስር ፍ/ቤት ያቀረባቸውን የክርክር ነጥቦች አጠናክሮ አቅርቧል።
ጉዲዩን የያዘው ከፍተኛ ፍ/ቤት በንግድ ህግ ቁ. 675 (1) ላይ በመመስረት መልስ ሰጭ የአሁን አመልካች ያቀረባቸውን መከራከሪያዎች ከመዘነ በኋላ በይግባኝ ባይ (ተጠሪ) እና በመልስ ሰጭ መካከል የመድን ሰጭና መድን ተቀባይ ውል አለ ለማለት የማያስችለ በመሆኑ አረቦኑን መክፈል ያለበት የስር 2ኛ ተከሳሽ ብቻ ነው በማለት ወስኗል ።
ፍ/ቤቱ በተጨማሪም የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት በተመሳሳይ ጉዲይ በአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል በነበረው ክርከር በሰበር መዝገብ ቁ. 43886 በቀን 22 /4/2002 ዓ/ም የሰጠው አስገዲጅ ውሳኔ የይግባኝ ባይን (የአሁን ተጠሪን) ክርከር የሚደግፍ በመሆኑ የይግባኝ ባይ (አመልካች) ማመልከቻን አልተቀበልነውም ሲል ወስኗል።
ጉዲዩ ለዚህ ችልት የቀረበው በከፍተኛው ፍ/ቤት ተፈጸመ የተባለው የህግ ስህተት እንዱታረም ነው። አመልካች በሰበር አቤቱታው ተጠሪ ተሸከርክሪዎችን ተረክቦ ከ5 ዓመት በላይ ካስተዲደረና ዋስትናው እንዱታደስ እየጠየቀ አርቦን በየአመቱ እየከፈለ ከቆየ በኃላ ንብረቶቹን ሽጦ ከብር 27 ሚሉዮን በላይ ከሰበሰበ በኋላ ውለን በማቋረጥ አርቦንን አልከፍልም ያለበትን ክርከር ከፍተኛ ፍ/ቤት ተቀብል መወሰኑ አግባብ አይደለም ይታረምልኝ ብሎል።
ተጠሪ በበኩለ የስር ክርክሩን በማጠናከር የከፍተኛው ፍ/ቤት አስገዲጅነት ያለውን የሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዝገብ መሰረት ያደረገ ውሳኔ መስጠቱ በአግባቡ ነው ሲል መልስ ሰጥቷል። እኛም መዝገቡን መርምረናል እንደመረመርነውም የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔውን መሰረት ያደረገው በውል ፖሉሲው ላይ ተጠሪና 2ኛ ተከሳሽ ‛እና“ በሚል በመጣመራቸው ሲሆን ተጠሪ ከውል የመነጨ ግዳታ ያለበት ለመሆኑ ግን አግባብ ያለውን ህግ ወይም የሰበር ውሳኔ ጠቅሶ አላብራራም።
በልላ በኩል ከፍተኛ ፍ/ቤት ከዚህ ቀደም ሰበር ችልቱ በተመሳሳይ ጉዲይ በመዝገብ ቁ. 43886 የሰጠውን አስገዲጅ ውሳኔ በመጥቀስ እና የንግድ ህግ ቁጥሮች 654 እና 657 -659 ን በአግባቡ በመተርጎም የሰጠው ውሳኔ ምንም ስህተት አልተገኘበትም። በዚህ መሰረት የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.