ከአንድ በላይ የሆኑ ከሳሾች በጋራ በመሆን የህብረት ክስ ሉያቀርቡ ስለሚችልበት ሁኔታ የመድን ሰጪውና የመድን ተቀባዩ ባደረጉት የመድን ሽፊን ውል ላይ የማግለያ ድንጋጌ በስምምነታቸው እስካሰፈሩ ድረስ ይኸው ሉጠበቅ የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.35
No summary available.
ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - የቀረበ የለም ተጠሪዎች፡-
ክርክሩ በተጀመረበት የሰሜን ምዕራብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሽሬ እንዲስላሴ ምድብ ችልት ተከሳሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ ያቀረበው በሰጠው የመድን ሽፊን መሰረት ለክሱ ኃላፉ መሆኑ በመረጋገጡ ከሳሾች ለነበሩት የአሁኖቹ ተጠሪዎች በድምሩ ብር 350,760.31 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ከሰላሳ አንድ ሳንቲም) ካሳ እንዱከፍል በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ25/03/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ26/09/2006 ዓ.ም. በፍርድ የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ተጠሪዎቹ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት ንብረትነቱ የ1ኛ ተጠሪ የሆነ የሰላዲ ቁጥር ኢት-312179 ማርቸዱስ የጭነት መኪና የ4ኛ ተጠሪ ልጅ በሆነው አቶ ተከስተ ካህሳይ ሲሽከረከር በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ ሾፋሩ እና በጋቢናው ውስጥ ተሳፍሮ የነበረ አቶ ኃይለማርያም ካህሳይ የሚባል የ2ኛ እና የ3ኛ ተጠሪዎች ልጅ መሞታቸውን እና በተሸከርካሪው ላይም ከፍተኛ ጉዲት የደረሰ መሆኑን፣ተከሳሽ ድርጅት በተሸከርካሪው ላይ ለሚደርስ ጉዲትም ሆነ በተሳፊሪ እና በአሽከርካሪው ላይ ለሚደርስ የሞት አደጋ የመድን ሽፊን የሰጠ መሆኑን፣ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች ከሟች ልጆቻቸው ያገኙት የነበረው ድጎማ የቀረባቸው መሆኑን እና ተከሳሽ ድርጅት ተሽከርካሪውን ከወደቀበት ያነሳ ቢሆንም ለማስጠገንም ሆነ የማስጠገኛ ወጪ ለመክፈል እንዱሁም ካሳ ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን እና በዚህም ምክንያት 1ኛ ተጠሪ ተሽከርካሪውን በራሳቸው ወጪ ያስጠገኑ መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ፡-
ፍርድ ቤቱም ክሱን እና የ1ኛ ተጠሪን ምስክሮች ከሰማ በኋላ በመድን ውለ አንቀጽ 3 አነጋገር አመልካች ድርጅት ኃላፉነት የማይኖርበት አደጋው በደረሰበት ጊዜ ተሽከርካሪው ሲሽከረከር የነበረው መንጃ ፈቃድ በላለው ሰው በሆነ ጊዜ እንጂ ሕጋዊ መንጃ ፈቃድ በላለው ሰው በሆነ ጊዜ ጭምር ተደርጎ መተርጎም የሚገባው አለመሆኑን፣1ኛ ተጠሪም አሽከርካሪውን የቀጠሩት ግለሰቡ የያዘውን መንጃ ፈቃድ አይተው ስለመሆኑ በምስክሮች ያስረደ መሆኑን፣መንጃ ፈቃደን ከማየት በቀር ሕጋዊነቱን ከሚመለከተው አካል የማረጋገጥ ግዳታ የመድን ውለ የማይጥልባቸው መሆኑን፣ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎችም በሟቾቹ ይረደ የነበረ ስለመሆኑ እና ወራሽነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ያቀረቡ መሆኑን፣1ኛ ተጠሪ ለተሽከርካሪው ማስጠገኛ ያወጡት ወጪ በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን እና የተሽከርካሪው የተቋረጠ ጥቅም ግን የመድን ሽፊን ያልተሰጠው መሆኑን ገልጾ አመልካቹን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ የተሽከርካሪውን የተቋረጠ ጥቅም አስመልክቶ ከተጠየቀው ገንዘብ ውጪ ያለውን በክሱ የተመለከተውን የካሳ መጠን አመልካች ለተጠሪዎቹ እንዱከፍል ውሳኔ ሰጥቷል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አደጋው በደረሰበት ጊዜ ተሽከርካሪውን ሲያሽከረክር የነበረው ግለሰብ ይዞት የነበረው መንጃ ፈቃድ ተገቢ ወይም ሕጋዊ ያልሆነ መንጃ ፈቃድ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የአመልካች ክርክር በስር ፍርድ ቤቶች ታልፍ አመልካች በንግድ ሕጉ እና በመድን ውለ መሰረት የመካስ ኃላፉነት አለበት ተብል የመወሰኑን አግባብነት ተጠሪዎቹ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው ነጥቦች፡-
ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በመሆን በቀጥታ በአመልካች ላይ ክስ ማቅረባቸው ስነ ስርዓታዊ ነው ወይስ አይደለም?
አመልካቹን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በክርክሩ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለ መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዚሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ ከአንድ በላይ የሆኑ ከሳሾች የህብረት ክስ ሉያቀርቡ የሚችለበትን ሁኔታ በተመለከተ ብዙ ሰዎች በአንድ ምክንያት ወይም ዓይነታቸው አንድ በሆኑ በብዙ ምክንያቶች የተመሰረተ ክስ ሲያቀርቡና ምክንያቱም እያንዲንደን ከሳሽ የሚመለከት ሲሆን ከሳሾቹም ተነጣጥለው በየራሳቸው ስም ክስ ለማቅረብ የሚችለ ሲሆኑ ለክሱ መነሻ የሆነው ሀብት ወይም መብት የጋራ ወይም የየራሳቸው ቢሆንም እንኳ በሚቀርበው ክስ ሉወሰን የሚችለው የሕግ እና የስረ ነገር ጭብጥ አንድ ዓይነት ከሆነ ከሳሾቹ በሕብረት ሆነው አንድ ክስ ብቻ ለማቅረብ የሚችለ ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 35 ይደነግጋል።
በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ የተሽከርካሪው ባለቤት ሲሆኑ ክሱን ያቀረቡትም ከአመልካች ጋር ያላቸውን የመድን ውል መነሻ በማድረግ የመድን ሽፊን የተሰጠውን እና የመገልበጥ አደጋ የደረሰበትን ተሽከርካሪ ጠግኖ ወደ ነበረበት ለመመለስ ተጠሪው ያወጡትን ወጪ ለማስተካት እና የተቋረጠ ጥቅም ለማስከፈል በመሆኑ በተናጠልም ቢሆን በአመልካቹ ላይ ክስ ለማቅረብ መብትና ጥቅም ያላቸው መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። ቀሪዎቹ ተጠሪዎቹ ክስ ያቀረቡት በተሽከርካሪው ተሳፍረው የነበሩት ሰው እና የተሽከርካሪው ሾፋር በመሞታቸው ከሟቾቹ ስናገኘው የነበረው ጥቅም ቀርቶብናል በሚል ተገቢውን ካሳ ለማስወሰን ነው። በመሰረቱ ጉዲቱን አደረሰ የተባለው ተሽከርካሪ ባለንብረት 1ኛ ተጠሪ ናቸው። ስለዚህ 2ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ተቋርጦብናል ለሚለት ጉዲት የካሳ ክፍያ ክስ ሉያቀርቡ የሚችለት አግባብነት ባላቸው የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት በተሽከርካሪው ባለቤት ላይ እንጂ በአመልካች ላይ ላሆን አይችልም።
2ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች በተናጠል በአመልካቹ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚችለበት አግባብ ከላለ ደግሞ በጋራም በመሆን በአመልካቹ ላይ ክስ ሉያቀርቡ የሚችለበት ስነ ስርዓታዊ አግባብ አይኖርም።ተሽከርካሪው ለሚያደርሰው አደጋ እና ጉዲት ከአመልካች የተሰጠ የመድን ሽፊን መኖሩም ቢሆን 2ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎችን በቀጥታ በአመልካቹ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችላቸው አይሆንም። 2ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ከአመልካቹ ጋር ሉከራከሩ የሚችለት በ1ኛ ተጠሪ ላይ ክስ መስርተው በ1ኛ ተጠሪ ጠያቂነት አመልካች በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 43 ድንጋጌ መሰረት ወደ ጉዲዩ እንዱገባ የተደረገ በሆነ ጊዜ ነው። በመሆኑም ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በመሆን በቀጥታ በአመልካች ላይ ክስ ማቅረባቸው ስነ ስርዓታዊ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ይህንኑ ተገንዝቦ በክሱ አቀራረብ ስነ ስርዓታዊነት ረገድ ተገቢውን ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ መስጠት ሲገባው ከስነ ስርዓት ውጪ በሆነ አግባብ የቀረበለትን ክስ መርቶ ውሳኔ መስጠቱ እና ውሳኔውም በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተቀባይነት ማግኘቱ ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገው የመድን ውል በአንቀጽ 3 ስር የመድን ሽፊን የተሰጠው ተሽከርካሪ ለመንዲት ተገቢ የሆነውን መንጃ ፈቃድ ባልያዘ ወይም ይህን መንጃ ፈቃድ እንዲይዝ በተከለከለ ግለሰብ ሲነዲ ለደረሰ አደጋ መድን ሰጪው ኃላፉነት የማይኖርበት መሆኑን የሚደነግግ የማግለያ ድንጋጌ መኖሩ አላከራከረም። የስር ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ በአመልካቹ የቀረበውን ክርክር ሳይቀበለ የቀሩት የማግለያ ድንጋጌው ተገቢውን መንጃ ፈቃድ ባልያዘ ወይም እንዲይዝ በተከለከለ ግለሰብ የሚል እንጂ ሀሰተኛ መንጃ ፈቃድ በያዘ የሚል አነጋገር የላለው መሆኑን፣እንዱሁም 1ኛ ተጠሪ አሽከርካሪውን የቀጠሩት መንጃ ፈቃደን በማየት በመሆኑ እና የመድን ውለም በተሽከርካሪው ባለቤት ላይ የመንጃ ፈቃደን እውነተኛነት የማረጋገጥ ግዳታ የማይጥል መሆኑን በመግለጽ ነው። በመሰረቱ መንጃ ፈቃድ ማለት ባለሞተር ተሽከርካሪዎችን ለመንዲት የሚያስችል አግባብነት ባለው አዋጅ መሰረት በሚወጣ ደንብና መመሪያ መሰረት የሚሰጥ የመንጃ ፈቃድ ስለመሆኑ በትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር 468/1997 በአንቀጽ 2 (8) ስር ትርጉም የተሰጠው ሲሆን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 600/2000 በአንቀጽ 2 (3) የተመለከተው የመንጃ ፈቃድ ትርጉምም ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው።የ1ኛ ተጠሪ ሰራተኛ የነበሩት የተሽከርካሪው ሾፋር በተጠቀሱት አዋጆች ድንጋጌዎቸ መሰረት የተሰጠ መንጃ ፈቃድ ያልነበራቸው እና ይዘውት የነበረው መንጃ ፈቃድም የተሰጠው ለእርሳቸው ሳይሆን ለላላ ግለሰብ መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ ግለሰቡ ይዘውት የነበረው መንጃ ፈቃድ ሀሰተኛ ነው ከሚባል በቀር ተገቢ መንጃ ፈቃድ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም።
የማግለያ ድንጋጌው መሰረታዊ ዓላማ ተሽከርካሪው ተገቢውን ትምህርት እና ስልጠና ባልወሰደ እና ስልጣን ካለው አካል አግባብነት ባለው ሕግ እና ደንብ መሰረት ተገቢው መንጃ ፈቃድ ባልተሰጠው ግለሰብ ሲነዲ ለሚደርሰው ጉዲት የመድን ሰጪውን ኃላፉነት ለማስወገድ እንደሆነ የሚታወቅ በመሆኑ የተሽከርካሪው የመገልበጥ አደጋ የደረሰው አሽከርካሪው አግባብነት ባለው ሕግና ደንብ መሰረት በባለስልጣኑ ያልተሰጠውን ሀሰተኛ መንጃ ፈቃድ ይዞ ሲያሽከረክር በነበረበት ጊዜ መሆኑ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ በማግለያ ድንጋጌ መሰረት መድን ሰጪው በኃላፉነት የሚጠየቅበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም። በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔዎች ላይ የተጠቀሱት የንግድ ሕግ ቁጥር 654፣664 እና 668 ድንጋጌዎችም በመድን ውለ አንቀጽ 3 ላይ የተቀመጠውን የማግለያ ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚያስቀሩ አይደለም። በመሆኑም 1ኛ ተጠሪ የማግለያ ድንጋጌው የመንጃ ፈቃደን ሕጋዊነት የማረጋገጥ ግዳታ የሚጥልብኝ አይደለም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ለማለት የሚቻል አይደለም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ሰሜን ምዕራብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሽሬ እንዲስላሴ ምድብ ችልት በመዝገብ በ25/03/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ26/09/2006 ዓ.ም. በፍርድ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ሥነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በመሆን በአመልካቹ ላይ በጋራ ክስ ሉያቀርቡ የሚችለበት ሥነ - ስርዓታዊ አግባብ የለም በማለት ወስነናል።
ንብረትነቱ የ1ኛ ተጠሪ በሆነው ተሽከርካሪ ላይ የመገልበጥ አደጋ የደረሰው ተገቢውን መንጃ ፈቃድ ባልያዘ ወይም ሀሰተኛ መንጃ ፈቃድ በያዘ ግለሰብ ሲሽከረከር በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ ላቀረቡት ክስ በመድን ውለ አንቀጽ 3 በተመለከተው የማግለያ ድንጋጌ መሰረት አመልካች ኃላፉነት የለበትም በማለት ወስነናል።
ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት ተጠሪዎች መብታቸውን መጠየቅ የሚችለት የተሽከርካሪው ባለንብረት ከሆኑት 1ኛ ተጠሪ ነው በማለት ወስነናል።
እንዱያውቁት የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.