የመድን ሥራ የሚሰሩ የመድን ኩባንያዎች በመድን ፖሉሲ ውስጥ ፖሉሲውን ተጠያቂነትን አያስከትልም ወይም በፖሉሲው መሰረት የካሳ ክፍያ ጥያቄ መነሻ የሆነው ክስተት ከደረሰ በኃላ የተወሰነ ድርጊት ከተፈፀመ ወይም ሳይፈፅም ከቀረ ኃላፉነቱ ቀሪ ይሆናል የሚል የውል ሁኔታ ተፈፃሚነት የላለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 559/2000 በአንቀፅ 6 ንዐስ አንቀፅ 1 XXV ጉዲት ከደረሰም ኃላፉነት ለመውሰድ አይገደድም ከሚል መደምደሚያ ለብድር (ደቤ) ላይ ለተመሰረተ ግንኙነት ተፈፃሚ ሰላለመሆኑ ፤ የን/ሕ/ቁ 666 (4)
No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓሉ መሀመድ ተኽሉት ይመስል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ነገረ ፈጅ ጄሲያክን ቀረቡ ተጠሪ፡- የኖላ ካባ ወረዲ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ተወካይ ተስፊዬ ተሾመ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የመድን ዋስትና ክፍያ የሚመለከት ክርክር ሲሆን የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በመዝገብ በአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ይዘትም አመልካች ንብረትነቱ የተጠሪ ለሆነው ሰላዲ ቁጥር 4-02912 ኦሮ በውል 2020046113 ተጠሪ ባቀረበው ጥያቄ የኢንሹራንስ ዋስትና የብር 38,431.80 መስጠቱን የመድን ዋስትናውም በንግድ ህጉ መሰረት ተሟልቶ ተፈርሞ ከየካቲት 9 ቀን 2005 ዓ.ም እስከ የካቲት የ9 ቀን 2006 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ የአንድ ዓመት ዋስትና ተጠሪ የገዛ ቢሆንም የሚፈለግበትን ክፍያ እንዱከፍል ሲጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ አመልካች ክስ ለማቅረብ እንደተገደደ በመግለጽ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ከዚህ ጉዲይ ጋር ተመሳሰይነት ባለው ጉዲይ አስገዲጅ ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ ተጠሪ የሚፈለግበትን ክፍያ እንዱፈጽም እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪ በበኩለ በሰጠው መልስ የመድን ዋሰትና ከአመልካች ጋር የገባ መሆኑን ሳይክድ ንብረትነቱ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሆነ መኪና በኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ ስር ውለ እንዱገባ ከኦሮሚያ ምክር ቤት በቀን 29/11/2005 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ ውሳኔ ስለተላለፈ ውለን ሉቀጥልበት አይገባም፣ ተጠሪም አያስገድድም። በዚህ ውል ግዳታም የተፈፀመልኝ ነገር የለም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆንለት ተከራክሯል።
የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ
የሰጠው አስገዲጅ ውሳኔ ከተያዘው ጉዲይ ተመሳሳይነት እንደላለው፣ በንግድ ሕግ አንቀጽ 664 መሰረት ክፍያ ለኢንሹራንስ ከተከፈለ በኃላ ቀጥል ቢሆንም ኖሮ ውል ተቀባይ ጉዲት በንብረቱ ላይ የሚደርስ ከሆነ ውለ እንደ አዱስ መቀጠል እንዲለበት የውለን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንጂ አመልካች በፈለገበት ጊዜ ከሶ ክፍያ ማስፈጸም ወይም ውል እንዱያቋርጥ ገደብ የላለው መብት ለማጎናፀፍ አይደለም። አመልካች በዚህ ውል የሚኖሩት መብቶች ካለ ክፍያ ፈፀሞ አንድ ወር ካለፈ ውለ እንደተቋጠ ስለሚቆጠር የሚመጣው ኋላፉነት ለመውሰድ አይገደድም። በዚህ ክርክር ውስጥ ደግሞ ተጠሪም ክፍያ ያቋረጠው ከዓመት በላይ ከመሆኑም በላይ የመድን ውል ጊዜ ገደቡም በቀን 09/06/2006 ዓ/ም የተጠናቀቀ ስለሆነ ተጠሪ የመድን ዋስትና ውል ገንዘብ እንዱከፍል የሚገደድበት ሁኔታ ስለላለ የቀረበውን ክስ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.
33/2/ መሰረት ውድቅ በማድረግ ተጠሪ በነፃ እንዱሰናበት ወስኗል።
አመልካች በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔና ትዕዛዝ በመቃወም ለማሳረም ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ሰረታዊ ይዘትም የተጠሪ ንብረት የሆነውን የሰላዲ ቁጥር 4-02912 ኦሮ አምቡላንስ ተሸከርካሪ ለአንድ ዓመት የሚቆይ በደቤ ማስታወሻ የመድን ሽፊን የሰጠ ስለመሆኑ የአርቦን ክፍያ ጊዜው በስምምነት ያልተገለጸ ስለሆነ መድን ሰጪ መብቱን ያለ ምንም ቅደመ ሁኔታ በ2 ዓመት ውስጥ ከሶ መጠየቅ እንደሚችል የውል ግዳታውም ተጠሪ ሽፊን ለተሰጠበት ጊዜ የ11 ወር ከ11 ቀን አርበን ተሰልቶ ሉከፈል እንደሚገባ የሚያስገደድ ስለመሆኑ በመግለጽ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔና ትዕዛዝ ተሸሮ ተጠሪ የመድን ሽፊኑ ለተገለገለበት ጊዜያት አርበን ተሰልቶ እንዱከፈለው እንዱወሰን የሚጠይቅ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
ይህ ችልትም መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ግራ ቀኙን ሐምል 27/2008 ዓ/ም በቃል ከማነጋገሩ በተጨማሪ በተጠሪ ተፃፈ የተባለትን የኢንሹራንስ ውል ማቋረጫ ደብዲቤዎች ወደ አመልካች መቼ ገቢ እንደተደረጉ ለመለየት ደብዲቤዎቹን በማስቀረብ ተመልክቷል።
ከስር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነውን ውሳኔ አግባብነት ከላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህ ችልት ምላሽ የሚያሻው ዓብይ ነጥብ የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ለአመልካች የመድን ውለ ሽፊን ለመክፈል አይገደድም በማለት የሰጡት ውሳኔ በሕጉ አግባብነት ወይስ አይደለም? የሚል ሆኖ አገኝቶታል።
ከስር የክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች እና ተጠሪ ለአንድ ዓመት ጸንቶ የሚቆይ የመድን ዋስትና ውል ስምምነት ያደረጉ ስለመሆናቸው ያከራከራ ጉዲይ አይደለም። የአሁኑ ተጠሪ የመድን ዋስትና ከአመልካች ጋር መግባቱን ላይክድ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውሳኔ መሰረት በክልለ ያለ የመንግስት መኪናዎች ከኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር ውል እንዱገቡ በመወሰኑ ከአመልካች ጋር የነበረውን ግንኝነት ማቋረጡን በስር ፍርድ ቤትና በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ካቀረበው ክርክር ተረድተናል። አመልካች በበኩለ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የንግድ ህግ ቁጥር 666 የተረጎመበት አግባብ ተገቢ አለመሆኑን፤ የኢንሹራንስ ውል ማቋረጫ ደብዲቤ ሁለት ጊዜ ቢፅፈም በአንድ ቀን ጥር 22/2006 ዓ/ም የደረሰው ስለመሆኑ፤ የአርቦን ክፍያውም በደቤ ማስታወሻ የተሰጠ እንጂ ከመጀመሪያውኑ የመክፈያ ቀን ያልተቆረጠለት ስለመሆኑ በመግለጽ የስር ፍርድ ቤቶች ድምዲሜ ተገቢነት እንደላለው መከራከሩን ተገንዝበናል።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች የአርቦን ከፍያው በአንድ ወር ጊዜ ባለመጠየቁ ውለ እንደተቋረጠ ስለሚቆጠር ክፍያውን መጠየቅም ሆነ ጉዲት ከደረሰም ኋላፉነት ለመውሰድ አይገደድም ከሚል ድምዲሜ ላይ መደረሱን የውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። አመልካች እና ተጠሪ አደረጉት የተባለው የመድን ውል ቆይታው አንድ ዓመት እንደነበር አላከራከረም ተጠሪ አመልካች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የአርቦን ክፍያውን መጠየቅ ነበረበት የሚል ክርክር ያቀረበ ቢሆንም የግራቀኙ ስምምነት ክፍያው በአንድ ወር ካልተጠየቀ ቀሪ እንደሚሆን ስለመስማማታቸው በህግ የተደገፈ ክርክር አላቀረበም። በልላ በኩል አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረገው የመድን ውል ስምምነት በደቤ ማስታወሻ የተሰጠ ስለመሆኑ ካቀረበው ክርክር ተመልክተናል። ተጠሪ በግራ ቀኙ የነበረው የመድን ውል ስምምነት በደቤ ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን በመካድ ያቀረበው ህጋዊ ክርክር የለም። የግራ ቀኙ ግንኙነት በብድር /ደቤ/ ላይ የተመሰረተ ከሆነ ደግሞ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የታወቀ ጊዜ የተቆረጠለት የአርቦን ክፍያ እንደሆነ በመውሰድ የንግድ ህግ ቁጥር 666 (4) መሰረት በማድረግ ከአንድ ወር በኋላ ክፍያ መጠየቅ እንደማይቻል ደምድሞ የአመልካችን ክስ ውድቅ ማድረጉ በሕጉ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
የአሁኑ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ላላ የክርክር ነጥብ እና በሥር የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተቀባይነት ያገኘው ውል የተቋረጠበት ጊዜ የተመለከተ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ የክልለ መንግስት በሰጠው ውሳኔ መሰረት የክልለ መኪናዎች ከክልለ እንሹራንስ ኩባንያ ጋር የመድን ውል እንዱገቡ ያዘዘ በመሆኑ የውል ማቋረጫ ደብዲቤ በቀን 12/11/2005 እና በ20/05/2006 ዓ/ም ለአመልካች ጽፈናል የሚል ነው። አመልካች በበኩለ ከተጠሪ የተፃፈ ደብዲቤዎች ገቢ የሆኑት ጥር 22/2006 ዓ/ም መሆናቸውን አጥብቆ ተከራክሯል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አስቀርቦ የተመለከታቸው ሁለቱም ደብዲቤዎች ለአመልካች ጽ/ቤት ገቢ የሆኑት ጥር 22 ቀን 2006 ዓ/ም መሆኑን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለአመልካች ተላኩ የተባለ ደብዲቤዎች በ12/11/2005 እና በ20/5/2006 የተፃፈ ስለመሆናቸው ግልጽ ቢሆንም ለአመልካች በተፃፈበት ቀን ገቢ ስለመሆናቸው በተጠሪ በኩል የቀረበ ማረጋገጫ የለም። እንዱህ ከሆነ ደግሞ የአሁኑ ተጠሪ ውለ እንዱቋረጥ በወቅቱ ጠይቀናል በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ በአመልካች የተጠየቀው የአርቦን ክፍያ የመክፈል ግዳታ የለበትም በማለት የደረሱበት ድምዲሜ የግራ ቀኙ ስምምነት የንግድ ሕጉ መሰረታዊ ይዘትና ዓለማ ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህታት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
ተጠሪ በደቤ ሽፊን ለተሰጠው ተሸከርክሪ መክፈል ያለበት አርቦን መኖሩ ከተረጋገጠ ቀጥል መታየት ያለበት የአርቦን መጠኑ ነው። በግራ ቀኙ ስምምነት መሰረት በአመት መከፈል ያለበት የገንዘብ መጠን 38,431.80 መሆኑ አላከራከረም። ተጠሪ ውል ማቋረጡን ያሳወቀው የውል ዘመኑ ከመጀረ ከ11 ወር ከ11 ቀን በኃላ ስለመሆኑ አመልካች ካቀረበው የሰበር አቤቱታ ተረድተናል። ተጠሪ በሰበር ሰሚ ችልት በሰጠው መልስ በአመልካች የተጠቀሰው ጊዜ ተገቢ አለመሆኑን በመካድ ያቀረበው ክርክር የለም። ተጠሪ የተገለገለበት የ11 ወር ከ11 ቀናት የአርቦን ክፍያ መጠን 36,403.45/ ሰላሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሶስት ከአርባ አምስት ሳንቲም /መሆኑን አመልካች በሰበር አቤቱታ አመልክቷል። የአሁኑ ተጠሪ በሰበር ችልት በሰጠው መልስ ከላይ የተገለፀውን መጠን ገንዘብ አለመሆኑን በግልጽ ያቀረበው ክርክር የለም በተጠሪ በኩል በግልጽ ያልተካዲ ፍሬ ጉዲይ እንደታመነ የሚቆጠር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 83 እና 235 ያስገነዘቡናል። ከዚህ አንፃር ተጠሪ ውለን እስከ ተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ለተገለገለበት የኢንሹራንስ ጊዜያት አርቦን ተሰልቶ የ11 ወር ከ11 ቀናት ብር 36,403.45 የመክፈል ኋላፉነት አለበት ብለናል። በዚህ ሁለ ምክንያቶች የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ በሰጠው የመድን ውል ሽፊን ተጠሪ ለተገለገለበት የኢንሹራንስ ጊዜያት በውለ መሰረት ተገቢ የአርቦን ክፍያ መክፈል እያለበት ተጠያቂ ላሆን አይገባም በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ሽረን ተከታዩን ወስነናል።
የኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 29030 በ19/06/2007 ዓ/ም የሰጠው ብይን የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በ25/9/2007 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል ። ይፃፍ።
ተጠሪ ለተገለገለበት የኢንሹራንስ ጊዜያት አርቦን የመክፈል ኋላፉነት አለበት በማለት ወስነናል። ተጠሪ ለአመልካች ብር 36,403.45 (ሰላሳ ስድስት ሺ አራት መቶ ሶስት ከአርባ አምስት ሳንቲም) ይክፈል ብለናል። ይፃፍ።
የዚህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ወደ መ/ቤት ይመለሰ።
No topics extracted.