የአንድ ሰው መብትና ግዳታ ለተወላጆቹ በውርስ ሉተላለፍ የሚችለው በሟቹ ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆነ በቀር ሟቹ በሞተበት ቀን የነበሩት መብቶችና ግዳታዎች ወ/ሮ ፅጌሬዲ በቀለ እና ወ/ሮ ፍቅርተ በቀለ XXIV የፍ/ሕ/ቁ. 826/2/ ሟች የድርሻ መልቀቅ ውል ፈጽሞ ከዚያም ኑዛዜ ቢያደርግና ይኽው ኑዛዜ የድርሻ መልቀቁን ውል እስካልነካ ድረስ የውለን ተፈጻሚነት ሉያስቀር የማይችል ወይም በአዱሱ ኑዛዜ ተተክቷል ልባል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 900 እና 901 ባንክና ኢንሹራንስ 319
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 16 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ረታ ቶልሳ አዲነ ንጉሴ ሙስጠፊ አህመድ አምልካች፡- ብሓራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ (አ.ማ) - ነ/ፈጅ ወርቅነህ ዘውደ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ነፃነት ሀቤቤ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፤
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ጉዲዩ ተሸከርካሪ የሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዲት የተሰጠ የመድን ሽፊን ኃላፉነትን የሚመለከት ነው። ከስር ፍርድ ቤት በዚህ ክርክር ወ/ሮ አለምነሽ ገብረ ማርያም በራሷና ሞግዚት በሆነችላቸው እነ ህፃን አዱስ ብርሃኑ(አራት ሕፃናት) ስም ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ አመልካች ደግሞ ሶስተኛ ወገን ተከራካሪ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ወ/ሮ አለምነሽ ገብረማርያም በተጠሪ ላይ ያስቀረበችው ክስ ነው ወ/ሮ አለምነሽ ገብረማርያም የተጠሪ ንብረት ቁጥር 3-178887 የሆነ መኪና የልጆች አባት የሆነውን አቶ ብርሃኑ ጥላሁንን የግጭት ጉዲት አድርሶበታል ባለቤቴና የልጆቼ አባት በአደጋው በደረሰበት ጉዲት ምክንያት ስለሞተ በእኔና ልጆቹ በመተዲደሪያ እረገድ ለደረሰብን ጉዲት ብር 541,538 (አምስት መቶ አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) ካሳ እንዱከፈል ውሳኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርባለች ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርባ የተጠየቀውን የካሳ መጠን በመቃወም ክርክር ያቀረበች ሲሆን አመልካች የመድን ሽፊን የሰጠ በመሆኑ በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ ትዕዛዝ እንዱሰጥላት ጠይቃለች አመልካች በክርክሩ ገብቶ የተጠሪ መኪና በሶስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው ጉዲት ለአንድ ሰው እስከ ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) የመድን ሽፊን የሰጠ መሆኑን ከገለፀ በኃላ ተጠሪ በመድን ታሳቢ መሰረት አደጋው የደረሰ መሆኑን የማሳወቅ ግዳታዋን አልተወጣችም። ስለዚህ በመድን ውለ መሰረት ሽፊን እንድሰጥ አልገደድም። በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን መከራከሪያ ውድቅ በማድረግ ተጠሪ ለወ/ሮ አለምነሽ ገብረማርያና ልጆቻቸው ብር 222,538 ወይም /ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ ስምንት እንድትከፍል ወስኗል። ከዚህ የካሳ ገንዘብ አመልካች ብር 40.000 (አርባ ሺህ) እንዱከፍል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቧል።
የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች መጋቢት 10 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ አደጋው የደረሰ መሆኑን በአስር ቀን ውስጥ ለአመልካች የማሳወቅ ግዳታ በመድን ውለ ገብታለች። ተጠሪ በ10 ቀን ውስጥ አደጋ የደረሰ መሆኑን ያላሳወቀች በመሆኑ አመልካች በመድን ውል መሰረት ብር 40.00 የመክፍል ግዳታ የለበትም የበታች ፍርድ ቤቶች በግልፅ የተቀመጠውን የውል ቃል በመተላለፍ አመልካች በመድን ውል መሰረት ኪሳራውን እንዱጋራ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ ሚያዝያ 21 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈው መልስ ተጠሪ በአስር ቀን ውስጥ አደጋው የደረሰ መሆኑን ለአመልካች አለማሳወቄ አመልካች በመድን ውል መሰረት ለሶስተኛ ወገኖች የመድን ሽፊን የሰጠበትን ገንዘብ የመክፈል ኃላፉነቱን አያስቀርም። ስለሆነም የአመልካች ክርክር የህግ ድጋፍ የላለው በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክራለች አመልካች ግንቦት 15 ቀን 2005 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል፤
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆነ እኛም አመልካች የመድን ሽፊን የሰጣት የመለያ ቁጥር 3-17887 የሆነችው መኪና በሟች ብርሃን ጥላሁን ላይ ባደረሰው የሞት እደጋ ተጠሪ ከተወሰነባት የካሳ ገንዘብ ውስጥ አመልካች ብር 40,000 (አርባ ሺህ) ለሟች አቶ ብርሃን ጥላሁን ሚስትና ልጆች እንዱከፍል የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የተጠሪ መኪና በልላ ሰው አካል ወይም ህይወት ላይ ለሚያደርሰው አደጋ እስከ ብር 40,000 (አርባ ሺህ) ኃላፉነቱን ለመጋራት የመድን ሽፊን የሰጠ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። አመልካች የመድን ሽፊን የሰጣት መኪና በሟች ብርሃን ጥላሁን ላይ የሞት አደጋ ማስከተሎና ተጠሪ ለጉዲቷ ኃላፉ መሆኗ በፍርድ ቤት ውሳኔ ተረጋግጧል። አመልካች የሚከራከረው በሰጠሁት የመድን ሽፊን መሰረት ገንዘቡን ለከሳሾች የምከፍለው ተጠሪ በመድን ውለ መሰረት በአስር ቀን ውስጥ አደጋው የደረሰ መሆኑን ብታሳውቀኝና ግዳታዋን ብትወጣ ነበር። ተጠሪ የውል ግዳታዋን ያልተወጣችና በአስር ቀን ውስጥ አደጋው መድረሱን ያላሳወቀችው በመሆኑ የመድን ሽፊን የሰጠሁበትን ገንዘብ ለከሳሾች የመክፈል ግዳታ የለብኝም በማለት ነው። ተጠሪ አደጋው የደረሰ መሆኑን በአሰር ቀን ውስጥ ለአመልካች ለማሳወቅ የውል ግዳታ የገባች መሆኑን በመካድ ያቀረበችው ክርክር የለም። ተጠሪ የምትከራከረው እኔና አመልካች በቅድመ ሁኔታነት በመድን ውል የተዋዋልነው ሃይለ ቃል በህግ ያልተፈቀደ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት ነው።
ሕግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች በቀር ተዋዋዮች ሁለ የሚዋዋለበትን ጉዲይ የመወሰን መብት ያላቸው መሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1711 ተደንግጓል። የመድን ሥራ የሚሰሩ የመድን ኩባንያዎች በመድን ፖሉሲ ውስጥ ፖሉሲውን ተጠያቂነትን አያስከትልም ወይም በፖሉሲው መሰረት የካሳ ክፍያ ጥያቄ መነሻ የሆነው ክስተት ከደረሰ በኃላ የተወሰነ ድርጊት ከተፈፀመ ወይም ሳይፈጸም ከቀረ ኃላፉነቱ ቀሪ ይሆናል የሚል የውል ሁኔታ ተፈፃሚነት የላለው መሆኑ ስለተሸከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ዋስትና የወጣው አዋጅ ቁጥር 559/2000 በአንቀፅ 6 ንዐስ አንቀፅ 1 በግልፅ ተደንግጓል። ከዚህ የህግ ድንጋጌ አንፃር ሲታይ አመልካች ተጠሪ አደጋው ከደረሰ በኃላ በአስር ቀን ውስጥ ካላሳወቀችኝ በመድን ፖሉሲው መሰረት ገንዘቡን ለተጎጂዋ (ለከሳሾች) የመክፈል ኃላፉነት የለብኝም በማለት ያቀረበው ክርክር ከላይ ይዘቱ የተገለፀውን የህግ ድንጋጌ የሚጥስና የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል። ከዚህ አንፃር አመልካች የበታች ፍርድ ቤቶች በመድን ፖሉሲው መሰረት ብር 40,000 (አርባ ሺህ) ብር ለከሳሾች እንዱከፍል መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት መጋቢት 16 ቀን 2005 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.