የአንድ ሰው መብትና ግዳታ ለተወላጆቹ በውርስ ሉተላለፍ የሚችለው በሟቹ ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆነ በቀር ሟቹ በሞተበት ቀን የነበሩት መብቶችና ግዳታዎች ወ/ሮ ፅጌሬዲ በቀለ እና ወ/ሮ ፍቅርተ በቀለ XXIV የፍ/ሕ/ቁ. 826/2/ ሟች የድርሻ መልቀቅ ውል ፈጽሞ ከዚያም ኑዛዜ ቢያደርግና ይኽው ኑዛዜ የድርሻ መልቀቁን ውል እስካልነካ ድረስ የውለን ተፈጻሚነት ሉያስቀር የማይችል ወይም በአዱሱ ኑዛዜ ተተክቷል ልባል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 900 እና 901 ባንክና ኢንሹራንስ 319
No summary available.
.. ጥቅምት 30 ቀን 2009 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወ/ሮ ጽጌረዲ በቀለ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፍቅርተ በቀለ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ውርስን የሚመለከት ክርክር ሲሆን የተጀመረውም የሟች አቶ በቀለ ካሣ ውርስ ይጣራልኝ ሲለ የአሁኗ አመልካች በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ነው።የአሁኗ ተጠሪም በጉዲዩ በጣልቃ ገብነት ተከራክረዋል።ግራ ቀኙ ከተለያዩ እናቶች የተወለደ የአንድ አባት ልጆች መሆናቸውን መዝገቡ ያመለክታል።
ፍርድ ቤቱም በጣልቃ ገቧ አቤቱታ ላይ የአመልካቿን አስተያየት ከተቀበለ በኃላ ጉዲዩን ወደ ውርስ አጣሪ የመራው ሲሆን አጣሪዋም ውርሱን ካጣሩ በኃላ አከራካሪ ሆኖ የቀረበውን በጉለላ ክፍለ ከተማ በወረዲ 3 የሚገኝ በቤት ቁጥር 460 የሚታወቀውን ቤት ሟች አቶ በቀለ ካሣ ግማሹ የጣልቃ ገቧ እናት የወ/ሮ በቀለች ጎሽሜ ሆኖ ግማሹ ግን የእርሳቸው መሆኑን ገልጸው የራሳቸውን ድርሻ በ19/11/1997 ዓ.ም. በአዋዋይ ፉት በተደረገ የድርሻ መልቀቅ ውል ለጣልቃ ገቧ እንደለቀቁ ከቀረቡት ማስረጃዎች አጣሪዋ መገንዘብ መቻላቸውን፣ይሁን እንጂ የቤቱን አጋማሽ ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ሆኖ ቀሪው ግማሽ ደግሞ በሟች አባታቸው በተደረገላቸው የድርሻ መልቀቅ ውል መሰረት የቤቱን ስመ ሀብት ወደ ራሳቸው አዛውረው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ በአንድ በኩል የአሁኗ ተጠሪ መከራከራቸውን፣በልላ በኩል ደግሞ አመልካች የድርሻ መልቀቅ ውለ ተደረገ የተባለው አመልካችን ሆነ ብል ከውርስ ለመንቀል በመሆኑ ተቀባይነት እንደላለው እና ሟች የድርሻ መልቀቅ ውለን አደረጉ ከተባለ በኃላም ቤቱን በስማቸው አድርገው ሲጠቀሙበት እንደቆዩ በመግለጽ የድርሻ መልቀቅ ውለ ተቀባይነት ሉኖረው እንደማይገባ መከራከራቸውን ገልጸው በጉዲዩ ላይ ፍርድ እንዱያርፍበት በሚል፣ እንዱሁም ከቤቱ ኪራይ የተገኘው ገንዘብ የውርስ ሀብት ነው የሚል እና ላልችም ፍሬ ነገሮች የተገለጹበትን በ18/09/2005 ዓ.ም. የተዘጋጀ ሪፖርት አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም በሪፖርቱ ላይ የግራ ቀኙን አስተያየት ተቀብል ጉዲዩን ከመረመረ በኃላ የቤቱ አጋማሽ በእናታቸው በኩል ለተጠሪዋ በውርስ የተላለፈ ሆኖ ቀሪውን ግማሽ ደግሞ ሟች በድርሻ መልቀቅ ውለ መሰረት ለተጠሪዋ ማስተላለፊቸው የተረጋገጠ በመሆኑ ቤቱ የውርስ ሀብት አካል አይደለም፣ቤቱ የውርስ ሀብት አይደለም ከተባለ ደግሞ ከቤቱ የተገኘው የኪራይ ገንዘብም የውርስ ሀብት ላሆን ስለማይችል አጣሪዋ ከዚሁ ቤት የተገኘው የኪራይ ገንዘብ የውርስ ሀብት ነው በማለት ሪፖርት ማቅረባቸው ተቀባይነት የላለው መሆኑን ገልጾ ሪፖርቱን በዚህ አግባብ በማሻሻል በመዝገብ በ29/09/2006 ዓ.ም. ውሳኔ የሰጠ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካቿ አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን በመዝገብ በ06/04/2007 ዓ.ም. ዘግቶ በማሰናበቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመሮምሮ በዚህ ጉዲይ አከራካሪው ቤት የውርስ ሀብት ሳይሆን የተጠሪዋ የግል ሀብት ነው በሚል በስር ፍርድ ቤቶች ተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ሟች በ19/11/1997 ዓ.ም. ለተጠሪ ጥቅም አድርገውት የነበረውን ስጦታ በ26/12/1997 ዓ.ም. ባደረጉት ኑዛዜ የተኩት እና ኑዛዜው ደግሞ አመልካችን ከውርስ የነቀለ ነው ተብል በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ በ30/11/2007 ዓ.ም. ከተሰጠው ገዥ ውሳኔ አንጻር ተጠሪዋ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የአንድ ሰው መብትና ግዳታ ለተወላጆቹ በውርስ ሉተላለፍ የሚችለው በሟቹ ሞት ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆነ በቀር ሟቹ በሞተበት ቀን የነበሩት መብቶችና ግዳታዎች ስለመሆናቸው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 826 (2) ድንጋጌ ይዘት ያመለክታል።በተያዘው ጉዲይ ሟች የአከራካሪው ቤት አጋማሽ ድርሻ የሟች ባለቤታቸው ማለትም የአሁኗ ተጠሪ እናት መሆኑን በማረጋገጥ በቤቱ ላይ ያላቸውን ግማሽ ድርሻ በ19/11/1997 ዓ.ም. በአዋዋይ ፉት በተደረገ የድርሻ መልቀቅ ውል ለአሁኗ ተጠሪ ያስተላለፈ ስለመሆኑ እና በሞት የተለዩትም በ28/08/2004 ዓ.ም. ስለመሆኑ በአመልካቿም ያልተካደ እና በክርክሩም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው።ሟች በአከራካሪው ቤት ላይ የነበራቸውን ግማሽ ድርሻ አስቀድመው በ1997 ዓ.ም. ለተጠሪዋ በውል ማስተላለፊቸው ከተረጋገጠ ደግሞ ይህ ቤት በሞቱበት 2004 ዓ.ም. የእርሳቸው ንብረት ነበር ልባል የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም።
አመልካቿ አጥብቀው የሚከራከሩት ሟች አድርገውት የነበረው የድርሻ መልቀቅ ውል ከአንድ ወር በኃላ አካባቢ በ26/12/1997 ዓ.ም. በተደረገ ኑዛዜ የተተካ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 900 እና 901 ድንጋጌዎች መሰረት የድርሻ መልቀቅ ውለ ውጤት እንደላለው መቆጠር አለበት በማለት መሆኑን የሰበር አቤቱታቸው ይዘት ያመለክታል።በቁጥር 900 የተመለከተው ድንጋጌ በኑዛዜ የተሰጠን ነገር በሙለ ወይም በከፉል ተናዛዡ ፈቅድ ለላላ ሰው ያስተላለፈ በሆነ ጊዜ አስቀድሞ ተደርጎ የነበረው ኑዛዜ ፈራሽ እንደሚሆን የሚደነግግ ሲሆን በቁጥር 901 የተመለከተው ድንጋጌ ደግሞ አንድ ተናዛዥ አስቀድሞ አንድ ኑዛዜ ካደረገ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ላላ ኑዛዜ አድርጎ መገኘቱ የሚያስከትለውን ሕጋዊ ውጤት የሚመለከት ነው።በተያዘው ጉዲይ ኑዛዜው የተደረገው ከድርሻ መልቀቅ ውለ በኃላ እንጂ በፉት ባለመሆኑ እና ሟች ኑዛዜ አድርገዋል የተባለውም አንድ ጊዜ ብቻ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ በቁጥር 900 እና 901 የተመለከቱት ድንጋጌዎች ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው አይደለም።ሟች በ26/12/1997 ዓ.ም.
ባደረጉት ኑዛዜም ቀደም ሲል አድርገውት የነበረው የድርሻ መልቀቅ ውል እንደተጠበቀ መሆኑ ከመገለጹ ውጪ ሟች የድርሻ መልቀቅ ውለን በኑዛዜው የመተካት ሀሳብ የነበራቸው መሆኑን የሚጠቁም እንዲልሆነ በዚሁ ፍርድ ቤት በመዝገብ ውስጥ ተያይዘው ከሚገኙት የድርሻ መልቀቅ ውል እና የኑዛዜ ሰነድች ይዘት ተገንዝበናል። በመሆኑም ሟች ቀደም ሲል አድርገውት የነበረውን የድርሻ መልቀቅ ውል በኑዛዜው እንደተኩት ተደርጎ በማስቀረቢያ ትዕዛዙ ላይ የሰፈረው ፍሬ ነገር የመዝገቡን ግልባጭ መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
የኑዛዜ ይሰረዝልኝ ጉዲይን አስመልክቶ በግራ ቀኙ መካከል በመዝገብ በነበረው ክርክር በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በ30/11/2007 ዓ.ም. የተሰጠውን ውሳኔ በተመለከተ ግራ ቀኙ ሲከራከሩ የነበረው የኑዛዜ ሰነደን ብቻ መሰረት በማድረግ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በዚህ ረገድ የቀረበውን ክርክር ከሕጉ አንጻር መርምሮ በኑዛዜው ለአሁኗ ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ቤት በተሰጠበት ሁኔታ ለአመልካቿ ብር አንድ ሺህ ብቻ መሰጠቱ ከውርስ እንደተነቀለ የሚያስቆጥር በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 938 እና 939 ድንጋጌዎች መሰረት ግራ ቀኙ የአከራካሪው ቤት እኩል ወራሽ ናቸው በሚል በስር ሁለቱ የበላይ ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ በማጽናት ውሳኔ ሰጥቷል።በመዝገብ በነበረው ክርክር የአሁኗ አመልካች መቃወሚያ ያቀረቡትም ሆነ በየእርከኑ ባለ ፍርድ ቤቶች አከራካሪ ጭብጥ ሆኖ ቀርቦ የነበረው የኑዛዜው ዋጋ እና ሕጋዊ ውጤት እንጂ የድርሻ መልቀቅ ውለ ሕጋዊነት ጉዲይ ጭምር አይደለም።በክርክሩ አመልካች የነበሩት የአሁኗ ተጠሪ ‛…በሕግ አግባብ የተደረገ ስጦታ አለ የሚለ ከሆነ በዚህ ረገድ የሚያቀርቡትን ክርክር ይህ ውሳኔ አያግደውም..“በሚል ተፈጻሚነት ባለው የውሳኔው ክፍል በተራ ቁጥር ሁለት ስር በግልጽ የሰፈረውም በዚሁ ምክንያት ነው።በመሆኑም በመዝገብ የተሰጠው ውሳኔ በስጦታ /በድርሻ መልቀቅ/ ውል ላይ በቀጣይ ሉነሳ የሚችለውን ክርክር ታሳቢ አድርጎ የተሰጠ እንጂ የድርሻ መልቀቅ ውለ በኑዛዜ ስለተተካ ሕጋዊ ውጤት የለውም ከሚል ድምዲሜ ላይ የተደረሰበት አይደለም።አመልካቿ በሕጉ አግባብ ያላፈሩት እስከሆነ ድረስ ደግሞ የድርሻ መልቀቅ ውለ ዋጋ የሚያጣበት ሕጋዊ ምክንያት ባለመኖሩ የስር ፍርድ ቤቶች የቤቱ አጋማሽ በእናት መስመር በውርስ ለተጠሪዋ የተላለፈ ሆኖ ቀሪውን ግማሽ ደግሞ የግራ ቀኙ አባት በ19/11/1997 ዓ.ም. በአዋዋይ ፉት በተደረገ የድርሻ መልቀቅ ውል ለአሁኗ ተጠሪ ያስተላለፈ በመሆኑ ቤቱ የሟች አቶ በቀለ ካሣ የውርስ ሀብት አይደለም በሚል የደረሱበት ድምዲሜ እና ይህንኑ ድምዲሜ መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሳኔ የሚነቀፍበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።አከራካሪውን ቤት የግራ ቀኙ አባት የአሁኗን ተጠሪ እናት ከማግባታቸው በፉት ያፈሩት ነው ከማለት በቀር በእናት መስመር ከቤቱ የውርስ ድርሻ አለኝ በማለት አመልካቿ በስር ፍርድ ቤቶችም ሆነ በዚህ ሰበር ደረጃ ያቀረቡት ክርክር አለመኖሩን ተገንዝበናል።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የውርስ አጣሪዋን ሪፖርት በማሻሻል በመዝገብ በ29/09/2006 ዓ.ም. የሰጠው እና በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ06/04/2007 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ፀንቷል።
የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ሰለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
የሐሳብ ልዩነት አብላጫው ድምጽ የቤቱ አጋማሽ በእናት መስመር በውርስ ለተጠሪ የተላለፈ ሆኖ ቀሪውን ግማሽ የግራቀኙ አባት ሐምላ 19 ቀን 1997 ዓ.ም በአዋዋይ ፊት በተደረገ የድርሻ መልቀቅ ውል ለአሁን ተጠሪ ያስተላለፉ በመሆኑ ቤቱ የሟች አቶ በቀለ ካሳ የውርስ ሀብት አይደለም ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል። ሆኖም ሟች ሐምላ 19 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገ የድርሻ መልቀቅ ውል ስምምነት አከራካሪውን ቤት ከሟች ባለቤታቸው ወ/ሮ በላይነሽ ጎሽሜ ጋር በጋራ ያፈሩት መሆኑን በመጥቀስ ድርሻቸውን ለተጠሪ የለቀቁ መሆኑን የሚያሳይ ቢሆንም ሟች ይህንኑ ቤት በተመለከተ ነሐሴ 26 ቀን 1997 ዓ.ም ባደረጉት ግልጽ ኑዛዜ ድርሻቸውን ለተጠሪ የተናዘዙላት መሆኑን የኑዛዜው ሰነድ ያሳያል። በዚህ የኑዛዜ ሰነድ ላይ ክርክር ተደርጎበት የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 88358 ሐምላ 30 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ሟች ያደረጉት ኑዛዜ አመልካችን በተዘዋዋሪ መንገድ በዝምታ ከውርስ የነቀለ በመሆኑ አመልካች ከጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል ወራሽ በመሆን የውርስ ንብረቱን ሉከፋፈለት ይገባል በማለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እና ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ መሆኑን ጠቅሶ ውሳኔውን በማጽናት ተጠሪ በሕግ አግባብ የተደረገ ስጦታ አለ የሚለ ከሆነ በዚህ ረገድ የሚያቀርቡትን ክርክር ውሳኔው አያግደውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ሟች ነሐሴ 26 ቀን 1997 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ ሐምላ 19 ቀን 1997 ዓ.ም ያደረጉት የድርሻ መልቀቅ ውል ስምምነት የተጠበቀ ነው በማለት የገለጹ ቢሆንም የሟች ኑዛዜ አመልካችን ከውርስ የነቀለ ነው በማለት አመልካች ከጠቅላላ የኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል ወራሽ እንድትሆን በዚሁ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ የተሰጠበት በመሆኑ ሟች በቤቱ ላይ አስቀድሞ ያደረጉት የድርሻ መልቀቅ ውል ስምምነት ውጤት ያበቃለት ነው፤ ይህ የሰበር ሰሚ ችልት አመልካች እና ተጠሪ እኩል ወራሽ ናቸው በማለት በሰጠው ውሳኔ መሰረት የሟች ድርሻ ሉከፋፈል ይገባል በማለት ስማችን በተ.ቁ. 3 እና 5 ላይ የተጠቀሰው ዳኞች አብላጫው ድምጽ ከደረሰበት ድምዳሜ በሃሳብ ተለይተናል።
No topics extracted.