ሟች በተወው ኑዛዜ መሰረት ውርሱ ሲጣራ እንዱሁም ኑዛዜው በፍ/ቤት ሲፀድቅ ተቃውሞ ሳያቀርብ ፤ ኑዛዜው ከፀደቀ በኃላ ኑዛዜው ይሻርልኝ በማለት የሚቀርብ አቶ ተስፊዬ በቀለ እና እነ ወ/ሮ እሸቷ ጎሸዬ 23/1/ 2009 ዓ.ም 304 XXIII ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ ፤ በሥር ፍ/ቤት ያልቀረበን ክርከር በይግባኝ ደረጃ ላይ ማቅረብ ተቀባይት የላለው ሰለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 329 (1) ( 3 ሰዎች ) 64. አንድ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ወራሽነት መብቱን ለአካላ መጠን ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 15 ዓመት ባለው ጊዜ ውሰጥ የውርሱን ንብረት ለመጠየቅ በይርጋ የማይታገድበት ስለመሆኑ ፤ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 198 ፣ 1000(2)
No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ቀነዓ ቂጣታ ክፍለጽዮን ማሞ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- አቶ ተስፊዬ መኮንን …….. ጠበቃ አቶ ጥባቡ ምህረቴ ቀረበ ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ሰብለ ለማ…… ቀረበ 2ኛ. ወ/ሮ ፀሐይ ለገሰ ….. አልቀረበም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጠ ።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች ያቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ የውርስ ሀብት ይጣራልኝ ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብል በፋደራል የመ/ደ/ፍ/ቤትና በፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው:: የጉዲዩ አመጣጥም ሲታይ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ ሆኖ ይዘቱም እናቴ ወ/ሮ አየለች ገ/ማርያም በ1989 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩና እኔ ብቸኛ ወራሽ ስሆን ተጠሪዎች የሟች የእህት ልጆች ሆነው ሳለ ሟች እናቴ ልጅ የላትም በማለት እራሳቸውን ምትክ ወራሽ በማድረግ የምትክ ወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት ከመውሰዲቸውም በተጨማሪ የሟች እናቴ ውርስ እንዱጣራ በማድረግ የውርሱ ባለሀብት ሆነዋል። እኔም ይህንኑ እንዲወኩኝ የፍርድ መቃወሚያ የተጠሪዎችን ምትክ ወራሽነት ተቃውሜ ማስረጃቸው ተሰርዞ ለእኔ ህጋዊ ወራሽነቴ ተረጋግጦ ማስረጃ ተሰጥቶኛል ስለሆነም በዚሁ መዝገብ የፍርድ መቃወሚያ ተጠሪዎች የጸደቀላቸው የውርስ አጣሪ ሪፖርት እንዱሻርና የሟች እናቴ የውርስ ሃብት እንደ አዱስ እንዱጣራልኝ ወጪና ኪሳራም የመጠየቅ መብቴ እንዱጠበቅልኝ የሚል ነው ።
ተጠሪዎችም በሰጡት መልስ አመልካች የሟች ወ/ሮ አየለች ገ/ማርያም ልጅ መሆኑን አምነው አመልካች የሟች እናቱ ውርስ ሲጣራ የሚያውቅና በዚሁ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.39542 ውርሱ ሲጣራ መቃወሚያ አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ስለሆነ 2 ጊዜ መቃወም አይችልም በተጨማሪም ወላጅ እናቱ ከሞቱ 21 ዓመት ያለፊቸው ስለሆነ መቃወሚያው በይርጋ ይታገዲል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የፋደ/መጀ/ደረጃ /ፍ/ቤት የአመልካች የፍርድ መቃወሚያ በይርጋ ይታገዲል ወይስ አይታገድም የሚለውን ጭብጥ መስርቶ ከመረመረ በኃላ የአመልካች እናት የሞቱት ህዲር 29 ቀን 1989 ዓ.ም ሲሆን አመልካች ወራሽነታቸውን ያረጋገጡት ጥር 25 ቀን 2004 ዓ.ም በመሆኑ 15 ዓመት ካለፈ በኃላ ከመሆኑም በተጨማሪ ሟች በሞቱ በ3 ዓመት ውስጥ ወራሽነታቸውን ያላረጋገጡ ሰለሆነ የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታው በይርጋ ይታገዲል በማለት ሲወስን ጉዲዩን በይግባኝ አይቶ እንዱያርም የይገባኝ ቅሬታ የቀረበለት የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅሬታው መ/ሰጪን ያስጠራል በማለት ያከራከረ ቢሆንም በውሳኔ ረገድ የስር የመ/ደ/ፍ/ቤትን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ሲሆን በቡኩላችንም አመልካች ነሐሴ 18 ቀን 2007 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበዉን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አቅርበን ክርክሩን ሰምተናል በመቀጠልም ከግራ ቀኙ ወገኖች የቀረበውን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
በመሆኑም በዚህ ሰበር ችልት የሚመረመረው ጭብጥ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ወራሸ የሆኑበት ውሳኔ እንዱሰረዝ ሲያስደርግና የሱን ወራሽነት ሲያረጋግጥ የይርጋ መቃወሚያ ሳይነሳ ታልፍ የተጠሪዎችን ወራሽነት አሰርዞና የሱን ወራሽነት አረጋግጦ የውርስ ማጣራት ሂደቱ ላይ በይርጋ ይታገዲል የተባለበትን አግባብነት ለማጣራት ሲሆን ተጠሪዎች ቀርበው የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካች አቤቱታ በይርጋ ይታገዲል ማለታቸው ተገቢ ነው ሲለ አመልካችም በበኩላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ በመልስ መልሳቸው አጠናክረው ተከራክረዋል።
ከክርክሩ መረዲት የተቻለው የአመልካች እናትና የተጠሪዎች አክስት ወ/ሮ አየለች ገ/ማርያም ህዲር 29 ቀን 1989 ዓ.ም ህይወታቸው ያለፈ መሆኑን የአሁን አመልካች የእናቱን ወራሽነት ጥር 25 ቀን 2004 ዓ.ም ያሳወጀ መሆኑን ተጠሪዎች ሚያዚያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም ሟች ልጅ የላቸውም በማለትና የእናታቸው ተተኪ ወራሽ መሆናቸውን ማስወሰናቸውንና መጋቢት 9 2005 ዓ.ም የሟች ወ/ሮ አየለች ውርስ ይጣራልን ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ፍርድ ቤቱ በ2/9/2005 ዓ.ም የውርስ አጣሪው ያቀረበውን ሪፖርት በማጽደቅ መወሰኑን ነው። በመቀጠልም የአሁን አመልካች በሐምል 22 ቀን 2005 ዓ.ም ባቀረበው አቤቱታ ተጠሪዎች የወራሽነት አቤቱታ ሲያቀርቡ ሟች ልጅ የላትም ያለት በሐሰት ነውና እኔም ልጅና ወራሽ ስለሆንኩኝ ለእነሱ የተሰጠው የወራሽነት ማረጋገጫ ይሰረዝልኝ በማለቱ ፍ/ቤቱ አጣርቶ ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም የተጠሪዎችን የወራሽነት ማስረጃ በመሰረዝ መወሰኑን ነው።
በመቀጠልም የአሁን አመልካች ተጠሪዎችን አቅርበው ያስወሰኑት የውርስ ሀብት ባለቤትነት ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ማቅረቡንና ተጠሪዎች የአመልካች አቤቱታ በይርጋ የሚታገድ ነው ማለታቸውን የስር ፍርድ ቤቶችም ክርክሩ በይርጋ ይታገዲል ማለታቸውን ነው።
ይህንን መነሻ ስናደርግ የተጠሪዎች ወራሽነት ማረጋገጫ የተሰረዘ መሆኑና በይግባኝ ያለመሻሩ ግልጽ እስከሆነ ድረስ ከወራሽነት ውሳኔው ጋር ተያይዞ የቀረበው የተሰጠ ውሳኔ ይሰረዝልኝና የውርስ ይጣራልኝ አቤቱታ በይርጋ ይታገዲል በማለት የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲወስን የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ብለናል በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችልት በመ/ በቀን 9/1/2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በአመልካች የቀረበው የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ በይርጋ አይታገድም ባልነው መሰረት የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገቡን አቅርቦ የግራ ቀኙን የፍሬ ነገር ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ የመሰለውን እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341/1/ መሰረት ይመለስ ብለናል ይጻፍ።
ለዚህ ውሳኔ አሰጣጥ አስፈላጊነት ከፋ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመጣው መ/ቁ.42445 የሆነ መዝገብ ይመለስ።
ለዚህ ፍ/ቤት ክርክር ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ወጪ ይቻለ።
መዝገቡ ተዝግቷል ተመላሽ ይደረግ ።
ሩ/ለ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.