ሟች በተወው ኑዛዜ መሰረት ውርሱ ሲጣራ እንዱሁም ኑዛዜው በፍ/ቤት ሲፀድቅ ተቃውሞ ሳያቀርብ ፤ ኑዛዜው ከፀደቀ በኃላ ኑዛዜው ይሻርልኝ በማለት የሚቀርብ አቶ ተስፊዬ በቀለ እና እነ ወ/ሮ እሸቷ ጎሸዬ 23/1/ 2009 ዓ.ም 304 XXIII ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ ፤ በሥር ፍ/ቤት ያልቀረበን ክርከር በይግባኝ ደረጃ ላይ ማቅረብ ተቀባይት የላለው ሰለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 329 (1) ( 3 ሰዎች ) 64. አንድ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ወራሽነት መብቱን ለአካላ መጠን ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 15 ዓመት ባለው ጊዜ ውሰጥ የውርሱን ንብረት ለመጠየቅ በይርጋ የማይታገድበት ስለመሆኑ ፤ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 198 ፣ 1000(2)
No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ክፍለጽዮን ማሞ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ ካባ ተካ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ድሪባ ዲዱ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለዉ ፍርድ ሰጥተናል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአሁን አመልካች አባቷን ተክታ ሟች አያቷን ወራሽ መሆኗን መሰረት በማድረግ ያቀረበችው የውርስ ንብረት የመካፈል ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ውድቅ በመደረጉ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በወልመራ ወረዲ ፍ/ቤት መናገሻ ችልት ሲሆን ፍ/ቤቱ ከተጠሪ የቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ በመቀበል እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 የተቀመጠውን የ10 ዓመት የጊዜ ወሰን መሰረት በማድረግ ክሱን ውድቅ አድርጓል። አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለፉኒፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ ብታቀርብም ፍ/ቤቱ የይግባኙ ቅሬታ መ/ሰጪን ያስቀርባል በማለት አከራክሮ ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1000/1/ መሰረት በ 3 ዓመት ይርጋ ይታገዲል በማለት የስር መጀመሪያ ፍ/ቤት ውሳኔን በማጽናት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታው የቀረበለት የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታው መልስ ሰጪን አያስጠራም በማለት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.337ን ጠቅሶ መዝገቡን ዘግቶታል።
አመልካች ታህሳስ 5/2008 ዓ.ም በጻፈችው ማመልከቻ አቤቱታ ባቀረበችበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የምትልበትን ምክንያት ገልጻ ስህተቱን የሚያርም ውሳኔ ይሰጥላት ዘንድ ጠይቃለች። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል፤ ክርክሩ የተሰማው የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ የሆነው በአግባቡ ነው አይደለም የሚለው ጭብጥ መሰረት ተደርጎ ነው። በዚሁ መሰረትም ግራ ቀኙ ወገኖች ጭብጡን በማስመልከት ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ እንደተመለከተው አመልካች ክስ የመሰረተችው የወራሽነት መብትን መነሻ በማድረግ ነው ለክስ ምክንያት የሆነው ንብረት ባለሀብት የነበሩ የአመልካች አያት የሞቱት ነሐሴ 10/1997 ዓ.ም ሆኖ አመልካች የውርስ ንብረቱ እንዱሰጣት ክስ የመሰረተችው ደግሞ መስከረም 23 ቀን 2007 ዓ.ም እንደሆነ ከመዝገቡ ተረድተናል ተጠሪ የይርጋ መቃወሚያ ያቀረበው ከዚህ በመነሳት ሲሆን ስር ፍ/ቤቶችም ተመሳሳይ ምክንያት በመስጠት ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ወስነዋል። አመልካች ግን ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው መባለ ትክክል አይደለም በሚል ክርክሩን በመግፊት የሰበር አቤቱታ አቅርባለች በዚህ ረገድ የሰጠችው ምክንያት ሟች አያቴ የሞተችው በ1997 ዓ.ም ሲሆን በዚህ ወቅት እኔ የ9 ዓመት ልጅ ነበርኩ የሚል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በወቅቱ ክስ ለማቅረብ እድሜዬ አልደረሰም ነበር ብላለች። ተጠሪም የአመልካች አያት የእኔ እናት የሞቱት በ1997 ዓ.ም ሳይሆን በ1992 ነው ከማለት በስተቀር ሟቹ ሲሞቱ አመልካች 9 አመቷ አልነበረም በሚል የቀረበው መከራከሪያ የለም።
በተጨማሪም አመልካች ሟች የሞቱት በ1997 ዓ.ም ነው ስትል ተጠሪ ሟች የሞቱት በ1992 ዓ.ም ነው ቢለም አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ ከማቅረቧ በፉት መስከረም 8/2007 ዓ.ም ወራሽነቷን በፍ/ቤት ውሳኔ ስታረጋግጥ ሟች የሞቱት በ1997 መሆኑን ጭምር ማረጋገጧን ያሳያል። ከዚህ መነሻ ሲደረግ ሟች የሞቱት በ1997 ዓ.ም ሆኖ አመልካች በወቅቱ 9 አመቷ እንደነበር አመልካች ስትገልጽ ተጠሪ ያልተቃወሙ በመሆኑ ሟች በ1997 ዓ.ም መሞታቸውንና አመልካች 9 አመቷ የነበረ መሆኑን ተረድተናል። ስለሆነም በ2007 ዓ.ም አመልካች ወራሽነቷን ባረጋገጠችበት ጊዜና አመልካች መብቷ ላይ ክስ ባቀረበችበት ጊዜ የ19 ዓመት ልጅ መሆኗን ተረድተናል። አመልካች የወራሽነት መብቷን ለመጠየቅም ሆነ ለመጠቀም ወይም ማናቸውንም ህጋዊው ተግባራት ለማድረግ ችልታ የሚኖራት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.198 በተገለጸው መሰረት 18 ዓመት ሲሞላት ነው። ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ወራሽነት መብቱን አላለ መጠን ካደረሰበት ጊዜ ጀምሮ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1000/2/ መሰረት በአሥራ አምስት ዓመት ውስጥ በፍ/ቤት ካረጋገጠ ንብረቱን ለመጠየቅ በይርጋ እንደማይታገድ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር መዝገብ እና በላልች መዛግብት አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል። በተያዘው ጉዲይ በ19 አመቷ አቤቱታ ማቅረቧ ግልጽ ሲሆን ከዚህ መነሻ ሲደረግ አመልካች በመብቷ መጠቀም ከጀመረችበት ጊዜ አሥራ አምስት ዓመት ሳያልፍ ወራሽነቷን ያረጋገጠች ስለሆነ ያቀረበችው ክስ በይርጋ ሉታገድ የማይገባ ሆኖ ሳለ ስር ፍ/ቤቶችም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1000/1/ እና 1845ን በመጥቀስ የአመልካች አቤቱታ በይርጋ ይታገዲል በማለት የሰጡት ውሳኔና የኦሮሚያ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ማረም ሲገባው ሳያርም ማለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ብለናል። ስለሆነም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የወልመራ ወረዲ ፍ/ቤት መናገሻ ችልት በመ/ቁ. 54576 ታህሳስ 27/2007 ዓ.ም የፉኒፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 24039 ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 229962 ጥቅምት 8 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአመልካች አቤቱታ በይርጋ የሚታገድ አይደለም ብለናል።
የወልመራ ወረዲ ፍ/ቤት መናገሻ ችልት የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ፍሬ ክርክሩን ሰምቶ እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/3/ መሰረት ጉዲዩን መልሰን ልከንለታል።
በየደረጃው ላለ ፍ/ቤቶች የውሳኔ ግልባጭ ይተላለፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.