No summary available.
መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳዉልስ አርሺሶ አመልካች፡- አቶ ተስፊዬ በቀለ …….ቀርበዋል ተጠሪዎ ፡- 1. ወ/ሮ እሸቷ ጎሽዬ……..ቀርበዋል 2. አቶ ሀብታሙ በቀለ…….ቀርበዋል 3. ወ/ሮ መብራት በቀለ……ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ ኑዛዜን መነሻ ያደረገ የዉርስ ክርክርን የሚመለከት ነዉ። የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ፡- በሥር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች /የሥር ተጠሪ/፣ የአሁን ተጠሪዎች /የሥር አመልካቾች/ ሁኖው ሲከራከሩ እንደነበር መዝገቡ ያመለክታል። የሥር አመልካቾች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ሟች ሻምበል በቀለ ደምሴ ጥር 13 ቀን 1988 ዓ.ም የሞተ ሲሆን፣ ሟች በሕይወት በነበረ ጊዜ በ22/11/1982 ዓ.ም የተጻፈ ኑዛዜ ያደረገ ስለሆነ የዉርስ አጣሪ ተሹሞ እንዱያጣራልን በማለት አመልክተዋል። የሥር ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ አመልካቾች የዉርስ ንብረቱን ሙለ ለሙለ ይዘዉ እያለ ተጠሪን ተከሳሽ ማድረጋቸዉ አግባብነት የለዉም፣ እኔም ወራሽ ስለሆንኩኝ የዉርስ ንብረቱ ቢጣራ አልቃወምም በማለት ተከራክሯል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የዉርስ አጣሪ በማሾም የዉርስ አጣሪዉ የዉርስ ሀብቱን በማጣራት በ28/02/2006 ዓ.ም የተጻፈ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን ግራ ቀኙ በሪፖርቱ ላይ አስተያየት አቅርበዋል። ፍ/ቤቱ የቀረበዉን ሪፖርት እና አስተያየት በማየት በሰጠዉ ዉሳኔ ግራ ቀኙ ሟች ያደረገዉን ኑዛዜ በጋራ ፍ/ቤት አቅርበዉ የፀደቁ በመሆኑ የዉርስ ማጣራት ሥራዉ እና ክፍፍለም መካሄድ ያለበት በዚህ አግባብ ነዉ። ይህ ኑዛዜ ገደብ ያለበት በመሆኑ 1ኛ አመልካች ወ/ሮ እሸቷ ጎሽዬ በሕይወት እስካለ ድረስ በዚህ ቤት የመጠቀም መብት ስላላቸዉ ወራሾች የመኖሪያ ቤት፣ የቤት ኪራይ እንዱሁም የቤት ዉስጥ ቁሳቁስ ለመጠየቅ መብት አይኖራቸዉም ። ነገር ግን ከ1ኛ አመልካች ህልፈተ ሕይወት በኋላ ከጠቅላላ ንብረት 50% የ2ኛ አመልካች አቶ ሀብታሙ በቀለ በመሆኑ፣ ቀሪዉ 50% የተጠሪ አቶ ተስፊዬ በቀለ እና 3ኛ አመልካች ወ/ሮ መብራት በቀለ ድርሻ እያንዲንዲቸዉ 25% ድርሻ ይኖራቸዋል፣ ስለዚህ በኑዛዜዉ መሰረት ሪፖርቱ በዚህ አግባብ ተሻሽሎል በማለት ወስኗል። የሥር ተጠሪ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ባለመቀበል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.337 መሰረት ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔን በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች መስከረም 6 ቀን 2008 ዓ.ም በተጻፈ ሁለት ገጽ አቤቱታ ሟች አባታችን በ22/11/1982 ዓ.ም ያደረገዉ ኑዛዜ በግል ሀብት ላይ ሳይሆን በአጠቃላይ በዉርስ ሀብት ላይ የተደረገ ኑዛዜ በመሆኑ ኑዛዜዉ ተሽሮ የዉርስ ሀብት ሳይናዘዝ እንደሞተ ሰዉ ተቆጥሮ የዉርስን ሀብት በሕግ አግባብ እንድንካፈል። 1ኛ ተጠሪ ኑዛዜዉን ወደጎን በመተዉ የዉርስ ሀብት እንዱጣራላቸዉ በሥር ፍ/ቤት ባመለከቱት መሰረት ኑዛዜዉ የማይሰራ በመሆኑ የዉርስ ሀብቱን ድርሻዬን 25% እንዲገኝ እንዱወሰንልኝ። ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቶች 1ኛ ተጠሪ በሕይወት እስካለ ድረስ ምንም ዓይነት የዉርስ ድርሻ መጠየቅ አትችልም በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱሻርልኝ እንዱሁም ኑዛዜዉ ተሽሮ የዉርስ ሀብቱን ሳይናዘዝ እንደሞተ ሰዉ የዉርስ ሀብት ድርሻ በሕግ አግባብ እንዱካፈል እንዱወሰንልኝ በማለት አመልክቷል።
የሰበር አጣሪ ችልት ጉዲዩን በመመርመር ፣የዉርስ ይጣራ ጥያቄ የቀረበዉ በኑዛዜዉ ተጠቃሚዎች ከመሆኑ አንጻር የግራ ቀኙ የዉርስ ድርሻ ጭምር እንዱጣራ ያለመደረጉን አግባብነት፣ ለመመርመር ሲባል አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱያቀርቡ በታዘዘዉ መሰረት የካቲት 17 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ ሁለት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዘት፡-የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ እንዱጸናልን፣ አመልካች ያቀረበዉ አቤቱታ ዉድቅ እንዱደረግልን፣ በዚህ ምክንያት የደረሰዉን ወጪና የጠበቃ አበል እንዱወሰንልን በማለት ተከራክሯል።
አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ለአቤቱታዉ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል። መዝገቡን እንደመረመርነዉ ሟች ሻምበል በቀለ ደምሴ በሕይወት በነበሩ ጊዜ በ22/11/1982 ዓ.ም የተጻፈ ኑዛዜ ማድረጋቸዉ ግራ ቀኙ የሚካካደት ጉዲይ አይደለም። የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ እንደሚያመለክተው የአሁን አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ የሟች አባታቸዉ ወራሽ፣ 1ኛ ተጠሪ ደግሞ የሟች ሚስት እንደሆኑ እና 3ኛ ተጠሪ የኑዛዜ ወራሽ እንደሆነች ተመልክቷል። ከግራ ቀኙ ክርክር እና ከሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ መገንዘብ እንደሚቻለዉ ሟች ይህን ኑዛዜ ያደረገዉ ጠቅላላዉን ንብረት በሚመለከት ሲሆን የአሁን 1ኛ ተጠሪ በሕይወት እስካለ ድረስ ሀብቱን የመጠቀም መብት እንዲላቸዉ እና ማንም ተወላጅ የአባቴ ዉርስ ይገባኛል በማለት መጠየቅ እንደማይችል እና ከ1ኛ ተጠሪ ህልፈተ ሕይወት በኋላ ከጠቅላላ ሀብቱ 2ኛ ተጠሪ 50% እንዱካፈል፣ አመልካች እና 3ኛ ተጠሪ ቀሪዉን ሀብት 50% ለሁለት እንዱካፈለ (እያንዲንዲቸዉ 25%) እንዱካፈለ በማለት የተናዘዘ መሆኑን ያመለክታል። ግራ ቀኙ ይህን ኑዛዜ በመቀበል እንዱጸድቅላቸዉ በጋራ ለፍ/ቤት አቤቱታ አቅርበዉ በፍ/ቤት ዉሳኔ የጸደቀ መሆኑን ተማምነዋል። የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረበዉ ክርክር ሲታይ ሟች ያደረገዉ ኑዛዜ በፍ/ቤት ቀርቦ ሲጸድቅ ያልተቃወመ መሆኑን፣ የዉርስ ማጣራትም ሆነ ክፍፍለ መሆን ያለበት በኑዛዜዉ አግባብ መሆን እንዲለበት ተከራክሯል። በልላ በኩል የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት ክርክር የኑዛዜዉ ይዘት ላይ የተለያየ ክርክር ቢያቀርቡም የዉርስ ማጣራት ሂደትም ሆነ ክፍፍለ በዚሁ አግባብ መሆን እንዲለበት ገልጸዉ ተከራክረዋል። እንዱሁም የሥር ፍ/ቤት የዉርስ አጣሪዉን ሪፖርት በማሻሻል ክፍፍለ በኑዛዜዉ አግባብ መሆን እንዲለበት ዉሳኔ የሰጠ ሲሆን የአሁን ተጠሪዎች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ያቀረቡት ቅሬታ የለም። የሥር ፍ/ቤት ኑዛዜዉ ገደብ ያለበት መሆኑን በመገንዘብ 1ኛ ተጠሪ በሕይወት እስካለ ድረስ ተጠሪዎች የዉርስ ሀብት መጠየቅ እንደማይችለ እና ከ1ኛ ተጠሪ ህልፈተ ሕይወት በኋላ ከጠቅላላ ሀብቱ 2ኛ ተጠሪ 50% እንዱካፈል፣ አመልካች እና 3ኛ ተጠሪ ቀሪዉን ሀብት 50% ለሁለት እንዱካፈለ እያንዲንዲቸዉ 25% እንዱካፈለ በማለት የወሰነ መሆኑን መዝገቡ ያመለክታል። ይህ ሆኖ ሳለ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ፍ/ቤት የኑዛዜዉን ይዘት በማየት ተርጉሞ የሰጠዉን ዉሳኔ በተመለከተ ሟች ኑዛዜዉን የሰጠዉ በአጠቃላይ ሀብት ላይ ሳይሆን በንብረቱ ግማሽ የግል ሀብታቸዉ ላይ ነዉ ተብል እንዱወሰን ያቀረቡት ክርክር የሥነ ሥርዓት ሕጉን ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የለዉም። የአሁን አመልካች ሟች በሰጠዉ ኑዛዜ መሰረት ዉርስ ቢጣራ እና ክፍፍል ቢደረግ እንደማይቃወም እንዱሁም ኑዛዜዉ መጀመሪያ በፍ/ቤት ሲጸድቅ እንዲልተቃወመ በመግለጽ ሲከራከር እንደነበር የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ ያሳያል። እነዚህ ሁለ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች መሆናቸዉ ግልጽ ነዉ። እነዚህ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮችን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ ተመርምሯል።
No topics extracted.
የአሁን አመልካች በኑዛዜዉ አግባብ የዉርስ መጣራት ሂደቱም ሆነ ክፍፍል ቢደረግ እንደማይቃወም እየገለጸ፣ ይህ ኑዛዜ በፍ/ቤት እንዱጸድቅ ከተጠሪዎች ጋር ለፍ/ቤት አቤቱታ አቅርበዉ ኑዛዜዉ በማጽደቅ ከጨረሰ በኋላ አሁን በኑዛዜዉ አግባብ የተሰጠዉን የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ እና ኑዛዜዉን እንዱሻርልኝ በማለት ያቀረበዉ ክርክር በሥር ፍ/ቤት ያልቀረበ አዱስ ክርክር በመሆኑ ለዚህ ሰበር ችልት ያቀረበዉ ቅሬታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.329 /1/ መሰረት ተቀባይነት የለዉም ። ላላዉ የአሁን አመልካች የሀብቱ 25% ድርሻ እንዱሰጠኝ በማለት ያቀረበዉ ክርክር ሲታይ የአሁን አመልካች ከጠቅላላ ሀብት 25% እንደሚገባዉ የሥር ፍ/ቤት በዉሳኔዉ ያረጋገጠ ሲሆን የአሁን አመልካች ኑዛዜዉ ገደብ ያለበት ነዉ በማለት እየተከራከረ እያለ አሁን ደግሞ ድርሻዬ አሁን እንዱሰጠኝ በማለት ያቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም።
ስለዚህ የሥር ፍ/ቤት ሟች የሰጠዉን ኑዛዜ እና በግራ ቀኙ ተቀባይነት ያገኘዉን ኑዛዜ መሰረት በማድረግ ዉሳኔ የሰጠ ሲሆን አመልካች በሥር ፍ/ቤት አሁን እንደቅሬታ ያቀረባቸዉን ነጥቦች ያላቀረበ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔዎች በሕጉ አግባብ የተሰጡ ናቸዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ነዉ ለማለት ስለማይቻል የሚከተለዉ ተወስኗል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.42390 በ17/06/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማጽናት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.167257 ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ ጸንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ ብለናል።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት ለደረሰባቸዉ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።