ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርስ ከተከፈተ በኋላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባያወጣም ለውርሱ አይገባም እስካልተባለ ድረስ የወራሸነት መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፍ ወ/ሮ እቴቱ ከንባው (ሁለት ሰዎች) እና ወ/ሮ ቀለሟ ዓለማየሁ 28/6/ 2008 ዓ.ም 295 62. አንድ ፍ/ቤት የውርስ ክርክርን አስመልክቶ የሚቀርብለትን የውርስ አጣሪዎች ቃለ- ጉባኤ ከማስጽደቁ በፉት በእርግጥ የውርስ ሀብት የማጣራት ሕጋዊ ሂደት ተከትል የተካሄደ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 946፣950፣1062፣1079፣1080
No summary available.
መጋቢት 13 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል እንደሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ ጫልቱ ዋቀዬ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ፈቃደ ዋቀዬ - ቀረቡ መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው በኦሮሚያ ክልል የወልመራ ወረዲ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በተጠሪ ላይ በቀረበው ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ይዘት ባጭሩ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ይዞታ የሟች አባታቸው አቶ ዋቀዬ ነገአ እና ወላጅ እናታቸው ወ/ሮ እሼቱ አባላቱ እንደነበረ፤ ወላጅ እናታቸው በ2001 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኃላ የቤተሰብ አባላት የውርስ ንብረት የማጣራት ሥራውን በስምምነት ማከናወን ባለመቻላቸው በፍ/ቤት በኩል በመ/ቁ.20782 ጠይቀው ወራሾች እንዱቀርቡ በሚኖርበት አካባቢ በማስታወቂያ ጥሪ ቢደረግም የቀረበ ሰው እንዲልነበረ፤ የውርስ አጣሪዎች የውርስ ንብረቱን ለይተው የየድርሻቸውን እንዲስረከቡዋቸው፤ በዚሁም አመልካች የድርሻቸውን 2262 ካሬ ሜትር ይዞታ ሳይረሱት አክርመውት የአሁኑ ተጠሪ ያለ አመልካች ፈቃድ በ2ዐዐ4/2ዐዐ5 ዓ.ም መሬቱን በማረስ ገብስ የዘራ በመሆኑ መሬቱን ለቆ የሰብል ግምት የ4 ኩንታል ብር 4,000 እንዱከፍል እንዱወሰን ዲኝነት ጠይቋል።
የአሁን ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በፍሬ ጉዲዩም መልስ አቅርበዋል። የአሁኑ ተጠሪ መሬቱን ለ5 ዓመታት የተጠቀሙበት መሆኑን በመግለጽ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1000/1/ መሰረት የይርጋ መቃወሚያ እንዱሁም ጉዲዩ በፍርድ ያለቀ ነው የሚል ክርክር ያቀረቡ ሲሆን በፍሬ ጉዲዩም አመልካች ያቀረቡት የውርስ ንብረትና ወራሾችን በግልጽ ያላስቀመጠ እንደሆነ ይዞታው ከተጠሪ እጅ በመውጣት በአመልካች ይዞታ ሥር አለመግባባቱን በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ አመልክቷል።
የሥር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ የይርጋ እና ጉዲዩን ውሳኔ ያገኘነው የሚል ክርክር ሳይቀበል በፍሬ ጉዲዩ ለክርክር ምክንያት የሆነውን የመሬት ይዞታ በተጠሪ እጅ ያለ ስለመሆኑ አልተካደም፤ የተጠሪ ምስክሮች ይህ የውርስ ንብረት አለመክፈለን አላየሁም ይበለ እንጅ በአመልካች የቀረቡ ምስክሮች በሚያሳምን መልኩ አሁን ክርክር ያስነሳው ይዞታ የአቶ ዋቀዬ ነገአ ወራሾች ሃብት ሲከፊፈል ለአመልካች ድርሻቸው የተሰጣችው ስለመሆኑ ያረጋገጡ በመሆኑ ተጠሪ አመልካች በውርስ ያገኙትን 2666 ካሬ ሜትር በእጃቸው የሚገኘውን እንዱለቁ አመልካች በ2004 ዓ.ም ያጡት የ2ዐዐ4 ዓ.ም ምርት 4,000 እንዱከፍለ ወስነዋል።
የአሁኑ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፍንፍኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኃላ በውርስ አጣሪዎች ቀረበ የተባለው ሪፖርት የውርስ ንብረት እና ወራሾች በአግባቡ የለየ አለመሆኑን የእያንዲንደ ወራሽ ድርሻ ተለይቶ ባልተወሰነበት፤ ፍርድ ቤትም የቀረበለትን ሪፖርት አጣሪው በሥልጣኑ መሰረት አጣርቶ ያቀረበው ስለመሆኑ በማረጋገጥ ያፀደቀው የአሁኑ ተጠሪ ይዞታ እንዱለቅ እና የሰብል ግምት እንዱከፍል የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ አለመሆኑን፤ አመልካች አቤቱታቸው የይርጋ ጊዜ ሳያልፈው ያቀረቡት በመሆኑ የእናታቸውን የውርስ ድርሻ የመጠየቅ መብታቸው የተጠበቀ ነው ሲል የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሯል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርመሮ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ አንኳር ነጥቦች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የመሬት ይዞታ በእጃቸው ገብቶ የነበረ ስለመሆኑ የወራሾች ድርሻ የተከፊፈለ ነው፣ ለአመልካች ከሚደርሳቸው በላይ እንዲልተሰጣቸው በመግለጽ የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱሻር የሚጠይቅ ነው። ተጠሪ በበኩላቸው የማጣራት ሥራው ወራሾች ባልተሳተፈበት ሁኔታ እንደተከናወነ፤ አጣሪዎች በሕግ ስልጣን ያልተሰጣቸው ስለመሆኑ በይዞታው እየተጠቀሙ ያለት ተጠሪ ስለመሆናቸው በመግለጽ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና አመልክተዋል። የመልስ መልስም አቅርበናል ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የውርስ አጣሪዎች ሪፖርት ነው ተብል በሥር ፍ/ቤት በመ/ቁ.
20782 ቀርቦ የተመዘገበው ቃለ-ጉባኤ የግራ ቀኙን ተከራካሪዎች በማስቀረብ ተመልክቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም በጽሐፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህ ችልት ዕልባት የሚያሻው ዓብይ ነጥብ የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው የውርስ ንብረት በአግባቡ ተጣርቶ የተወሰነ አይደለም በማለት የሥር ወረዲ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔንና ትዕዛዝ መሻሩ በሕጉ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ሆኖ አግኝተናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ አመልካች ባቀረቡት ክስ በውርስ አጣሪዎች ድርሻቸው ተለይቶ ከታወቀ በኃላ የአሁኑ ተጠሪ ከሕግ ውጪ በመያዝ እየተጠቀመበት መሆኑን በመግለጽ ተጠሪ ይዞታውን እንዱለቁ እንዱሁም የሰብል ግምት አራት ሺህ ብር እንዱከፈላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን ነው። ተጠሪ ጉዲዩ በይርጋ እንደሚታገድ፤ ከአሁን በፉትም በፍርድ ያለቀ ጉዲይ ስለመሆኑ እንዱሁም የወራሾች ድርሻ በሕጉ አግባብ አለመወሰኑን መከራከራቸውን ተመልክተናል። አመልካች የውርስ ሃብት ለወራሾች በአግባቡ ተከፊፍሎል ይበለ እንጂ በሥር ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 20782 ተመዘገበ የተባለው የውርስ አጣሪዎች ሪፖርት ወራሾች እነማን አንደሆኑ፤ የአውራሾቻቸው የሚንቀሳቀስና የማይቀሳቀስ ንብረት ምን እንደሆነ፤ እያንዲንደ ወራሽ የሚደርሰው የሃብት መጠን ምን ያህል እንደሆነ? በግልጽና በማያሻማ መልኩ ያስቀመጠ ስለመሆኑ ሰነደ አያሳይም። በሥር ፍርድ ቤት የውርሰ አጣሪዎች የተባለ ሽማግላዎችም ወራሾች በማጣራት ሂደት እንዱሳተፈ በማስታወቂያ ጥሪ አድርገን ነበር ያለ ቢሆንም በእርግጥ ከአመልካች ውጭ ያለ ወራሾች በሕጉ አግባብ ጥሪ ተደርጏላቸው ውርስ እንደሚጣራ አውቀው በዲታኝነት የቀሩ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ አይደለም።
በመሰረቱ ውርስ የሚጣራው በወራሾች ሲሆን ስምምነት ከላለ ወይም ላላ ሕጋዊ ምክንያት ካለ አጣሪዎች በፍ/ቤት እንደሚሰየሙ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 946 እና 950 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት የምንረዲው ነው። የውርስ ሃብት ማጣራት በሕጉ አግባብ ከተከናወነም ወራሾች ድርሻቸውን የመጠየቅ መብት ያላቸው ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1062 ተመልክቷል። የክፍፍል ሥርዓቱም በወራሾች ስምምነት ላሆን እንደሚችል፤ በውርስ ክፍፍል ጊዜ ያልተወከለ ወራሽ ካለም በፍ/ቤት እንደሚፀድቅ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1079 እና 1080 ተደንግጓል፣ የውርስ ሀብት የክፍፍል መርህም በዓይነት እንደሚሆን፤ ንብረቱን በዓይነት ለማከፊፈል ባልተቻለበት ሁኔታ በማቻቻል ሕጋዊ መፍትሄ እንደሚያገኝ የፍ/ሕ/ቁ. 1086 እና 1087 ድንጋጌዎች ያስገነዝቡናል። በተያዘው ጉዲይ የሥር ወረዲ ፍርድ ቤት ቀረበ ያለውን የውርስ አጣሪዎች ቃለ ጉባኤ ከማፅደቁ በፉት በእርግጥ የውርስ ሃብት የማጣራት ሕጋዊ ሂደት ተከትል ወራሾች እና የውርስ ሀብት በአግባብ የተካሄደ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፉነት ነበረበት። ከዚህ አንፃር የሥር ወረዲ ፍርድ ቤት የሟቾች የውርስ ሀብት ምን ምን እንደሆነ፤ ወራሾች እነማን እንደሆኑ እና ድርሻቸውን በሕጉ አግባብ በመለየት ስለመወሰኑ መዝገቡ አያሳይም። እንዱህ ከሆነ ደግሞ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የውርስ ሀብት በሕጉ አግባብ ተጣርቶ የተወሰነ አይደለም በማለት የወረዲውን ውሳኔ እና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውድቅ ማድረጉ በሕጉ አግባብ ነው ብለናል። ምክንያቱም የወረዲው ፍርድ ቤት ወራሾችና የውርስ ሀብት በአግባቡ በመለየት ውሳኔ አልሰጠም። በዚህ ረገድ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም።
የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች የውርስ ሃብት ድርሻቸውን ከሰው የመጠየቅ መብታቸውን የጠበቀ ስለመሆኑ የውሳኔ ግልባጭ ያስረዲል። ይሁንና አመልካች የውርስ ሃብት ድርሻቸውን ለመጠየቅ ክስ እንዲቀረቡ መዝገቡ ስለሚያሳይ አመልካች ላላ ክስ ማቅረብ ሳይጠበቅባቸው አለኝ የሚለትን ድርሻ በሕጉ አግባብ ክሳቸውን እንዲያሻሽለ በማድረግ እና ተገቢ ዲኝነት በመክፈል በሥር መ/ቁ. 46789 ክርክራቸውን የመቀጠል መብታቸው ሉነፈግ አይገባም። በዚህ ረገድ የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አመልካች አዱስ ክስ እንዱያቀርቡ በሚጋብዝ አግባብ መወሰኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ዓላማ አንፃር ሲታይ ተገቢ አይደለም ብለናል። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሥር ወረዲ ፍ/ቤት ወራሾችና የውርስ ሀብት በመለየት ውሳኔ አልሰጠም በማለት የውርስ አጣሪ ሪፖርት ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ ሆኖ አመልካች አዱስ ክስ እንዱያቀርቡ በመፍቀድ የሰጠው የውሳኔ ክፍል ግን ሉሻሻል የሚገባው ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ተከታዩን ወስነናል።
በ26/01/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት የወልመራ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 46789 በ14/06/2006 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ፤ የአዱስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 72261 በ6/09/2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በመሻር የሰጠው ፍርድ ተሻሽሎል።
የውርስ አጣሪዎች ሪፖርት ወራሾች እና የውርሰ ሀብት በአግባቡ ለይቶ ያላስቀመጠ ነው ተብል ውድቅ መደረጉ በሕጉ አግባብ ነው ብለናል።
አመልካች ላላ ክስ ማቅረብ ሳይጠበቅባቸው ድርሻ አለኝ ካለ በሕጉ አግባብ ክሳቸውን አሻሽለውና ተገቢ ዲኝነት ከፍለው ክርክሩን የመቀጠል መብታቸው የተጠበቀ ነው ብለን ወስነናል። የወልመራ ወረዲ ፍርድ ቤትም የመ/ቁ. 46789 በመክፈት የውርስ ሀብት ክርክር ከቀረበ በሕጉ አግባብ ለማጣራት ተገቢ ሕጋዊ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
የዚህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
የማየነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.