በፍ/ብ/ህ/ቁ. 842/3/ መሰረት የተተኪ ወራሽነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዱያገኝ ሉሟለ ስለሚገባቸው እነወ/ሮእሴተማርያምአክል ግ (ሶስት ሰዎች) እና የለም
No summary available.
የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካቾች፡
ጉዲዩ የውርስ ይገባኛል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም የአሁኖቹ አመልካቾች የአባታቸው እናት ማለትም የሴት አያታቸው የሟች ወ/ሮ ላቀች ቸርነት ታፊይ ውርስ እንዱጣራላቸው በአሁኗ ተጠሪ ላይ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ተጠሪዋን መልስ ከተቀበለ በኃላ ውርሱ ተጣርቶ እንዱቀርብ ትዕዛዝ በመስጠቱ በ19/07/2006 ዓ.ም. የተዘጋጀ የውርስ አጣሪ ሪፖርት ቀርቦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል። የሪፖርቱ ይዘትም የአመልካቾቹ አባት አቶ ከንባው ወርቅነህ ሟች እናታቸው (የአመልካቾች አያት) ወ/ሮ ላቀች ቸርነት በሞቱበት ጊዜ በሕይወት የነበሩ ሆኖ ነገር ግን የእናታቸው ወራሽ መሆናቸውን ሳያረጋግጡ ቆይተው የሞቱ በመሆኑ አመልካቾቹ በአባታቸው እግር ተተክተው አያታቸውን ሉወርሱ የሚችለበት የሕግ አግባብ ባለመኖሩ ውርሱን ከእናታቸው ወ/ሮ ላቀች ቸርነት በኃላ ነገር ግን የእናታቸው ወራሽ መሆናቸውን አረጋግጠው በሞቱት ሟች የሸዋመብራት ወርቅነህ እግር ተተክተው የእኒሁ የሸዋመብራት ወርቅነህ ልጅ እና ወራሽ የሆኑት ተጠሪ፣እንዱሁም የወ/ሮ ላቀች ቸርነት ላላ ወራሽ ካለ እንዱቀርብ አጣሪው ባወጣው ማስታወቂያ ተጠርተው የቀረቡት ወ/ሮ የማርያምወርቅ ወርቅነህ በጋራ ይወርሳለ የሚል ነው።በሪፖርቱ ላይ ግራ ቀኙ አስተያየት እንዱሰጡ የተደረገ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የአሁኖቹን አመልካቾች አስተያየት ውድቅ አድርጎ የአጣሪውን ሪ‹ፖርት በማጽደቅ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካቾቹ አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን ዘግቶ በማሰናበቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ የተደረገ ቢሆንም ተጠሪዋ በምስክሮች ፉት መጥሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው በመሀላ ቃል በመረጋገጡ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፍ ጉዲዩ ለምርመራ እንዱቀጠር የተደረገ መሆኑን መዝገቡ ያመለክታል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የአመልካቾቹ ወላጅ አባት አቶ ከንባው ወርቅነህ ከሟች እናታቸው ወ/ሮ ላቀች ቸርነት የሚያገኙት ውርስ ለአመልካቾቹ ሉተላለፍ የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም በማለት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህም መሰረት የአመልካቾቹ አባት እናት (የአመልካቾቹ አያት) የሆኑት ወ/ሮ ላቀች ቸርነት ታፊይ በሞት የተለዩት በ14/02/1979 ዓ.ም. መሆኑን፣የአመልካቾቹ አባት አቶ ከንባው ወርቅነህ የሞቱበትን ጊዜ የመዝገቡ ግልባጭ የሚያመለክት ባይሆንም የሞቱት ከእናታቸው ሞት በኃላ ረዥም ጊዜ ቆይተው መሆኑን፣የተጠሪዋ እናትም የሞቱት በተመሳሳይ ሁኔታ ከእናታቸው ከወ/ሮ ላቀች ቸርነት ሞት ከ24 ዓመታት በኃላ በ2003 ዓ.ም. መሆኑን፣ የአመልካቾቹ አባት የሞቱት የእናታቸው ላቀች ቸርነት ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሳይወስደ መሆኑን፣በአንጻሩ የተጠሪዋ እናት የሞቱት የእናታቸው ወ/ሮ ላቀች ቸርነት ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በ1997 ዓ.ም. ከወሰደ በኃላ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።እናታቸው በሞቱበት ጊዜ የአመልካቾቹ አባት በሕይወት የነበሩ እና ለወራሽነት አይገቡም ያልተባለ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 830 ድንጋጌ መሰረት እናታቸውን የመውረስ መብት አላቸው።አንድ ሰው የሞተ እንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው ስፍራ በሆነበት ቦታ የሟቹ ውርስ የሚከፈት ስለመሆኑ እና በሟቹ ሞት ምክንያት የሚቋረጡ ካልሆኑ በቀር በውርሱ ውስጥ የሚገኙት የሟቹ መብቶች እና ግዳታዎች ለወራሾቹ እና የኑዛዜ ባለስጦታዎች የሚተላለፈ ስለመሆኑ በዚሁ ሕግ በቁጥር 826 የተመለከተ ሲሆን ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርሱ ከተከፈተ በኃላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነቱ መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፍ ስለመሆኑም በቁጥር 833 ተደንግጎ ይገኛል።በመሆኑም ከላይ በተጠቀሰው ቁጥር 833 ድንጋጌ መሰረት የወ/ሮ የሸዋመብራት ወርቅነህ ድርሻ ወራሻቸው ለሆኑት የአሁኗ ተጠሪ እንደተላለፈው ሁለ የአመልካቾቹ አባት አቶ ከንባው ወርቅነህ ከእናታቸው ከሟች ላቀች ቸርነት የሚያገኙት የውርስ ድርሻ ለሟች ከንባው ወርቅነህ ወራሾች የሚተላለፍ ከሚሆን በቀር አቶ ከንባው ወርቅነህ በሕይወት እያለ የእናታቸው ላቀች ቸርነት ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ባለመውሰዲቸው ብቻ የአቶ ከንባው ወርቅነህ የውርስ ድርሻ ለላልች የሟች ላቀች ቸርነት ወራሾች እንዱተላለፍ ላደረግ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም። በመሆኑም የአመልካቾቹ አባት ከእናታቸው የሚያገኙት የውርስ ድርሻ ወደ አሁኖቹ አመልካቾች ሉተላለፍ የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም በማለት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ከላይ የተጠቀሱትን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ሕጋዊ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚችል ሆኖ አልተገኘም።
ከላይ የሰፈረው ትችት እንደተጠበቀ ሆኖ በስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ተጠሪዋ በአመልካቾቹ ላይ የይርጋ መቃወሚያ አላነሱም።ከመዝገቡ መገንዘብ እንደሚቻለው ወ/ሮ ላቀች ቸርነት ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ የአመልካቾቹ አባት በዚሁ የውርስ ቤት ውስጥ ሲኖሩ የነበረ በመሆኑ እና አመልካቾቹም እየኖሩ የሚገኙት በዚሁ ቤት በመሆኑ የይርጋ መቃወሚያ ሉነሳ የሚችልበት አግባብ የለም። ይህ ብቻ ሳይሆን ውርሱ እንዱጣራላቸው አመልካቾቹ ላቀረቡት አቤቱታ ተጠሪዋ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾቹ ከቤቱ የውርስ ድርሻ እንዲላቸው በማመን ውርሱ ቢጣራ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን በመግለጽ መልስ የሰጡ መሆኑን መዝገቡ ያመለክታል። በመሰረቱ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከራካሪዎቹ ወገኖች በዝርዝር ባላቀረቡት ወይም በግልጽ ባላመለከቱት ጉዲይ ላይ ፍርድ መስጠት የማይችል ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 182 (2) በግልጽ ይደነግጋል። በመሆኑም የአመልካቾቹ አባት ከእናታቸው የሚያገኙት የውርስ ድርሻ ወደ አሁኖቹ አመልካቾች ሉተላለፍ አይገባም በማለት በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የተሰጠው ከተጠሪዋም ሆነ ከላላኛዋ ወራሽ ምንም ዓይነት ተቃውሞ ባልቀረበበት እና ይልቁንም የአመልካቾቹ የመውረስ መብት በግልጽ በታመነበት ሁኔታ ጭምር በመሆኑ አመልካቾቹን ከውርሱ በማግለል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት መሰረት አድርጎ የተሰጠ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉታረም የሚገባው በመሆኑ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ30/06/2007 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።
የውርስ አጣሪው በ19/07/2006 ዓ.ም. ባቀረበው ሪፖርት ላይ ተገቢው ማስተካከያ ተደርጎ የሟች ወ/ሮ ላቀች ቸርነት ውርስ ከሆነው በጉለላ ክፍለ ከተማ በወረዲ 5 ከሚገኘው ቁጥሩ 147 ከሆነው ቤት ውስጥ የአሁኗ ተጠሪ ወ/ሮ ቀለሟ ዓለማየሁ አንድ ሶስተኛ፣ወ/ሮ የማርያምወርቅ ወርቅነህ አንድ ሶስተኛ፣የአሁኖቹ ሁለቱ አመልካቾች ደግሞ በጋራ አንድ ሶስተኛ ድርሻ አላቸው በማለት ወስነናል።
እንዱያውቁት የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
በዚህ መዝገብ በ24/02/2008 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.