የመጀመሪያ ሚስት በንብረትዋ ላይ ስምምነት ባላደረገችበት ፤ባል ሁለተኛ ሚስት ሲያገባ መቃወሚያ አላቀረበችም በማለት በንብረትዋ ላይም ስምምነት አድርጋለች በማለት በመደምደም ፤ሁለተኛ ሚስት እኩል እንድትካፈል በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ህጋዊ አቶ ሃንደግባ ሸኩር እና ወ/ሮ አለምቴ ኢብራሑም 27/8/ 2008 ዓ.ም 279 59. አንድ ሰው ህጋዊ ባለይዞታው ሳይቃወም በልላ ሰው ይዞታ ላይ ቤት ወይም ንብረት ያፈራ እንደሆነ የዚሁ ቤት/ ንብረት/ ባለመብት የሚሆን ስለመሆኑ፣ የፍትሐ ብሓር ህግ ቁጥር 1179(1)(2) ከኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40 አኳያ ላታይ ስለሚችልበት አቶ አህመድ ዐመር እና እነ አቶ ተስፊዬ አብርሃ /ሁለት ሰዎች/ XXII
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 110040 የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡-
ይህ ጉዲይ ውርስ ጥያቄን የሚመለከት ነው። አመልካቾች ለአ.አ.ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የአያታቸው ወ/ሮ ደብረወርቅ ሀ/ሚካኤል ወራሽነት ይረጋገጥልን በማለት አቅርበዋል።የአባታቸው ሻለቃ አክልግ አድማሱ ወራሽነት ያረጋገጡ ሲሆን የወላጅ አባታቸውን እናት ወራሽነት ለማረጋጥ የቀረበ አቤቱታ ነው።ወላጅ አባታቸው በ1981 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ሲሆን አያታቸው ወ/ሮ ደብረወርቅ ሀብተ ሚካኤል የሞቱት ደግሞ በ1978 ዓ/ም ነው። በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤቱም አያታችህ ከአባታችሁ ቀድመው የሞቱ ስለሆነ ተተኪ ወራሽ ልትሆኑ አትችለም በማለት ብይን ሰጥተዋል። በዚህ ብይን ባለመስማማት አቤቱታቸውን ለአ.አ.ከተማ ይግባኝ ሰሚና ለሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሳያገኝ በትእዛዝ ሰርዞውታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔን በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች ተወካይ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ/ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ብይን ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ወላጅ አባታችን እናቱ ከሞቱ ጀምሮ እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ በህመም ላይ እንደነበር ለስር ፍርድ ቤቶች አስረድተን እያለን የአያታች ወራሽነት አታረጋግጡም መባለ ከፍተኛ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ወላጅ አባታችን ለ3 አመት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ የእናቱን ወራሽነት ሳያረጋግጥ ቢቀርም አመልካቾች ተተኪ ወራሾች የአያታችንን ወራሽነት የሚከለክለን አንዲችም ህግ የላለ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ብይንና ትእዛዝ በመሻር የአያታቸውን ወራሽነት እንዱረጋገጥላቸው አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተተኪ ወራሾች ሉሆኑ አይችለም በማለት የተሰጠ ብይን ከፍ/ብ/ህ/ቁ/ 830፣831/3/844 እና 839 አንፃር ለመመርመር በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ላቀርብ የቻለው የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ብይን እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
የአመልካቾች ጥያቄ ወላጅ አባታቸውን ተክተው የአያታቸው ወራሽነት እንዱረጋጥላቸው ነው።
የስር ፍርድ ቤቶች ደግሞ ተተኪ ወራሾች ልትሆኑ አትችለም በማለት ብይን ሰጥተዋል።
የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 842/3/ ስር እንደተመለከተው የሟች ልጆች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ሲሆኑ ልጆች ቀድመው ከሞቱና ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ ትተው ከሆነ ተወላጆቹ ወላጃቻውን ተክተው ሟችን እንደሚወርሱ ያመላክታል። የተተኪ ወራሽነት የተፈፃሚነት ወሰን ወደ ታች የሚቆጥሩ ተወላጆች እንደሆነ መረዲት ይቻላል። ወላጅ አባታቸው የእናታቸው የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ናቸው። አመልካቾችም የወላጅ አባታቸው የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች እንደሆኑ የህጉ መገንዘብ ይቻላል። ተተኪ ወራሽ ለመሆን ከፍ/ብ/ህ/ቁ/ 842/3/ አንፃር ሲታይ የአመልካቾች ጥያቄ የሚያሟላ አይደለም። ምክንያቱም ወላጅ አባታቸው የእናታቸው የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ በመሆን የወረሱ ስለሆነ የምትክ ጉዲይ ሉነሳ አይችልም። በልላ አነጋገር አመልካቾች አባታቸውን ተክተው አያታቸውን መውረስ የሚችለት አባታቸው ከአያታቸው በፉት የሞቱ እንደሆነ ብቻ ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይንና ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። በልላ በኩል አመልካቾች የሟች አባታቸውን ወራሽነት ስለማረጋገጣቸው ከክርክሩ ስለተረዲን አባታቸው የወረሱትን ንብረት ለመጠየቅ ይህ ውሳኔ አያግዲቸውም ብለናል። በዚሁ መሰረትም የሚከተለው ውሳኔ ሰጥተናል።
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪየ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 1118/07 ጥር 6 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ብይን፤ የአ/አ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ/23073 ጥር 21 ቀን 2007 ዓ/ም እና የአ/አ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 23140 የካቲት 2 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጡት ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ/ 348/1/መሰረት በአብላጫ ድምጽ ጸንቷል።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.