የመጀመሪያ ሚስት በንብረትዋ ላይ ስምምነት ባላደረገችበት ፤ባል ሁለተኛ ሚስት ሲያገባ መቃወሚያ አላቀረበችም በማለት በንብረትዋ ላይም ስምምነት አድርጋለች በማለት በመደምደም ፤ሁለተኛ ሚስት እኩል እንድትካፈል በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ህጋዊ አቶ ሃንደግባ ሸኩር እና ወ/ሮ አለምቴ ኢብራሑም 27/8/ 2008 ዓ.ም 279 59. አንድ ሰው ህጋዊ ባለይዞታው ሳይቃወም በልላ ሰው ይዞታ ላይ ቤት ወይም ንብረት ያፈራ እንደሆነ የዚሁ ቤት/ ንብረት/ ባለመብት የሚሆን ስለመሆኑ፣ የፍትሐ ብሓር ህግ ቁጥር 1179(1)(2) ከኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40 አኳያ ላታይ ስለሚችልበት አቶ አህመድ ዐመር እና እነ አቶ ተስፊዬ አብርሃ /ሁለት ሰዎች/ XXII
No summary available.
መ/ ሕዲር 05 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ተኽሉት ይመስል ቀነዓ ቂጣታ ክፍለፅዮን ማሞ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- አቶ አህመድ ዐመር ተጠሪዎች፡- 1ኛ. አቶ ተስፊዬ አብራሃ 2ኛ. አቶ ኃይለ ማሪያም አብራሃ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ አከራካሪ የሆነውን ጭብጥ የመሬት ባለይዞታ ሳይቃወም የተሰራ ቤት የሚኖረው ሕጋዊ ውጤት ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት፣ የፍትሐብሕር ሕግ አንቀፅ 1179/1/ እና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ከሰጠው አስገዲጅ ውሳኔዎች አንፃር አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ጉዲይ ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ዓዱግራት ወረዲ ፍርድ ቤቶች የአሰበሰበያ ምድብ ችልት የአሁኑ አመልካች በተጠሪዎች ላይ በፍ/መ/ ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው።
የአመልካች ክስ ይዘትም አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰው 490 ካሬ ሜትር የመሬት ይዞታ ያላቸው ሲሆን ተጠሪዎች በጉልበታቸው በሕጋዊነት ሳይሰጣቸው በኃይል በ1998 አንዲንድ ሰርቪስ ሁለት ክፍል ቤት እንደሰሩ፣ እንዱሁም በ2006 ዓ.ም በቀበላ በታገደበት ሁኔታ ፉት ለፉት ባለው ይዞታ ላይ በክብ ድንጋይ ቆርቆሮ ተክለው በሕጋዊ መንገድ ከተሰጣቸው ይዞታ ላይ ከሕግ ውጭ ስለወሰደባቸው ተጠሪዎች የሰሩቷ ቤት በራሳቸው ወጪ አፍርሰው ይዞታውን እንዱመልሱ እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ተጠሪዎች በሰጡት መልስም በ1998 ዓ.ም ቤቱን መስራታቸውን ሳይክደ ከዛ በኋላ ግን ምንም እንዲልሰሩና የሰሩት ቤትም አስተዲደር በሰጣቸው ቦታ ስለመሆኑ ተከራክረዋል።
የስር ወረዲ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ አጠቃላይ ይዘት በመዝገቡ ካሰፈረ በኋላ የአሁኑ ተጠሪዎች የሰሩት ሰርቨስ ቤት በ1998 ዓ.ም መሆኑ እንዲልተካደ፣ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40/6/ እና የፍትሐብሕር ሕግ አንቀፅ 1179/1/ መሰረት በማድረግ አመልካች ሳይቃወሙ የተሰሩት ሁለት ሰርቪስ ሆነ አጥር ግቢው ለመቃወም የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት የላቸውም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። የአሁኑ አመልካች በስር የወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለዞኑ ከፍተኛ እና ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ ያቀረበውም የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ነው። የአመልካች ሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- አከራካሪው ይዞታ ለቆዲና ላጦ ድርጅት እንደተሰጣቸው የተጠሪዎች ሕገ ወጥ ተግባር ይቃወሙ እንደነበር በመግለፅ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔና ትዕዛዝ እንዱሻር ማመልከታቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አከራካሪው ይዞታ የአሁኑ የሰበር አመልካች መሆኑ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ከመሆኑ አንፃር የሰበር አመልካች ተጠሪዎች ቤቱን ሲሰሩ ሳይቃወም ነው ቤቱ የተጠሪ ነው በሚል አግባብ ተጠሪዎች ቤት የሰሩበትን ይዞታ መልቀቅ የለባቸውም ተብል የተሰጠው ውሳኔ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1179/2/ እና /3/ እና ፍ/ብ/ሕ/ቁ 1180 ድንጋጌዎች አንፃር ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ተጠሪዎችን ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ተጠሪዎች የካቲት 06 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዱፀና አመልክቷል። ከስር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በፅሁፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ተገቢ ከሆነው ድንጋጌ በማገናዘብ እንዱሁም ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመርነውም አመልካች በሚመለከተለው የአስተዲደር ክፍል 490 ካሬ ሜትር የተሰጣቸው ስለመሆኑ ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ተጠሪዎች አከራካሪ በሆነው ይዞታ ላይ ቤት እንዱሰሩ በሚመለከተው አስተዲደር የተፈቀደላቸው መሆኑን በመግለፅ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ባያገኝም ለክርክሩ መነሻ የሆኑ ቤቶች በ1998 ዓ.ም ስለመስራታቸው ግን በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። የአሁኑ ተጠሪዎች በአከራካሪው ይዞታ ላይ ቤት ሲሰሩ አመልካች ያቀረቡት ተቃውሞ እንደነበረ ቢከራከሩም በስር ፍርድ ቤት በተደረገው የማጣራት ሂደት ግን መቃወሚያ ስለማቅረባቸው አልተረጋገጠም። አንድባለይዞታ ሳይቃወም የተሰራ ቤት ቤቱን የሰራው ሰው ባለመብት እንደሚሆን በፍ/ሕ/ቁ 1179/1/ ስር በግልፅ ተመልክቷል። አመልካች እየተከራከሩ ያለት የይዞታ ባለቤት በማንኛውም ጊዜ ተጠሪዎችን የማስለቀቅ መብት አለው በሚል እሳቤ ነው። በእርግጥ የይዞታ ባለመብት በይዞታው የተሰራው ቤት እንዱነሳለት ወይም ከ ¼ ኛ የማይበልጥ ካሳ ከፍል ቤቱን የማስቀረት መብት እንዲለው ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1179/2/ እና 1180 ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ነው። ይሁንና የፍትሐብሕር ሕግ በታወጀበት ዘመን መሬት በግል ባለሀብትነት የሚያዝ በመሆኑ በየትኛውም መልኩ በመሬቱ ላይ ከሁለም የሰፊ መብት ያለው በመሆኑ በባለቤቱ መቃወሚያ ሳይቀርብ የተሰራ ቤት ጭምር እንዱፈርስ የመጠየቅ መብት እንዲለው ተደንግጎ ነበር። ከላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች የሕዝብና የመንግስት መሆኑን ከደነገገው አንቀፅ 40/3/ ጋር በተጣጣመ መልኩ ነው። በዚሕም መሰረት የመሬት ባለይዞታ በፍትሐብሕር ሕግ አንቀፅ 1179/2/ እና 1180 በተደነገገው አግባብ በይዞታ ላይ ምንም ተቃውሞ ሳያቀርብ የተሰሩ ቤቶች ላይ የፈለገው እርምጃ የመውሰድ መብት የለውም። መሬት የሕዝብና የመንግስት ከመሆኑ አንፃር በባድ መሬት ላይ የተሰራው ቤት ላይ የመሬት ይዞታ መብት አለኝ የሚለው ወገን ቤቱን ከሰሩ ሰዎች የተሻለ መብት ሉኖረው አይችልም። በተያዘው ጉዲይ አመልካች በ490 ካሬ ሜትር ላይ የይዞታ ባለመብት ሁኖ የነበረ ቢሆንም አመልካች ሳይቃወም ተጠሪዎች በባድ መሬት ላይ ቤት ገንብተዋል። ተጠሪዎች በሕጉ አግባብ አልተሰጣቸውም ቢባል እንኳ የሚመለከተውን አስተዲደር ከሚጠይቅ በቀር በባድ የመሬት ይዞታ ላይ ጉልበትና ገንዘባቸውን በማፍሰስ የሰሩበት ቤት ላይ ከአመልካች የተሻለ መብት እንዲላቸው ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40/7/ እንደተመለከተው ተጠሪዎች በአከራካሪው ይዞታ ላይ የገነቡት ቤት ባለይዞታ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው።
አመልካች በአከራካሪው ይዞታ አለኝ የሚለትን መብት ለማስከበር ተገቢ ጥረት ባለማድረጋቸው ተጠሪዎች ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ቤት ሰርተው እየኖሩ እንደሚገኙ ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ መረዲት ይቻላል። አመልካች በፍትሐብሕር ሕጉ አንቀፅ 1179/2/ እና 1180 የተመለከቱትን መሬት በግል መያዝ በተፈቀደበት ስርዓት በነበረው አካሄድ በማንኛውም ጊዜ ተጠሪዎችን ከሰሩት ቤት ማፈናቀል እንደሚችለ በመግለፅ ያቀረቡት ክርክር የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40/2/ እና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ እና በላልች መዝገቦች የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ያላገናዘበ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የአሁኑ ተጠሪዎች አመልካች ሳይቃወሙ የሰሩት ሁለት ሰርቨስ ቤት ሆነ አጥር ግቢው ባለይዞታ መሆናቸውን በማረጋገጥ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40/3/ እና /7/ እንዱሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ የሰጣቸው ገዥ ውሳኔዎች መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በስተቀር በጉዲዩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን አያሳይም። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች አመልካች ሳይቃወሙ የተሰሩ ቤቶች እንዱፈርሱ የመጠየቅ መብት የላቸውም ብለናል። ተጠሪዎች አመልካች ሳይቃወሙ የሰሯቸው ቤቶች ባለመብት ናቸው ብለናል።
በዚህም ተከታዩን ወስነናል።
በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የዓዱግራት ወረዲ ፍርድ ቤቶች የአሰበሰበያ ምድብ ችልት በመዝገብ በቀን 8/07/2006 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 13/09/2006 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በ23/10/2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በድምፅ ብልጫ ፀንቷል።
ተጠሪዎች አመልካች ሳይቃወሙ የሰሩት ሁለት ሰርቨስ ቤት እና አጥር /ግቢው/ ባለመብት ናቸው በማለት ወስነናል።
የዚህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳራቸው ይቻለ ብለናል።
የልዩነት ሐሳብ እኛ ስማችን በ2ኛ እና 4ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰዉ ዳኞች አብላጫዉ ድምጽ ከሰጠዉ ዉሳኔ በመለየት የሚከተለዉን የልዩነት ሐሳባችንን እናስቀምጣለን።
በዚህ ጉዲይ መታየት ያለበት አሁን በአገራችን ባለዉ ሥርዓት እና የሕግ ማዕቀፍ ግለሰቦች ወይም ዜጎች የመሬት ነክ ንብረት ጋር በተያያዘ ያላቸዉ መብት ነዉ። የኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የመሬት ነክ ንብረት በግለሰብ ደረጃ በግል መያዝ እንደሚቻል በወቅቱ በሥራ ላይ የነበሩት የሕግ ማዕቀፍ የሚያመለክት ጉዲይ ነዉ። የኃይለ ስላሴ መንግስት ከወቀደ በኋላ የመሬት ነክ ንብረት በግለሰብ በግል የመያዝ ሁኔታ በደርግ መንግስት ቀሪ መደረጉ ይታወቃል።
በአገራችን ከደርግ መንግስት ዉድቀት በኋላ እና የኢህአዳግ መንግስት ስልጣን ከያዘ ወዱህ የመሬት ነክ ንብረት ባለቤትነት የኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ሀብት መሆኑ ተረጋግጧል።
በዚህ መሰረት የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት በ1987 ዓ.ም ከመዉጣቱ በፉት የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የመንግስትና የሕዝብ ሀብት መሆኑን ባረጋገጠ መልክ የሕግ መዕቀፍ ወጥቶ ሲሰራበት እንደነበር ይታወቃል። በዛን ወቅት የከተማ መሬትን በተመለከተ የከተማ ቦታ በኪራይ ስለመያዝ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 80/1986 ዓ.ም መሰረት የሚመራ ነበር። በመቀጠል በኢ.ፋ.ዳ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 40 /3/ መሰረት የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ ነዉ። መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሓሮች፣ ብሓረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነዉ። በማለት ይደነግጋል። ስለሆነም የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ባለቤትነት የመንግስትና የሕዝብ እስከሆነ ድረስ ግለሰቦች በመሬቱ ላይ ሉኖራቸዉ የሚችለዉ የባለይዞታነት መብት እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም።
ይህን በሕገ መንግስቱ የተመለከተዉን መርህ ተከትል የመንግስትና የሕዝብ የመሬት ባለቤትነትን ባረጋገጠ መልኩ እና ግለሰቦች ደግሞ የመሬት ባለይዞታነት መብት የሚያገኙበት ሥርዓት እና ይህ መብት የሚከበርበት የሕግ ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራበት ይገኛል። የከተማ መሬትን በተመለከት የከተማ ቦታን በሉዝ መያዝን እንደገና ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 272/1994 ዓ.ም በሚደነግገዉ አግባብ ሲመራ የነበረ ሲሆን፣ ይህ አዋጅ ከተሻረ በኋላ በአሁኑ ወቅት የከተማ ቦታን በሉዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ዓ.ም እና ይህን አዋጅ ተከትል በወጣዉ ደንብ መሰረት እየተሰራበት መሆኑ ግልጽ ነዉ። ግለሰቦች ወይም ዜጎች የመሬት ነክ ንብረትን በተመለከተ የባለይዞታነት መብት ለማግኘት የሚችለት እነዚህ ሕገ መንግስቱን ተከትል በወጡት ዝርዝር ሕጎች መሰረት ስልጣን ባለዉ የመንግስት አካል መሆን አለበት። ከዚህ ዉጭ ግን የከተማ መሬት መያዝ እንደማይቻል እና ከዚህ ሕግ አግባብ ዉጭ ማንም ግለሰብ የከተማ መሬትን በመያዝ ሕጋዊ የባለይዞታነት መብት ሉያገኝ አይችልም። በዚህ ሕግ አግባብ አንድ ግለሰብ የከተማ መሬት ስልጣን ባለዉ የመንግስት አካል የተሰጠዉ እንደሆነ ይህ መብት ሉከበርለት ይገባል፤ ከሕግ ዉጭ የባለይዞታነት መብቱን በመንግስትም ሆነ በልላ አካል ወይም ግለሰብ ሉነጠቅ አይገባም። ይህ ማለት በዚህ አግባብ ባገኘዉ የከተማ መሬት ላይ የግል ንብረት የማፍራት መብት አለዉ። አንድ ሰዉ በሕጉ አግባብ ባገኘዉ የከተማ መሬት ላይ በጉልበቱ፣ በእዉቀቱ ወይም በገንዘቡ ንብረትን ያፈራ እንደሆነ የንብረቱ ባለሀብት እንደሆነ የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 40 /2/ ያመለክታል። በመሆኑም አንድ ግለሰብ የከተማ መሬት መያዝ የሚችለዉ በሕጉ አግባብ ሲሆን፣ በዚህ አግባብ ባገኘዉ የመሬት ይዞታ ላይ የግል ሀብት ማፍራት ይችላል። ከዚህ ዉጭ የከተማ መሬትን በሕገ ወጥ መንገድ በመያዝ በመሬቱ ላይ ንብረት ስላፈራ ብቻ የባለይዞታነት መብት ሉሰጠዉ የሚችል አይሆንም። ሕግ የዘረጋዉን ሥርዓት ተከትል የተገኘዉን የባለይዞታነት መብት በዚህ ይዞታ ላይ ከተፈራ ንብረት መብት አንጻር በአግባቡ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ። የመሬት ባለይዞታነት መብት ትልቅ መብት በመሆኑ በሕገ ወጥ መንገድ ተይዞ ንብረት ስለተፈራ ብቻ ከባለይዞታነት መብት ይልቅ ለንብረት መብት የበለጠ ክብደት በመስጠት ያነሰ ዋጋ ሉሰጠዉ አይገባም። ይህ ደግሞ የመሬት ባለይዞታነት መብትን ተገቢ ክብደት የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ ሕገ ወጥ የሆነ የከተማ መሬት ወረራን ለመከላከልም የሚያግዝ ነዉ።
በዚህ መሰረት አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች ለክርክር ምክንያት የሆነዉን 490 ካ.ሜ የከተማ መሬት በሕጉ አግባብ ስልጣን ባለዉ የመንግስት አስተዲደር አካል የተሰጠዉ እና የባለይዞታነት መብት ያገኘ መሆኑ በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ።
ይህ በመሆኑ የአሁን አመልካች በዚህ መሰረት ያገኘዉን የባለይዞታነት መብት የሕግ አግባብ ተከትል ስልጣን ባለዉ አካል ከሚወስነዉ ዉሳኔ ዉጭ ይህን የባለይዞታነት መብቱን ሉያጣ የሚችልበት ሁኔታ ሉኖር አይችልም። የአሁን አመልካች ይህን ይዞታ ለታለመለት ዓላማ ያላዋለ እንደሆነ የሚመለከተዉ የአስተዲደር አካል በሕግ አግባብ በሚወስደዉ እርምጃ ይህን የባለይዞታነት መብቱን ከሚያጣ በስተቀር ማንም ግለሰብ ይህን ይዞታ ከሕግ ዉጭ ይዞበት ንብረት ስላፈራ አመልካች መብቱን የሚያጣበት አግባብ የለም። የአሁን ተጠሪዎች በዚህ ይዞታ ላይ ሁለት ሰርቪስ ቤቶችን መስራታቸዉ በሥር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። ነገር ግን የአሁን ተጠሪዎች በዚህ ይዞታ ላይ ሰርቪስ ቤቶች ይስሩ እንጂ በይዞታዉ ላይ የባለይዞታነት መብት በሚመለከተዉ የመንግስት አስተዲደር አካል ማግኘታቸዉን በሥር ፍ/ቤቶች ያረጋገጡት ነገር የለም። በመሆኑም የአሁን ተጠሪዎች ይህን የከተማ መሬት የባለይዞታነት መብት የሕጉን አግባብ ተከትለዉ ባላገኙበት ሁኔታ በዚህ ይዞታ ላይ ቤት በመሥራታቸዉ ብቻ የባለይዞታነት መብት የሚያጎናጽፊቸዉ ነገር የለም። ከላይ የተመለከቱትን የከተማ መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ እና ደንብ ሲታይ በሕግ አግባብ ባልተገኙ ይዞታ ንብረት ማፍራት የባለይዞታነት መብት የሚያጎናጽፍ መሆኑን የሚያመለክተዉ ነገር የለም።
ከዚህ አንጻር በ1952 ዓ.ም በኃይለ ስላሴ መንግስት የታወጀዉን የፍትሐብሕር ሕግ አሁን ያለዉ የመሬት ነክ ንብረት ተፈጻሚነት አለዉ ወይ? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ። ይህ ሕግ የታወጀበት ወቅት መሬት እንደግል ሀብት የሚታይ እና በግል መያዝ እና እንደግል ሀብት እንደሚቆጠር የሚያመለክት ነዉ። በመሆኑም በዚህ ሕግ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ሲታዩ መሬት በግል ሀብትነት የሚያዝ መሆኑን በሚያመለክት መልኩ ‹‹ባለመሬቱ›› በማለት ይደነግጋል። በዚህ ረገድ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1178፣ 1179 እና 1180 ማየት ይቻላል። የእነዚህ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ሲታይ መሬት በግለሰብ እንደግል ሀብት መያዝ በሚችልበት ሥርዓት ዉስጥ እንደሆነ ግልጽ ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስት እና ሕገ መንግስቱን ተከትል ከወጡት ዝርዝር ሕጎች አንጻር ሲታይ እነዚህ የፍትሒ ብሓር ድንጋጌዎች የከተማ መሬት ነክ ንብረትን በተመለከተ ተፈጻሚነት የላቸዉም። ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት የከተማ መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም ለመቆጣጠር የወጡት ሕጎች አንድ ሰዉ ሕጋዊ ባለይዞታ መብት ሳይኖረዉ ሕጋዊ ባለይዞታዉ ሳይቃወም በልላ ሰዉ ይዞታ ላይ ቤት ወይም ንብረት ያሳረፈ ወይም ያፈራ እንደሆነ ይህ ጉዲይ በምን አግባብ ይታያል? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ።
በዚህ ረገድ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ሕገ መንግስትን ተከትለዉ የከተማ መሬት ነክ ንብረትን ለማስተዲደር የወጡት ሕጎች የሚለት ነገር ባለመኖሩ በግለሰቦች መካከል የተፈጠረዉን አለመግባባት ለመፍታት የፍትሒ ብሓር ሕግ እንደአግባብነቱ ተፈጻሚነት ሉኖረዉ ይገባል የሚባል ከሆነ የግራ ቀኙን መብት ፍትሒዊና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በሚያስጠብቅ ሁኔታ ተፈጻሚ መደረግ አለበት እንጂ የአንደን ወገን ተጠቃሚነት ብቻ በሚያረጋግጥ መንገድ ተፈጻሚ መደረግ የለበትም። ይህ ማለት የባለይዞታዉን መብት ብቻ ወይም በይዞታዉ ላይ ንብረት ያፈራዉን ወገን መብት ብቻ ባስጠበቀ መልኩ ተፈጻሚ መሆን የለበትም። የሁለቱንም ወገኖች መብት ፍትሒዊና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ባስጠበቀ ሁኔታ ተፈጻሚ ማድረጉ ተገቢ ነዉ። በዚህ መሰረት የአሁን አመልካች በይዞታዉ ላይ ተጠሪዎች የሰርቪስ ቤቶችን ሲሰሩ ባለመቃወሙ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1179 /1/ ተፈጻሚ ላሆን ይገባል የሚባል ከሆነ፣ የአንቀጹ ላልች ንዐስ አንቀጾችም ተፈጻሚነት ሉኖራቸዉ ይገባቸዋል። የድንጋጌዉ ንዐስ አንቀጽ 1 እንደሚደነግገዉ ‹‹ባለመሬቱ ሳይቃወም በልላ ሰዉ መሬት ሕንጻ የሰራ ሰዉ የዚሁ ሕንጻ ባለሀብት ነዉ›› የሚል ነዉ። አሁን ለተያዘዉ ጉዲይ ይህን ድንጋጌ ብቻ ተፈጻሚ አድርጎ መተዉ፣ የተጠሪዎችን የንብረት መብት ብቻ ባስጠበቀ መንገድ ተፈጻሚ መደረጉን እንጂ የአመልካችን የባለይዞታነት መብት ከግምት ያስገባ ሆኖ አይታይም። ይህን ድንጋጌ ፍትሒዊ በሆነ ሁኔታ ተፈጻሚ ማድረግ ካስፈለገ ለንብረት መብት ብቻ ሳይሆን ለባለይዞታ መብትም ተገቢዉ ክብደት ሉሰጠዉ ይገባል። ይህ ደግሞ ሉረጋገጥ የሚችለዉ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1179 ሥር የተመለከቱትን ንዐስ አንቀጾች በአጠቃላይ ተፈጻሚ በማድረግ ነዉ። ይህ ማለት የፍትሐብሕር ሕግ አንቀጽ 1179 እና 1180 እንደሚደነግገዉ ባለይዞታዉ በሕጉ በተዘረጋዉ ሥርዓት ሕንጻዉን ለገነባዉ ሰዉ ተገቢዉን የካሳ ግምት በመክፈል ይዞታዉን የማስለቀቅ መብቱ ሉጠበቅለት ይገባል።
አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስ የአሁን አመልካች በዚህ ድንጋጌ በተዘረጋዉ ሥርዓት መሰረት ለአመልካቾች ተገቢዉን የንብረት ካሳ ግምት በመክፈል ይዞታዉን የማስለቀቅ መብቱ ሉጠበቅለት ይገባዉ ነበር። ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶችም የአሁን አመልካች ለክርክር ምክንያት በሆነዉ ይዞታዉ ላይ ተጠሪዎች የሰሩት ቤቶች ግምት ምን ያህል እንደሆነ በባለሙያ አስገምተዉ አመልካች ተገቢዉን ካሳ ከፍል ይዞታዉን እንዱያስለቅቅ ማድረግ ሲገባቸዉ የተጠሪዎችን መብት ብቻ በሚያስጠብቅ መልክ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1179 /1/ ተርጉመዉ ተፈጻሚ በማድረግ የሰጡት ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተሽሯል። እንዱሁም የሥር የወረዲዉ ፍ/ቤት ጉዲዩን ድጋሚ በማየት በባለሙያ ቤቱን በማስገመት አመልካች ይህን ግምት ለተጠሪዎች እንዱከፍል በማድረግ ይዞታዉ ለአመልካች እንዱለቀቅ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ እንዱሰጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343 /1/ መሰረት ሉመለስለት ይገባ ነበር በማለት ወስነናል።
No topics extracted.