No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ሃንደግባ ሽኩር - ቀርቧል።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ አለምቴ ኢብራሂም - ወኪል ለይላ ሃንዲግባ - ቀርቧል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በመ/ቁ. 66280 ህዲር 20 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። በተመሳሳይ ጥያቄ በ
አመልካች የሆኑት ወ/ሮ መኪያ ሐጂ ማመጫ ያለው ክርክር ጭብጥ ተመሳሳይና አንድ አይነት በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.11/1/ መሰረት እንዱጣመሩ ተደርገዋል።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካች እና ተጠሪ በትዲር የቆዩ ሲሆን ለዚህ ክርክር መነሻው ጋብቻው በፍቺ በመፍረሱ የተጀመረው የጋራ ንብረት ከፍፍል ጉዲይ ነው። በአመልካች እና ተጠሪ የነበረው ጋብቻ በመፍረሱ የአሁኗ ተጠሪ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ በማቀርቧ ወ/ሮ ሚኪያ ሐጂ ሁለተኛ ሚስት ጣልቃ መግባቷን በስር መዝገብ ተመልክቷል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ ተጠሪ በክስዋ ከተራ ቁጥር 1ኛ-4ኛ ድረስ አዋሳኝ ተጠቅሶ በአራት ቦታዎች የሚገኙ መሬቶች በአጠቃላይ 0.85 ሄ/ር ይካፈለ። ጣልቃ ገብ/2ኛ ሚስት/ለአሁን አመልካች በሚደርሰው የመሬት እርሻ መጠን ላይ ግማሽ መብት አላት። እልፍኝ እና የሳር ክዲን ቤት የአመልካች እና የተጠሪ የጋራ ንብረት በመሆኑ ቢቻል በአይነት አሉያም በገንዘብ ተገምቶ እኩል ይካፈለ።
በጓሮው የሚገኘውን ጫትና ቡና ላልች አትክልቶች ከብቶች እና እንስሳቶችን አመልካች እና ተጠሪ እኩል ይካፈለ እንዱሁም በ2004 ዓ.ም ለመንገድ ስራ ምክንያት የተከፈለ ብር 20,000 /ሃያ ሺ ብር/ የንብረት ካሳን በተመለከተ 1ኛ አመልካች እና ተጠሪ እኩል እኩል ከተካፈለ በኋላ ጣልቃ ገብ ከአመልካች ድርሻ ላይ ግማሽ ወይም ከአጠቃላዩ የካሳ ብር ላይ 1/4ኛ ሉደርሳት ይገባል በማለት ውሳኔ ስጥተዋል።
ይህን ውሳኔ በመቃወም የአሁኗ አመልካችና ጣልቃ ገብ የየራሳቸውን ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ሁለቱንም ይግባኝ መዝገቦች አጣምሮ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ተጨማሪ ማስረጃ እንዱቀርብ አድረጎ ከመረመረ በኋላ በስር ፍርድ ቤት በተገቢው ዲኝነት ሳይከፈልበት የቀረቡትን ቅሬታዎች ዲኝነት ከፍለው የመጠየቅ መብታቸው ከጠበቀ በኋላ በተቀሩት ላይ በመንገድ ስራ ምክንያት ንብረት ካሳ የተከፈለ ሙለ በሙለ ለጋራ ጥቅም አለመዋለን በበቂ ሁኔታ በተጠሪ ማረጋገጥ ሳይቻል የተሰጠ ውሳኔ ነው በማለት ሽሮታል። በ2006 ዓ.ም የተገኘ መሬት ላይ ተጠሪ 2.5 ኩንታል ስንዳ ይድረሳት ተብል በስር ፍርድ ቤት የተወሰነውን አጽንቶታል። እንዱሁም እልፍኝ ቤት የስር ፍርድ ቤት ለሶስት እኩል ይካፈለ የተባለው ውሳኔ የሚነቀፍበት ነጥብ የላለው ሆኖ ለአፈፃፀም እንዱመች የእልፍኝ ቤቱን 1/3ኛ ግምት ለተጠሪ እንዱከፈል በማሻሻል ውሳኔ ሰጥቷል።ሁለቱ ሚስቶች በየጓሯቸው ያለውን አንድ ጥማድ እንሰት፤ጫት እንዱሁም አቡካድ ያላቸው መሆኑን በወረዲ ፍ/ቤት በሰው ምስክር ያረጋገጡ ቢሆንም እንዱሁም ጣልቃ ገብ ከ21 አመታት በላይ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ስትፈጽም ተጠሪ ሳትቃወም እና በጋራ ስትኖር መቆየቷ እየታወቀ በጋራ የሚጠቀሙበትን አጠቃላይ መሬት 1/4ኛ ብቻ ይገባታል በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት የላለው በመሆኑ የወረዲው ውሳኔ ተሽሯል ካለ በኋላ እያንዲንዲቸው ሚስቶች በይዞታቸው በስተጀርባ ያለውን እንሰትና አትክልት ከአመልካች ጋር እኩል ይካፈለ፤ ቀሪውን ሁለት መሬት እና መሬቱ ላይ የሚገኙ ዛፍች ደግሞ ሶስቱም እያንዲንዲቸው 1/3ኛ መጠን ይካፈለ። በሬና ፈረስ እንዱሁም እልፍኝ የሳር ቤቱን በተመለከተ የወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔውን በማጽናት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ አፈፃፀሙ ግን እያንዲንዲቸው 1/3ኛ ይካፈለ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለደ/ብ/ብ/ህ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ብታቀርብም የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ላይ ጉድለት የላለው መሆኑን ገልፆ የተጠሪን ይግባኝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.337 መሰረት በትእዛዝ ሰርዞታል።
በተጠሪ አመልካችነት ቀጥል በሰበር የተመለከተው የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ግራ ቀኙ አስቀርቦ ከሰማቸው በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ቤት ጓሮ ያለው የእርሻ ይዞታ ብቻ ከስር ተከሳሽ ጋር ይካፈለ በማለት የሰጠው ውሳኔ ተጠሪ በላልች ይዞታዎች ላይ ያላትን መብት ያላገናዘበ በመሆኑ በመሻር የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዲ ፍርድ ቤት በአራቱ የተለያዩ አዋሳኛቸው የተጠቀሱት ስፊታቸው 0.85 ሄ/ር ከሳሽና ተከሳሽ እኩል ሉካፈለ ይገባል በማለት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል። እልፍኝ የሳር ክዲን ቤት የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለሶስት ይካፈለ ለአፈፃፀም ያመች ዘንድ ተጠሪ ግምት ትውሰድ በማለት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የወረዲ ፍ/ቤት ተጠሪና የስር አመልካች እኩል እንዱካፈለ የሚለውን ውሳኔ አጽንቶታል።
አሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካቾች ታህሳስ 6 ቀን 2008 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት በመግለፅ ስህተቱ እንዱታረምላቸው ዘንድ ጠይቀዋል። አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ ተጠሪም ሳትቃወም ጣልቃ ገብ ከስር ተከሳሽ ጋር ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በጋብቻ ተሳስረው ንብረት ሁለ በጋራ ማፍራታቸው እየታወቀ አሁን በተጠሪና ተከሳሽ መካከል የነበረው ጋብቻ ፈርሶ የጋራ ንብረት ሲደረግ አመልካች በጋብቻ ላይ ጋብቻ የፈፀመች ስለሆነ ድርሻዋን ከስር ተከሳሽ ግማሹን ታግኝ በማለት በክልለ ሰበር ችልት የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። አመልካቾችና ተጠሪ ክርክራቸውን በፅሁፍ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን በዚህ መሰረትም አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል። አመልካቾች በጣልቃ ገብና ተከሳሽ ስም የተመዘገበ በደማላ ደስይበር ቀበላ ስፊቱ 0.486 ሄ/ር ይዞታ መኖሩ ተረጋግጦ ከግብርና ለፍርድ ቤት ተልኳል። ከተከሳሽ እናት ለወ/ሮ ሚኪያ ሒጂ ጎጆ መውጫ መቋቋሚያ ይሆን ዘንድ ከ21 አመት በፉት የሰጠችን ይዞታ ላይ ከወ/ሮ ሚኪያ ሒጂ ጋር የሰራነው ቤት እና በጓሮው በቆጮና በላልች ቋሚ ሰብልች በማልማት የቆየንበት የአሁኗ ተጠሪም ይዞታዋና ልማቷን የማይነካ በመሆኑ ጋብቻችንን ሳትቃወም 21 አመት የቆየች ስትሆን የወ/ሮ መኪያ ሒጂ የራሷን ይዞታ እና መሬት በስሟ ግብር እየገበረች ቆይታ በ1997 ዓ.ም በስሟ 3 የሆነ የገጠር መሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርቲፍኬት የሁለታችን ፍቶ ያለበት አውጥታበተለች። ይህን ማስረጃ ስታወጣ ተጠሪ ተቃውሞ አልነበራትም እስከ ዛሬ ድረስ ተቃውሞ አቅርባ ደብተሩን አላሰረዘችም። በስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሕጉን ተከትል አጣርቶ የሰጠው ውሳኔ የክልለ ሰበር ችልት በቂና አሳማኝ ምክንያት ሳይሰጥ መሻሩ እንዱሁም ከወ/ሮ መኪያ ጋር ያለ ጋብቻ ሳይፈርስ ሁላችንም እንድንከፊፈል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የቤተሰብ ህግ መርህ የጣሰ በመሆኑ የክልለ ሰበር የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ተሽሮ እንዱወሰልን የሚል ነው።
በተጠሪ በኩል ደግሞ ከአመልካች ጋር በ1970 ዓ.ም ጋብቻ ከፈፅምን ጀምሮ መጠኑ 0.85 ሄ/ር በጋራ ማፍረታችን በማስረጃ ተረጋግጦ ከዚሁ ግማሽ ድርሻ እንድታገኝ የሰጠው ውሳኔ ስህተት የለውም። አመልካች ከወላጅ እናቱ ለማቋቋሚያ የተሰጠው አስመስል ያቀረበው በስር ወረዲ ፍ/ቤት ክርክር ያልተነሳና በጭብጥነት ያልተያዘ ከስነ-ስርዓት ህጉ ውጭ አዱስ የቀረበ ክርክር ስለሆነ አቤቱታው ውድቅ እንዱደረግ። አመልካችና ተጠሪ እኩል ድርሻ እንድናገኝ የሰጠው ውሳኔ ጣልቃ ገብ አመልካች በደረሰው ድርሻ ላይ መብት እንዲላት በመግለፅ የቤተሰብ ህግ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር በመ/ቁ. 45548 የሰጠው አስገዲጅ ትርጉም መሰረት አድርጎ የተሰጠ ትክክለኛና ፍትሒዊ ነው። የይዞታ ማረጋገጫ የተገኘበት መንገድ የህግን አግባብ ያልተከተለ መሆኑ በማረጋገጥ ሰነደን ውድቅ በማድረግ የስር ተከሳሽና የተጠሪ ንብረት መሆኑን ማስረጃ የመስማትና የመመዘን ስልጣን በተሰጠው የስር ፍርድ ቤት ተረጋግጦ የተሰጠ ውሳኔ ነው።
ጋብቻ ሲፈርስ የንብረት ክፍፍል ሲደረግ የሁለተኛ ሚስት ጋብቻ በፀናበት በንብረቶቹ ላይ ያለን ድርሻ መወሰኑ የቤተሰብ ህግ መርህ የሚጥስ አይደለም። ስለሆነም የክልለ ሰበር ውሳኔ በአግባቡ ስለሆነ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በአመልካችና ተጠሪ የተመሰረተው ጋብቻና አከራካሪው የእርሻ መሬት ይዞታዎች በምሪት የተሰጣቸው አመልካችና ጣልቃ ገብ ከመጋባታቸው በፉት መሆኑ በግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች የተካደ አይደለም። አመልካች እና በስር ጣልቃ ገብ በመሬት ይዞታቸው ይገባናል የሚለት በስጦታ የተሰጠን በልላ በኩል ደግሞ በስማችን ተመዝግቧል፤መቃወሚያ በማቅረብ አልተሰረዘም የሚለ ናቸው። እነዚህ መከራከሪያ ነጥቦች በስር ክርክር ሂደት ያልነበሩና ያልተረጋገጡ ናቸው።
በክርክር አመራር ስርአት አንድ ተከራከሪ ወገን ማንሳት የሚገባው በመጀመሪያ በሚሰጠው የመከላከያ መልስ በግልፅ ማቅረብ እንዲለበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.234 ስር ተመልከቷል። በስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃ የመመዘንና የማጣራት ስልጣን ባለቸው ቀርቦ ውሳኔ ያልተሰጠበት ነጥብ በዚህ ደረጃ ማንሳቱ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.329 እንዱሁም በህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ሀ/ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 አንፃር ተቀባይነት የለውም። አመልካች እና ተጠሪ የተሰጣቸው የእርሻ መሬት ይዞታ ከአመታት በኋላ ወ/ሮ መኪያ ሐጂ በሁለተኛ ሚስትነት ጋብቻ መመስረት የነበረው የመሬት ይዞታ ላይ ተጠሪ ስምምነት ባላደረገችበት በቀጥታ እኩል የምታገኝበት የህግ ድጋፍ የለውም። ተጠሪ አመልካች ሁለተኛ ሚስት ሲያገባ መቃወሚያ ባለማቅረብዋ በንብረቶችዋ ላይም ተስማምታለች ለማለት አይቻልም። ስለሆነም በክልለ ሰበር ችልት በእርሻ መሬት ይዞታዎችና እልፍኝ የሳር ክዲን ቤት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የወረዲ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማፅናት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ. 66280 ህዲር 20 ቀን 2008 ዓ.ም በክስ ተራ ቁጥር 1-4 የተዘረዘሩት የመሬት ይዞታዎች 0.85 ሄክታር እና እልፍኝ የሳር ክዲን ቤት በተመለከተ የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር የወረዲ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማፅናት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348/1/ መሰረት ፀንቷል።
የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.11537መስከረም 7 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችልት በላልች ጉዲዮች የተሰጠ ውሳኔ አልተነካም።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ከመ/ቁ.120843 ጋር እንዱያያዝ ይደረግ።
ከዚህ ፍርድ ቤት በቀን 19/04/2008 ዓ.ም በዋለው ችልት በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዲ በመ/ቁ. 03867የተጀመረው አፈፃፀም ላይ ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።
ይፃፍ።
መዘገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.