በአባት በኩል ያለን መወለድ መቃወም የሚቻለው የልጁ አባት ነው ተብል በህግ ግምት የሚሰጠው ሰው እሱ የሞተ ወይም ችልታ ያጣ እንደሆነ ከተወላጆቹ አንደ የመካድ ክስ በማቅረብ መቃወም የሚችል ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/1992/አንቀጽ 167፣174 እና 179
No summary available.
ቀን 22/09/08ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ ሙለ በዲዲ -አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የተጀመረው አዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ነው። አመልካች ለአ/አ/ከ/አስ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርበውት በነበረው አቤቱታ መሰረት አመልካች የሟች አቶ በዲዲ ባቱ ህጋዊ ወራሽ ናቸው። በማለት የወሰነ ሲሆን ተጠሪዎች ይህን ውሳኔ በመቃወም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት ባቀረቡት መቃወሚያ የመቃ/ተጠሪ የሟች አቶ በዲዲ ባቱ ልጅ አይደለም። የተሰጣቸው የወራሽነት ውሳኔ ይሻርልን ብለዋል። የመቃ/ተጠሪ በበኩላቸው ሟች አባቴ ናቸው የተወለድኩት ሟች ከእናቴ ጋር በትዲር አብረው ሲኖሩ በነበሩበት ጊዜ ነው። የወራሽነት ውሳኔው ሉሻር አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱ የግራቀኙን ክርክር ከቀረቡት ማስረጃ ጋር በመመርመር ለመቃ/ተጠሪ ቀደም ሲል የሰጠው የወራሽነት ውሳኔ እንዲይፈጸም በማገድ የመቃ/ተጠሪ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ልጅነታቸውን አረጋግጠው በመጡ ጊዜ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብታቸው ተጠብቋል ብል መዝገቡን ዘጋው።
የመቃ/ተጠሪ (የአሁን አመልካች) በዚህ ትእዛዝ ላይ ቅሬታቸውን በየደረጃው ለይግባኝ ሰሚ ችልቱ እና ለሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት የስር ፍ/ቤትን ትእዛዝ ለማሳረም ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች አቶ በዲዲ ባቱ ልጅ መሆናቸው ተረጋግጦ የወራሽነት ማስረጃ ካገኙ በኋላ ተጠሪዎች በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 167 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት የመካድ ክስ ባላቀረቡበት ሁኔታ በልላ የመቃወም ዘዳ ተጠቅመው የአመልካችን የወራሽት ማስረጃ ውድቅ እንዱሆን ያደረገበትን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ተደርጓል።
አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥና ይዘት ከዚህ በላይ የተመዘገበው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ የሰበር አቤቱታው እንዱመረመር ከተያዘው ጭብጥ አንጻር የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
እንደመረመርነውም፡- በአባት በኩል ያለን መወለድ መቃወም የሚቻለው የልጁ አባት ነው ተብል በህግ ግምት የሚሰጠው ሰው፤ እሱ የሞተ ወይም ችልታ ያጣ እንደሆነ ከተወላጆቹ አንደ የመካድ ክስ በማቅረብ ብቻ ስለመሆኑ ከተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/1992 አንቀጽ 167፣174 እና 179 ድንጋጌዎች ተመልክቷል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ተጠሪዎች ስር ፍ/ቤት የመቃወም አቤቱታ ያቀረቡት የአሁን አመልካች የሟች አቶ በዲዲ ንጋቱ ልጅ ሳይሆኑ የወሰደት የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዝልን በሚል ሲሆን የአሁን አመልካች የተወለድኩት በጋብቻ ውስጥ ነው። ይህን መቃወም የሚቻለው የመካድ ክስ በማቅረብ ነው። ጉዲዩ የቀረበለት ስር ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት ክርክር ያደረጉ መሆኑን ከስር ፍ/ቤት ውሳኔ መገንዘብ የሚቻል ነው። የአሁን አመልካች ስር ፍ/ቤት በነበረ ክርክር እና በዚህ ሰበር ችልት ባቀረቡት ክርክር በጋብቻ ውስጥ የተወለደ መሆኑን ጠቅሰው የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪዎች ይህን በማስተባበል በሰበር መልሳቸው በግልጽ ያቀረቡት ክርክር የለም። አመልካች በጋብቻ ውስጥ የተወለደ መሆኑ ካልተካደ ደግሞ ልጅነታቸውን እንዱያረጋግጡ አይጠበቅም። የአሁን ተጠሪዎች የአመልካችን ተወላጅነት ለመካድ ክስ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የስር ፍ/ቤት ከዚህ በላይ በተጠቀሱ የቤተሰብ ህጉ ድንጋጌዎች መሰረት ጉዲዩን ለማየት በህግ ስልጣን በተሰጠው ፋ/ፍ/ቤት የመካድ ክስ እንዱያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቶ የመቃወም አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ ሲገባው የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ተመልክቶ ለአሁን አመልካች የተሰጠውን የወራሽነት ውሳኔ እንዲይፈጸም በማገድ የአሁን አመልካች ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ልጅነታቸውን አረጋግጠው ባቀረቡ ጊዜ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብታቸው ተጠብቋል በማለት የሰጠው ትእዛዝ ህጉን የተከተለ ባለመሆኑ ጉዲዩን በይግባኝ እና በሰበር አቤቱታ የተመለከተው የአ/አ/ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትም ይህን ሳያርም ማለፈ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
በቀን 26/10/2007ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪዎች የአመልካችን ተወላጅነት መካድ የሚችለት የመካድ ክስ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት በማቅረብ ነው ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት ግራቀኙ ያወጡትን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.