ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ተጠቃሚ ሆነው ባለበት ፍቺ ቢከሰት የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነው ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ለባል ወይም ለሚስት ሉያካፍል የሚገባ ስላለመሆኑ ፣ የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/95 አንቀጽ XXI
No summary available.
ሚያዚያ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ባልቻ አበበ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ አልማዝ ዓሉ - ቀርበዋል መዝገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች የልሜ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ በ12/12/2006 የሰጠውን ብይን የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 09/04/2007 ዓ.ም የሻረው ቢሆንም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ችልት በመ/ በቀን 01/07/2007 የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ የሻረ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ በ17/07/2002 ዓ.ም መሰረታዊ ስህተት አልተፈፀመም በማለቱ በዚሀ ሰበር ችልት ታይቶ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
ጉዲዩ የቀረበው የጡረታ አበልን አስመልክቶ ከፍቺ በኋላ ስለሚኖረው ውጤት ነው በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት ተጠሪ ሲሆኑ አመልካች ተከሳሽ ነበሩ። የክሱ ይዘት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍቺ ከተጠናቀቀ በኋላ የንብረት ክፍፍል አድርገዋል ፣አመልካች በተጠሪ ኪራይ ቤት ላይ የተደገፈውን ቤትና ሱቅ አፍርሶ ያንሳልኝ የጡረታ አበልም እንድንካፍል ይወሰንልኝ የሚል ነው።፡ አመልካችም በሰጠው መልስ ሱቁን አስመልክቶ በ5/11/2006 የተጻፈ የስምምነት ደብዲቤ አለ በዚሁ መሰረት ቀበላው አካፍልን ተለያይተናል። የጡረታ አበልን አስመልክቶ የማግኘት መብት የላትም ብሎል። ፍርድ ቤቱም መርምሮ የሞጆ ከተማ ቀበላ 02 አስተዲደር በቁጥር 602/930/2006 በ7/11/2006 በተጻፈ ደብዲቤ በ5/11/2006 ዓ.ም የተስማሙ መሆኑን የገለፀ በመሆኑ ቤቱን አፍርሶ እንዱያነሳ በማለት የቀረበውን አልተቀበልኩም የጡረታ አበል አመልካችና ተጠሪ አብረው በቆዩ ወቅት ከደመወዝ ላይ ተቆርጦ ሲከማች የኖረ በመሆኑ እንደጋራ ሀብት የሚወሰድ ነው ስለዚህ እኩል ይካፈለ በማለት ሲወስን አመልካች በዚህ ውሳኔ ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በጡረታ የሚኖር በመሆኑ በኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 78/1/ መሰረት አብረው ሰርተው የሚያገኙትን እንጂ የጡረታ አበልን አይጨምርም በአዋጅ ቁ 45/95 አንቀጽ 44 የጡረታ አበልን እኩል ይካፈለ የሚል መሰረታዊ ህግ ያለው ስላልሆነ ተቀባይነት የለውም የቀበላ ቤት በስምምነት በኪራይ የሚገኝ ነው የግል ንብረት አይደለም ተጠሪ የግል ቤት እንዲላት ከሞጆ ከተማ ቀበላ 02 የተጻፈ ደብዲቤ ያለ በመሆኑ የቀበላውን ኪራይ ቤት እንድትለቅ በማለት ወስኗል።
የአሁን ተጠሪ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችልት ያቀረቡትን ይግባኝ ፍርድ ቤቱ ተመልክቶ የኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አዋጅ 83/96 አንቀጽ 78/1/ ባልና ሚስት በጋብቻ ውስጥ እያለ የግልም ሆነ የጋራ ንብረት ከጋራ ንብረት ላይ የሚገኝ ገቢ ሁለ የጋራ ንብረት እንደሆነ አስቀምጧል። በግል ጥረት የሚገኘው ደመወዝ ላይ የሚቆረጠው የጋራ ንብረት እንዱሆን ነው ጡረታ አዋጅ 345/1995 አንቀጽ 7 የጡረታ ገንዘብ ከደመወዝ የሚቆረጥ ነው ሰራተኛው የሞተ እንደሆነ ሚስት የሚከፈላት ጡረታ ገንዘብ ግማሹን እንደሆነ አንቀጽ 35 ደንግጓል ስለዚህ ከ1960 ጀምሮ ባልና ሚስት ሆነው ከጋራ ደመወዝ ሲቆረጥ የቆየው ገንዘብ ጡረታ በሚወጣ ጊዜ የሚከፈለው ገንዘብ ስለሆነ የጋራ ነው እኩል ይካፈለ የመንግስት ቤትን በተመለከተ ደሀ ለሆኑ የግል ቤት መስራት ለማይችለ አቅመ ደካማ ተከራይተው እንዱኖሩ ነው ተጠሪ የግል ቤት እንዲላት አላስተባበለችም ስለዚህ ቤቱ ለአሁን አመልካች ላሆን ይገባል በማለት የቀበላ ቤት እንድታስረክብ ብሎል። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልትም መሰረታዊ ስህተት የለውም በማለት አፅድቋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንን በመቃወም ሲሆን የሰበር አቤቱታው በአጭሩ አመልካች የመንግስት ሰራተኛ ሆኜ የተቀጠርኩት ተጠሪን ከማግባቴ 2 ዓመት በፉት ሲሆን ተጋብተን ብዙ ልጆች ወልደን ጋብቻችን በፍቺ ከተቋረጠበት 2006 ዓ.ም በፉት በጡረታ ተገልዬ ኖረናል። አብረን በመኖር ላይ ሳለን እኔ ቀድሜ ብሞት ግማሽ ጡረታ የማግኘት መብት እንዲላት የማይካድ ቢሆንም ከፍቺ በኋላ በእኔ ድካም የተገኘውን የጡረታ አበል እንድትካፈል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ የሚል ነው። ፍርድ ቤቱም ይህንን አቤቱታ መርምሮ ባልና ሚስት ጋብቻቸው ከፈረሰ በኋላ ለአንደኛው ወገን ይከፈል የነበረ ጡረታ ለላላኛው ወገን ሉከፈል የሚገባ መሆን አለመሆኑን ከአዋጅ ቁ 345/95 አንቀጽ 7 እና ከቤተሰብ ህጉ ዓላማ አንጻር ለመመርመር ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በሰጠችው መልስ ስለቀበላ ቤት እና ውርስ ቤት በተመለከተ የተነሳው ክርክር በልላ ፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን በመግለጽ ያስቀርባል ከተባለው ነጥብ አንጻር ሲመረመር አመልካች የ9 ወር ደመወዝ ከወሰደ በኋላ ነው ጋብቻ የመሰረትነው፣ በአመልካች መ/ቤት በጡረታ ተመዝግቦ የጡረታ አበለን 7 ዓመት ሙለ አብረን ተጠቅመናል ስለዚህ የጋራ በመሆኑ ልንካፈል የሚገባ ሲሆን በህይወት መኖርና ከዚህ ከጡረታ አበል ድርሻዬን ብቻ እንጂ የአመልካችን የሚመለከት አይደለም። የሚል ነው አመልካችም የመልስ መልስ አቅረበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ያስቀርባል ከተባለው ነጥብ አንጻር አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረነዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የሚቻለው አመልካች እና ተጠሪ በባልና ሚስትነት ተጋብተው አብረው በሞጆ ከተማ ውስጥ ከ40 ዓመት ላላነሰ ጊዜ የኖሩ ቢሆንም ጋብቻቸው በፍቺ በመጠናቀቁ የፍቺ ውጤት በሆነው የንብረት ክፍፍል ክርክር አድርገዋል። ተጠሪ እና አመልካች በዚሁ የንብረት ክፍፍል ላይ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እያገኘ በመጣው የቀበላ የኪራይ ቤት ባለ ይዞታነት አስመልክቶ በልላ ፍርድ ቤት ክርክር ላይ በመሆናቸው በዚህ መዝገብ አልተመረመረም ሆኖም የአመልካችን የጡረታ ክፍያ አስመልክቶ የስር ፍርድ ቤት የጋራ በመሆኑ ሉከፈል ይገባል በማለት የሰጡትን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ተመርምሯል። አመልካችና ተጠሪ አመልካች ከጋብቻ በፉት በመንግስት ሥራ ላይ የጡረታ መዋጮ እየከፈለ የቆዩበትን ጊዜ በተመለከተ 2 ዓመት እና 9 ወር በማለት ከመለያየታቸው ውጭ በጋብቻ የቆዩበትን ጊዜ እና በጋብቻ ውስጥ እያለ አመልካች በጡረታ ከሥራው መገለለን አስመልክቶ ልዩነት የላቸውም። ስለሆነም በዚህ ላይ ምላሽ ማግኘት የሚገባው ከተጋቢዎቹ አንደ በጡረታ የሚተዲደር በሆነ ጊዜ ጋብቻው በፍቺ ቢጠናቀቅ የጡረታ አበል ክፍያው በጋብቻ ወቅት በተደረገ መዋጮ ወደፉት የሚከፈል በመሆኑ የጋራ ሆኖ ለተጋቢዎች የመከፈል ውጤት ይኖረዋል ወይስ አይኖረውም የሚለው ነው።
የጡረታ ገንዘብ ምንጩ ምን እንደሆነ በወቅቱ ተፈፃሚነት በነበረው በመንግስት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 5 እንደተመለከተው ከአሰሪው ስድስት በመቶ /6%/ ከመንግስት ሰራተኛው አራት በመቶ /4%/ ነው። እዚህ ላይ የአሁን ተጠሪ መከራከሪያ በጋብቻ ውስጥ በነበርን ጊዜ ከአመልካች ደመወዝ እየተቀነሰ የሚከፈለው 4% በኦሮሚያ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 83/96 አንቀጽ 78/1/ መሰረት የጋራ ከሆነው ደመወዝ በመሆኑ የጡረታ አበለ የጋራ ልባል ይገባል በሚል ሲሆን አመልካች ደግሞ የሚከራከረው የጡረታ አበል የሚከፈለው ለአመልካች ነው ተጠሪ ልትካፈል የምትችለው በጋብቻ ውስጥ ሳለን ብሞት ብቻ ነው ከፍቺ በኋላ ግን ልትካፈል የሚያስችል መብት የላትም በማለት ነው፡ በመሰረቱ ለጡረታ ተብል ከህግ በመነጨ ቅድመ ሁኔታ የሚከማች ገንዘብ ባል ወይም ሚስት ካከማቹት ተጠራቅሞ እራሱን ችል ለክፍያ ይውላል ወይም ይሸፍናል ተብል መደምደሚያ ሉያሰጥ የሚችል አይደለም።የጡረታ አበል ለአንድ ሰራተኛ የሚከፈለው ዕድሜው በገፊበት እና ጉልበቱ በደከመ ጊዜ መጦሪያ የሚሆነው ለመኖር የሚያስፈልገውን ወጪ በከፉልም ቢሆን በመሸፈንና ማህበራዊ ደህንነቱን ዋስትና ለመስጠት መንግስት ካለው የማህበራዊ ደህንነት ዋስትና ፖሉሲ የመነጨ በመሆኑ እንደማንኛውም ገቢ የጋራ ንብረት ነው የሚባል እንዲልሆነ የሰበር ችልት በመ/ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል።አመልካችና ተጠሪ በጋብቻ በነበሩ ጊዜ አመልካች ጡረታ አበል ማግኘት መጀመሩን 7 ዓመት መኖራቸውን ከዚህ በኋላ ፍቺ የተፈፀመ መሆኑ በስር ፍ/ቤት በማስረጃ የተረጋገጠ ሆኖ የሚገኝ ፍሬ ነገር ነው። አመልካች በጡረታ ከተገለለ በኋላ ፍቺ መፈፀሙን ምክንያት በማድረግም የጡረታ አበል ሉካፈል አይገባም የሚለውን መከራከሪያ ያነሳለ በመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ 345/95 አንቀጽ 35 ለሟች ሚስት ወይም ባል የሚከፈለውን የጡረታ አበል ሲደነግግ ሟች ያገኝ የነበረውን የጡረታ አበል 50% /ሃምሳ በመቶ/ የሚሆን እና ሆኖም ይህንን በመቀበል ላይ እያለ ካገባ በመከፈል ላይ ያለ አበል እንደሚቋረጥ ያመለክታል። ከዚህ ድንጋጌ መረዲት የሚቻለው ባልና ሚስት በጋብቻ ውስጥ ሳለ የጡረታ ባለመብት የሆነው ባል ወይም ሚስት ከሞቱ ስለሚኖር የጡረታ አበል ክፍያ ነው ስለሆነም ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ተጠቃሚ ሆነው ባለበት ፍቺ ቢከሰት የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነው ባልና ወይም ሚስት የጡረታ አበል ለባል ወይም ለሚስት ሉያካፍል የሚገባ ስለመሆኑ አይደለም።ስለሆነም የአመልካች የጡረታ አበል ለተጠሪ ሉከፈል ይገባል በማለት የስር ፍ/ቤቶች የደረሱበትን ድምዲሜ መሰረታዊ ስህተት ያለበት በመሆኑ የሚከተለው ተወስኗል።
የልሜ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ በ12/12/2006 የኦሮምያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ችልት በመ/ በቀን 01/07/2007 ዓ.ም እና የኦሮምያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ በቀን 17/07/2002 የሰጡት ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 04/04/2007 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በውጤት ደረጃ ፀንቷል።
አመልካች የሚያገኘው የጡረታ አበል የጋራ ንብረት ተደርጏ ለተጠሪ ሉካፈል አይገባም ብለናል። ግራ ቀኙ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.