የገጠር መሬት እንደላላው ንብረት በመቁጠር ከቤተሰብ ህጉ አንጻር የሚታይ ስላለመሆኑ ፣ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በአንድ ተጋቢ ስም ተዘጋጅቶ ከተሰጠ በኋላ ጋብቻ ቢፈፀምና ተጋቢዎቹ መሬቱን የጋራ ለማድረግ ሉስማሙ የሚችለ ስለመሆኑ፣ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 133/1999 አንቀጽ 24/3/ ደንብ ቁ. 151/1999 አንቀጽ 20/6/
No summary available.
መጋቢት 30 ቀን 2008ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ ደስታ ታከለ - ወኪል አቶ ታከለ በቀለ ቀርቧል /VC/ ተጠሪ፡- አቶ ፀጋ ታዱየስ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በባልና ሚስት በገጠር የእርሻ ይዞታ ላይ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበረችው የአሁኗ አመልካች በአንከሻ ጓግሳ ወረዲ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በነበረው የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበችው ክስ ነው። ከሳሽ በ6/10/2006 ዓ.ም አዘጋጅታ ያቀረበችው ክስ ይዘትም ባጭሩ ከተጠሪ ጋር በባልና ሚስትነት ስንኖር ጋብቻው በፍቺ የፈረሰ ሲሆን የጋራ የሆነ 8 ቃዲ መሬት በድርሻዬ እንዱያካፍለኝ ይወሰንልን በማለት ዲኝነት ጠይቃለች።
ተከሳሽ በበኩለ በ13/10/2006 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ማመልከቻ በስሜ የተመዘገበ የግላ እንጂ አመልካችን የሚመለከታት አይደለም ልትካፈል አትችልም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ሲል ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ 4 ቃዲ መሬት መኖሩን በማረጋገጥ ግራ ቀኙ በጊዚያዊ የይዞታ መረጋገጫ ደብተርና በጋብቻ ውል ያደረጉ ስለመሆኑ ተረጋግጠዋል። የአ/ብ/ክ/መ ቤተሰብ ህግ ቁጥር 79/1995 አንቀጽ 53/1/ የመሬት ይዞታ በአንደ ስም ከተሰጠ በኋላ ጋብቻ ሲፈፀም ተጋቢዎች መሬትን የጋራ ለማድረግ ሉሰማሙ አንደሚችለ አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 24/3/ ይደነግጋል። ስለዚህ 4 ቃዲ ግማሹ ይሰጥ ወይም ያካፍል ሲል ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለአዊ ብሓረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ይኸው ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል።
ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ተቀባይነት በማግኘቱ የግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ይህ ጋብቻ ሲመሰረት የጋራ የማድረግ ስምምነት የለም። ጋብቻ ፀንቶ ባለበት በአዋጅ ቁጥር 79/1995 አንቀጽ 58 መሰረት ጋብቻ የማደስ ሁኔታ መኖሩን ይደነግጋል። ይህ ውል ፍርድ ቤት ቀርቦ መፅደቅ አለበት ካልፀደቀ ግን ፈራሽ ይሆናል። ግራ ቀኙ ያደረጉት ጋብቻ የማደስ ውል በፍርድ ቤት አልፀደቀም ስለሆነም ፈራሽ ነው በማለት በስር ፍርድ ቤቶች አመልካች 4 ቃዲ ግማሽ ልትካፈል ይገባል በማለት የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር ተጠሪ ክስ የቀረበባቸውን መሬቶች ሉያካፍል አይገባም ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁኑ ሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስለወጥ ነው። አመልካች ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም የተፃፈ ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የምትልበትን ምክንያቶች ዘርዝራ አቅርባለች።
የቀረበውን የሰበር አቤቱታ በመመርመር በዚህ ጉዲይ ግራ ቀኙ ተጠቃሹን የመሬት ይዞታ በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑ ባልተካደበት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የጋብቻ ውለ ለፍርድ ቤት ቀርቦ አልተመዘገበም በማለት የእርሻ መሬቱ የተጠሪ የግለ ነው ሲለ የመወሰናቸውን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ጥሪ የተደረገለት ቢሆንም ባለመቅረቡ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው መሬት አመልካችና ተጠሪ 18 ዓመት በጋራ ሲጠቀሙበት ከዚያም ጋብቻቸው ጥር 23 ቀን 2005 ዓ.ም በተደረገው የማደስ ስምምነት የጋራ እንደሆን ያደረጉ መሆናቸው በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠና በተጠሪም የተካደ አይደለም። ከስምምነት በኋላ በይዞታ ማረጋገጫ ላይ በጋራ በስማቸው የተቆጠረ መሆኑ የተረጋገጠ ነው። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ትዲር ፀንቶ ባለበት የትዲር ውል በፍርድ ቤት ያልተመዘገበ ስለሆነ ውለ ፈራሽ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ አግባብነት ያለውና የላለው መሆኑን መመርመር ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
የተሻሻለው የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 24/3/ መሰረት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ በአንደ ስም ተዘጋጅቶ ከተሰጠ በኋላ ጋብቻ ከተፈፀመ ተጋቢዎቹ መሬቱን የጋራ ለማድረግ ሉስማሙ እንደሚችለ በግልፅ ተመለክቷል። ይህ አዋጅ ለማስፈፀም የወጣው ደንብ ቁጥር 51/1999 አንቀጽ 20/6/ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ በአንደ ስም ተዘጋጅቶ ከተሰጠ በኋላ ጋብቻ የተፈፀመ እንደሆነ ተጋቢዎች ይህንኑ ፍሬ ነገር አግባብ ላለው የቀበላ መሬት አስተዲደርና አጠቃመም ኮሚቴ በወቅቱ ገልፀው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ ተሻሽልና በሁለቱም ስም ተዘጋጅቶ እንዱሰጣቸው ማመልከት እንደሚችለ ይደነግጋል። አመልካችና ተጠሪ ህጉን ተከትለው በተጠሪ ሰም የነበረውን የጋራ ማድረግ በመሰማማት ለሚመለከተው አካል ጥያቄ አቅርበው በሁለቱ ተጋቢዎች ስም የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ የተሰጣቸው መሆኑን ፍሬ ነገር የማጣራትና መመዘን ስልጣን በተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።
የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀምን በተመለከተ ባለው ልዩ ባህሪ ራሱን ችል ሕግ የወጣለት ሲሆን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ በአንደ ስም ተዘጋጅቶ ከተሰጠ በኋላ ጋብቻ ከተፈፀመ ተጋቢዎቹ መሬቱን የጋራ ለማድረግ ሲፈልጉ እንዳት ሉለወጥ እንደሚችል ስርዓት የተዘረጋለት መሆኑን ከህጉ መገንዘብ ይቻላል። የገጠር መሬትን በሚመለከት በሚነሱ ጉዲዮች ህጉ ግልፅ እስከሆነ ድረስ ተግባራዊ ማድረግ የግድ ይላል። የገጠር መሬትን እንደ ላላው ንብረት በመቁጠር በቤተሰብ ህጉ አንፃር የሚታይ አይደለም። መታየት ያለበት የግራ ቀኙ ተጋቢዎች በገጠር መሬት አዋጁ መሰረት በአንድ ተጋቢ ሰም ብቻ የነበረውን የጋራ ለማድረግ ስምምነት መኖሩን ወይም አለመኖሩን ነው።
ስለዚህ አመልካችና ተጠሪ የገጠር መሬት አዋጅና ደንብ ተከትለው በመስማማት የጋራ ያደረጉትን በሁለቱ ስም የይዞታ መረጋገጫ ደብተር የተሰጣቸውን በፍርድ ቤት ያልፀደቀ ነው በማለት አግባብነት የላለው የቤተሰብ ህግ ቁጥር 79/1995 አንቀጽ 58 በመጥቀስ ውለ ፈራሽ ነው ሲል የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
የአ/ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.38441 ግንቦት 10 ቀን 2007 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በአንከሻ ጓግሳ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.2743/05 የካቲት 12 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ እና በአዊ ብሓረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መ/ቁ. 01-08191 መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠ ትእዛዝ ፀንቷል።
ተጠሪ 4 ቃዲ መሬት ግማሹን ለአመልካች ያካፍል ብለናል።
የአንከሻ ጓግሳ ወረዲ ፍርድ ቤት በዚህ ውሳኔ መሰረት እንዱያስፈፅም የውሳኔው ቅጂ ይላክለት።
በዚህ ችልት ለተደረገው ወጭ እና ኪሳራ የግራ ቀኙን ተከራካሪ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.