በመሬት ይዞታዬ ላይ ጉዲት ደርሶብኛል በማለት የሚቀርብ ክስ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሰለመሆኑ ፍ/ሕ/ቁ 2143 119563 ኢትዩጵያ ኤላክትሪክ ኃይል አገልግልት እና አቶ ሐጂ ነገዋ 26/1/ 2009 ዓ.ም 255 ቤተሰብ 258 53. እድሜው ያልደረሰ ልጅ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል የሞግዚት ስልጣን ይሰጠኝ ጥያቄ ፍ/ቤቶች የህፃንን መብትና ድህንነት ቅድሚያ እንዱሰጠው በማደረግ ሲወሰኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቀረበውን መሰረታዊ ጥያቄ እና አማራጭ መፍትሓ መኖሩን አለመኖሩን በማጣራት መወሰን ያለበት ሰለመሆኑ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ መንግሰት 36 (2) ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 280 እና 289(1) የቤተሰብ ህግ አዋጅ 213/1992 አንቀፅ 43
No summary available.
መጋቢት 27 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች-፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ተሾመ ጎርፋ - ወራሽ ወ/ሮ መቅደስ ተሾመ - ጠበቃ አብርሃም ሀዱስ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፈሰሰች ወንድማገኘሁ - ወራሽ አቶ ጣሰው ተሾመ - ጠበቃ ሃልማ አቻሜ ጋር ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የውርስ ይጣራልኝ አቤቱታን አስመልክቶ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም የአመልካች ባለቤት የነበሩት ልጃቸው ወ/ሮ ተናኘ ተሾመ በሞት መለየታቸውን እና በጋብቻ ውስጥ ያፈሩት ንብረት በአመልካች እጅ የሚገኝ መሆኑን ገልጸው ውርስ እንዱጣራላቸው ተጠሪ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ08/08/2004 ዓ.ም.
አዘጋጅተው ባቀረቡት ክስ ሲሆን አመልካቹም በ02/02/2005 ዓ.ም. በሰጡት መልስ በአመልካች እጅ ይገኛል የተባለው ንብረት የሟች ወ/ሮ ተናኘ ተሾመ የጋራ ንብረት ሳይሆን የአመልካቹ የግል ሀብት በመሆኑ ውርሱ ሉጣራ አይገባም ተብል ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክረዋል።ፍርድ ቤቱም ውርሱ ተጣርቶ እንዱቀርብ አጣሪ የመደበ ሲሆን አጣሪውም በተመራለት መሰረት ውርሱን አጣርቶ በ14/05/2005 ዓ.ም. የተጻፈ ሪፖርት አቅርቧል። የሪፖርቱም ይዘት በአዱስ አበባ ከተማ በቦላ ክፍለ ከተማ በወረዲ 7 የሚገኘው ቁጥሩ 1177 የሆነው ቤት የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት መሆኑ ስለተረጋገጠ የቤቱ አጋማሽ እና ከኪራዩ የተገኘው ገንዘብ ብር 35,400 ውስጥ አጋማሹ ብር 17,700 የውርስ ሀብት ነው፣ለቤቱ ዕድሳት ወጣ የተባለው ብር 4,400 አጋማሽ የውርሱ ዕዲ አይደለም የሚል መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
ፍርድ ቤቱም በሪፖርቱ ላይ የግራ ቀኙን አስተያየት ከተቀበለ በኃላ የአሁኑ አመልካች ቤቱ የአመልካቹ የግል ሀብት በመሆኑ ሪፖርቱ ሉመዘገብ አይገባም በማለት ያቀረቡትን የመቃወሚያ አስተያየት ውድቅ በማድረግ ሪፖርቱን ተቀብል በመመዝገብ በመዝገብ በ26/09/2005 ዓ.ም. ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት ይግባኙን የተመለከተው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቤቱ ኪራይ የተገኘውን ገቢ ወደ ብር 29,400 ዝቅ አድርጎ የውርስ ሀብት ላሆን የሚገባውን የኪራይ ገንዘብ ወደ ብር 14,700 ዝቅ በማድረግ እና ለቤቱ ዕድሳት የወጣ ነው ከተባለው ብር 4,400 ውስጥ አጋማሹ ብር 2,200 የውርሱ ዕዲ መሆን ይገባዋል በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በዚህ አግባብ በማሻሻለ የሁለቱም የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ በተጠሪ አውራሽ እና በአመልካች መካከል በ1975 ዓ.ም. ባህላዊ ጋብቻ ስለመፈጸሙ የተረጋገጠ ነገር እንደላለ ከመንግስት ተቋም ተገናዝቦ የተሰጠ ማስረጃ ስላለመኖሩ ከመንግስት ተቋም ለስር ፍርድ ቤት ከተሰጠው ምላሽ እና በባህል ጋብቻ ውለ ላይ በእማኝነት የፈረሙት ግለሰቦች በ1975 ዓ.ም. ከፉልቹ ያልተወለደ እና ከፉልቹም በወቅቱ ለአካለመጠን ያልደረሱ በመሆናቸው በግራ ቀኙ መካከል በ1975 ዓ.ም. ጋብቻ መፈጸሙ አልተረጋጠም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገውን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በምስክሮች ተረጋግጧል የሚል ምክንያት በመስጠት ብቻ የመሻሩን አግባብነት ተጠሪዋ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዘት እና ለሰበር ክርክሩ በጭብጥነት የተያዘው ነጥብ በስር ፍርድ ቤቶች የተደረገውን የክርክር ጭብጥ መሰረት ያደረጉ ናቸው ወይስ አይደለም?
የአከራካሪው ቤት አጋማሽ እና የኪራይ ገቢው አጋማሽ የውርስ ሀብት ነው በሚል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ወይስ አይደለም?
የሚለ ነጥቦች መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዚሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ26/09/2005 ዓ.ም.
የተሰጠው ውሳኔ እና ይህንኑ ውሳኔ በከፉል በማሻሻል በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ28/11/2006 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ ነው።ይህንንም አመልካቹ በ12/12/2006 ዓ.ም. አዘጋጅተው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መግቢያ ላይ በትክክል አስፍረዋል።አመልካቹ ይህንን በትክክል ካሰፈሩ በኃላ ግን ዝርዝር አቤቱታቸውን ያቀረቡት በሁለቱ የስር ፍርድ ቤቶች ከላይ በተጠቀሱት መዝገቦች በተሰጡት ውሳኔ ላይ ሳይሆን ይልቁንም የአመልካች እና የተጠሪዋ አውራሽ የጋብቻ የምስክር ወረቀት ተገቢውን ስርዓት አሟልቶ የተሰጠ ባለመሆኑ ሉሰረዝ ይገባል በማለት የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ02/04/2006 ዓ.ም. ከሰጠው ውሳኔ ጋር አያይዘው ነው።
በመሰረቱ ይህ በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ አመልካቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን በይግባኝ የተለወጠ ስለመሆኑም የመዝገቡ ግልባጭ የሚጠቁመው ነገር የለም። በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ02/04/2006 ዓ.ም. በተሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ የተሰማው ወገን ካለ ጉዲዩ ስርዓቱን ጠብቆ ሲቀርብ ከሚታይ በቀር በስር ሁለቱ ፍርድ ቤቶች ከነበረው ክርክር ጋር ግንኙነት የላለውን ውሳኔ መሰረት አድርገው አመልካች የሰበር ክርክር ሉያቀርቡ የሚችለበት ስነ ስርዓታዊ አግባብ የለም። በውርስ ማጣራቱ ጉዲይ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ቤቱን ያፈራሁት ከጋብቻው በፉት ነው ከማለት በቀር የተጠሪዋ አውራሽ ባለቤታቸው የነበሩ ስለመሆኑ አመልካች ክደው ያቀረቡት ክርክር ባለመኖሩ ምክንያት በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በውርስ ማጣራቱ ጉዲይ በስር ፍርድ ቤቶች ከነበረው የክርክር ጭብጥ እና ከተሰጠው ውሳኔ ጋር ግንኙነት የላለው መሆኑ እና ውሳኔው ተጠቃሚ የሚያደርገውም አመልካቹን መሆኑ እየታወቀ፣እንዱሁም በይግባኝ የተለወጠ ስለመሆኑ የመዝገቡ ግልባጭ የሚጠቁመው ነገር ሳይኖር ውሳኔው የሰበር ክርከሩ መነሻ እንደሆነ እና በበላይ ፍርድ ቤትም እንደተሻረ ተወስድ በአጣሪው ችልት የተያዘው ጭብጥ የመዝገቡን ግልባጭ መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይዘት እና ለሰበር ክርክሩ በጭብጥነት የተያዘው ነጥብ በስር ፍርድ ቤቶች የተደረገውን የክርክር ጭብጥ መሰረት ያደረጉ ናቸው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ከላይ እንደተገለጸው በውርስ ማጣራቱ ጉዲይ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ቤቱን ያፈራሁት ከጋብቻው በፉት ነው ከማለት በቀር የተጠሪዋ አውራሽ ባለቤታቸው የነበሩ ስለመሆኑ አመልካች ክደው ያቀረቡት ክርክር አለመኖሩን የመዝገቡ ግልባጭ በግልጽ ያመለክታል። ይህንን ክርክር በስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርቤ ነበር በማለት አመልካች በዚህ ሰበር ደረጃም ቢሆን ያቀረቡት ክርክር የለም። አከራካሪው ቤት በአመልካች እና በተጠሪዋ አውራሽ በጋራ የተሰራ ስለመሆኑ በተጠሪዋ ብቻ ሳይሆን አመልካች ራሳቸው ካሰሟቸው ምስክሮች መካከል በከፉልቹ ጭምር የተረጋገጠ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።አመልካች ከስርዓት ውጪ የተሰጠ ነው የሚለትን የጋብቻ የምስክር ወረቀት በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዱሰረዝ ካደረጉ በኃላ ይኸው ውሳኔ በተጨማሪ ማስረጃነት እንዱታይላቸው በይግባኝ ሰሚው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠይቀው የነበረ መሆኑን ከመዝገቡ ግልባጭ ማረጋገጥ የተቻለ ቢሆንም በመሰረቱ በስር ፍርድ ቤት ክደው ያልተከራከሩበትን ነጥብ በይግባኝ ደረጃ ክደው እና ክርክራቸውንም ለውጠው የሚከራከሩበት አግባብ በስነ ስርዓት ሕጉ በአንቀጽ 329 (1) ድንጋጌ መሰረት ተቀባይነት የላለው በመሆኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጨማሪ ማስረጃ ጥያቄያቸውን አልፍ የመዝገቡን ግልባጭ መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠቱ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት ካለመኖሩም በላይ አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሰጡት መልስ ይዘት እና በግራ ቀኙ ምስክሮች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር አንጻር የጋብቻ የምስክር ወረቀቱ ተገቢውን ስርዓት ተከትል የተሰጠ አይደለም ተብል መሰረዙ በአመልካች እና በተጠሪዋ አውራሽ መካከል ጋብቻ አልነበረም ከሚል ድምዲሜ ላይ ለመድረስ የሚያስችል ባለመሆኑ አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ02/04/2006 ዓ.ም. ከሰጠው ውሳኔ ጋር አያይዘው የሚያቀርቡት ክርክር ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው ነው ለማለት የሚቻል አይደለም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ28/11/2006 ዓ.ም.
ተሻሽል የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ፀንቷል።
እንዱያውቁት የውሳኔው ቅጂ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይላክ።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ የተያዘው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ19/09/2007 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ፣እንዱሁም በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ የተያዘው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ26/09/2007 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቷል።ይጻፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.