በመሬት ይዞታዬ ላይ ጉዲት ደርሶብኛል በማለት የሚቀርብ ክስ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሰለመሆኑ ፍ/ሕ/ቁ 2143 119563 ኢትዩጵያ ኤላክትሪክ ኃይል አገልግልት እና አቶ ሐጂ ነገዋ 26/1/ 2009 ዓ.ም 255 ቤተሰብ 258 53. እድሜው ያልደረሰ ልጅ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል የሞግዚት ስልጣን ይሰጠኝ ጥያቄ ፍ/ቤቶች የህፃንን መብትና ድህንነት ቅድሚያ እንዱሰጠው በማደረግ ሲወሰኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቀረበውን መሰረታዊ ጥያቄ እና አማራጭ መፍትሓ መኖሩን አለመኖሩን በማጣራት መወሰን ያለበት ሰለመሆኑ የኢ.ፋ.ዳ.ሪ መንግሰት 36 (2) ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ 280 እና 289(1) የቤተሰብ ህግ አዋጅ 213/1992 አንቀፅ 43
No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ተኽሉት ይመስል እንደሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ወ/ሮ አስቴር በቀለ ጭጭ አይበለ ሞግዚት አድራጊ ህፃን ማህደር የማነህ በሸህ ተጠሪ፡- የለም ።
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል ።
ጉዲዩ የማይንቀሳቀስ ንብረት (ቤት) ለመሸጥ የሚያስችል የሞግዚትነት ስልጣን ይሰጠኝ ጥያቄ የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩ የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች በመ/ቁ 562/07 ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ነው።
የአመልካች አቤቱታ ባጭሩ በቦላ ክ/ከተማ ወረዲ 13 የቤት ቁጥር 1590 የሆነው መኖሪያ ቤት ከላልች ወራሾች ጋር የሚካፈል ድርሻ ያላቸው በመሆኑ አመልካች ቤቱን መሸጥ መለወጥ እንዱችለ ተጨማሪ የሞግዚትነት ስልጣን እንዱሰጣቸው መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የስር ፍርድ ቤትም ምስክሮች አስቀርቦ እንደሰማ አመልካች ቤቱን በማከራየት በሚያገኙት ገቢ እንደሚተዲደሩ ቤቱን የሚወርሱ ላልች ልጆችም እንዲለ ከእነዚህ የተወሰኑት ራሳቸውን ችለው እንደሚኖሩ አመልካች ሞግዚት የሆኑላት ዕድሜዋ 15 ዓመት እንደሆነ ከዚህ ቤት ውጪ ላላ መኖሪያ ቤት እንደላላቸው በመግለጽ መመስከራቸውን ፍ/ቤቱ መመዝገቡን የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል።
ፍርድ ቤቱም አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ ከመረመረ በኋላ ህፃን ማህደር የማነ ከሞግዚት ለመውጣት የተቃረበች ሲሆን ላላ መኖርያ ቤት ስለላላቸው እንዱሁም በዚሁ ቤት ኪራይ እየተማረች እንደምትገኝ አስቀድሞ ቤቱ ቢሸጥ አካለመጠን ስላላደረሰኝ ድርሻዬ ሉጠፊበት እንደሚችል ፍ/ቤቱ ግምት በመውሰድ እንዱሁም ቢሸጥ ላላ መኖሪያ ቤት እንደላላቸው ፍ/ቤቱ የተገነዘበ ስለሆነ የአመልካችን አቤቱታ ፍ/ቤቱ ባለመቀበል መዝገቡን በብይን ዘግቶታል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እንዱሁም ለሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የስር ፍርድ ቤቶችን ብይን ትዕዛዝና ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የጤና ችግር ያለበቸው በመሆኑ የህፃን ማህደር የማነን መሰረታዊ የኑሮ ወጪ ማሟላት እንዲልቻለ ቤቱ ተሸጦ የቀለብ የልብስ የትምህርት ወጪ ካልተሸፈነ በቀር ቤቱን በማከራየት በሚያገኙት ገቢ ማሟላት አለመቻላቸውን ላልች ወራሾችም ቤቱ ቢሸጥ እንደማይቃወሙ በተገለጸበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው በሕጉ አግባብ አይደለም የሚል ክርክር ማቅረባቸውን የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል።
አመልካች ከአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 562/07 በ12/02/2007 ዓ/ም የማህደር የማነ በሻህ ሞግዚትና አስተዲዲሪ መሆናቸውን ፍ/ቤቱ እውቅና መስጠቱን በኢፋዳሪ ፍትህ ሚኒስቴር የሰነድች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ነሐሴ 01 ቀን 2007 ዓ/ም የውክልና ስልጣን መውሰዲቸውን የሚያሰይ ማስረጃ ከመዝገቡ ጋር አያይዟል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት መጋቢት 16/2008 ዓ/ም በሰጠው ትዕዛዝም ህፃን ማህደር የማነ በሻህ በችልት ቀርባ እንድታሰረዲ ያደረገ ሲሆን መጋቢት 19 ቀን 2008 ዓ/ም በዋለው ችልት በሰጠችው ቃል ወላጅ እናቷ ወቅታዊ የኑሮ ወጪ ማሟላት ከማይችለበት ደረጃ የደረሱ በመሆኑ ቤቱ ተሸጦ ከዚህ የሚገኘው ገንዘብ ለቀለብ፤ ለትምህርት፤ ልብስ እና ላልች ወጪዎች እንዱሸፈኑላት ተቃውሞ እንደላላት አስረድታለች። የአሁኑ አመልካችም ከቤቱ የሚያገኙት ገቢ ላልች ወራሾችም የሚካፈለት እንደሆነ የጤና ሁኔታቸውም በጥሩ ሁኔታ የላለ በመሆኑ ቤቱ እንዱሸጥ አመልክተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ይዘት ያለው ሲሆን ይህ ችልትም አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ በአመልካች የቀረበው ተጨማሪ የሞግዚትነት ስልጣን ይሰጠኝ ጥያቄ በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ከህፃኗ የተሻለ ጥቅም /Best interest of the child/ አንፃር ተገቢ መሆን ያለመሆኑን መመርመር መሆኑን ተረድተናል።
አመልካች ከስር ፍርድ ቤት አንስቶ አጥብቀው የሚከራከሩት የሞግዚት አድራጊያቸውን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት ባለመቻላቻው ከአባቷ በውርስ የምታገኘው የማይንቀሳቀስ ቤት ተሸጦ ለቀለብ ፣ትምህርት፣ ልብስና ተያያዥ ወጪዎች መሸፈኛ እንዱሆን ጠይቀው የስር ፍርድ ቤት ተማሪ (ህፃን) ማህደር የማነ ከሞግዚት ነፃ ለመውጣት ጥቂት ዓመት የቀራት መሆኑ ላላ ቤትም የላላቸው መሆኑ በመረጋገጡ ቤቱ ሉሸጥ አይገባም ከሚል ድምዲሜ ላይ ደርሷል።
አመልካች አሁን ያላቸው ህመም ቤተሰቡን ማስተዲደር የሚችል ገቢ ለማመንጨት የሚያስችላቸው እንዲልሆነና ቤቱ ካልተሸጠ በቀር የህፃን ማህደር የማነን የኑሮ ወጪ መሸፈን እንደማይችለ ከስር ፍ/ቤት ጀምሮ ባቀረቡት ክርክር የገለጹ ሲሆን አሁን ለአከለ መጠን ያልደረሰችውን ልጅ ጨምሮ ሁለም ልጆቻቸው ቤት ቢሸጥ ተቃውሞ እንደላላቸው የሚያሳይ ክርክር አቅርበዋል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ያነጋገራት ተማሪ ማህደር የማነም እናቷ ቤተሰቡ የሚያስፈልገውን መሰረታዊ ነገሮች ለማሟላት በማይችለበት ደረጃ በመድረሳቸው ቤቱ ቢሸጥ እንደማትቃወም አስረድታለች።
በመሰረቱ አካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ሀብት በህጉ አግባብ ሉተዲደር እንደሚገባ ከፍ/ህ/ቁ. 280 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት ያስገነዝቡናል። አካለ መጠን ያልደረሰው ሀብት ሉሸጥ እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 289 (1) የተመለከተ ሲሆን መቃወሚያ የሚቀርብበት ስርዓትም በዚህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 2 ተመልክቷል፡፤ ፍርድ ቤቶች ስለህፃናት መብትና ጥቅም ሲወስኑ የጉዲዩ ዓይነት ይዘትና ባህሪ ያገናዘበ መሆን እንዲለበት በየትኛውም መልኩ መብትና ደሕንናታቸው ቅድሚያ ሉሰጠው እንደሚገባ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 36 (2) ሥር ተመልክቷል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ፍቺ በሚወሰንበት ጉዲይም የህፃናቱ አያያዝና የቀለብ ጉዲይ ትኩረት ከሚሹ ነጥቦች እንደ ስለመሆኑ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213 /1992 አንቀጽ 113 ስር ተደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች የህፃን ማህደር የማነ ወቅታዊ የኑሮ ወጪ መሸፈን አለመቻላቸውን በዝርዝር ምክንያት አሰደግፈው ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ህፃን ማህደር የማነ ለአካለ መጠን እየደረሰች እንደሆነና ቤቱ ከተሸጠ ለወደ ፉቱ ችግር ሉያጋጥም ይችላል በሚል እሳቤ ስለመሆኑ ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል።
አመልካች ቤቱን በማከራየት የሚያገኙት 2000 ብር ለላልች ወራሾችም ድርሻ ድርሻቸው እንደሚያከፊፍለ ገልጸው ይህ ቤት ከማከራየት የሚያገኙት ገቢ በየትኛውም መልኩ አሁን ያለውን ወቅታዊ የኑሮ ወጪ ፍላጎት የማያሟላ ስለመሆኑ መከረከራቸውን ተረድተናል።
የአመልካች መሰረታዊ ጥያቄ ሞግዚት የሆኑለት ልጅ ወቅታዊ የኑሮ ወጪ ቤቱን በማከራየት ከሚገኘው ገቢ የማይሸፈን ከሆነ ላላ ህጋዊ መፍትሓ መስጠቱ የህፃን ማህደር የማን ቀጣይ ሕይወት በተደለደለ መሰረት ለማኖር ወሳኝ ነው። ህፃን ማህደር የማነ የ10ኛ ክፍል ተማሪ እንደሆነች በችልቱ ቀርባ አስረድታለች። ከዚህ መገንዘብ የምንችለው እስከ ኮልጅ መግቢያ ድረስ ያለው ጊዜ ረጅም መሆኑን ነው። ወላጅ እናቷም ካላቸው የጤና እክል የህፃን ማህዲር የማን መሰረታዊ ፍላጎት ማሟላት በማይችለበት ደረጃ መድረሳቸውን ችልቱ ገልጿል የስር ፍ/ቤት የተማሪ ማህደር የማነ ከሚግዚት አስተዲደር ነፃ ለመውጣት የቀራት ጊዜ አጭር መሆንና ለወደ ፉቱ ያለው ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገበ ቢሆንም ህፃን ማህደር የማን አሁን ያለው ተጨባጭ የኑሮ ሁኔታ መሸፈን የሚችል አስተማማኝ የገቢ ምንጭ ያላት ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። የህፃን ማህደር የማነ ወቅታዊ የኑሮ ወጪ ፍላጎት የማሟት ጉደይ የማይታለፍ መሰረታዊ ጥያቄ ከሆነ ቤቱን በመሸጥ ኑሮ እንድትደጉም ከማድረግ ውጭ ላላ ህጋዊ መፍትሓ ያለውም። ህፃን ማህደር የማነ ትምህርቷን ሳይስተጓጎል መቀጠል የምትችለው መሰረታዊ የሆነውን ምግብ፣ ልብስ ፣ህክምና የተለያዩ የትምህርት መረጃ መፃሕፍት ማግኘት ስትችል ብቻ ነው። ህፃኗ ለወደፉቱ ራሷን መቻል የምትችለው አሁን በሚሰራው ስራ ነው። ህፃን ማህደር የማነ ትምህርቷን ሳታቋርጥ እስከ ዩኒቨርስቲ መዝለቅ የምትችለው ከወዱሁ በሚደረግ ድጋፍ ክትትልና እንክብካቤ ነው። በመሆኑም አመልካች ህፃን ማህደር የማነ እና ላልች ወራሾች የሚጋሩት ቤት ሁለም ባለመብቶች በተሳተፈበት አግባብ ሉሸጥ የሚገባው ነው። የስር ፍርድ ቤቶች በአመልካች የቀረበው ቤቱን በመሸጥ የህፃን ማህደር የማነ ወቅታዊ የኑሮ ወጪ ፍላጎት ላሟላ በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ያለበቂ ምክንያት ውድቅ መደረጉ በጉዲዩ መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸሙን የሚያሳይ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው።
አመልካች ህፃን ማህደር የማነ እና ላልች ወራሾች የሚጋሩት ቤት እንዱሸጥ መወሰኑ ተገቢ መሆኑ ከታመነ ቀጥል የሚነሳው ጥያቄ የህፃን ማህደር የማነ ድርሻ ገንዘብ በምን ሁኔታ ሉቀመጥ ይገባል የሚል ነው። ቤቱ ከተሸጠ በኃላ የህፃን ማህደር የማነ ድርሻ የሚታወቅ ሲሆን ገንዘቡ ለረጅም ጊዜ ኢኮኖሚያዊ በሆነ አግባብ እንድትጠቀምበት ሞግዚት አድራጊዋ በህፃኗ ስም የሂሣብ ቁጥር ከፍተው ገንዘቡን ሉያስቀምጡ ይገባል። በዚህም መሰረት የአሁኗ አመልካች በህፃን ማህደር የማነ የባንክ ሂሣብ ደብተር ከፍተው ቤቱ ከተሸጠ በኃላ ገንዘቡን በሙለ ገቢ ካደረጉ በኃላ ለልጀቷ ተፈጥሮአዊና ሰብአዊ ፍላጎቷ ለቀለብ፤ ለትምህርት፤ለመኖሪያ ቤት ለጤና አጠበበቅ እና ለልዩ ልዩ ወጪዎች በየወሩ 1,000 (አንድ ሺህ/ ብር ወጪ እያደረጉ ሉጠቀሙ ይገባል ብለናል። በየወሩ ወጪ የሚደረገው 1,000 ብር የህፃን ማህደር የማነ ወቅታዊ የኑሮ ወጪ ፍላጎት የማያሟላ ከሆነና ይኽውም በበቂ ምክንያት ተደግፍ ከቀረበ የስር ፍ/ቤቶች ተገቢ ህጋዊ ትዕዛዝ የሚሰጡበት ሁኔታ በዚህ ውሳኔ የሚገደብ አይሆንም፡: በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረቡት ቤት ለመሸጥ ይፈቀድልኝ ጥያቄ ውድቅ መደረጉ የህፃን ማህደር የማነ ወቅታዊ የኑሮ ወጪ ፍላጎት ያላገናዘበ በመሆኑ ተገቢ አይደለም ብለናል። ቤቱም በንብረቱ መብት ያላቸው ወገኖች በተሳተፈበት ይሸጥ በማለት ወስነናል። ቤቱ ከተሸጠ በኃላ የህጻን ማህደር የማነ ድርሻ በስሟ በተከፈተ የሂሣብ ቁጥር ገቢ ሆኖ በየወሩ አንድ ሺህ ብር ወጪ ይደረግ ብለናል። በዚህም ተከታዩን ወስነናል።
የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ.562/07 በ19/09/2007 ዓ/ም የሰጠው ብይን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 23752 በ8/10/2007 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ የአስተዲደሩ ሰበር ሰሚ ችልት በወ/ቁ. 23834 በ14/11/2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ተሸሯል።
አመልካች የህፃን ማህደር የማነ ወቅታዊ የኑሮ ወጪ ፍላጎት ማሟላት ባለመቻላቸው አመልካች እና ላልች ወራሾች የሚጋሩት በአዱስ አበባ ከተማ ቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 13 የቤት ቁጥር 1590 የሆነውን መኖሪያ ቤት ሁለም ባለመብቶች ባሳተፈ መልኩ ይሸጥ ብለናል።
ለክርከሩ ምክንያት የሆነው ቤት ከተሸጠ በኃላ የአመልካች ህፃን ማህደር የማነ ድርሻ በስሟ በተከፈተ የሂሣብ ቁጥር ገቢ ይሁን ብለናል። ህፃኗ በየወሩ ለሚያስፈልጋት መሰረታዊ የኑሮ ወጪ 1,000 (አንድ ሺህ /ብር በሞግዚቷ በኩል ወጪ እየተደረገ ይከፈል በማለት ወስነናል።
በየወሩ ወጪ እንዱሆን የታዘዘው መጠን ገንዘብ የህፃኗ መሰረታዊ የኑሮ ወጪ የማይሸፍን መሆኑ ከተረጋገጠ ለመሻሸል የሚቀርበውን ጥያቄ ይህን ውሳኔ አያግድም ብለናል።
No topics extracted.