No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ተፈሪ ገብሩ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላትሪክ ኃይል አገልግልት የአለቶ ላንጋኖ ጂኦተርማል አለቶ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ -- ነ/ፈጅ ቦንቱ ቢራቱ ቀርበዋል።
ተጠሪ፡- አቶ ሐጂ ነገዎ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በእርሻ መሬት ይዞታ ላይ ለደረሰ ጉዲት በኃላፉነት ስለመጠየቅና የካሳ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው የምስራቅ ሽዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክሯል።
የተጠሪ ክስ አመልካች በ2001 ዓ.ም መንገድ ሲሰራ ለውሃ መውረጃ ቦይ ሳያወጣ በመቅረቱ ውሃው 4 ቀረጥ የእርሻ መሬትን ስላበላሸ የ7 አመት የእርሻ ገቢ በመቋረጡ የ7 ዓመት ምርት 178 ኩንታል ስንዳ በ900 ብር ሑሳብ 151,200 / አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ሺ ሁለት መቶ ብር / ያጣሁ ስለሆነ አመልካች በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1254፤ 2027 እና 2092 መሰረት እንዱከፍለኝ ሲለ ክስ አቅርበዋል። አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ጉዲቱ ከደረሰ 7 ዓመት ስለሞላው በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.2143 መሰረት በይርጋ ይታገዲል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማቅረብ በፍሬ ነገሩም የመከላከያ መልሱን አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም ክርክሩ የአላባ ስለሆነ በማለት በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በፍሬ ጉዲዩ በአመልካች ጥፊት ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት በማለት የ6 ዓመት ምርት ብር 151,200 / አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ሺ ሁለት መቶ ብር / እንዱከፍል ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ምድብ ችልት አቅርበዋል።
በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤቱም በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2143 ካሳ የሚመለከት ሲሆን ካሳ ለመጠየቅ ደግሞ በሁለት አመት ውስጥ የሚል ስለሆነ በሁለት አመት አልጠየቀም። የሰባት ዓመት ሉጠይቅ አይችልም ስለሆነም የሁለት አመት ብቻ ነው መጠየቅ የሚችለው በማለት የሶስት አመት እንዱከፈለው ይኸውም የ151,200 ብር ግማሽ አመልካች እንዱከፍል ሲል የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በማሻሻል ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በሚል ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ ለሰበር እንዱቀርብ ተደርጎ ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
የአመልካች ጥያቄ በ2001 ዓ.ም ይህን መንገድ በከፍተኛ ወጪ ሲሰራ የቀበላውም ነዋሪዎች ከሳሽን ጨምሮ የወረዲውና የቀበላው መስተዲድር አንድ ላይ በመሆን ከአዲሚ ቱለ አስከ አለታ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ድረስ የሚሰራው መንገድ ለአከባቢው ህብረተሰብ ጠቃሚ መሆኑን አምኖበት በደስታ ተቀብለው መንገደን እየተገለገለበት ለ7 ዓመት ያህል ምንም አይነት ቅሬታ ለአመልካች ሆነ ለላልች ጉዲዩን ስልጣን ላላቸው የመንግስት አካል ሳያቀርቡ ዛሬ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የላለው፤ በሁለት አመት ይርጋ ጊዜ የታገደ ነው በሚል የቀረበው ክርክር ውድቅ በማድረግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበውን ግምት ሙለ በሙለ ይከፈል ብል ሲወሰን የክልለ ጠ/ፍ/ቤትም የ3 ዓመት ይከፈለው ሲል በማሻሻል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩለ ደግሞ የቀረበው የይርጋ ጥያቄ ከጉዲዩ ጋር ስለማይገናኝ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ትክክለኛና ህገ መንግስታዊ መብቴን ያረጋገጠልኝ ስለሆነ ምንም የህግ ስህተት የለበትም ይህ የሚታለፍ ከሆነ በአማራጭ የጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ እንዱያፀናልኝ በማለት ተከራክሯል። በዚህ ጉዲይ ቅድሚያ መታየት ያለበት ለክርክር ምክንያት የሆነው ጉዲት ደርሷል የተባለው በ2001 ዓ.ም ከመሆኑ አኳያ አመልካች ያነሳው የይርጋ ጥያቄ በስር ፍርድ ቤቶች በትክክል የመታየት ያለመታየቱን ይህ ቢታለፍ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ተፈፃሚነት ያለው የሁለት አመት ይርጋ ነው ካለ በኋላ ተመልሶ የ3 አመት የታጣ ጥቅም የመወሰኑን አግባብነት ነው። አመልካች ለሚያሰራው የአለቶ ላንጋኖ ጂኦተርማል አለቶ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሚወስድ መንገድ ስራ ምክንያት በተጠሪ መሬት ይዞታ ላይ ጉዲት መድረሱ ፍሬ ነገሩን የማጣራት ስልጣን ባለቸው በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ነው። በተጠሪ ክስ እንደተመለከተው በይዞታቸው ጉዲት የደረሰው ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑና እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ሳገኝ የነበረውን ጥቅም ማጣታቸውን ገልፀዋል። የተጠሪ ጥያቄ በቀጥታ ከውል ውጭ ኃላፉነት ጋር የሚገናኝ መሆኑ ግልፅ ነው። በዚሁ መሰረትም ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ በአመልካች እየተነሳ ያለው ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል መቃወሚያ ነው።
No topics extracted.
ከውል ውጭ ኃላፉነት ምክንያት ጉዲት የደረሰበት ሰው ጉዲቱ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ክስ ማቅረብ እንዲለበት በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2143 ተመልክቷል። ይህ ማለት ከሁለት አመት በኋላ የሚቀርብ ክስ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል።
ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስ በተጠሪ ሀብት ወይም ጥቅም ጉዲት የደረሰው ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑ አከራካሪ ጉዲይ አይደለም። በአመልካች ተግባር ምክንያት ለደረሰባቸው ጉዲት ካሳ የሰባት ዓመት ማግኘት የነበረባቸውን የምርት ዘመን ገምተው ክስ የመሰረቱት መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም ነው። ክሱ የቀረበው ከስድስት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው። ተጠሪ በመሬት ይዞታቸው ላይ ጉዲት መድረሱን ከማወቅና በወቅቱ ከመጠየቅ ያገዲቸውን ምክንያት አቅርበው የተከራከሩበት ሁኔታ የለም። በመሬት ይዞታቸው በየአመቱ ምርት የሚያገኙበት ላይ ጉዲት ለመድረሱ ወይም የቀረባቸውን ጥቅም ለማወቅ አንድ የምርት ዘመን ጊዜ በቂ ነው። በተጠሪ በኩል ያቀረበው ክርክር ጉዲቱ በየአመቱ እየጨመረ የሄደ እንጂ በአንድ ጊዜ የተከሰተ አይደለም በማለት ላቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም የጉዲቱ መጠን ሉጨምር እንደሆነ እንጂ ጉዲት ስለመድረሱ ላለማወቅ በቂ ምክንያት ላሆን አይችልም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች ክሱ ከውል ውጭ ኃላፉነት ለሚደርስ ጉዲት ካሳ ክስ መቅረብ ያለበት በህጉ በግለፅ የተቀመጠውን በማለፍ ከስድስት አመት በኋላ የቀረበ ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ ሆኖ እያለ ይህንኑ በማለፍ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል። በዚሁ መሰረትም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የምስራቅ ሽዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.40951 ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ በመ/ቁ.225865 መስከረም 27 ቀን 2008 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የተጠሪ ክስ በፍ/ብ/ህ/ቁ.2143 መሰረት ጉዲት ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በሁለት አመት ውስጥ ያልቀረበ በመሆኑ በይርጋ ቀሪ ስለሆነ አመልካች ሉጠየቅ አይገባም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ወጭ እና ኪሳራ የግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዘገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዘገብ ቤት ይመለስ። የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።