(የፍ/ሕ/ቁ. 2091፣ 2092 የኢ.ፋ.ድ.ሪ የቤተሰብ ህግ ቁ.. 213/92 አንቀጽ 197 50. በአንድ ውል ውስጥ ውልን የሚያፈርሱ የስምምነት ቃልች ተገልጾ ከተጻፈና የዚህም ስምምነት አፈጻጸም ጉዲይ ተሟልቶ ከተገኘ አንደኛው ተዋዋይ ውል ፈርሷል ሲል መግለጽ የሚችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ. 1786
No summary available.
ህዲር 26/2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- አቶ አዱሱ ግርማሁን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች አከራይ ቀረቡ ተጠሪ፡- ጉዝ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፊዬ ታዳ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጠ።
ጉዲዩ፡- የኪራይ ውልን መሰረት ያደረገ ሲሆን የአሁን ተጠሪ የሆነው የስር ከሳሽ በአሁን አመልካች የስር ተከሳሽ ላይ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በሺርካ ወረዲ ለሶል ዲጋልና ጎልቤሳ ሴሩ መንገድ ስራ አገልግልት የሚውል ሞዳለ D7H CAT ድዘር በሰዓት በብር 2,127.50 /ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ ሂሳብ ለ 200 ሰዓት ሉያቀርብልኝ ተዋውለን ህዲር 28/2005 ዓ.ም ብር 422,500.00 /አራት መቶ ሃያ ሁለት ሺኅ አምስት መቶ ብር/ ከፍየዋለሁ። ተከሳሽም ድዘሩን አቅርቦ ከታሕሳስ 4/2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 6/2005 ድረስ ለ 13 ሰዓት ያህል ከሰራ በኋላ ተበላሽቶ በመቆሙ ምክንያት ከተከሳሽ ጋር ውላችንን አሻሽለን ታህሳስ 17/2005 ዓ.ም CAT 322L ኤክስካቫተር በሰዓት 1,322.50 /አንድ ሺኅ ሶስት መቶ ሃያ ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ በጠቅላላ ለ 301 ሰዓት በብር 398,072.50 /ሶስት መቶ ዘጠና ስምንት ሺኅ ሰባ ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ ሉያቀርብልኝ ተዋውለናል። በዚህም መሰረት ተከሳሽ ኤክስካቫተሩን አቅርቦ ታህሳስ 23/2005 ዓ.ም ለ 3፡45 የሰራና ታህሳስ 26/2005 ለ 4፡45 በድምሩ 8፡30 ሰዓት ብቻ ሰርቶ በብልሽት ቆሟል።
ተከሳሽ በድዘሩ ማሽን ለ 13 ሰዓት ብቻ ያገለገለ በመሆኑ የ 13 ሰዓት ክፍያ 13X 2,127.50= 27657.50 /ሃያ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ ሲሆን በኤክሳካቫተሩ ለ 8፡30 ያገለገለ በመሆኑ 8፡50 X በ 1,322.50= 11,241.25 በድምሩ ብር 38,898.75 /ሰላሳ ስምንት ሺኅ ስምንት መቶ ዘጠና ስምንት ብር ከሰባ አምስት ሳንቲም/ ተቀንሶ ቀሪው ብር 386,601.30 /ሶስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺኅ ስድስት መቶ አንድ ብር ከሰላሳ ሳንቲም/ እንዱመልስልኝ ብጠይቀው ፍቃደኛ አይደለምና ዋናውን ገንዘብ ከነህጋዊ ወለደ ይክፈለኝ በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
ተከሳሽ ኢንተርፕራይዝም በሰጠው መልስ ከከሳሽ ጋር ውል መኖሩን አምኖ መጀመሪያ ለድዘሩ የተዋዋልነውን ውል በስምምነት ታህሳስ 17/2005 ዓ.ም በተጻፈ ውል ወደ ኤክስካቫተር ለውጠነዋል ኤክስካቫተሩ እስከ ታህሳስ 26/2005 ዓ.ም ሰርቶ ተበላሽቶ ለመቆሙ የማውቀው ነገር የለም ከሳሽም በብልሽት ለመቆሙ ማስረጃ አላቀረበም። ቢበላሽ እኳን በውላችን አንቀጽ 5 ላይ ማሽኑ ለአስር ተከታታይ ቀናት ካልሰራ የተከፈለው ገንዘብ እንደሚመለስ እየታወቀና በ 26/4/2005 ዓ.ም ማሽኑ አገልግልት መስጠቱን በከሳሽ እየታወቀ አስር ቀን ሳይሞላው በ 2/5/2005 ዓ.ም ከሳሽ ውለታ አቋርጠናል ማለቱ አግባብ አይደለም፤ በተጨማሪም ከተከሳሽ ብር 422,500.00 /አራት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ የተቀበልኩ ቢሆንም አስራ አምስት ፏርሰንት ተጨማሪ እሴት ታክስ ለመንግስት የከፈልኩ ስለሆነ የከሳሽ ትክክለኛ ገንዘብ 370,000.00 /ሶስት መቶ ሰባ ሺኅ ብር/ ብቻ ነው ብሎል።
ፍ/ቤቱ የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተከሳሽ የመጀመሪያው ውል በሁለተኛው ውል የተተካው በድዘሩ ብልሽት ሳይሆን በግራ ቀኙ ስምምነት ነው ቢልም የግራ ቀኙ ስምምነት የተደረገው በድዘሩ መበላሸት ምክንያት መሆኑን ከማሻሻያው ውል መረዲት ተችሎል።
በተጨማሪም ተከሳሽ ማሽኖቹን በራሴ ወጪ አጓጉዤ ለማምጣት ወጪ አውጥቻለሁ ቢልም በውላቸው ላይ ተከሳሽ በራሱ ወጪ አጓጉዞ ለማስገባት እና ማሽኑ በቀን ስምንት ሰዓት በሳምንት ስድስት ቀን ሉሰራና ማሽኑ ሳይበላሽ ስራ ካልሰራ ሃላፉ ከሳሽ መሆኑን፤ መስማታቸውንና፤
ማሽኑ ለተከታታይ አስር ቀናት በብልሽት ቢቆም የሰራበት ታስቦ ያልሰራበትን ተከሳሽ ሉመልስ የተስማሙ ቢሆንም ሁለተኛው ማሽንም በብልሽት ምክንያት ከ 23/4/2005 ዓ.ም ጀምሮ በየቀኑ አስር ሰዓት ሉሰራ አለመቻለ በሰዓት መመዝገቢያ ላይ ተመዝግቦ ይገኛል። በተጨማሪም የከሳሽ ምስክሮች በወቅቱ በማሽኑ መበላሸት ስራ ያለመስራታቸውን ሲገልጹ የተከሳሽ ምስክሮች ማሽኑ ስራውን ያልሰራው በመበላሸት ምክንያት ሳይሆን በገና በዓል ምክንያት ኦፕሬተሩና ረዲቱ ወደ ቤተሰብ በመሄዲቸው ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ማሽኑ ባለመስራቱ ከሳሽ ለተከሳሽ በ 2/5/2005 ዓ.ም በጻፈው ማስጠንቀቂያ ከጥር 3/2005 ዓ.ም ጀምሮ ውለ መቋረጡን መግለጹን በተከሳሽም ታምኗል በማለት አትቶ ተከሳሽ ከተከፈለው ገንዘብ ውስጥ ማሽኑ የሰራበት ብር 38,818.70 ሳ ተቀንሶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን ጨምሮ ብር 386,601.30 ከሚታሰብ ወለድ እና ተያያዥ ከሆኑ ክፍያዎች ጋር ይክፈል በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የአሁን አመልካች የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ቅሬታው የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቅሬታው መልስ ሰጭን አያስጠራም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዞታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበው የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታልና ሉታረም ይገባል በሚል አመልካች በመጠየቃቸው ነው። የሰበር አጣሪው ችልትም በግራቀኙ መካከል ያለው ውል በአንቀጽ 5 ላይ ኤክስካቫተሩ ለአስር ተከታታይ ቀናት በብልሽት ምክንያት ካልሰራ ውለ እንደሚቋረጥና የተከፈለው ገንዘብ እንደሚመለስ የተስማሙና ማሽኑ እስከ ታህሳስ 26/2005 ዓ.ም ድረስ የሰራ መሆኑ እየታወቀ አመልካች የከፈለውን ገንዘብ በተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን ጨምሮ ሉከፍል ይገባል በማለት የተወሰነበትን አግባብነት ተጠሪ ባለበት ለማጣራት ያስችል ዘንድ ተጠሪን ያስቀርባል ብሎል።
ተጠሪም በወኪለ አማካኝነት በጽሐፍ በሰጠው መልስ ተጠሪ በውለታችን መሰረት መጀመሪያ ያቀረበው ማሽን በብልሽት ምክንያት ባለመስራቱ ውለታችንን አሻሽለን ላላ ማሽን እንዱያስገባ ብንስማማም 2ኛው ማሽንም በውላችን መሰረት በቀን 8 ሰዓት በሳምንት 6 ቀን ሉሰራልኝ አልቻለም። ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለም ቢሆን በማሽኑ ብልሽት ምክንያት ስራ ላልተሰራበት ያልተከፈለ መሆኑን በማሳወቅ ተጠሪ ገንዘቡን ማስመለስ ይችላል በአጠቃላይ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተገቢ ነውና ሉጸና ይገባል ብሎል።
አመልካችም የጽሐፍ የመልስ መልስ አቅርቧል የክርክሩ አመጣጥና በዚህ ችልት ግራቀኙ ያቀረቡት የጽሐፍ ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረነዋል።
እንደመረመርነውም ተጠሪ በገባው ውል መሰረት በቀን ለስምንት ሰዓት በሳምንት ለስድስት ቀናት አገልግልት ለመስጠት የሚያስችል ማሽን ማቅረብ ሲገባው ያቀረበው ማሽን በብልሽት ምክንያት ሉሰራ አልቻለም በሚል የስር ፍ/ቤቶች ተጠሪ ለአመልካች የከፈለውን ገንዘብና ተያያዥ ክፍያዎችን እንዱመልስ መወሰናቸው አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ መመርመሩ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሰረቱ አመልካችና ተጠሪ የማሽን ኪራይ ውል ያላቸው መሆኑን በዚህም መነሻ ተጠሪ ብር 422,500 ለአመልካች የከፈለ መሆኑን አመልካችም በውለታው መሰረት ማሽን ማቅረቡንና ማሽኑ ለ 3 ቀንና ለ 13 ሰዓት መስራቱ በግራቀኙ የታመነ ጉዲይ ነው። አመልካች ከተጠሪ ጋር በስምምነት ውለታውን ወደ ኤክስካቫተር ቀይረናል ሲል ተጠሪ ውለን ልንቀይር የቻልነው በማሽኑ ብልሽት ምክንያት ነው ብሎል። የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በውሳኔ ላይ እንዲተተውም ውለታቸው የተሻሻለው በድዘሩ መበላሸት ምክንያት መሆኑን ውለታቸው የሚገልጽ መሆኑን ነው። በመቀጠልም አመልካች በተሻሻለው ውለታ መሰረት ኤክስካቫተሩን ያቀረበ ቢሆንም ይህም ማሽን ለሁለት ቀን በድምሩ ለ 8፡30 አገልግልት መስጠቱን በግራቀኙ የታመነ ጉዲይ ሲሆን ስራው የቆመው ግን አመልካች የገና በዓል ስለነበረ የማሽኑ ኦፏሬተርና ረዲቱ ለበዓል ወደ ቤተሰብ እንዱሄደ ከተጠሪ ጋር በተነጋገርነው መሰረት ነው ሲል ተጠሪ በብልሽት ምክንያት መሆኑን ገልጾ በዚሁ ምክንያት መሆኑን በሰውና በሰነድ ማስረጃ መረጋገጡን የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከተደረገው ክርክርና ማስረጃ መረዲት ተችሎል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ዋናው ምክንያት በውለታችን አንቀጽ 5 ላይ ማሽኑ በቀን ለስምንት ሰዓት በሳምንት ለስድስት ቀን አገልግልት መስጠት እንዲለበት ተዋውለን እያለ ማሽኑ ታህሳስ ታህሳስ 23/2005 ዓ.ም ለ 3፡45 ታህሳስ 26/2005 ዓ.ም ለ 4፡45 ሰዓት የሰራ ሆኖ እያለ ማሽኑ መስራት ካቆመ አስር ቀን ሳይሞላ ጥር 2/2005 ዓ.ም ተጠሪ ለአመልካች የውል ማቋረጫ ማስጠንቀቂያ በመላክ በቀን 3/5/2005 ዓ.ም ውለ መቋረጡ ተገቢ አይደለም የሚል ነው። እኛም ይህን ጭብጥ አስመልክቶ እንደመረመርነው በግራቀኙ ውል አንቀጽ 5 ስር እንደተመለከተው ማሽኑ በቀን ለስምንት ሰዓት በሳምንት ለስድስት ቀን ሉሰራ እንደሚገባና በዚህ በተቀመጠው መለኪያ /እስታንዲርድ/ መሰረት ለአስር ተከታታይ ቀናት አገልግልት ካልሰጠ ውለ ፈርሶ አመልካች በውለ ምክንያት የተቀበለውን ገንዘብ እንዱመልስ መስማማታቸውን ከግራቀኙ ክርክር በመታመኑ ከመረጋገጡም በተጨማሪ በማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ መሆኑን ከስር ፍ/ቤት መዝገብ ማረጋገጥ ተችሎል። ይህ ከሆነ ዘንዲ ተጠሪ የውለታውን ገንዘብ መክፈለ ግልጽ እስከሆነ ድረስ አመልካች በውለታው መሰረት ማሽን አቅርቦ አገልግልቱን የመስጠቱን ጉዲይ ሲታይ በውላቸው የተስማሙት ማሽኑ በቀን 8 ሰዓት በሳምንት 6 ቀን አገልግልት ላሰጥ የነበረ ቢሆንም ማሽኑ በውለ መሰረት አገልግልት ያለመስጠቱን በግራቀኙ የታመነ ሆኖ አመልካች በበአል ምክንያት ነው ቢልም በዚህ መልኩ ያለማስረዲቱ ከስር ክርክር መረዲት ተችሎል።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1786 ስር እንደተመለከተው በአንድ ውል ውስጥ ውልን የሚያፈርሱ የስምምነቶች ቃል ተገልጾ ከተጻፈበትና የዚህም ስምምነት አፈጻጸም ጉዲይ ተሟልቶ ከተገኘ አንደኛው ተዋዋይ ውል ፈርሷል ሲል ለመግለጽ እንደሚችል ተደንግጓል። ከዚህ ስንነሳ አመልካች በገባው የውል ግዳታ መሰረት ግዳታውን ያልተወጣ በመሆኑ ተጠሪ ውለን ያቋረጠ መሆኑን መግለጹ ከውለታቸውም ሆነ ከሕጉ የወጣ አሰራር አይደለም።
ሲጠቃለል የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ በጠየቀው ዲኝነት መሰረት ውለ ስለፈረሰ ለአመልካች ከተከፈለው ክፍያ ውስጥ አገልግልት የሰጠበት ሰዓት ክፍያ ብር 38,818.70 /ሰላሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ስምንት ብር ከሰባ ሳንቲም/ ተቀንሶ የተጨማሪ እሴት ታክስን በተመለከተ አመልካች ከፍል ከሆነ በሚያቀርበው ማስረጃ ለከፈለው አካል ከሚጠይቅ በስተቀር ተጠሪ ላላገኘው አገልግልት ሉከፍል አይገባም በማለት ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለ ክፍያን ጨምሮ ብር 386,601.30 /ሶስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺኅ ስድስት መቶ አንድ ብር ከሰላሳ ሳንቲም/ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9 ፏርሰንት ህጋዊ ወለድ ጋር፤ ውሳኔ ያገኘበት የገንዘብ መጠን 8 ፏርሰንት የጠበቃ አበል ብር 30,934.50 /ሰላሳ ሺኅ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አራት ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ ለዲኝነት የተከፈለ ብር 6716.05 /ስድስት ሺኅ ሰባት መቶ አስራ ስድስት ብር ከዜሮ አምስት/ አመልካች ለተጠሪ ይመልስ፤ በማለት ሲወሰን የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህን ውሳኔ በማጽናት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ሰጥተናል።
የስር የፋዳራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 10332 የካቲት 20 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ. 150808 በቀን ሐምል 23 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
ለዚህ ፍ/ቤት ክርክር ግራቀኙ ያወጡት ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ።
ትእዛዝ
በዚህ ፍ/ቤት የተሰጠው የአፈጻጸም እግድ ተነስቷል ይጻፍ።
የውሳኔው ግልባጭ በየደረጃው ለሚገኙ የስር ፍ/ቤቶች ይተላለፍ።
No topics extracted.