የደረሰው ጉዲት አጓዥ በፈጸመው ተግባር ወይም ባደረገው ጉድለት እንዱሁም ይህ ተግባር አደጋ ሉያደርስ ወይም ሉፈጥር የሚችል መሆኑ እየታወቀ ሲሆን የኃላፉነት መጠኑ በህጉ ከተቀመጠው ውጪ ላሆን የሚችል ስለመሆኑ፣ በልጅ ቀለብ አወሳሰን ረገድ ልንከተላቸው ስለሚገቡ መሰረታዊ ወ/ሮ ነጋሪነት ሰለሞን የህጻን የአብስራ ቴዎድሮስ እና ስካይ ባስ ትራንስፖርት ሲስተም XVIII ( የን/ሕ/ቁ. 597፣
No summary available.
ሕዲር 19 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወ/ሮ ነጋሪት ሰለሞን ሞግዚት ለሆኑለት ሕፃን የአብስራ ቴዎድሮስጠበቃ ሙለታ ደበል ቀርቡ ተጠሪ፡- ስካይ ባስ ትራንስፖርት ሲስተም አ.ማ - ጠበቃ በላይ ከተማ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ግንኙነቱ የመጓጓዣ ውልን መሰረት ያደረገ ቢሆንም የጉዲት ካሳ ክፍያው ከውል ውጪ ኃላፉነትን መሰረት አድርጎ ሉከፈለን ይገባል የሚለውን የአመልካችን ጥያቄ መነሻ አድርጎ የታየውን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡ንብረትነቱ የአሁኑ ተጠሪ የሆነና የታርጋ ቁጥር 3-40411ኢት በሚል የሚታወቀው የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ የአመልካች ባለቤትና ሞግዚትና አስተዲዲሪ ለሆኑለት ህጻን ደግሞ ወላጅ አባት የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ተሳፍረውበት ጥር 08 ቀን 2004 ዓ/ም ከአዱስ አበባ ወደ ጎንደር እየተጓዙበት እያለ አባይ በርሃ ላይ ከአሽከርካሪው ጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ለሕልፈት የተዲረጉ መሆኑን፣ ሟች በሕይወት እያለ በወር ብር 3136.00 ገቢ በሚያስገኙ ስራ ላይ ተሰማርተው በሚያገኙት ገቢ አመልካችን ያስተዲድሯቸው እንደነበር፣የህጻኑንና የሟች እድሜ በመግለጽ እንዱሁም የሕሉና ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑን በመጥቀስና የተቋረጠባቸውን ጥቅም በመዘርዝር በድምሩ ብር 395,816.00(ሶስት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ስድስት ብር) ለክሱ ከአወጡት ወጪና ኪሳራ ጋር ተጠሪ ኃላፉ ተብል እንዱከፍል ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በሰጠው መከላከያ መልስም፡-ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት የግዛት ስልጣን የላለው መሆኑ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ከአስቀደመ በኋላ በፍሬ ነገር ረገድ ደግሞ ተጠሪ ጉዲቱን አምኖ መረጃዎችን በማሰባሰብ ወደ መድን ድርጅት በማስተላለፍ የሚጠበቅበትን ማድረጉን፣ አመልካች የሚፈለግባቸውን አሟልተው ከመድን ሰጪው ጋር ከመነጋገር ውጪ ተጠሪው ኃላፉነት የላለበት መሆኑን፣ ካሳው በአሰሪውና በሰራተኛው አዋጅ መሰረት በኢንሹራንስ ወይም በመጠባበቂያ ጡረታ ገንዘብ የሚሸፈን መሆኑን፣ መጠኑ ከጉዲቱ ጋር ተመጣጣኝ መሆን ያለበት መሆኑን፣ ለወደፉቱ ሉደርስ ይችላል ተብል በሚገመተው ጉዲት የተረጋገጠ መሆን ያለበት መሆኑን፣ ሟች በሕይወት ሳለ ለሕጻኑ ይህን ያህል ወጪ ያወጣ ነበር ተብል በማስረጃ ተደግፍ ያለመቅረቡን፣ በመተዲደሪያ በኩል የተቋረጠ ገቢ ሳይኖር የቀረበ ክስ መሆኑን፣ የቀረበው መጠን በማስረጃ ያለመረጋገጡን ዘርዝሮና በአጠቃላይ የአስራ ሰባት አመት የተጠየቀው የሕግ መሰረት የለውም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን ለመኪናው መድን ሽፊን የሰጠው አካል ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዱገባለትም ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል።
የኢትዩጵያ መድን ድርጅት ወደ ክርክሩ እንዱገባ ተደርጎም የሃላፉነት መጠኑ እስከ ብር 40,000.00(አርባ ሺህ) መሆኑን፣አመልካች የህጻኑ እናት ስለመሆናቸውና ከሟቹ ጋር የነበራቸው ምን እንደሆነ እንደማይታወቅ፣ሕጻኑ ሲወለድ ሟች በሕይወት ስለላለ ህጻኑ ሉያገኘው የሚገባው ጥቅም ተቋርጧል የተባለው ከእውነት የራቀ ምክንያታዊነት የላለው መሆኑን፣ የሟች ደመወዝ ብር 3,136.00 የተባለው ተጣርቶ የሚደርሳቸውን ያለመሆኑን፣ የተቋረጠው የጥቅም መቋረጥ የተጋነነ እና ከሟች ችልታ እንዱሁም ከመሰረታዊ ፍላጎት ውጪ የሆኑትን ያካተተ መሆኑን ዘርዝሮ ኃላፉነት የለብንም፣ አለ ቢባል እንኳን ያላግባብ የቀረበ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ተደርጎ ልንሰናበት ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት የአሁኗ አመልካች በራሳቸው በኩል ያቀረቡት የካሣ ጥያቄ የላለ መሆኑን ገልፆና ህጻኑ ግን ወራሽነቱ ተረጋግጦ በሞግዚቱ በኩል ክስ የአቀረበ በመሆኑ ክስ ለማቅረብ መብት እንዲለው ገልፆ በዚህ ረገድ ተጠሪና ጣልቃ ገቡ ያቀረቡትን ክርክር በማለፍ በፍሬ ነገሩ ደግሞ ሟች ከተጠሪ ጋር የመጓጓዣ ውል ግንኙነት የነበረው መሆኑ መረጋገጡን፣ በዚህ ምክንያትም ለደረሰው የሞት አደጋ ተጠሪ በን/ሕ/ቁጥር 596 መሰረት ኃላፉነት አለበት በማለት ወስኗል። ከዚህ በኋላ የካሣ መጠኑን በተመለከተ ደግሞ አደጋው በመደበኛ የመኪና ክስተት የደረሰ በመሆኑ በን/ሕ/ቁጥር 597 ከተመለከተው የካሳ መጠን በላይ ሉያልፍ የሚችልበት አግባብ የላለ መሆኑን ጠቅሶና ሟች በየወሩ ያገኙ ከነበረው ደመወዝ ውስጥ ለህጻኑ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር) ወጪ ሉያደርጉ ይችለ እንደነበር፣ ህፃኑ በወቅቱ የነበረው ዕድሜ አንድ አመት ሁኖ ቀለቡ ለምግብ፣ ለልብስ፣ ለትምህርት፣ ለጤና እና ለላልች ለመልካም አስተዲደግ የሚበጁ ፍላጎቶች ለቀጣይ አስራ ሰባት አመት ድረስ የሚያስፈልገው መሆኑን ጠቅሶ በድምሩ ብር 102,000.00(አንድ መቶ ሁለት ሺህ ብር) ሉደርስ እንደሚችል ከገለፀ በኋላ በን/ሕ/ቁጥር 597 ድንጋጌ መሰረት የጉዲት ካሳ መጠኑ ከብር 40,000.00(አርባ ሺህ) ሉበልጥ አይችልም በማለት ይህንኑ ብር ተጠሪና ጣልቃ ገብ ባልተነጣጠለ ሁኔታ እንዱከፍለ በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የሥር ፍርድ ቤት የአመልካችን ኃላፉነት በተመለከተ አደጋው በተለመደው የማሽከርከር ሂደት የተከሰተ ነው የሚለውን ድምዲሜ ያላግባብ ማስፈሩንና መረዲቱን፣ መኪናው መንገደን ስቶ መግባቱ በን/ሕ/ቁጥር 599 ድንጋጌን መሰረት ተጠያቂነትን የሚያስከትል አይደለም በማለት ለህጻኑ በቀለብ ረገድ እንዱከፈል ካሳው ሲወሰን መጠኑ ከብር 40,000.00 ሉበልጥ አይችልም መባለ የአመልካችን ክስና ማስረጃ እንዱሁም የተጠሪን ክርክር ይዘት ያላገናዘበ ነው በማለት የተጠሪ ኃላፉነት በን/ሕ/ቁጥር 599 ታይቶ የካሳው መጠንም በተጠየቀው አግባብ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ በመደረጉ ተጠሪ ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዙት ጭብጦች መገንዘብ የተቻለው፡-
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡-ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች የሕዝብ ማመላለሻ በሆነው የአመልካች መኪና በመጓጓዝ ላይ እንዲለ መኪናው አባይ በርሃ ተብል በሚታወቀው አከባቢ ተገልብጦ ለሕልፈተ-ሕይወት የተዲረጉ መሆኑ መረጋገጡን፣ አመልካች አሁን አጥብቀው የሚከራከሩት የተሽከርካሪው አሽከርካሪ መንገድ ስቶ መግባቱ ተረጋግጦ እያለ አመልካች አሽከርካሪው የፈፀመው ጥፊት ስለመኖሩ የሚያሳይ ክርክርና ማስረጃ በአመልካች አልቀረቡም ተብል በተጠሪና እና በሟች መካከል ያለው ግንኙነት የመጓጓዣ ውልን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የካሳ መጠኑ ከብር 40,000.00 ሉበልጥ አይችልም በሚል መወሰኑ ያላግባብ ነው በሚል መሆኑን ነው።
በሟች ላይ ጉዲት እንዱደርስ ያደረገው የአመልካች መኪና የሕዝብ መጓጓዣ የሚሰጥ መሆኑን አመልካች በስር ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰርቱ ከመግለጻቸውም በላይ አደጋው የደረሰበትን ሁኔታ ለማስረዲትም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ዘርዝረው ማቅረባቸውን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ በገጽ ሁለት በግልጽ ያሳያል። አመልካች በሕጉ አግባብ የቆጠሩአቸው ምስክሮች ያልተሰሙት በምን ምክንያት እንደሆነ የስር ፍርድ ቤትም ሆነ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጮች የሚያሳዩት ነገር የላለ ሲሆን ለጉዲዩ ቀረበ የተባለው የሰነድ ማስረጃ ግን ተሽከርካሪው መንገደን ስቶ በመግባቱ አደጋው መድረሱን እንደሚገልጽ ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች የተቀበለት ጉዲይ መሆኑን የክርክሩ ሂደት የሚያሳይ ሁኖ ተገኝቷል። የበታች ፍርድ ቤቶች ተሽከርካሪው መንገደን ስቶ ገድል መግባቱ መረጋገጡን ተቀብለው ይህ ክስተት በን/ሕ/ቁጥር 599 አግባብ ተጠያቂነት አያስከትልም ወደሚለው ድምዲሜ የደረሱት እንዱዚህ አይነት አደጋ በመደበኛ የመኪና ክስተት የደረሰ መሆኑን የሚያስረዲ ነው በሚል ምክንያት ነው። ይሁን እንጂ አንድ አሽከርካሪ የመኪናውን መንገድ ስቶ የሚገባው በመደበኛው የማሽከርከር ሂደት ነው ተብል ድምዲሜ የሚያዝበት አግባብ የላለ ሲሆን በማሽከርከር ሂደት መንገድ መሳት ሉከሰት የሚችለው በመኪናው ላይ በሚያጋጥመው የቴክኒክ ችግር ወይም በሹፋሩ የአነዲድ ችግር ወይም ላላ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ትክክለኛውን መስመር ይዞ ለማሽከርከር የማያስችል ሁኔታ ሲያጋጥም መሆኑ የሚታወቅ ነው። የአሁኑ ተጠሪ አደጋው መደረሱን አምኖ መኪናው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በልላ ሕጋዊና አሳማኝ ምክንያት አደጋው የደረሰ ስለመሆኑ ገልፆ ያቀረበው ክርክር የላለ መሆኑን የክርክሩ ሂደት በግልጽ ያሳያል።
ከዚህ አንጻር ጉዲዩ ሲታይ መኪናው መንገደን ስቶ ገደል የገባው በሹፋሩ በተፈፀመው የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን የሚያስረዲ እንጂ በተለመደበው የመኪና ክስተት ነው ልባል የሚችል ሁኖ አልተገኘም። የተጠሪ መኪና አሽከርካሪ ጥፊት የነበረበት ስለመሆኑ በዚህ ችልት በሰ/መ/፣ በቀረቡት ጉዲዮች ላይም የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በመሆኑም መኪናው መንገድ ስቶ ገድል መግባቱን የሚያሳይ ማስረጃ አመልካች ከማቅረባቸውና ተጠሪ ደግሞ ለአመልካች ክስ በሰጠው መልስ መኪናው መንገድ ስቶ ገደል የገባው ከአሽከርካሪው ጥንቃቄ ጉድለት ስለመሆኑ ገልጾ ያልተከራከረ የመሆኑ ጉዲይ አደጋው በአሽከርካሪው ጥፊት የደረሰ ስለመሆኑ ተመሳሳይ በሆኑ መዝገቦች ተረጋግጧል ተብል ድምዲሜ ከመያዙ ጋር ተዲምሮ ሲታይ በዚህ ጉዲይም የአመልካች ኃላፉነት መጠን በን/ሕ/ቁጥር 597 የሚገደብበትን አግባብ አላገኘንም።
ሟቹን ለሕልፈት የዲረገው ተሽከርካሪ ሟቹ የመጓጓዣ ውል የመሰረቱበትና በጉዞ ላይ እንዲለ ተገልብጦ ጉዲቱ መድረሱ ከተረጋገጠ ጉዲዩ መገዛት ያለበት በንግድ ሕጉ ስለሰዎች መጓጓዣ በሚደነግጉት ድንጋጌዎች አግባብ ስለመሆኑ በመርህ ደረጃ በንግድ ሕጉ የተደነገገ ጉዲይ ነው።
የመንገደኛውን ግዳታ በሚደነግገው በን/ሕ/ቁጥር 687 ስር መንገደኛው በውለ ላይ የተወሰነውን ዋጋ መክፈል፣ ጉዞውን በሚጀምርበትን ስፍራ በተወሰነው ሰዓት መድረስና እንዱሁም በጉዞው ጊዜ ሁለ አጓዡ የሚሰጠውን ትዕዛዝና በሕግ የታዘዘውን ማክበር እንደሚገባው በአስገዲጅ ሁኔታ ተደንግጓል። አጓዡ ደግሞ መንገደኛውን በመልካም ይዞታና ጥበቃ እንዱሁም ስለ ምቾቱና ስለጉዞው በውለ በተወሰነው ጊዜ አክብሮ እንደተወሰነው መድረሻው ስፍራ የማድረስ ግዳታ ያለበት መሆኑን የን/ሕ/ቁጥር 588 በግልጽ ያሳያል። እነዚህ ድንጋጌዎች የመንገደኛውን እና የአጓዡን ተነፃፃሪ ግዳታዎችን የሚደነግጉ ሲሆን አጓዡን ኃላፉነት ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 547/1999 የተሻሻለት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሁነው ከቁጥር 589 እና ተከታይ ድንግጌዎች ስር አስፍሯል።
በመንገደኛው አካል እና ሕይወት ላይ ለሚደርሰው ጉዲት የአጓዡን የኃላፉነት መጠን በን/ሕ/ቁጥር 597 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ስር ተመልክቷል። በእነዚህ ድንጋጌዎች ስር ያለት የአላፉነት አይነቶች የሚከሰቱት በሕግ አግባብ የተቋቋመ የመጓጓዣ ውል መኖሩ ሲረጋገጥ መሆኑ ግልጽ ነው። በአዋጅ ቁጥር 547/1999 ያልተሻረውን የሰው መጓጓዝን መሰረት አድርገን ስናየው የመጓጓዣ ውል የሚባለው አጓጓዥ ዋጋ በመቀበል ሰውን የተወሰነ ስፍራ ለማድረስ ግዳታ የገባበት ስምምነት ስለመሆኑ በን/ሕ/ቁጥር 561 ስር የተደነገገ ሲሆን የን/ሕ/ቁጥር 567(1) ድንጋጌ ሲታይም ሰውን ለማጓጓዝ የሚደረግ ውል በሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሰረት ስለመሆኑና አጓዡ መንገደኛው የማጓዣ ሰነድ ትኬት ወይም የደንበኛነት ቲኬት እንዱቀርብና ጉዞውን እስኪፈጽም ድረስ ጠብቆ መያዝ የሚገባው መሆኑን ሉያስታውቀው እንደሚችል ደንግጓል። የን/ሕ/ቁጥር 567(2) ድንጋጌ ደግሞ የመጓዣ ሰነድ ሳይኖረው የሚጓዝ መንገደኛ ከዋጋው በላይ ተጨማሪ ገንዘብ ይከፈላል የሚል ማስታወቂያ ላደረግ እንደሚችል ሲደነግግ ለመንገደኛው በሚሰጠው ቲኬት ላይ የሚከፈለው ዋጋና የሰዓቱ መነሻና መድረሻ የተመለከተ መሆን እንዲለበትም የተጠቃሹ ድንጋጌ በንዐስ ቁጥር ሶስት ስር በግልጽ አስፍሯል። ጉዲዩን የሚገዛው ልዩ ሕግ የንግድ ሕጉ ነው ከተባለ ደግሞ የጉዲት ካሳ የሚሰላውም በዚሁ ሕግ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ነው።
በመሰረቱ በንግድ ህግ ቁጥር 596 መሰረት አደጋው የደረሰ መሆኑን ለማስረዲት ካልቻለ በመንገደኛው ላይ ለደረሰው ጉዲት በሀላፉነት የሚጠየቅ መሆኑን የንግድ ሕግ ቁጥር 597 ድንጋጌ ያሳያል። የሀላፉነት መጠንን በተመለከተ ደግሞ ለአንድ መንገደኛ ከብር 40,000 /አርባ ሺ ብር/ እንደማይበልጥ የንግድ ህግ አንቀጽ 597 በግልጽ ይደነግጋል። ይሁን እንጂ በንግድ ህግ አንቀጽ 597 የተደነገገው የሀላፉነት መጠን አጓዡ በንግድ ህግ አንቀጽ 596 የተደነገጉትና ከሀላፉነት ነጻ የሚያደርጉት ሁኔታዎች መኖራቸውን ለማስረዲት ባልቻለበት ሁኔታና መንገደኛው በንግድ ህግ አንቀጽ 599 በሚደነገገው መሰረት አጓዡ አደጋ ሉያደርስ የሚችል መሆኑን እያወቀ በፈጸመው ተግባር ወይም ጉድለት ምክንያት አደጋው የደረሰ መሆኑን ለማስረዲት ባልቻለበት ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆን ድንጋጌ ነው።
በንግድ ህግ ቁጥር 588 በሚደነግገው መሰረት የመንገደኛውን መልካም ይዞታ ደህንነትና ምቾት በመጠበቅ መንገደኛውን የማጓጓዝ ሀላፉነቱን ሉወጡ የሚገባቸውን ወገኖች የመኪና ባለቤት፣ ሹፋር፣ረዲቱና ላልች ሰራተኞች ሉሆኑ የሚችለበት አግባብ መኖሩን፣ በንግድ ህግ አንቀጽ 599 ‛አጓዡ የተፈፀመው ተግባር ወይም ጉድለት“ የሚለው ሀረግ አጓዡ በግለ የፈጸመውን ተግባር ወይም ጉድለት የሚመለከት ሣይሆን የአጓዡ ሰራተኞች አደጋ ሉያደርስ ወይም ሉፈጠር እንደሚችል እያወቁ የፈጸሙትን ተግባር ወይም ጉድለት የሚያካትት ስለመሆኑ በሰ/መ/ በሆነው መዝገብ ላይ በቀረበው ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት በማናቸውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያሰገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። በዚህ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም የተያዘው ጉዲዩ ሲታይም አደጋው የደረሰው የአመልካች መኪና ሲያሸከረክር የነበረው ሹፋር ባጠፊው ጥፊት ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች የክርክር ሂደት የተረጋገጠ በመሆኑ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የን/ሕ/ቁጥር 599 ሁኖ አግኝተናል። እንዱህ ከሆነ አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት በንግድ ህግ አንቀጽ 597 ከተደነገገው በላይ ካሣ የመክፈል ሀላፉነት የለብንም በማለት ያቀረቡት ክርክር የህግ መሰረት ያለው አደለም። በመሆኑም አመልካች በንግድ ህግ አንቀጽ 597 ከተደነገገው የሀላፉነት መጠን በላይ ለተጠሪ ካሣ የመክፈል ሀላፉነት እንዲለባቸው የንግድ ህግ አንቀጽ 599 ድንጋጌ የሚያስገነዝበን በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የካሳው መጠን ብር 40,000.00 ላሆን ይገባል ሲለ የደረጓት ድምዲሜ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። ምክንያቱም የንግድ ህግ አንቀጽ 599 ድንጋጌ በን/ሕ/ቁጥር 597 ስር የጉዲት ካሳ ከብር 40,000.00 እንደማይበልጥ በመርህ ደረጃ የተቀመጠውን የሀላፉነቱን መጠን በልዩ ሁኔታ የደነገገ፣ መንገደኛው ከአጓዡ ከብር 40,000 በላይ ካሣ ለመጠየቅና ለማግኘት የሚችልበትን ልዩ ሁኔታ የሚደነግግ ድንጋጌ ነውና። በን/ሕ/ቁ. 599 ድንጋጌ መሰረት ለመንገደኛው ካሣ የመክፈል ሀላፉነት ያለበት አጓዥ ለመንገደኛው የሚከፍለው የካሣ መጠን ለመወሰን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091 እና 2092 የተደነገጉት የካሳ አከፊፈል መርሆች አግባብነት ያላቸው ስለመሆናቸውም ይህ ችልት ከላይ በተጠቀሰው የሰበር መዝገብ አሰገዲጅ የሕግ ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ ነው።
በተያዘው ጉዲይ ግን የተጠሪ ንብረት የሆነውን የህዝብ ማመላለሻ ያሽከረክር የነበረው የተጠሪ ሰራተኛና የመኪናው ሹፋር በፈጸመው ከባድ ጥፊት ምክንያት አደጋው መድረሱ በሚገባ ተረጋግጧል።ተጠሪ በዚህ ሰበር ደረጃ አጥብቆ የሚከራከረው የተጠሪ ንብረት የሆነውን የህዝብ ማመላለሻ መኪናን ያሽከረክር የነበረው የተጠሪ ሰራተኛና የመኪናው ሹፋር የሆነው ከባድ ጥፊት የነበረበት ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው ፖሉስ አልቀረበም፣ ተሽከርካሪው ፍጥነት የነበረው ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረበም፣ አመልካች ባቀረቡት የሰነድ ማስረጃ መኪናው መንገድ ስቶ ገደል ገብቷል ተብል መጠቀሱ የአሽከርካሪውን ጥፊት የሚያሳይ አይደለም በማለት ስለመሆኑም ተገንዝበናል።
ይሁን እንጂ የክፍለ ፖሉሲ በሰ/መ/፣115724 በቀረቡት ጉዲዮች ለስር ፍርድ ቤቶች በቀን 26/06/2007 ዓ/ም በላከው ማስረጃ ስለአደጋው በወቅቱ የተደራጀ የምርመራ መዝገብ እንደላለ፣ በተሽከርካሪው ላይ የቴክኒክ ምርመራ ባለመደረጉ እና ፕላን ባለመነሳቱ በወቅቱ የነበረውን የተሽከርካሪውን ፍጥነት ለማወቅ ያለመቻለን በመግለፁ የሥር ፍርድ ቤቶች በእነዚህ መዛግብት በከሳሾች የተቆጠሩትን ምስክሮች መስማታቸውን የክርክሩ ሂደት በግልጽ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ የስር ከሳሾች በዚህ ረገድ ለይተው ያሰሟቸው ምሰክሮች በወቅቱ ተሳፊሪ የነበሩና መኪናው የነበረውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በጊዜውና በቦታው ሁነው በስሜት ሕዋሳቶቻቸው በአዩት እና በተገነዘቡት መጠን የመሰከሩ መሆናቸውን ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች አረጋግጠዋል።
ከላይ እንደተገለጸው ስለአደጋው የተደራጀ የትራፉክ ማስረጃ የላለ መሆኑና በአሁኗ አመልካች በኩል ቀረበ የተባለው የሰነድ ማስረጃም መኪናው መንገድ ስቶ ገድል መግባቱን የሚያሳይ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን የተደራጀ የትራፉክ ማስረጃ ቢቀርብ እንኳን ማስረጃው የባለሙያ ማስረጃ እንደመሆኑ መጠን ባለሙያው መጨረሻ ላይ የሚደርስበት መደምደሚያ /ግኝት/ ሙያዊ አስተያየት /opinion/ ከመሆን አልፍ ፍሬ ነገር /fact/ መሆን እንደማይችል፣ ኤክስፏርቱ የሚደርስበት የመጨረሻ አስተያየት ከሚኖረው ሙያዊ ዕውቀት አድማስ ከሚታገዝበት መሣሪያና ከመሳሰለት ጋር የተሟላና ሙለ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ /conclusive evidence/ ላሆን ስለማይችል በዓይን ምስክሮች የተነገረን ፍሬ ነገር ለማስተባበል የሚያበቃ አቅም ሉኖረው አይችልም። ይህ ሰበር ችልትም ቀደም ሲል በሰበር መ.ቁ. 14981 የኤክስፏርት ማስረጃ ሙለ ዕምነት ሉጣልበት የሚችል ማስረጃ እንዲልሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ከዚህም ላላ የኤክስፏርት ማስረጃ በማስረጃነት በቀረበ ጊዜ ይበልጥ ተቀባይነት የሚኖረው ከቀጥተኛ ማስረጃ ጋር በተጣጣመ ጊዜ እንጂ ቀጥተኛ ማስረጃውን በሚፃረር ጊዜ የበለጠ ክብደት የሚሰጠው ለቀጥተኛ ማስረጃው ስለሆነ የኤክስፏርት ማስረጃው ተቀባይነት ሉኖረው እንደማይችል መገንዘብ ስለሚቻል የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍሬ ነገሩን በቀጥተኛው ማስረጃ በማጣራት የተጠሪን የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ሲያሽከረክር የነበረው ሹፋር በማሽከርከር ሂደቱ ከመጠን በላይ ፍጥነት ጨምሮ ሲያሽከረክር የነበረ በመሆኑ ጥፊት መፈፀሙን ተረጋግጦ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ከማስረጃ አቀራረብና አመዛዘን መሰረታዊ መርህ ውጪ በሆነ ሁኔታ አመልካች ካሳው በን/ሕ/ቁጥር 599 አግባብ የሚታይበትን ሁኔታ አላስረደም በማለት የደረሱበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል። በመሆኑም በዚህ ረገድ ተጠሪ ያቀረበውን ክርክር ባለመበቀል ተጠሪ በን/ሕ/ቁጥር 599 አግባብ ለጉዲዩ ኃላፉ አለበት ብለናል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡-ከላይ እንደተገለጸው የተጠሪ ሃላፉነት መታየት ያለበት በን/ሕ/ቁጥር 599 አግባብ ነው ከተባለ ይህ ድንጋጌ የካሳ መጠኑ በብር 40,000.00 የማይገደብ መሆኑንና ካሳው ከውል ውጪ ኃላፉነትን በሚገዛው የሕግ ክፍል ስር ባለት ድንጋጌዎች አግባብ መሰላት እንደለአበት ያስገነዝባል።እንዱህ ከሆነ ተጠሪ በሟች ላይ ለደረሰው ጉዲት በንግድ ህግ አንቀጽ 597 ከተደነገገው በላይ ካሣ የመክፈል ሀላፉነት የለብንም በማለት የሚያቀርበው ክርክርም ሆነ የበታች ፍርድ ቤቶች ይህንኑ የተጠሪን ክርክር በመቀበል የሰጡት ዲኝነት የህግ መሰረት ያለው አይደለም። ስለዚህ በን/ሕ/ቁ ህግ ቁጥር 599 ድንጋጌ መሰረት ለመንገደኛው ካሣ የመክፈለ ሀላፉነት ያለበት አጓዥ ለመንገደኛው የሚከፍለው የካሣ መጠን ለመወሰን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091 እና 2092 የተደነገጉት የካሳ አከፊፈል መርሆች አግባብነት አላቸው።
በመሰረቱ ካሳ የሚከፈለው ጉዲት መኖሩ ሲረጋገጥ ሲሆን የካሳ አተማመን ፣መጠንና አከፊፈልን በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2090፣2091፣2092 ፣ 2095 እና በላልች ድንጋጌዎች የተቀመጠ ሲሆን ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለውም ካሳው በተቻለ መጠን ከጉዲቱ ጋር መመጣጠን ያለበት መሆኑን ነው።
ከውል ውጪ ኃላፉነትን በተመለከተ የሚገዙት የፍትሒብሓር ሕጋችን ድንጋጌዎች መንፈስ የጉዲትን ጠቅላላ ባህርይና የካሣ ልክ አተማመን ሁኔታዎችን ያስገነዝቡናል። በዚህም መሰረት ጉዲት በሰው ጥቅም ላይ ችግር የሚያደርስ መሆኑን፣ ይህም ጥቅም ማቴሪያላዊ /በሰው አካል ወይም ንብረት የደረሰ/ ወይም ሞራሉዊ ላሆን እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል። የተጎዲ ሰው ደግሞ መካስ እንዲለበት ያስረዲለ። የካሣውን አተማመን በተመለከተም መጠኑ በተበዲዩ ላይ ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ መመዘን ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2091 ድንጋጌ ያሣያል።
የጉዲት ካሣ ከደረሰው ጉዲት ጋር እኩል ሆኖ ሲመዘንም በተጎጂው ላይ በእርግጠኝነት መድረሱ የታወቀ /actual damage/ ወይም ወደ ፉት ሉደርስ የሚችል ጉዲትን/future damage/ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት የግድ የሚል መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2091/1/ እና 2092 ድንጋጌዎች መንፈስ ያስረዲል። በእነዚህ ድንዲጌዎች የጉዲት ካሣ ሉተመን የሚገባ መሆኑን ሕጉ በግልጽ ከማስቀመጡም በተጨማሪ የአተማመኑ ሥርዓትም እንደጉዲቱ ዓይነትና ማስረጃ አቀራረብ ውስብስብነት ሉለያይ የሚችል መሆኑን የሕጉ መንፈስ ያስገነዝባል፡ ፡በዚህም መሰረት የጉዲት ካሣ መጠን አጥጋቢና በቂ ማስረጃን ወይም ርትዕን መሰረት በማድረግ ሉወሰን የሚገባው መሆኑን የካሣ አከፊፈለን ልክ በሚደነግገው የሕጉ ክፍል የተቀመጡ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ።
በመሆኑም ጉዲት መድረሱ በማስረጃ ከተረጋገጠና ጉዲቱ እርግጠኝነት ያለው መሆኑ ከተረጋገጠ ካሣ መወሰን ከአጠቃላይ የሕጉ ዓላማና ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2091 እና 2092 ድንጋጌዎች መንፈስ አኳያ አግባብነት ያለው ነው።ጉዲቱ መድረሱና የጉዲቱ መጠን ከታወቀ ተጎጂው በጉዲቱ ልክ ሉካስ የሚገባው መሆኑን በአጠቃላይ ከውል ውጪ ኃላፉነትን ከሚገዛው ሕግ አላማ ጋር አንድ ላይ የሚሄድ ነው። ወደያዝነው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች የህፃን የአብስራ ወላጅ አባት የሆኑት ቴዎድሮስ ጌታቸው ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው ሕፃኑ ለወደፉቱ የተቋረጠበትንና ሉቋረጥበት የሚችል ጥቅም ያለው መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም ህፃኑ ለወደፉቱ የተቋረጠበት ጥቅም ምን ያህል እንደሆነ ከወዱሁ በትክክል ማስቀመጥ የማይቻል መሆኑ የክርክሩ ሂደትና ባህርይ ያስገነዝባል። ሟች በወቅቱ የብር 3136.00 ወርሃዊ ደመወዝተኛ የነበሩ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። የስር ፍርድ ቤት ከዚህ ገቢ ውስጥ ለህጻኑ ቀለብ ሉውል ይችላል ያለው መጠን ብር 500.00(አምስት መቶ) ነው። ይህንኑ መጠን ሲይዝም የቀለብ ወጪ ሲታሰብ ግንዛቤ ውስጥ የሚገቡ የልብስ፣ ምግብ፣ትምህርት፣ ጤና እና ላልች ለመልካም አስተዲደግ የሚበጁ ፍላጎቶች ወጪዎችን ሉያካትት እንደሚገባ በውሳኔው ላይ አስፍሯል። በእርግጥ በልጅ ቀለብ አወሳሰን ጊዜ ሉታዩ የሚገባቸው መሰረታዊ ጉዲዩች በህጉ በግልጽ ባይመለከቱም የልጆችን ጥቅም ቀዲሚ ማድረግ፣መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ታሳቢ ማድረግንና መሰረታዊ ፍላጎቶችና ልዩ ወጪዎች ታሳቢ ማድረግን የሚጠይቁ መሆኑን ከቀለብ ባህርይና ከህጉ መሰረታዊ አላማ የምንረዲው ጉዲይ ነው።ወላጆች ለራሳቸው መሰረታዊ ፍላጎቶች ሉያሟለ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባትም የግድ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
ከዚህ አንጻር ጉዲዩን ስንመለከትም የስር ፍርድ ቤት ሟች አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው በወቅቱ ያገኙ ይችለ የነበረውን ወርሃዊ ደመወዝ ለሟቹ ፍላጎቶች ሉወጣ ከሚችለው ወጪና ከሕጻኑ መሰረታዊ ፍላጎቶችና ልዩ ወጪዎች ጋር ለማገናዘብ የሞከረ ቢሆንም ሟቹ በሕይወት ቢኖሩ ኑሮ ለወደፉቱ አቅማቸውን ገንብተውና ተገቢውን ጥረት በማድረግ የተሻሻለ ደመወዝ ላይ ሉደርሱ የሚችለበትን ሁኔታንና ለመሰረታዊ ፍላጎቶች የሚወጣው ወጪ መጠን በየጊዜው ከፍ እያለ የሚሄድበት አጋጣሚ የሚከሰት ስለመሆኑ ማገናዘቡን ግን የውሳኔው ግልባጭ አያሳይም።
ይህም ለህጻኑ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት መልካም አስተዲደግን በተቻለ መጠንና አቅም በሚፈቅደው ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የወጪ መጠን ለመወሰን ግንዛቤ ውስጥ መገባት ያለባቸው አጠቃላይ ከባባዊ ሁኔታዎች ያለመያዛቸውን የሚያሳይ ሁኖ አግኝተናል።
ከዚህ አንጻር ሲታይ ለሕጻን የአብስራ ቴዎድሮስ በወር ሉወጣ የሚችለው የቀለብ ገንዘብ መጠን ብር 500.00(አምስት መቶ) ነው ተብል በስር ፍርድ ቤት ተይዞ የነበረው መነሻ በተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 197 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ስለቀለብ መጠን አወሳሰን የተደነገጉትን ድንጋጌዎችን መሰረታዊ ይዘትና ዓላማ ያላገናዘበ ሁኖ አግኝቶናል።
ሟች በሕይወት ቢኖሩ ኑሮ ከፍ ወደ አለ ደረጃ በመድረስ የተሻለ ደመወዝ ሉያገኙ የሚችለበት ሁኔታ መኖሩና ለህጻኑ የወደፉት ኑሮ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ፍላጎቶች ሉያስወጡ የሚችለት የወጪ መጠን ወደፉት ሉኖር ከሚችለው አጠቃላይ የህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ ቢገባ እንኳ በእርግጠኝነት የቀለቡን መጠን ከወዱሁ ለመወሰን የሚያስችል ነው ለማለት የሚያስደፍር አይደለም። በመሆኑም በዚህ ጉዲይ ለህፃኑ የቀለብ መጠኑን ለመወሰን አስቸጋሪ ሁኔታ ያለ መሆኑ ተገንዝበን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2102 ድንጋጌ መሰረት በርትዕ መወሰኑ ተገቢ ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ለህጻኑ በወር ለወደፉቱ የሚያስፈልገው ወጪ ብር 1000.00(አንድ ሺህ) ነው በማለት ህጻኑ አባቱ በመኪናው አደጋ በሞተበት ጊዜ የአንድ አመት እድሜ የነበረው መሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች በተረጋገጠው መሰረት አስራ ስምንት አመት እስኪሞላው የቀረበት የቀለብ ጥቅም ታስቦ የሚመጣው ውጤት ማለትም ብር1000.00x12x17= 204,000.00(ሁለት መቶ አራት ሺህ) ለአመልካች ሉከፈላቸው የሚገባ ሆኖ አግኝተናል።
የቀለቡን አከፊፈል በተመለከተም አመልካች የህጻኑ ወላጅ እናትና ሞግዚት በመሆናቸው ተገቢውን ግዳታቸውን እንደሚወጡና ለተሻለ ጥቅምም ገንዘቡን ሉያወለ የሚችለበት ነባራዊ ሁኔታዎች መኖራቸውን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባትና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2154 ድንጋጌ ለፍርድ ቤቶች የሚሰጠውን ስልጣን በማገናዘብ በአንድ ጊዜ ተጠቃልል እንዱከፈል ማድረጉ ተገቢ ሁኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለልም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪን በን/ሕ/ቁጥር 599 አግባብ ተጠቂነት የለበትም በማለት የካሳ መጠኑን ብር 40,000.00(አርባ ሺህ ብር) አድርገው የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለተገኘ ተከታዩን ወሰነናል።
ውሣኔ
የአመልካች ሞግዚት የሆኑት ህጻን የአብስራ ቴዎድሮስ በደረሰው የሞት ጉዲት ምክንያት የጉዲት ከሳ በን/ሕ/ቁጥር 599 አግባብ ሉከፈለው ይገባል ብለናል።
ለህፃኑ ሉከፈለው የሚገባው የጉዲት ከሳ መጠን ብር 204,000.00(ሁለት መቶ አራት ሺህ) ሁኖ አካፊፈለም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2154 ድንጋጌ አግባብ በአንድ ጊዜ ላሆን ይገባል ብለናል።
አመልካች በህጻኑ ስም የባንክ ሂሳብ ከፍተው ገንዘቡን የሞግዚትነት ስልጣን በሚፈቅደው አካሄድ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዱያውለም ብለናል።
የኢትዩጵያ መድን ድርጅት በሰጠው የመድን ሽፊን እስከ ብር 40,000.00(አርባ ሺህ) ለመሸፈን የተስማማ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ በመሆኑ ብር 40,000.00(አርባ ሺህ ብር) ተጠሪና የኢትዩጵያ መድን ድርጅት ባልተነጣጣለ ሃላፉነት ሉከፍለ ይገባል ብለናል። ቀሪውን ብር 164,000.00(አንድ መቶ ስልሳ አራት ሺህ) ደግሞ ተጠሪ ብቻውን ሉከፍል ይገባል ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ኪሳራና የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.