በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2472 ላይ ገንዘብ ሰለመከፈለ ማሰረጃን በተመለከተ የተደነገገው ፤ ከብድር ውጭ ለሆነ ግንኙነት ከተከፈለ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚነት የላለው ሰለመሆኑ ወ/ሮ አስቴር አርአያ እና ወ/ሮ አወጣሽ መሐሪ 19/11/ 2008ዓ.ም 216 XVII 47. በአንድ ሰነድ ላይ ያለን ፊርማ በቴክኒክ ምርመራ የማን እንደሆነ ለማረጋገጥ ባልተቻለ ጊዜ ፊርማው ሲፈረም የነበሩ ምስክሮችን ቃል በመስማትና በላልች ማስረጃዎች ፊርማው የማን እንደሆነ በመመዘን ማረጋገጥ የሚቻል ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 2472(1)
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 29ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አቶ ኤልያስ ስሜ ተሰማ …………. አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዘነበች ተመስገን ጫካ………….. አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 08/09/2005 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ያቀረብኩትን የፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን መጋቢት 15/2007 ዓ.ም ያፀናው በመሆኑ መሰታዊ ስህተት ያለበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
ጉዲዩ የብድር ውልን የሚመለከት ነው በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት ተጠሪ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ። የክሱ ይዘት ጥቅምት 28/2004 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል አመልካች ነሐሴ 30/2004 ዓ.ም ለመመለስ ብር 200,000 ተበድረው ወስደው ሉመልሱ አልቻለም ስለዚሀ ዋናውን ገንዘብ፣ ወለድ፣ ወጪና ኪሳራ እንዱከፍለኝ የሚል ሲሆን አመልካች በሰጡት መልስ ከተጠሪ ጋር ገንዘብ ሉያስበድር የሚችል ትውውቅ የለንም አመልካች በመ/ በተጠሪ ባለቤት ክስ የቀረበባት ወ/ሮ መስከረም አሰግድ ሰፉ ቦታ ገዝተን አርት ጋለሪ መስራት በመፈለጋችን በኮሚሽን ሰራተኞች አማካኝነት በተጠሪ ባለቤት አቶ ደጁ አበራ ስም የተመዘገበውን ለመግዛት ተስማምተን በተፈራረምነው የቤት ሽያጭ ውል ላይ ግን በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት የተገዛው ቢሆንም በውልና ማስረጃ በተደረገው የሽያጭ ውል የተጻፈው ሲሆን ከዚህ በኋላ የከረረ ፀብ ውስጥ ነን ውልቹ በአንድ ኮምፒውተር መጻፊቸው ሙለ ፊርማዬ በሰነድ ላይ ያለው አይደለም፡ ብፈርም ኖሮ ሙለ ስሜን ከጏን እጽፍ ነበር አጭር ፊርማዬን ለማስመሰል የተሞከረ ነው። ፍርድ ቤቱ ማጣራት ይችላል ስለሆነም ክሱ በሀሰት የቀረበብኝ በመሆኑ ኪሳራ ተከፍል በነፃ ልሰናበት ብለዋል። ፍርድ ቤቱ የአመልካች ፊርማ በፋደራል ፖሉስ ፍረንሲክ ምርመራ መምሪያ እንዱጣራ ተደርጏ ምስክሮችን ሰምቷል። በአመልካች በብድር ውለ ሉገደደ የሚችለት የብድር ውለን ከፈፀሙ ነው። በጽሁፍ የተደረገውን የብድር ውል በሰው ማስረጃ ማስተባበል አይቻልም።
አመልካች የብድር ውለን አልፈፀምኩም የሚለት ፊርማውን በመካድ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፊርማው እንዱመረመር አዞ በአመልካች የተፈረመ መሆኑ ተረጋግጧል። በመሆኑም በተጠሪና በአመልካች መካከል የብድር ውል መደረጉን የሚያረጋግጥ ሲሆን በውለ ላይ ያለ ምስክሮቹም የብድር ውለ መደረጉን አረጋግጠዋል። ስለሆነም ክስ የቀረበበትን ገንዘብ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ከነሐሴ 30 ቀን 2004 ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ እንዱሁም ወጪና ኪሳራ ብር 4850 ለቴምብርና ቀረጥ ብር 10 ለጥብቅና አገልግልት ብር 15,000 እንዱከፍል ብሎል።
አመልካች በዚሀ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተው የፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስቀርቦ ከመረመረ በኋላ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንን በመቃወም መሰረታዊ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ሲሆን ይዘቱም ሙለ ፊርማዬ በሰነደ ላይ ያለው አይደለም። አጭር ፊርማ ስፈርም ስሜን ከጏን አልጽፍም ስለዚሀ አጭር ፊርማዬን ለማስመሰል የተደረገ ጥረት መኖሩን ሰነደ ያስረዲል በፍ/ሕ/ቁ 1728/1/ ፊርማ በውለ ተገዲጅ የሆነ ሰው እጅ መጻፍ እንዲለበት የተደነገገ በመሆኑና የሰነድ ምርመራ ውጤትም የመጨረሻ ማስረጃ ባለመሆኑ ባልተሟላ ፊርማ የተወሰነ በመሆኑ መሰረታዊ ስህተት የተፈፀመበት ነው። በሰነደ ተዓማኒነት ላይ የተነሱትን ክርክሮች የስር ፍርድ ቤት ሳይመረምር ማለፈ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 182/2/ መሰረት የውል ስምምነቱ አጠራጣሪ በሚሆንበት ጊዜ ተገዲጅ የሆነውን በሚጠቅም መልኩ መታየት እንዲለበት ከተደነገገው አኳያ ሳይታይ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ስህተት የተፈፀመበት ነው። የቀረቡት ምስክሮች አመልካችና ተጠሪ የብድር ውለን አለመፈፀማቸውን፣ አመልካችም ከተጠሪ ገንዘብ መበደር ደረጃ የሚያደርስ ግንኙነት የላላቸው መሆኑን ይግባኙን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ከቀረበው ክርክርና ማስረጃ ውጭ ስለጭብጥ አመሰራረት የተደነገገውን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል የሚል ነው።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ የአመልከች ፊርማ የለም እየተባለ በግራ ቀኙ መካከል የብድር ውል አለ መባለንና ላልች ተያያዥ ጉዲዮችን ለመመርመር ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በሰጡት መልስ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የብድር ውል እና የሽያጭ ውል በተመሳሳይ ቀን ተደርጓል ምስክሮቹም አንድ ናቸው።ፍርድ ቤቱም እነዚህኑ አስቀርቦ ሰምቷል። አመልካች እኔ ስፈርም ከጏኑ ስሜን እጽፊለሁ ብለው ክደው ቢከራከሩም ፊርማው በፍረንሲክ ተመርምሮ ፊርማቸው መሆኑ ተረጋግጧል ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ በውለ ላይ የተመለከቱትን ምስክሮችንም ሰምቶ አረጋግጧል። ይህንን አላስተባበለም አመልካች ከተጠሪ የተሻለ እውቀት ያላቸው ባለሙያ ናቸው የውል ክፍለ ሳያነቡላቸው እና ሳያረጋግጡ የሚፈርሙ አይደለም ፊርማው የአመልካች መሆኑ እስከተረጋገጠ ሙለ ፊርማ እና አጭር ፊርማዬ በማለት ከኃላፉነት ማምለጥ አይችለም ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ይጽናልኝ ብለዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አንጻር አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምረነዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘበ የሚቻለው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም ተደርጓል የተባለውን /ሁለት መቶ ሺ ብር/ ብድር ውል ላይ አመልካች ከተጠሪ ገንዘብ ለማስበደር የሚያደርስ ትውውቅ የለንም በውለ ላይ የተመለከተው ፊርማ የኔ አይደለም ልገደድ አይገባም ሲለ ተጠሪ በመካከላችን በነበረው መኖርያ ቤት ሽያጭ ውል ከአጠቃላይ /አንድ መቶ ሺ ብር ከፍለውኝ/ ቀሪውን /ሁለት መቶ ሺ ብር/ በብድር ውል ለነሐሴ 30/2004 ዓ.ም ለመመለስ ተስማምተናል የሚል ነው። በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ውል አለ ለማለት ከሚያስችለት ነጥቦች አንደ ደግሞ በፍ/ሕ/ቁ 1728 እንደተመለከተው በውለ ተገዲጅ የሆነው ሰው እጅ የተጻፈ ፊርማ መኖር ነው። በዚሀ ጉዲይ ደግሞ ፊርማው የተካደ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። እዚህ ላይ ተበዲሪው በፍትሐብሕር ህግ ቁ. 2472/1/ መሰረት የብድር ውለን ለማስረዲት በቀረበው የሰነድ ማስረጃ ላይ ያለው ፊርማ የእኔ አይደለም በማለት የካደ በሆነ ጊዜ ፊርማው የተበዲሪ መሆኑን ለማረጋገጥ ምን ዓይነት ማስረጃ ተቀባይነት አለው የሚለው በሰነድ ላይ ያለ ፊርማዎችን ለማረጋገጥ /Authenticate/ ተቀባይነት ያላቸው ማስረጃዎች መመልከቱ አስፈላጊ ነው።
በሰነድ ላይ ያለ ፊርማ በተካደ ጊዜ ፊርማውን የማረጋገጫው የመጀመሪያው መንገድ የቴክኒክ ምርመራ እንዱደረግ ማድረግ ነው። ሆኖም ፊርማው በቴክኒክ ምርመራ የማን እንደሆነ ለማረጋገጥ ባልተቻለ ጊዜ ፊርማው ሲፈረም የነበሩ ምስክሮችን ቃል በመስማትና በላልች ማስረጃዎች ፊርማው የማን እንደሆነ በመመዘን ማረጋገጥ እንደሚቻል ከማስረጃ ምዘና ጠቅላላ መርሆዎች ለመረዲት ይቻላል። የስር ፍርድ ቤት አመልካች ፊርማውን በመካዲቸው ምክንያት ለፋደራል ፖሉስ ፍረንሲክ ምርመራ መምሪያ በኩል የቴክኒክ ምርመራ እንዱደረግ አዞ የአመልካች ፊርማ ስለመሆኑ የተረጋገጠ መሆኑን ገልጿል ፍርድ ቤቱ በአመልካች የተፈረመ መሆኑ በቴክኒክ ምርመራ መረጋገጡ ሳያበቃ ሁለተኛውን አማራጭም በመከተልም በውለ ላይ ያለትን ምስክሮች በመስማት ፊርማው በአመልካች የተፈረመ ስለመሆኑ ፍሬ ነገርንና ማስረጃን በሚመዝንበት ወቅት አረጋግጧል። አመልካች ፊርማው አጭር እና ረጅም ሲሆን የሚፈጥሯቸውን ልዩነቶች በመግለጽ ከመከራከር ውጭ ፊርማውን የፈረመው በልላ ህጋዊ ተጽፅኖ ወይም ግዳታ ምክንያቶች መሆኑን መሰረት በማድረግ አልተከራከረም። ፊርማ ሀሳብን ወይም ፈቃድ መስጠትን የሚረጋገጥበት በመሆኑ በአመልካች የተፈረመ መሆኑ ከተረጋገጠ አጭር እና ረጅም መሆኑ ደግሞ በውጤቱ ላይ ልዩነት አያመጣም። በልላው በብድር ውለ ስምምነት ላይ የመክፈያ ጊዜው ተወስኖ የተቀመጠ በመሆኑ አመልካች በፍ/ሕ/ቁ 2482/2/ /3/ መሰረት የመመለሻ ጊዜው ከማለፈ በፉት የመክፈል ግዳታ ያለበት በመሆኑ አለመክፈለ እስከተረጋገጠ ጊዜ ድረስ የብድሩን ገንዘብ ህጋዊ ወለድ ጋር የመክፈል ግዳታ አለበት።
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የብድር ውል አለ በማለት በውለ ላይ የተመለከተውን ገንዘብ ከነወለደ አመልካች እንዱከፍል በማለት የደረሱበት ድምዲሜ መሰረታዊ ስህተት ያልተፈፀመበት በመሆኑ ተከታዩ ተወሰነ።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 08/09/2005 እና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
አመልካችና ተጠሪ በዚህ ችልት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
ትእዛዝ የስር ፍርድ ቤት በአፈ/መ/ የጀመረው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በ17/02/2008 ዓ.ም የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ
ሩ/ለ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.