No summary available.
ሐምል 19 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች- ወ/ሮ አስቴር አርአያ ተጠሪ- ወ/ሮ አወጣሽ መሐሪ - ጠበቃ ሐየልም በቀለ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የተጀመረው የአሁን አመልካች ሰኔ 9 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ያቀረቡት ክስ ነው።
የክሱ ይዘት፡- ባላቸው የጥብቅና ሙያ ተከሳሽ ከባለቤታቸው ከአቶ ወርቁ ወ/ማርቆስ ጋር የነበረባቸውን የፍች ክርክር እና የንብረት ክፍፍል ጉዲይ እንዱከታተለላቸው በመፈለግ ታህሳስ 19 ቀን 1999 ዓ.ም በተደረገ የጥብቅና አገልግልት ውል በንብረት ክፍፍለ ተከሳሽ ከሚደርሳቸው ድርሻ 10% (አስር በመቶ) ለመክፈል ተስማምተው ስራውን በመጀመር የፍች ውሳኔ በማሰጠት፤
የንብረት ክፍፍል አቤቱታ በማቅርብ እና በአፈፃፀም ጉዲዩ እስከ ፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት ሁለት ጊዜ ደርሶ ሲመለስ ተከታትለው የተከሳሽን መብት ለማስከበር ከ8 ዓመት በላይ ስራውን በአግባቡ በመስራት ግዳታቸውን እንደተወጡ፤ ተከሳሽ መጋቢት 25/2006 ዓ.ም ባደረጉት የዕርቅ ስምምነት ድርሻቸውን ብር 11,000,000.00 (አስራ አንድ ሚሉዮን) በመቀበል ክርክሮችን በሙለ እንዲቌረጡ፤ ከዚህ በኋላ ግራ ቀኙ ባላቸው የአገልግልት ውል ስምምነት መሰረት ክፍያ እንዱፈፅሙ እና መዝገቦችን እንዱረከቡ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ስላልሆኑ በውለ መሰረት ካገኙት ገንዘብ አስር በመቶ ብር 1,100,000.00 (አንድ ሚሉዮን አንድ መቶ ሺህ) ከነወለደ እንዱከፍለ እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪ በሰጡት መልስ ከከሳሽ ጋር የጥብቅና አገልግልት ውል እንደነበራቸው፤ በውለ እንደተመለከተውና በክሱም እንዲልካደት ብር 65,000.00 (ስድሳ አምስት ሺህ) የወሰደ በመሆኑ ይህን ሳይቀንሱ የጠየቁት ክፍያ አግባብነት እንደላለው፤ እንዱሁም ከሳሽ በገቡት ግዳታ መሰረት ባለመወጣታቸው ጉዲዩ ረጅም ጊዜ ስለተጓተተና በአግባቡ እንዱከታተለ ሲጠየቁም ግዳታዬን ተወጥቻለሁ በማለት ድክመንቶችን ጥለው በመሄዲቸው ላላ ጠበቃ በመቅጠር ክርክር የቀጠለ መሆኑን፤ ከዚያ በኋላ ብር 11,000,000.00 (አስራ አንድ ሚሉዮን) በመውሰድ ጉዲዩን በዕርቅ እንደጨረሱት፤ ተከሳሽም ከሳሽ በውለ መሰረት ጉዲዩን ሳይጨርሱ ቢያቌርጡም እስከሰሩበት ጊዜ ሉከፈላቸው የሚገባ መሆኑን በማመን ከሳሽ ብር 800,000.00 (ስምንት መቶ ሺህ) ጠይቀው በመጨረሻ ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) ለመክፈል በመስማማት ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ቅርንጫፍ በመሄድ ተከሳሽ 3340011 ከሆነ የቁጠባ ሂሳባቸው ሚያዝያ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ ሃምስ ሺህ) ወጪ አድርገው ከሳሽ በዚያው ባንክ ሂሳብ እንዱከፍቱ ተደርጎ ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ) ወደ ሂሳባቸው እንዱተላለፈላቸው የተደረገ ሲሆን ቀሪውን ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) በእጃቸው እንደተሰጡ፤ በዚህ መልኩ ተከፍሎቸው እያለ ከሳሽ አልተከፈለኝም በማለት የጠየቁት አግባብነት እንደላለው፤ በውለ መሰረት ከተከሳሽ ድርሻ 10% (አስር በመቶ) ለከሳሽ ሉከፈል የሚገባው ጉዲዩን ተከታትለው አስጨርሰው ንብረት ሲያስረክቡ ብቻ እንደሆነ በመግለፅ ከሳሽ በአጠቃላይ ብር 815,000.00 (ስምንት መቶ አስራ አምስት ሺህ) የተቀበለ በመሆኑ እና ቀሪውም ሉከፈላቸው የማይገባ በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክረዋል።
ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከሳሽ ብር 65,000.00 (ስድሳ አምስት ሺህ) አስቀድመው የከፈለ መሆኑን ለማስረዲት ያቀረቧቸው ምስክር ተከሳሽ ገንዘቡን ለከሳሽ ከፍያለሁ በማለት በስልክ ሲነጋገሩ መስማታቸውን ከሚገልፁ በቀር ስለመክፈላቸው ላላ ማስረጃ ስላላቀረቡ ተከሳሽ ከሚጠበቅባቸው ክፍያ ውስጥ ብር 65,000.00 (ስድሳ አምስት ሺህ) እንዱከፍለ፤ በባንክ ቀርበው ክፍያ መፈፀሙን በተመለከተ የቀረበውን ክርክር ለማጣራት ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ቅርንጫፍ ስለጉዲዩ ማብራሪያ እንዱሰጥ ጠይቆ ባንኩ በቁጥር ልደ/ዲአ/026/1/15 በቀን 18/5/2007 ዓ.ም በሰጠው ምላሽ ተከሳሽ ሚያዝያ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) ከሂሳባቸው እዲወጡ እና በዕለቱም በከሳሽ ስም ሂሳብ ተከፍቶ ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ) ወደ ሂሳባቸው ገቢ እንደተደረገ መግለፁን፤ ይህም የተከሳሽን ክርክር የሚያጠናክር አስረጅ ሆኖ መገኘቱን፤ ከዚህም ላላ ገንዘቡ በከሳሽ ሂሳብ ገቢ መደረጉን እና ቀሪው ገንዘብ በእጃቸው የተሰጣቸው መሆኑን ያውቃለ ተብለው በእለቱ የገንዘብ ልውውጡን የሰሩት የባንክ ባለሙያ አቶ ደረጀ ካሳ ቀርበው በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም ተከሳሽ በባንኩ ቀርበው ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) ከሂሳባቸው አውጥተው ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ) በዕለቱ ወደተከፈተው የከሳሽ ሂሳብ ገቢ እንደተደረገና ብር 150,000.00 (መቶ ሃምሳ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ለከሳሽ የተሰጠ መሆኑን እንደሚያውቁ መመስከራቸውን፤ ስለሆነም ባንኩ በሰጠው መግለጫ እና ሂሳቡን የሰሩት ባለሙያ ከሰጡት የምስክርነት ቃል ተከሳሽ በአጠቃላይ ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ ሃምስ ሺህ) የከፈለ መሆኑ በመረጋገጡ ይኸው ገንዘብ ከሳሽ ከጠየቁት ክፍያ ሉቀነስ እንደሚገባ፤ በልላ በኩል ከሳሽ ጉዲዩን ተከታትለው ያላስጨረሱ በመሆኑ ቀሪው ክፍያ ሉከፈላቸው እንደማይገባ ተከሳሽ ቢከራከሩም ፍርድ ቤቱ ክርክር የተደረገባቸውን መዝገቦች በትዕዛዝ አስቀርቦ እንደተመለከተው ከሳሽ በየቀጠሮው ይከራከሩ እንደነበር እና ከሳሽ ውለን ከፈረሙበት 1999ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ለ 7 ዓመታት ተከሳሽን በመወከል የተከራከሩ መሆኑ ስለተረጋገጠ ተከሳሽ በውለ መሰረት አገልግልት አልሰጡኝም በማለት የሚያቀርቡት መከራከሪያ ተቀባይነት እንደላለው፤
ስለሆነም ቀሪውን ክፍያ ብር 285,000.00 (ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ሉከፍለ ይገባል ብሎል። በአጠቃላይ ተከሳሽ ብር 285,000.00 + ብር 65,000.00 = ብር 350,000.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ተከፍል እስኪጠናቀቅ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ለከሳሽ እንዱከፍለ፤ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን እንዱቻቻለ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኙ የቀረበለት የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዟል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን በመቃወም ነው። አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተጠሪ ለአመልካች ብር 750.000.00 (ሰባት መቶ ሃምስ ሺህ) ስለመክፈላቸው በፍ/ብ/ህ/ቁ/2472(2) እና (3) በተደነገገው መሰረት ላቀርብ በሚገባው ማስረጃ ማለትም ደረሰኝ ወይም የሰነድ ማስረጃ አቅርበው ሳያረጋገጡ ይኸው ገንዘብ መከፈለ ተረጋግጧል ተብል መወሰኑ ስህተት በመሆኑ ታርሞ ገንዘቡን ከነወለደ እንዱከፍለ እንዱወሰን፤ እንዱሁም የወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብቴ ሉጠበቅ ሲገባ ይቻቻለ ተብል የተሰጠው ውሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉን ድንጋጌ የሚቃረን በመሆኑ ዝርዝር የማቅረብ መብቴ ተጠብቆ ይወሰንልኝ ብለዋል።
አቤቱታው ተመርምሮ ለሰበር ችልት እንዱቀርብና ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት የተደረገ ሲሆን ተጠሪ በሰጡት መልስ አመልካች ቀደም ሲል የተከፈላቸውን ብር 750.000.00 (ሰባት መቶ ሃምስ ሺህ) ሙያዊ ኃላፉነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለሁለተኛ ጊዜ እንዱከፈላቸው ክስ ማቅረባቸው የሚያሳዝን እና የሙያውን ክብር የሚያዋርድ በመሆኑ፤ ወጪና ኪሳራን በተመለከተ ያቀረቡት ጥያቄም እንደነገሩ ሁኔታ ለመወሰን ፍርድ ቤቱ ሙለ ስልጣን ያለው በመሆኑና በጉዲዩም ረችና ተረቺ ባለመኖሩ ይኸው ግምት ውስጥ ገብቶ ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ ተብል መወሰኑ ምንም ስህተት ስላልተፈፀመበት ቅሬታው ውድቅ እንዱደረግ ተከራክረዋል። አመልካችም ክርክራቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከላይ ባጭሩ የገለፅነው የጉዲዩን አመጣጥ እና በሰበር የተደረገውን ክርክር ሲሆን ክርክሩን ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌ ጋር በማያያዝ መርምረናል።
እንደመረመርነው የአመልካች መሰረታዊ ክርክር ብር 750.000.00 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) ስለመከፈለ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባልቀረበበት መከፈለ ተረጋግጧል ተብል በስር ፍርድ ቤት መወሰኑን የሚመለከት ነው። በመሰረቱ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበትን የመጨረሻ ውሣኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ስልጣን እንዲለው በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ሀ/ እንዱሁም በፋዳራለ ፍርድ ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 ሥር ተደንግጓል። ነገር ግን የሰበር ችልቱ የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን ጥንካሬ በመመዘንና በመመርመር ውሣኔ እንዱሰጥ የቀረበው አቤቱታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ለማረም ከላይ በተጠቀሱት ህጎች ለችልቱ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፉነት የተከተለ ባለመሆኑ የምንቀበለው አይሆንም።
በልላም በኩል አመልካች ገንዘቡ ስለመከፈለ በፍ/ብ/ህ/ቁ/2472(2) እና (3) በተደነገገው መሰረት ሉረጋገጥ እንደሚገባ የተከራከሩ ሲሆን ለክርክሩ ምክንያት የሆነው የጥብቅና አገልግልት ውል እንጂ የብድር ውል ባለመሆኑና የፍ/ብ/ህ/ቁ 2472 ከብድር ውል ውጪ በሆነ ግንኙነት ከተከፈለ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ተፈፃሚ የሚሆንበት አግባብ የላለ ስለመሆኑ ይኸው ሰበር ችልት በሰ/መ/ እና ላልችም ተመሳሳይ መዛግብት የሰጠው አስገዲጅ ትርጉም ለተያዘውም ጉዲይ ተፈፃሚነት እንደሚኖረው ከአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2 ድንጋጌ መረዲት ስለሚቻል በዚህም ረገድ የቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
በአጠቃላይ ፍሬ ነገሩን ለማጣራት እና ማስረጃ ለመመዘን በህግ ስልጣኑ የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች ዲኝነት ከተጠየቀበት ገንዘብ ውስጥ ብር 750.000.00 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) ለአመልካች አስቀድሞ ስለመከፈለ በማስረጃ በማረጋገጥ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ተገንዝበናል። አግባብነት እና ተቀባይነት ባለው ማስረጃ የተረጋገጠው ገንዘቡ አስቀድሞ መከፈለ ከሆነ ደግሞ ይኸው ገንዘብ አመልካች ከጠየቁት ክፍያ ሉቀነስ እንደሚገባ በመወሰኑ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚያሰኝ አይሆንም።
የስር ፍርድ ቤት ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ በማለት ያሳለፈው ውሳኔም የስነ ስርዓት ህጉን የተከተለ አይደለም በሚል ውሳኔው እንዱታረም ቅሬታ ቀርቧል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 462 እንደተደነገገው በክርክር ምክንያት የወጣን ወጭና ኪሣራ ማን እንደሚከፍልና ምን ያህል እንደሚከፍል ፍ/ቤቱ በመሰለው ሉወስን እንዱችል ፍቅድ ስልጣን ተሰጥቶታል ። ፍርድ ቤቱ በህጉ የተሰጠውን ፍቅድ ስልጣን ተጠቅሞ ሲወስን ከግምት ውስጥ ሉገቡ የሚገባቸውን ጉዲዩች ሁለ ተመልክቶና አረጋግጦ ሉወስን እንደሚገባ በህጉ ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች እንዱከፈላቸው ከጠየቁት ገንዘብ ከፉለን አስቀድመው ስለወሰደ በሙለ ሉከፈላቸው እንደማይገባ፤ በአንፃሩ ተጠሪ ብር 350,000.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ከነወለደ እንዱከፍለ በመወሰኑ ባለዕዲ መሆናቸውን፤ አመልካች በራሳቸው ተጠሪ ደግሞ በጠበቃ ተወክለው መከራከራቸውን እና የነገሩን አጠቃላይ ሁኔታ በማየት ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ ተብል መወሰኑ የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች ያሳለፈት ውሳኔ እና ትዕዛዝ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ/ 153169 ሰኔ 12 ቀን 2007 ዓ.ም ያሳለፈው ውሳኔና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ ሐምል 27/2008 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/348(1) መሰረት ፀንቷል።
በተጠሪ ቤት ላይ በዚህ ፍርድ ቤት የካቲት 16 ቀን 2008 ዓ.ም የተላለፈው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ለሚመለከታቸው ሁለ ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ስለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
No topics extracted.