የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በይዞታው ስር የሚገኙትን የመንግስት ቤቶች ለማከራየት የሚያደርጋቸው ውልች ያልተጠበቁ ምክንያቶች ካልተከሰቱ እና በተለይም ደግሞ ውለን ለማቋረጥ የሚያስችል በተከራይ ወገን በኩል ጥፊት ተፈጽሟል ካልተባለ በቀር በድርጅቱና በተከራዮች መካከል የሚደረጉ ውልች በየዓመቱ እየታደሱ የሚቆዩ ስለመሆኑ፣ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር 555/2000 አንቀጽ 6/1/
No summary available.
ግንቦት 22 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ መህቡብ ከድር -ጠበቃ ሂሩት ሂላይ ቀረቡ ተጠሪ፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ -ነ/ፈጅ መብራቱ ግርማይ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ክሳቸውን ውድቅ በማድረግ ፍርድ ቤቱ በመዝገብ በ12/07/2006 ዓ.ም. የሰጠው እና በይግባኝ ሰሚው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ05/02/2007 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
አመልካች በ02/01/2006 ዓ.ም. አዘጋጅተው ያቀረቡት ክስ አጭር ይዘት በአራዲ ክፍለ ከተማ በወረዲ 2 የሚገኝ ቁጥሩ 507 የሆነውን የንግድ ቤት ከ18/12/2004 ዓ.ም. ጀምሮ ከተጠሪ ተከራይተው ሲገለገለበት ከቆዩ በኃላ የውለ ዘመን ሲጠናቀቅ ውለን ለማደስ አመልካች በ17/12/2005 ዓ.ም. ብር 246.00 የቴምብር ቀረጥ፣እንዱሁም እስከ ጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም.
ድረስ ያለውን የሁለት ወር ኪራይ የከፈለ መሆኑን፣በዚህ ሁኔታ ተጠሪ ውለን አራዝሞ ኪራይ ከተቀበላቸው በኃላ በ28/12/2005 ዓ.ም.በተጻፈ ደብዲቤ ውለን ከ30/12/2005 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲቋረጠ የገለጸላቸው መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ ተጠሪ የውል ማደሻ እና የወደፉቱን ኪራይ ከተቀበለ በኃላ የፈጸመው የውል ማቋረጥ ተግባር ተገቢ አይደለም ተብል ውል እንዱቀጥል ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት የተጠየቀበት ሲሆን ተጠሪው በበኩለ በ18/03/2006 ዓ.ም. በሰጠው መልስ በ18/12/2004 ዓ.ም. የተደረገው የኪራይ ውል የሚቆየው ለአንድ ዓመት ብቻ መሆኑን፣ውለ ከዚህ በኃላ ላለው ጊዜ የታደሰ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን፣ የውለ ዘመን ሲጠናቀቅ ተጠሪው ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውለን ለማቋረጥ የሚችል መሆኑን፣የቴምብር ቀረጥ የተከፈለውም ውለን ለማራዘም ታስቦ ነው የሚያሰኝ አለመሆኑን እና አመልካች የቤቱን ኪራይ የከፈለት በራሳቸው አነሳሽነት በመሆኑ የኪራዩ መከፈል የውለን መታደስ የሚያረጋግጥ አለመሆኑን ገልጾ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም ክሱን ከሰማ በኃላ የግራ ቀኙን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ የመጀመሪያው ውል የጊዜ ቆይታ የተጠናቀቀ መሆኑን፣ውለ የታደሰ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን፣የውለ ዘመን ካበቃ በኃላ የሁለት ወር ኪራይ ተከፍል መገኘቱም ውለ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ የሚያስቆጥር መሆኑን እና ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገን ውል ደግሞ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2966 በተመለከተው መሰረት አከራዩ ማስጠንቀቀቂያ በመስጠት ማቋረጥ የሚችል መሆኑን ገልጾ የኪራይ ውለ እንዱቀጥል እንዱወሰን የቀረበውን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሰጥቷል።አመልካች ለዚህ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ የኪራይ ውል ማደሻ ቅጽ ተሞልቶ የቴምብር ቀረጥ ክፍያ ከተፈጸመ በኃላ ጥፊት ተፈጽሟል ሳይባል ቀደም ብል የነበረው የኪራይ ውል እንዱታደስ አመልካች ካቀረቡት ክስ አንጻር የስር ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን በአግባቡ ያስተናገደ መሆን አለመሆኑን ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ክርክሩ የተስተናገደበትን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገብ በማስቀረብ ጭምር አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዲዩ ከተያዘው ነጥብ አንጻር መርመረናል።
በዚህም መሰረት በ18/12/2004 ዓ.ም. ለአንድ ዓመት ተደርጎ የነበረው የኪራይ ውል የቆይታ ጊዜ ያለቀ መሆኑ ያላከራከረ ሲሆን አመልካች ውለ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ታድሷል በማለት ቢከራከሩም ውለ በዚህ አግባብ የታደሰ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ ስለመኖሩ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም።ተጠሪው በ28/12/2005 ዓ.ም. ለአመልካች በጻፈው የውል ማቋረጫ ደብዲቤ ላይ ውለን ማቋረጡን ከመግለጽ በቀር ውለን ያቋረጠበትን ምክንያት አልገለጸም።ተጠሪው በስር ፍርድ ቤት በሰጠው የጽሁፍ መልስ የውለ ዘመን ሲያልቅ ውለን የማቋረጥ መብት አለን በማለት የተከራከረ ሲሆን የስር ፍርድ ቤትም የአመልካችን ክስ ውድቅ ያደረገው የውለ ዘመን ካበቃ በኃላ የሁለት ወር ኪራይ ተከፍል መገኘቱ ውለ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ የሚያስቆጥር መሆኑን እና ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገን ውል ደግሞ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2966 መሰረት አከራዩ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማቋረጥ የሚቻል መሆኑን በመግለጽ ነው።ተጠሪው በሰበር ደረጃ በሰጠው መልስ የውለን አንቀጽ 10 (2) እና (4) ድንጋጌዎች ጠቅሶ የተከራከረ ሲሆን እነዚህ ድንጋጌዎችም የውለ ዘመን ሲያልቅ ውለ የሚቋረጥ መሆኑን እና የውለ ዘመን ያላለቀ በሆነ ጊዜ ደግሞ አንደኛው ወገን በሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ውለ ሉቋረጥ የሚችል መሆኑን የሚያመለክቱ ናቸው።
በመሰረቱ ቤቱ በኪራይ የተሰጠው ለንግድ ዓላማ ሲሆን ከተጠሪ ድርጅት ስልጣንና ተግባር መካከል አንደ በይዞታው ስር የሚገኙትን የመንግስት ቤቶች ማከራየት እና ኪራይ መሰብሰብ ስለመሆኑ ኤጀንሲውን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 555/2000 አንቀጽ 6 (1) ስር ተመልክቷል።ይህም ውለን ለማቋረጥ የሚያስችለ ያልተጠበቁ ምክንያቶች ካልተከሰቱ እና በተለይ ደግሞ ውለን ለማቋረጥ የሚያስችል በተከራይ ወገን በኩል ጥፊት ተፈጽሟል ካልተባለ በቀር በተጠሪው ድርጅት እና በተከራዮች መካከል የሚደረጉ ውልች በየዓመቱ እየታደሱ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆዩ መሆኑን መገንዘብ የሚያስችል ነው።በመሆኑም በውለ ውስጥ የተመለከቱት ከላይ የተጠቀሱት የውል ማቋረጫ ድንጋጌዎች፣እንዱሁም ተጠሪው በሕግ ያለው የመዋዋል መብትና ነጻነት ለኤጀንሲው በሕግ ከተሰጠው ስልጣን እና ተግባር አንጻር በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን የውለ ዘመን ሲያልቅ ያለማስጠንቀቂያ፣እንዱሁም የውለ ዘመን ያላለቀ በሆነ ጊዜ ደግሞ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ለተጠሪው ያለተገቢ እና ሕጋዊ ምክንያት የኪራይ ውልችን ለማቋረጥ መብት እንደሚሰጡት ተደርገው ሉተረጎሙ የሚገባቸው አይደለም።በመሆኑም ተጠሪው በዚህ ረገድ ያቀረበው መከራከሪያ በስር ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው በአግባቡ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል ተጠሪው ለዚህ ሰበር ችልት በሰጠው መልስ ላይ አመልካች የንግድ ድርጅቱን የገዙት አቶ ድራር ገዛኢ ከተባለ ኤርትራዊ ዜጋ መሆኑን እና ውለም እንዱቋረጥ የተደረገው አመልካች የንግድ ድርጅቱን ካልተፈቀደለት ግለሰብ የገዙት በመሆኑ ነው በማለት ተከራክሯል።ይሁን እንጂ ተጠሪው ይህንን የክርክር ነጥብ በስር የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በጽሁፍ መልሱም ሆነ ክሱ በተሰማበት ጊዜ አንስቶ ያልተከራከረበት መሆኑን ቀርቦ ከተያያዘው የስር መዝገብ ተገንዝበናል።በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳ እና ለውሳኔው መሰረት ያልተደረገ ክርክር ደግሞ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 329 (1) መሰረት አሁን በሰበር ደረጃ ሉስተናገድ የሚችልበት ስነ ስርዓታዊ አግባብ የለም።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው ተጠሪው ውለን ስላቋረጠበት ምክንያት በውል ማቋረጫ ደብዲቤው ላይ የገለጸው ነገር ባይኖርም በስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውለን ያቋረጠው ቤቱን ስለፈለገው እንደሆነ በመግለጽ የተከራከረ መሆኑን የስር መዝገብ ያመለክታል።ይሁን እንጂ ተጠሪው በመደበኛ ሁኔታ የንግድ ቤቶችን የሚያስተዲድረው ለሶስተኛ ወገን በኪራይ እየሰጠ እንደመሆኑ መጠን ውለን ያቋረጠው በርግጥም ቤቱን ለላላ ተገቢ እና ሕጋዊ ምክንያት ፈልጎት ከሆነ ይህንኑ ምክንያት ጠቅሶ መከራከር የሚጠበቅበት ሆኖ ሳለ በደፈናው ውለን ያቋረጥኩት ቤቱን ስለፈለግሁት ነው ከማለት በቀር የፈለገው ለምን ዓላማ እንደሆነ በግልጽ ያቀረበው ክርክር የለም።ውለን ያቋረጥኩት ቤቱን ስለፈለግሁት ነው የሚለውን የክርክር ነጥብ በዚህ ሰበር ደረጃ በሰጠው መልስ ውስጥም አላካተተም።በመሆኑም ተጠሪው ውለን ያቋረጠው ቤቱን ለማስለቀቅ የሚያስችል ተገቢ እና ሕጋዊ ምክንያት ኖሮት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉታረም የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ12/07/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በይግባኝ ሰሚው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ05/02/2007 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪው ከአመልካቹ ጋር የነበረውን የኪራይ ውል ያቋረጠው በአግባቡ አይደለም በማለት ወስነናል።
እንዱያውቁት የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶቷል።
No topics extracted.