የስጦታ ዉል ውስጥ ተቃራኒ የሚሆን ቃል ከላለ በቀር ስጦታ ከተደረገ በኋላ ልጅ መወለደ ስጦታውን ለመሻር ምክንያት የማይሆን ስለመሆኑ፣ ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2450
No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ተኽሉት ይመሰል እንደሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካቾች፡- 1ኛ. ሕፃን መይሙና ሀሰን 2ኛ. ሕፃን መሳይ ሀሰን 3ኛ. ሕፃን ረሂማ ሀሰን ጠበቃቸው ጌታቸው አለሙ ቀረቡ ተጠሪ፡- የሕፃን ሳሉሃ ሀሰን ሞግዚት ወ/ሮ ፀሃይ አድማሱ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ የሚመለከት ክርክር ሲሆን የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ ክልል ዱላ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው።በስር ወረዲ ፍርድ ቤት የአሁኗ ተጠሪ አመልካች፤አመልካቾች ፤ተጠሪዎች፤ የአመልካቾች ሞግዚት ወ/ሮ ዙልፊ ከማል ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል።የተጠሪ ሞግዚት ወ/ሮ ፀሐይ አድማሱ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ባጭሩ፡- ሟች ሀሰን አዱል የህፃን ሳሉሃ ሀሰን ወላጅ አባት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውንና ህፃን ሳሉህ ሀሰን ወራሽ መሆኗ የተረጋገጠበትን ማስረጃ አያይዘው በማቅረብ ሟች በህይወት እያለ ያፈሯቸውን ንብረቶች ዝርዝር አቅርበው የውርስ አጣሪ ተሹሞ ተጠርተው የህጻን ሳሉህ ሀሰን ድርሻ እንዱወሰን በማለት ዲኝነት ጠይቋል።
የአሁኑ አመልካቾች ሞግዚት በሰጡት መልስም ጉዲዩ ከአሁን በፉት በፍርድ ያለቀ ስለመሆኑ፤
ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤትም የግላቸው መሆኑን በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ አመልክቷል።
የስር ፍርድ ቤትም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን በብይን ውድቅ ካደረገ በኋላ ለክርክሩም ምክንያት የሆነው ቤት በጣልቃ ገብ ስም የሚታወቅ ነው።ተጠሪ የሟች ንብረት ስለመሆኑ አላስረዲችም።ንብረት በአመልካቾች ሞግዚት ስለመኖሩ ተጠሪ አላረጋገጠችም።ላልች የቤት ቁሳቁሶች በአመልካቾች ሞግዚት ስለመኖሩ ተጠሪ በሰው ይሁን በሰነድ ማስረጃ አላስረዲችም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል።የአሁኗ ተጠሪ በስር ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለጌዳኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርባ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙ ከአከራካረ እና ተገቢ ነው ያለውን ማጣራት ከአደረገ በኋላ ሟች ለክርክሩ መነሻ የሆነውን የቤት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር 1303 የተሰጠው በ1988 ዓ.ም ለአሁኗ የአመልካቾች ሞግዚት ተሰጠ ከተባለ በኋላ በ1992 ዓ.ም የእድሳት ፍቃድ ጠይቆ ማሳደሱን፤ስጦታ ተሰጠ የተባለው ቤትም መኖሪያ ቤቴ ነው በሚል ሲገብርበት እንደነበረ ማስረጃ በመቅረቡ የስጦታ ውለን በዝምታ በመሻር ቦታውንና ቤቱን በባለቤትነት ስር አድርጎ ሲጠቀምበትና ሲገለገልበት የነበረ መሆኑን ያሳያል፡፤የስር ፍርድ ቤት በአግባቡ ሳያጣራና ሳይመረምር የደረሰበት መደምደሚያና የሰጠው ውሳኔ የሕግና የማስረጃ ድጋፍ የላለው ነው በማለት ውሳኔውን ሽሮ በይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር 1303 ላይ ያለውን ይዞታና ቤት ሟች አቶ አዝጊ (ሀሰን) አዱል እና የአመልካቾች ሞግዚት ወ/ሮ ዙልፊ ከማል የጋራ ንብረት በመሆኑ ሟች አቶ አዝጊ አዱል ድርሻ የውርስ ሀብት ነው።የሟች ልጆች የአባታቸው የውርስ ድርሻ ይክፈለ በማለት ወስኗል።የአሁኑ አመልካቾች ሞግዚት የጌዳኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 የተሰረዘ ሲሆን በሰበር ስልጣኑ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች የሚያከራክረውን ንብረት ላይ ድርሻ የላቸውም ያለ አለመሆኑን የአመልካቾች ሞግዚት ባለቤቷን በፍቺ ስለተለያዩ የደረሰኝ ነው ትበል እንጂ ፍቺና የንብረት ክፍፍል መኖሩን አላስረዲችም።በይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ቁጥር 1303 የሆነውን የአመልካቾች ሞግዚት ድርሻ ከተለየ በኋላ የሟች ልጆች ይክፈለ መባለ በአግባቡ ነው በማለት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አጽንቷል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ ያቀረበውም የስር ከፍተኛ እና በየደረጃውን ጉዲዩን የተመለከቱት ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው:: የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡-ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤትና ይዞታ የግላቸው ስለመሆኑ፤የስጦታ ውለም እንዲልተሻረ፤የተጠሪ ሞግዚት ከአሁን በፉት ክስ አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸው ስለመሆኑ፤ተጠሪ በማይመለከታት ንብረት አጣርታ እንደቀረበች በመግለጽ ውሳኔው እንዱሻር የሚጠይቅ ነው።የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ይቅረብ በመባለ ግራ ቀኙ የፁሁፍ ክርክር አድርጓል።ተጠሪ በሰጠችው መልስም ሟች ልጅን መሻር እንደማይችል፤የተወለደቺው ከስጦታ በኋላ ስለመሆኑ ፤ስጦታውን በዝምታ የተሻረ መሆኑን በመጥቀስ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱጸና አመልክቷል።የመልስ መልስም ቀርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጹሁፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዱሁም ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ "በዚህ ጉዲይ አመልካች አከራካሪውን ንብረት ከሟች ጋር በጋብቻ ተሳስረው በነበሩበት ወቅት በስጦታ ያገኙት እና ጋብቻቸው ሲፈርስ የንብረት ክፍፍል አድርገው መለያየታቸው እየገለጹ ተጠሪ /ህጻን/ ሳሉህ ሀሰን ድርሻ አለው ተብል የመወሰኑን አግባብነት ከሰ/መ/ አንጻር ለመመርመር" የሚል ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ከስር ፍርድ ቤት አንስቶ አጥብቀው የሚከራከሩት ከሟች አቶ ሀሰን አዱል የነበራቸው ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ የንብረት ክፍፍል መደረጉን፤በይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት 1303 የሚታወቀው ቤትና ይዞታ በ1988 ዓ/ም ከሟች በስጦታ ያገኙትና የግላቸው ቤትና ይዞታ ስለመሆኑን ነው።የአሁኗ ተጠሪ ሞግዚት በበኩላቸው ከአሁን በፉት የተደረገው ክርክር ሚስት መሆናቸውን መሰረት ያደረገ እንጂ ተጠሪ ወራሽ በመሆኗ ምክንያት የቀረበ ክስ አለመሆኑን ክርክር የተደረገበት በቁጥር 1303 የሚታወቀው ቤት የአመልካቾች ሞግዚት የግል ቤት አለመሆኑን መከራከራቸውን ተመልክተናል።የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህን ጉዲይ በይግባኝ እና ሰበር የተመለከቱት ፍርድ ቤቶች ቤቱ በመጀመሪያ የአሁን ተጠሪዎች ሞግዚት በስጦታ ያገኙት መሆኑን ገልጸው፤ነገር ግን ሟች ከስጦታ በኋላ በአከናወኗቸው ድርጊቶች ስጦታቸው በዝምታ ተሸሯል ከሚል መደምደሚያ ደርሰዋል።
ከመዝገቡ ጋር ከተያያዙ ሰነድች መገንዘብ የተቻለው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት ባለቤትነት የምስክር ወረቀት 1303/83 የሚታወቀው የሟች ንብረት ስለመሆኑ ሐምል 17 ቀን 1988 ዓ.ም በተደረገው ስጦታ ለወ/ሮ ዙልፊ ከማል መስጠታቸውን፤ስጦታውም በስረ ፊይል መዝገብ ቁጥር 156/88 ፍርድ ቤት ቀርቦ መጽደቁን ነው።በልላ በኩል የአሁኗ ተጠሪ ሞግዚት በጌዳኦ ዞን ወናጎ ወረዲ ፍርድ ቤት በፍ/መ/ ክስ አቅርበው ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ጥር 30/05/2003 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል።የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይዘትም የአሁኗ ተጠሪ ሞግዚት በይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር 1303/83 በሚታወቀው ቤት ላይ ድርሻ እንዲላቸው የጠየቁ ቢሆንም የአሁን አመልካቾች ሞግዚት በስጦታ ያገኙት ነው በማለት የተጠሪ ሞግዚት ክስ ውድቅ ማድረጉን የሚያሳይ ነው።ይህ ውሳኔም ጉዲዩን በየደረጃው ባዩት ፍርድ ቤቶች የጸና ሲሆን፤
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም በሰመ/ በ12/08/2004 ዓ.ም መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል።ከዚህ መረዲት የሚቻለው የአሁኗ ተጠሪ ሞግዚት ድርሻ አለኝ በማለት ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ ከመደረጉ በተጨማሪ የአሁን አመልካቾች ሞግዚት ቤትና ይዞታውን ያገኙት በስጦታ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።ከክርክሩ ይዘት መገንዘብ የተቻለው የስጦታ ውለ የጸና ስለመሆኑ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት መወሰኑን ነው።የአሁኗ ተጠሪ ሞግዚት በ2003 ዓ.ም በአመልካቾች ሞግዚት ላይ ክስ አቅርበው ውድቅ ከተደረገ በኋላ በስር ወረዲ ፍርድ ቤት ተጠሪን ወክለው በ2005 ዓ.ም ክስ ማቅረባቸው መዝገቡ ያሳያል።የስር ፍርድ ቤቶች ሟች የስጦታ ውለን በዝምታ ሽሮታል ከሚል ድምዲሜ የደረሱ ቢሆንም በ2003 ዓ.ም አስቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ የስጦታ ውለ የጸና ስለመሆኑ በየትኛውም ፍርድ ቤት ያልተሻረ ውሳኔ መስጠቱን ካቀረቡት የውሳኔ ግልባጮች መገንዘብ ተችሎል።
የአሁኗ ተጠሪ ሞግዚት በስር ፍርድ ቤት ይሁን በሰበር ደረጃ ባደረጉት ክርክር ወላጅ ልጅን ከስጦታ መሻር አይችልም የሚል ነው።ስጦታው የአሁኗ ተጠሪ ከመወለዶ በፉት የተሰጠ ስለመሆኑ አልተካደም።ስጦታው በፍርድ ቤት ቀርቦ መጽደቁም ያከራከረ ጉዲይ አይደለም።ሟች ባደረጉት ስጦታ በምስክር ወረቀት ቁጥር 1303/83 በስማቸው ተመዝገቦ የሚታወቀውን 27x12፡ 324 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራውን አንድ ክፍል ቆርቆሮ ክዲን ቤት ከነቦታው ለወ/ሮ ዙልፊ ከማል መስጠታቸው አረጋግጠዋል።በመሰረቱ የስጦታ ውል በፍ/ብ/ሥ/ስ/ሕ/ቁ 2427 እና ተከታይ ድንጋጌዎች የሚመራ ሲሆን ሟች ያደረጉት ስጦታ በህጋዊነቱ ይሁን ፍረማሉቲ የተነሳ ክርክር የለም። የተጠሪ ሞግዚት ስጦታው ውድቅ ለማድረግ እንደ ምክንያት ያቀረቡት ከስጦታ መደረግ በኋላ የተጠሪ መወለድን ነው።የአሁኗ ተጠሪ ሞግዚት ክርክር ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 2450 አንጻር እንደተመለከተው ተገቢነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።የድንጋጌው ሙለ ይዘት "በተደረገው የስጦታ ውል ውስጥ ተቃራኒ የሚሆን ቃል ከላለ በቀር ስጦታ ከተደረገ በኋላ ልጅ በመውለደ ምክንያት ስጦታውን ለመሻር አይቻልም"።በማለት የተደነገገ ሲሆን የእንግሉዝኛው አቻ ትርጉም " unless otherwise provided in the contract of donation, a donation may not be revoked where a child is born to the donor" በሚል ተቀምጧል። የዚህ ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት እንደተመለከተው የስጦታ ውል ተቃራኒ ቃል ከላለው በቀር የልጅ መውለድ የስጦታ ውለን ለመሻር በቂ ምክንያት አለመሆኑን በግልጽ ተደንግጓል ሟች ሐምል 17 ቀን 1988 ዓ/ም ያደረጉት የስጦታ ውልም ለወ/ሮ ዙልፊ ከሚል ከመስጠት ውጭ ላላ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠበት ስለመሆኑ ከመዝገቡ ጋር የተያያዘው የስጦታ ውል አያሳይም። እንዱህ ከሆነ ደግሞ የአሁኗ ተጠሪ በመውለዶ ምክንያት የስጦታ ውለ የሚሽርበት የህግ ምክንያት አይኖርም።
በመሆኑም የስር ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እና ሰበር ሰሚ ችልት የስጦታ ውለ የጸና ስለመሆኑ የፍርድ ቤት የጸና ውሳኔ በቀረበበት /ባለበት/ እና ልጅ መውለድ ስጦታ ለመሻር ምክንያት እንደማይሆን በፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2450 በግልጽ በተደነገገበት ሁኔታ የሟች ስጦታ በዝምታ ተሸሯል ከሚል ድምዲሜ የደረሰው የስር ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሻራቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸማቸውን የሚያሳይ ነው ብለናል። በዚህም ተከታዩን ወስነናል።
የጌድኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 09588 በሀምላ 17 ቀን 2006 በዋለው ችልት የዱላ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሐሮ ወለቡ ምድብ ችልት በመ/ቁ/ 00670 በ18/02/2006 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ በመሻር የሰጠው ፍርድ፤ የደ/ብ/ብ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/63836 በ20/06/2007 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ቁ/ 64413 በ18/09/2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ተሸሮአል።
በይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር 1303 ላይ ያለውን ይዞታና ቤት የአመልካቾች ሞግዚት ወ/ሮ ዙልፊ ከማል የግል ቤትና ይዞታ ነው በማለት ወስነናል።
የዱላ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 00670 በ18/02/2006 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ጸንቷል።
በዚህ ፍ/ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.