በተሸጠ ነገር ላይ የተገኘው ጉድለት ለውል ማፍረሻ ምክንያት ላሆን ስለማይችልበት ምክንያት የፍ/ሕ/ቁ.2344(2) ፣2289(1) XVI
No summary available.
ቀን 14/08/2008 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል እንደሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- አሻም ትሬዱንግ ኤንድ ኢንደስትሪ ስራ ኃ/የተ/የግል ማህበር - ስራ አስከያጅ አሸበር ውንድሦስሽ ቀረቡ ተጠሪ፡- የንግፊን ሞተርስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ጠበቃ ደባስ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች ተጠሪ የሽጠልኝ ሉፊን መኪና ከአዱስ መኪና የማይጠበቅ በተደጋጋሚ ብልሽት ምክንያት ወደ ተከሳሽ ጋራዥ የምትገባና መሰረታዊ ጉድለት ያለባት በመሆኑ ተከሳሽ (ተጠሪ) በልላ አዱስ መኪና እንዱተካ ወይም መኪናዋን ለመግዛት የከፈለኩትን ገንዘብ እንዱመልስ ውሳኔ ይስጥልኝ በማለት ያቀረበውን ጥያቄ የበታች ፍርድ ቤቶች ውድቅ ያደረጉት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የተያው በፉዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች ያቀረበው ክስ ነው። አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሆኖ ቀርቦ ከተከሳሽ LF7132 የሞተር ጉልበት 1300 cc የሆነ አዱስ መኪና ጥር 4 ቀን 2002 ዓ/ም በተዋዋልነው ውል ሽጦልኛል። ተከሳሽ መኪናዋን የሸጠልኝ በብር 189,800 (አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺ ስምንት መቶ ብር) ሲሆን ተከሳሽ ብር 94,900 (ዘጠና አራት ሺ ዘጠኝ መቶ ብር) በቅድመ ክፍያ፣ ቀሪውን መኪናዋን ስረከብ ከፍያለሁ። ተከሳሽ ለከሳሽ የሸጠልኝ መኪና በሃያ አራት ወራት ውስጥ 3000 ኪል ሜትር ሳትነዲ ጉድለት ቢገኝበት በራሱ ወጭ ለማስተካከል ወይም ለመቀየር የውል ግዳታ ገብቷል። ሆኖም መኪናዋን ከተረከብኩበት ጊዜ ጀምሮ ባለበት መሰረታዊ ጉደለት በተደጋጋሚ ወደ ተከሳሽ ጋራዥ የገባች ሲሆን ጉድለት ከአዱስ መኪና የማይጠበቅ በመሆኑ በልላ አዱስ መኪና እንዱቀይርልኝ ብጠይቀው ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህ የሽያጭ ውለ ፈርሶ መኪናዋ ፍርድ በተሰጠበት ቀን ከምታወጣው ዋጋ ለከሳሽ ከወጭና ኪሳራ ጋር እንዱመልስ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርቦ መኪናዋ የነበረባት አነስተኛ ጉደለቶች በተከሳሽ ጋራዥና ወጭ ተስተካክላ በአዱስ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ከሳሽ መኪናዋን ተረክቦ ወስድ አገልግልት ላይ ለማዋል የሚችል በመሆኑ ውለ ፈራሽ ይሁን በማለት ያቀረበው ክስ የህግ መሰረት የለውም። ከሳሽ መኪናዋን በጋራዣችን ትቶ የሄደ በመሆኑ መኪናዋ በጋራዥ ለቆየችበትና ወደፉት ለምትቆይበት ኪራይ የመጠየቅ መብታችን ይጠበቅልን በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመር በኃላ መኪናዋ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ባለሙያዎች ተመርምራ መግለጫ እንዱቀርብለት ካደረገ በኃላ መኪናዋ መሰረታዊ ችግር ያለበት መሆኑ በማስረጃ ስላልተረጋገጠ የከሳሽ ክስ የህግ መሰረት የለውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች ይግባኝ በፉዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል።
አመልካች ህዲር 30 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ የሸጠልን መኪና ሶስት ሺ ኪ.ሜትር ሳይነዲ ለአምስት ጊዜ ያህል ሞተሩ ጭምር በድንገትና ሳይታሰብ እየቆመ ለከፍተኛ አደጋ ጭምር ያጋለጠን መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃና ተጠሪ መኪናዋን በተደጋጋሚ በራሱ ጋራዥ ቢጠግናትም መኪናዋ የአመራረትና የጥራት ጉድለት ያለባት በመሆኑ ሉስተካከል አለመቻለን ለስር ፍርድ ቤት በማስረጃ አስርድተን እያለ የስር ፍርድ ቤት መኪናዋ መሰረታዊ ጉድለት የለባትም በማለት የሰጠው ውሳኔ አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያላደረገና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ ሚያዝያ 12 ቀን 2007 ዓ/ም በተጻፈ መልስ፤ መኪናዋ መሰረታዊ ጉደለት የላለበት መሆኑን የባለሙያ ማስረጃ በማቅረብ ጥያቄ አቅርበን ነበር በመኪናዋ ላይ የተከሰተው ችግር መሰረታዊና የማይጠገን ችግር አይደለም ተጠሪ መኪናዋን አስተካክል ለመስጠት በውል የገባውን ግዳታ ሲፈጽም ቆይቷል። አመልካች ለተጠሪ መኪናዋን ማስተካከል ከአቅሙ በላይ መሆኑን ሳይገልጽላት መኪናዋን ከተጠሪ ጋራዥ ጥል ጠፍቷል። መኪናዋ የአመራረት ጉድለት የለባትም ስለዚህ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካች ሚያዝያ 26 ቀን 2007 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ለዚህ ሰበር ችልት ያቀረቡት ጽሐፍ ክርክር ከላይ በአጭሩ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ ለአመልካች በክሱ አይነት የተገለጸቸውን መኪና በብር 189,800 ( አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺ ብር) የሽጠ መሆኑንና በመኪናዋ ላይ ለሚታይ ጉድለትም ዋስትና የሰጠ መሆኑ አከራካሪ ጭብጥ አይደለም። አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩት አመልካች መኪናዋ ሶስት ኪል ሜትር ሳትነዲ የሞተርና ላልች ጉድለቶች ተከስተው ለአምስት ጊዜ ከሻጭ ጋራዥ ገብታ፣ ሻጭ(ተጠሪ) የመኪናዋን ጉድለት ለማስተካከል አልቻለም። አመልካች በገዛት መኪና በአዱስ መኪና ሉያገኝ የሚገባውን አገልግልት ያላገኘ በመሆኑ መኪናዋ መሰረታዊ ችግር ያለበት ስለሆነ ውለ ፈራሽ ነው ይባልልኝ በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ በተቃራኒው በመኪናዋ ላይ የተከሰቱ ብልሽቶች በማንኛውም አዱስ መኪና ላይ ሉከሰቱ የሚችለ ቀላል ብልሽቶች ናቸው። አመልካች በመኪናዋ ላይ አለ የሚላቸውን ጉድለቶች ሙለ በሙለ ያስተካከልኩ በመሆኔ አመልካች መኪናዋን ወሰድ ከመጠቀም በስተቀር የሽያጭ ውለ የሚፈርስበት ህጋዊ ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል።
ከላይ ከተገለጸውና ግራ ቀኙ ከተካካደባቸው ነጥቦች ለመረዲት እንደሚቻለው ተጠሪ ለአመልካች በሽጣት መኪና ላይ የታዩ ብልሽቶችና መኪናዋ ወደ ሉፊን ጋራዥ እየገባች ጥገና ያገኘችበት ሁኔታ ከአዱስ መኪና የሚጠበቅ ነው ወይም አይደለም? ብልሽቱ ከአዱስ መኪና የሚጠበቅ አይደለም ከተባለ ውለን ፈራሽ ለማድረግ በቂ ምክንያት ነው ወይስ አይደለም? የሚለት ነጥቦች መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ከላይ የተገለጹትን ነጥቦች፣ ላይ ውሳኔ ለመስጠት እንዱመቸው የስር ፍርድ ቤት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.136 ንዐስ አንቀጽ 1 በሚደነግገው መሰረት ለጉዲዩ ገለልተኛ በሆኑ በመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ጉዲዩ ተጣርቶ የሙያ አስተያያት እንዱቀርብለት ትዕዛዝ ሰጥቶ፣ የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ዕወቀትና ክህልት አላቸው የሚላቸውን ሶስት ባለሙያዎች መድቦ ባለሙያዎቹ መኪናዋን በአካል ከፈተሸና ከመርመሩ በኃላ ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም ሪፖርት ያቀረቡ መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተረድተናል።
የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ባለሙያዎች መኪናዋን በአካል በፈተሸበትና በመረመሩበት ወቅት አመልካች መኪናዋን ሉፊን ጋራዥ እንዱያስገባት ምክንያት የሆኑ ጉድለቶች ሉፊን ጋራዥ ያስተካከላቸው መሆኑን ከሪፖርታቸው የገልጸ ሲሆን፣ ባለሙያዎች የመኪናዋን ፊይል በማስቀረብ የተመለከቱ መሆኑንና መኪናዋ 3000 ኪል ሜትር ሳትነዲ ከአምስት ጊዜ በላይ ወደ ሉፊን ጋራዥ እየገባች የተለያዩ የጥገና አገልግልት የተሰጣት መሆኑን እንዲረጋገጡ ገልጸው አንድ አዱስ መኪና 3000 ኪል ሜትር ሳይነዲ እንዱዚህ አይነት የበዛ ችግሮች ማጋጠም ስለላለበት ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ከአዱስ መኪና የሚጠበቁ ችግሮች አይደለም በማለት ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ተጠሪ ለአመልካች በሸጣትና በአገር ውስጥ ተጠሪ ባቋቋመው የመኪና መገጣጠሚያ ፊብሪካ በተገጣጠመችው አዱስ መኪና ላይ በተደጋጋሚ የተከሰተው ብልሽት በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2344 መሰረት የሽያጭ ውለ ፈራሽ ለማድረግ በቂ ምክንያት ነው ወይስ አይደለም የሚልውን ተመልክተናል። ‛የተሸጠው ነገር ጉድለት“ የሚል ርዕስ ያለው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2344 ‛የተሸጠው ነገር ሻጩ ለገዥው ዋቢ ላሆንለት የሚገባው ጉድለት የተገኘበት እንደሆነ ውለ ሉፈርስ እንደሚችል በንዐስ አንቀጽ 1 በግልጽ ደነግጋል። አንድ ሻጭ የሸጠው ነገር ለደንበኛው አገልግልት ወይም ንግድ ረገድ ለመጠቀሚያነት ጥሩነት የላለው ሲሆንና የሸጠው ነገር በውለ ውስጥ በግልጽ ወይም በውስጣዊ ሀሳብ ለተነገረው ልዩ አገልግልት የሚሆኑ አስፈላጊ የሆኑ ጥሩነት የላለው በሆነ ጊዜ ሻጭ ለገዥው ዋቢ እንደሚሆን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2289 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል።
ከዚህ አንጻር ተጠሪ በሸጠው አዱስ መኪና ላይ እስከ 3000 ኪል ሜትር ለሚደርስ ብልሽት ዋቢ በመሆን ዋስትና የሰጠ ሲሆን፣ መኪናዋ 3000 ኪል ሜትር ሳትነዲ የተለያየ ብልሽት እያጋጠማት ከአምስት ጊዜ በላይ ሉፊን ጋራዥ እየገባች ተጠግና መውጣቷ ተረጋግጧል።
ይህም ገዥው አዱስ ከፊብሪካ የወጣ መኪና በመግዛትና በመረከብ ከገዥው የአጠቃቀም ጉድለት ካልፈጸመ ወይም አደጋ ካላጋጠማት በስተቀር ቀላልና መለስተኛ የሆኑ ጥገና ለትንሽ ቀናት ብቻ እያቆመች መኪናዋን ለትራንስፖርት እገለገልባታለሁ በሚል ሀሳብ የገዛ መሆኑንና ተጠሪ ለአመልካች የሸጣት መኪና ግን ለአመልካች መስጠት የሚገባትን መደበኛ የትራንስፖርት አገልግልት ሳትሰጥ በየወቅቱ የተለያዩ ክፍልቿ እየተበላሹ ሉፊን ጋራዥ ለጥገና ስትገባ የቆየች መሆኑን በገለልተኛ ባለሙያዎች የቀረበው ሪፖርት ያሳያል።
በተሸጠው ነገር ላይ የተገኘው ጉድለት ለውል ማፍረሻ ምክንያት የማይሆነው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2344 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገው ሁኔታ ሲሟላ ነው። የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2344 ንዐስ አንቀጽ 2 የአማርኛ ቅጅ ቃል በቃል ሲነበብ ‛እንዱህም በሆነ ጊዜ ጉድለቱ እጅግም የማይጎዲ እንደሆነና ገዥው ጉደለቱን አውቆ ኖሮም ቢሆን ጉደለት የተገኘበትን ነገር ሳይገዛው የማይቀር እንደነበር ሲታይ ውለን ለማፍርስ አይችልም“ የሚል ይዘት ያለው ሲሆን የዚህ ድንጋጌ የእንግለኛው ቅጅ፣ ‛the contract may however not be cancelled where the defect is of small importance and it oppears that buyer would have bougut the thing had he known the defect“ የሚል ይዘት ያለው ነው።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ለአመልካች በሽጠለት መኪና ላይ በየወቅቱ የታዩ ብልሽቶች ከሞተር አሰራር ጀምሮ የፍሪስዮንና ላልች ችግሮች እየጋጠሙ መኪናዋ 3000 ኪል ሜትር ሳትነዲ ከአምስት ጊዜ በላይ ለጥገና ወደ ሉፊን ጋራዥ የገባች መሆኑ ግራ ቀኙ ካደርጉት ክርክርና ከስር ፍርድ ቤት በውሳኔው ካስፈራቸው ነገሮች ተረድተናል። ተጠሪ የሚያከራከረው ከዚህ በፉት በመኪናዋ ላይ የታዩ ጉድለቶችና ብልሽቶች ቀላል በመሆናቸው በተጠሪ በቀላለ ተስተካክለዋል በማለት ነው። ሆኖም ተጠሪ ለአመልካች የሸጠው ያገለገለ መኪና ሳይሆን ከፊብሪካ ተገጣጥሞ የወጣ አዱስ መኪና ከመሆኑ አንጻር መኪናው ትንሽ ኪል ሜትር እየተነዲ በሚያጋጥመው ብልሽት ምክንያት አመልካች በመኪናው ሉያገኝ የሚገባውን መደበኛ የትራንስፖርት አገልግልት ማግኘት ያልቻለና በየወቅቱ መኪናዋን ወደ ሉፊን ጋራዥ እየወሰደ ጉድለቶችን በመዘርዘርና የስራ ትዕዛዝ በመስጠት፣ መኪናዋ በጥገና ለመስተካከል የምትችል መሆኗን ምክሮ ያልተሳካ በመሆኑ ውለ እንደፈርስ የጠየቀ መሆኑን፣ ለመገንዘብ ችለናል።
ይህም ተጠሪ ለአመልካች የሸጣት መኪና ከአዱስ መኪና የማይጠበቅ ተደጋጋሚ ብልሽት የጋጠማትና ተጠሪ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2289 ንዐስ አንቀጽ 1 በዋቢነት ሉያልፍበት የሚገባውን ለመደበኛው ትራንስፖርት አገልግልት ጥሩነት የላላት መሆኑን የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ አመልካች መኪናዋ 3000 ኪል ሜትር ሳትነዲ ከአምስት ጊዜ በላይ ጋራዥ እየገባች ለጥገና የምትቆም መሆኑን መኪናዋን ከመግዛቱ በፉት ቢያወቅ ኖሮ መኪናዋን ይገዛታል ተብል የማይገመትን በመኪናዋ ላይ የታዩት ብልሽቶች ቀላል ሉባለ የማይችለ እንደሆኑ የሚያሳይ ነው።
ከዚህ አንጻር አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረገውን የመኪና ግዥ ውል እንዱፈርስለት ለመጠየቅ የሚያስችለውና ውለንም ፈራሽ ለማድረግ የሚያስችለ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2289 ንዐስ አንቀጽ 1 በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2344 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 የተገለጹት ጉደለቶች ተጠሪ በሸጣት መኪና ላይ የታዩ መሆኑን፣ የስር ፍርድ ቤት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 136 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት በመደባቸው የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ባለሙያዎች ተጠሪ በሸጣት መኪና 3000 ኪል ሜትር ሳትነዲ ያጋጠሙ ብልሽቶችና ችግሮች በአዱስ መኪና ሉታዩ የሚገቡ ችግሮች አይደለም በማለት የሙያ አስተያያት የሰጡበት ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት መኪናዋ በተደጋጋሚ ጋራዥ መግባቷ ውለን ለማፍረስ በቂ ምክንያት አይደለም በማለት መወሰኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2344 ንዐስ አንቀጽ 1 የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2289 ንዐስ አንቀጽ 1 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2344 ንዐስ አንቀጽ 2 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና ዓላማ ሳያገናዝብ የተሰጠና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ተጠሪ አመልካች ጋር ያደረገው የመኪና ሽያጭ ውል ፈራሽ ነው ከተባለ ውጤቱ ምን ይሆናል የሚለውን በማስከተል መመልከቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። መኪናዋ ሉፊን ጋራዥ የቆመችና ተጠሪ የተረከባት መሆኑ ተረጋግጧል። በልላ በኩል አመልካች መኪናዋን ለመግዛት የከፈለው ብር 189,800 (አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺ ስምንት መቶ ብር) ተጠሪ ለአመልካች የመመለስ ግዳታ አለበት አመልካች ተጠሪ በአሁኑ ወቅት መኪናዋ የምታወጣውን ዋጋ እንዱከፍለው ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም፣ ይህ ጥያቄ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። በአንጻሩ ተጠሪ አመልካች የከፈለውን ብር 189,800 (አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺ ሰምንት መቶ ብር) አመልካች ለስር ፍርድ ቤት ክስ ካቀረበበት መጋቢት 14 ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ሉመልስ ይገባል በማለት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1815 እና በፍታብሓር ቁጥር 1751 መሰረት ወስነናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 14 ቀን 2005 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 17 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
በተጠሪና በአመልካች መካከል የተደረገው የመኪና ሽያጭ ውል ፈራሽ ነው በማለት በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2289 ንዐስ አንቀጽ 1፣ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2344 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ወስነናል።
ተጠሪ ሉፊን ጋራዥ ገብታ የቆመችውን መኪና ተረክቦ ለሚፈልገው አገልግልት ሉውል ይችላል ብለናል።
ተጠሪ አመልካች መኪናዋን ሲገዛ የከፈለውን ብር 189,800 (አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺ ስምንት መቶ ብር) ከመጋቢት 14 ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ይክፈል በማለት ወሰነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ። መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.