የዋስትና ውል ግዳታ ሰራተኛው ተቀጥሮ በሚያገለግልበት ወቅት ለሚደርሰው የገንዘብና የንብረት መጥፊትና መጉደል ተጠያቂ የሚያደረግ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሓር/ሕ/ቁ. 1933/1/ 1897
No summary available.
ቀን 28/7/2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- አቶ ሶፍኒያስ ሀብተማርያም ጠበቃ ሀ/ማርያም መልካ ተጠሪ፡- ካልዱስ ኮፉ ኃላ/የተ/የግ/ማ- ጠበቃ አሰፊ መኮንን - ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ የሰበር አቤቱታ መዝገብ ክርክር አመልካች አቶ ሶፋኒያስ ሀብተማሪያም ጥር 9/2007 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 104228 ጥቅምት 2/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት የቀረበ ሲሆን የአሁን አመልካች የዋስትና ስምምነት 1ኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ ቢኒያም አሰፊ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በእስቶር ኪፏር ወይም ዕቃ ግምጃ ቤት ሰራተኛ የሥራ ቅጥር መደብ ተመድቦ ሲሰራ ለሚደርሰው የንብረት ጉድለት ዋስ መሆኔ እየታወቀ 1ኛ ተከሳሽ የገንዘብ ያዥነት ስራ እንዱያከናውን ከተመደበበት ስራ ውጪ ከ100000 ብር በላይ በመስጠት በተላላኪነት ተጠሪ እራሱ አሰማርቶት በደረሰው የገንዘብ ጉድለት አመልካች ተጠያቂ ነው ተብል መወሰኑ አለአግባብ በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ካልዱስ ኮፉ የኃ/የተ/የግ/ማ በፋ.የመ.ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ 1ኛ ተከሳሽ አቶ ቢኒያም አሰፊ በከሳሽ ድርጅት በቦላ ቅርንጫፍ ለንብረት ክፍል ሲቀጠሩ 2ኛ ተከሳሽ አቶ ሶፋኒያስ ሀብተማሪያም እስከ የዋስትና ግዳታ ነሐሴ 8/2004 ዓ.ም በተጻፈ የዋስትና ግዳታ ውል ገብቷል። 1ኛ ተከሳሽ በንብረት ክፍል ተቀጥረው በሚሰሩበት ጊዜ መስከረም 2/2005 ዓ.ም ወደ ባንክ እንዱያስገባ ከሳሽ የሰጠውን ይዘው በመሰወራቸው 2ኛ ተከሳሽ በተገኙበት የንብረት ቆጠራ ተደርጎ የብር 5643.49 ንብረት ጎሎል። ተከሳሽ በእምነት ማጉደል ወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ ሆነው የ1 ዓመት ከ7 ወር ቅጣት ተወስኖባቸዋል። ስለዚህ 1ኛ ተከሳሽ እና 2ኛ ተከሳሽ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1995 መሰረት በገቡት የዋስትና ውል ግዳታ .49 ከህዲር 2/2005 ዓ.ም በሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍለኝ ሲል ከሷል። የተከሳሾች መልስ የ1ኛ ተከሳሽ መልስ የስራ ኃላፉነቴ የንብረት ክፍል ተቆጣጣሪ እንጂ ገንዘብ የማንቀሳቀስ ኃላፉነት የለብኝም። ስለዚህ በፍ/ብ/ህ/ቁ.
1928(1) መሰረት ተጠያቂ ልሆን አይገባም። የብር 5643.49 የንብረት ጉድለት ለተባለው ተጠያቂ ነኝ ሲል 2ኛ ተከሳሽም በሰጠው መልስ የብር 5643.49 ንብረት ጉድለት ለተባለው ብቻ በገባሁት የዋስትና ውል ግዳታ መሰረት ተጠያቂ እሆናለሁ። 1ኛ ተከሳሽ ከተቀጠረበት ስራ ውጪ አሰማርተውት ለደረሰው ጥፊት ሀላፉነት የለብኝም ብለዋል።
የፋ.የመ.ደረጃ ፍ/ቤት በመ. ግንቦት 27/2005 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው 1ኛ ተከሳሽ አቶ ቢኒያም አሰፊ በሰነድ ተረክበው ለባንክ ገቢ ያላደረጉና የብር 5643.49 ንብረት ያጎደለ መሆኑን በቀረበው የሰነድ ማስረጃና 1ኛ ተከሳሽም በጽሁፍና በቃል ክርክር ያመኑ በመሆኑ ተጠያቂ ናቸው። 2ኛ ተከሳሽ የዋስትና ግዳታቸው 1ኛ ተከሳሽ የንብረት ክፍል ሰራተኛ ሆነው ሲቀጠሩ ለንብረት ጉድለት ኃላፉነት እንጂ ከጥሬ ገንዘብ ብር ጋር በተገናኜ እንዲልሆነ የቀረበው የዋስትና ግዳታ ውል ያስረዲል። በመሆኑም 2ኛ ተከሳሽ ለብር 5643.49 ንብረት ለጎደለው ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1933(1) እና 1897 መሰረት በአንድነትና በነጠላ ኃላፉ ነው 1ኛ ተከሳሽ ከህዲር 2/2005 ዓ.ም ጀምሮ በሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ለከሳሽ ይክፈለው። 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ ለብር 5643.49 ከግንቦት 27/2005 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጨምሮ ለከሳሽ ይክፈለት ሲል ወስኗል። ለፋ.ከፍ/ፍ/ቤት ከሳሽ ይግባኝ አቅርቦ የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት በመ. አከራክሮ ሰኔ 16/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ 1ኛ ተከሳሽ አቶ ቢኒያም አሰፊ ተቀጥረው በሚያገለግለበት ወቅት ለደረሰው የንብረት መጉደል ብቻ ሳይሆን ለገንዘብ መጥፊትና የንብረት መጉደል 2ኛ ተከሳሽ (የአሁን መልስ ሰጪ) በገቡት የዋስትና ግዳታ ላይ በግልጽ ተመልክቷል። የስር ፍ/ቤት የመልስ ሰጪን (2ኛ ተከሳሽን) የዋስትና ግዳታ ወሰን በግልጽ ከተጻፈው የግዳታ ዝርዝር አንጻር ተመልክቶ መወሰን ሲገባው 1ኛ ተከሳሽ የስራ መደብ ባልተቀየረበት እና የዋስትና ውለን ከሰራተኛው የስራ መደብ ብቻ በማያያዝ አለአግባብ መተርጎሙ የዋስትናውን ግዳታ ወሰን አላማ ያላገናዘበ በመሆኑ የደረሰበት የውሳኔ መደምደሚያ ስህተት ያለበት ነው በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን አሻሽል 2ኛ ተከሳሽ (መልስ ሰጪ) 1ኛ ተከሳሽ ለጎደለው እና በስር ፍ/ቤት የተወሰነውን ብር 5643.49 ጨምሮ እስከ ብቻ ተጠያቂ ነው ሲል ወስኗል። የአሁን አመልካች (2ኛ ተከሳሽ) ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 24/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት በሰጠው ትዕዛዝ ይግባኝ የተባለበት ውሳኔ ጉድለት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል።
የአሁኑ አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ቀርበዋል። መዝገቡ ተመርምሮ አመልካች ዋስ የሆነለት አቶ ቢኒያም አሰፊ ሲቀጠር በዋስትና ውለ ላይ የንብረት ክፍል ሰራተኛ መሆኑ በተገለጸበት ከስራ መደቡ ውጪ ባንክ እንዱያስገባ በተጠሪ የተሰጠውን ገንዘብ ይዞ በመጥፊቱ አመልካች ሃላፉነት አለበት ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ ግንቦት 28/2007 ዓ.ም በተጻፈ መልስ በአመልካችና በተጠሪ መሃከል ነሐሴ 8/2004 ዓ.ም በተደረገው የዋስትና ውል የስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ በተጠሪ ድርጅት ተቀጥረው በሚያገለግለበት ወቅት ለሚያደርሱት የገንዘብና የንብረት መጥፊትና መጉደል እስከ በጋራ እና በተናጥል የዋስትና ግዳታ ውል ገብተዋል። በዚሁ መሰረት የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ቅር የሚያሰኝ ባለመሆኑ ይጽናልኝ በማለት ተከራክረዋል።
አመልካችም አቤቱታቸውን አጠንክረው ተከራክረዋል።
በዚሁ መሰረት ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መዝገቡን እንደመረመርነው የአሁን አመልካች (የስር ፍ/ቤት 2ኛ ተከሳሽ) አጥብቀው የሚከራከሩት የስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ አቶ ቢኒያም አሰፊ በተጠሪ ድርጅት ሲቀጠሩ የንብረት ክፍል ሰራተኛ ሆነው ሲሆን የዋስትና ግዳታዬም የስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ በንብረት ክፍል ሰራተኛነት ለሚያጎድለት ንብረት እና ገንዘብ እንጂ ከተቀጠሩበት ስራ ውጪ እንዱሰራ ተደርጎ ለደረሰው ጉድለት ሃላፉነት ሉኖርብኝ አይገባም በሚል ነው። የስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ አቶ ቢኒያም አሰፊ አጉድለዋል የተባለውን በአጠቃላይ .49 ያጎደለት የስራ መደባቸው ሳይቀየር የንብረት ክፍል ሰራተኛ ሆነው እየሰሩ በነበሩበት ወቅት ነው። የአመልካች የዋስትና ውል ግዳታ ሰራተኛው ተቀጥረው በሚያገለግለበት ወቅት ለሚደርሰው የገንዘብና የንብረት መጥፊትና መጉደል ተጠያቂ ለመሆን ነው። በመሆኑም አመልካች የገቡት የዋስትና ግዳታ ሰራተኛው በስራቸው ወቅት ለሚያደርሱት የገንዘብና የንብረት መጥፊትና መጉደል እንጂ ለሚከራከሩበት የንብረት መጉደል ብቻ ተብል አይደለም። የስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ ያጎደለትን ገንዘብ የድርጅቱ ሰራተኛ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት በእጃቸው የገባ ገንዘብ መጉደለ አመልካች ከገቡት የዋስትና ግዳታ ውል ውጪ የሚባል አይደለም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት አመልካችን በገቡት የዋስትና ግዳታ ውል መሰረት ሃላፉነት አለባቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም።
የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 24/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ፣ የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 16/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ መዝገብ ወጪና ኪሳራ ተቻቻለ ብለናል።
በዚህ መዝገብ
No topics extracted.