የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈጸመ ወንጀል ሲኖርና በዚህ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሉያስከስስም ሆነ ሉያስቀጣ አይችልም ፣ ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ የሚቋረጥ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 5/3/ አዋጅ ቁ. 622/2001 አንቀጽ 99፣ አዋጅ ቁ. 859/2006
No summary available.
ህዲር 06 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዲማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዐ/ህግ - አልቀረበም ተጠሪ፡- ሰይፈ አበበ ንጉሴ - በላለበት ታይቶ የተወሰነ በመሆኑ አልቀረበም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የአሁኑ አመልካች ለአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ተከሳሽ (ተጠሪ) አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 በመተላለፍ የኮንትሮባንድ እቃ የጉምሩክ ስርዓት ያልተፈጸመበት መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ እያለበት 21 ጀሪካን ዘይት ቀረጥና ታክስ መጠኑ በአጠቃላይ ብር 6025.45 (ስድስት ሺህ ሃያ አምስት ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም) የሆነ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሽንት ቤት ክፍል ውስጥ ተከማችቶ እጅ ከፍንጅ ስለተያዘ የኮንትሮባንድ እቃ ይዞ በመገኘት ወንጀል ፈጽሞ ተከሷል የሚል ነው።
ተከሳሽ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል ፍቃድ እያለኝ ከእኔ ላይ የተያዘው ስለሆነ ህጋዊ ነኝ ጥፊት የለብኝም በማለት ተከራክሯል። የስር ከሳሽ የአሁኑ አመልካች የሆነው ዐቃቤ ህግ ሁለት ምስክሮችን ያሰማ ሲሆን ተከሳሽም ሁለት መከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ አስመስክሯል። የጽሁፍ መከላከያ ማስረጃ በቀን 30/01/2004 ዓ/ም የተሰጠ እስከ 2007 ዓ/ም የታደሰ የምግብ ዘይት የንግድ ፈቃድ ተከሳሽ አቅርቧል።
ጉዲዩን የተመለከተው የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽን (የአሁኑ ተጠሪን) ተከላክሎል በማለት በወንጀል ስነስርዓት ህግ ቁጥር 149(2) መሰረት በነጻ እንዱሰናበት በማለት የአሁኑ አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ በወንጀል ስነስርዓት ህግ ቁጥር 195(1) መሰረት በመ/ቁ.200935 በቀን 01/07/2007 ዓ/ም ዘግቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ለማስለወጥ ነው።
የአቤቱታው ይዘት በአጭሩ፡-
አቤቱታው ተመርምሮ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ ትዕዛዝ ተሰጥቶ አመልካች ተጠሪን ፈልጎ ያለማግኘቱን ገልጾ ጥሪ በአዱስ ዘመን ጋዜጣ እንዱደረግ ጠይቋል። በዚሁ መሰረት ሀምላ 6 ቀን 2007 ዓ/ም በታተመ አዱስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎ ተጠሪ ስላልቀረበ በላለበት ታይቶ እንዱወሰን ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
የክርክሩ ሂደት አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ እንደተገለጸው ሲሆን ጉዲዩን ከስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ፤አመልካች ካቀረበው አቤቱታ እንዱሁም አጣሪው ከያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነውም በተጠሪ መኖሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ሸንት ቤት ውስጥ በክሱ የተጠቀሰው 21 ጀሪካን ዘይት ተይዟል። በክሱ ውስጥ የተጠቀሰ መጋዘን እየታደሰ ዘይቱ አዱስ ሸንት ቤት ውስጥ ከላልች የሱቅ እቃዎች ጋር መገኘቱን የከሳሽም ሆነ የተከሳሽ ምስክሮች በተመሳሳይ ሁኔታ መስክረዋል። ተከሳሽ (ተጠሪ) በ2004 ዓ/ም የተሰጠ የዘይት ንግድ ፍቃድ እስከ 2007 ዓ/ም ድረስ የታደሰውን ማቅረቡ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጧል። የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ተከላክሎል በማለት በነጻ አሰናብቷል። በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 መሰረት ተጠሪው ከተከሰሰበት ወንጀል ሃላፉነት ነጻ ለመሆን ለእቃው የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ መከፈለን የሚያስረዲ የዕቃው ጉምሩክ ዱክላራሲዮን (ሰነድ) የማቅረብ ህጋዊ ግዳታ እንዲለበት ተመልክቷል። በስር ፍርድ ቤት ተጠሪው የዘይት ንግድ ፈቃድ አለው ከመባለ በስተቀር ዘይቱን ከማንና ከየት እንደገዛ እንዱሁም ለገዛበት ዘይት የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ መከፈለን የሚያስረዲ የእቃው ጉምሩክ ዱክላራሲዮን (ሰነድ) ተጠሪ አቅርቦ አላረጋገጠም። ይህ በሆነበት ሁኔታ ተጠሪ ተከላክሎል ለማለት የሚያስችል ሆኖ አልተገኘም።
ሆኖም ግን አከራካሪ ሆኖ የታየው ተጠሪ በተከሰሰበት አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 ‛ህገ ወጥ እቃዎች ይዞ ስለመገኘት“ ተብል የተደነገገው ድንጋጌ ይህን አዋጅ በተካው በአዋጅ ቁጥር 859/2006 ላይ ወንጀል ሆኖ ተደንግጓል ወይስ አልተደነገገም? የሚለውነው። የአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 ላይ አልተደነገገም። በዚህ አዋጅ አንቀጽ 168 የተደነገገው ‛የኮንትሮ ባንድ ወንጀል“ በሚል ነው። ይህም በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91 ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ የተደነገገነው። በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 የተደነገገው በአዋጅ ቁጥር 859/2006 ካልተደነገገ ህጋዊ መፍትሓ (legal remedy) ምንድነው?
የሚለው ምላሽ ሉያገኝ ይገባል። ይህ አዋጅ ግን ይህንን ጥያቄ የሚመልስ የህግ መርህ አይደነግግም። በዚህ ጊዜ በኢፋዱሪ ህገ መንግስት የተደነገገው መሰረታዊ መርህ እንዱሁም በወንጀል ህጉ በመርህነት የተደነገገው ተግባራዊ ላደረግ ይገባል። በልላ አነጋገር በኢፋዱሪ ህገ መንግስትና በወንጀል ህግ ከተደነገገው መሰረታዊ መርህ አንጻር ታይቶ መተርጎም ይኖርበታል።
በኢፋዱሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 22 የወንጀል ህግ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑ የተደነገገ ሲሆን የኢፋዱሪ የወንጀል ህግ አዋጅ ቁጥር 414/1996 አንቀጽ 5 በተመሳሳይ መልኩ ደንግጎታል። በህገ መንግስቱ አንቀጽ 22(2) ድርጊቱ ከተፈጸመ በኃላ የወጣ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ከድርጊቱ በኃላ የወጣ ህግ ተፈጻሚነት ይኖረዋል በማለት ተደንግጓል። በወንጀል ህግ አንቀጽ 5(3) የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈጸመ ወንጀል ሲኖርና በዚህ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሉያስከሰሰም ሆነ ሉያስቀጣ አይችልም፤
ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ ይቋረጣል ተብል ተደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ የፈጸመው ድርጊት ምንም እንኳን በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 99 ላይ ወንጀል ሆኖ የተደነገገ ቢሆንም በዚህ አዋጅ ምትክ በተተካው አዋጅ ቁጥር 859/2006 ወንጀል ሆኖ አልተደነገገም። ስለዚህ በኢፋዱሪ ህገ መንግስት እና በወንጀል ህጉ በተደነገገው መሰረታዊ መርህ አንጻር ሲደመደም ተጠሪ ጥፊተኛ ተደርጎ ቅጣት የሚወሰንበት የህግ አግባብ የለም ብለናል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 44610 በቀን 22/04/2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 200935 በቀን 01/07/2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ከላይ በፍርድ ሀተታው የተገለጸውን የኢፋዱሪ ህገ መንግስቱንና የወንጀል ህጉን መሰረታዊ መርህ መሰረት ያደረገ ባይሆንም በውጤት ደረጃ ግን ልዩነት ስለላለው በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 195(2) (ለ) (2) መሰረት ጸንቷል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤትይመለስ።
No topics extracted.