ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው ጠቃሚ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ተፈጻሚነት ሉኖረው የሚገባው ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የወጣው ህግ ስለመሆኑ፣ በአዱሱ የጉሙሩክ አዋጅ ቁ. 859/2006 አንቀጽ 182 ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚነት ሉኖረው የሚገባው ክርክር ካላስነሳው ጉዲይ በላልች ህጎች የተመለከቱት ድንጋጌዎች በማይነካ ሁኔታ ስለመሆኑ፣ የኢ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 22/2/ የኢፋድሪ የወንጀል ህግ ጠቅላላ ክፍል በአንቀጽ 6 XV
No summary available.
ሐምል 20 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ነጂብ አደም አቡበከር - ጠበቃ ጌቱ ሶሬሳ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዐቃቤ ሕግ - ነስሪያ ሡልጣን - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ተጠሪ ያቀረበባቸውን ሁለት የወንጀል ክሶች የተመለከተው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሁለቱም ክሶች ጥፊተኛ በማለት በመዝገብ በ14/02/2006 ዓ.ም. እና በ22/02/2006 ዓ.ም. የሰጠባቸው እና በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ08/07/2006 ዓ.ም. በፍርድ የጸናው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ በነበሩት በአሁኑ አመልካች እና የተጠሪ ተቋም ሰራተኛ በነበሩት የስር 2ኛ ተከሳሽ አቶ ስዩም በላቸው ላይ በ15/03/2004 ዓ.ም. አሻሽል ያቀረበው ክስ ይዘት ባጭሩ፡በአንደኛ ክስ ተከሳሾቹ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) እና በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 95 (1) (ሐ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ 1ኛ ተከሳሽ ረዲት የጉምሩክ አስተላላፉ፣2ኛ ተከሳሽ ደግሞ የጉምሩክ መጋዘን ሰራተኛ ሆነው ሲሰሩ በ17/08/2003 ዓ.ም.
ተለይቶ ባልታወቀ ሰዓት 1ኛ ተከሳሽ ቁጥሩ C-5446/2011 የሆነ ሀሰተኛ ዱክላራሲዮን እና ሀሰተኛ የናሙና መጠየቂያ ፍርም ይዞ ወደ መጋዘን ቁጥር 8 በመቅረብ እና የዚሁ መጋዘን ሰራተኛ የነበረው 2ኛ ተከሳሽም በዚሁ ድርጊት በመተባበር በግል ተበዲይ ለትውልድ ምስክር አስመጪነት በመጋዘኑ ውስጥ የነበረውን ኮንቴይነር ቁልፍ ገንጥለው ቀረጥና ታክስን ጨምሮ የዋጋ ግምታቸው ብር 54,733.07 የሆነ ሁለት ቴላቪዥኖችን የወሰደ በመሆኑ አግባብ ካለው የባለስልጣኑ ሹም ፈቃድ ሳያገኙ እሽጎችን የመፍታት እና ምልቶችን የማንሳት ወንጀል አድርገዋል፤በሁለተኛ ክስ ተከሳሾቹ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) እና በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 94 (1) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ የባለስልጣኑን ሰነድች እና መለያዎች ወደ ሀሰት የመለወጥ ወንጀል አድርገዋል የሚል ነው።
አመልካቹ ያቀረቡት መቃወሚያ ውደቅ ተደርጎ የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ ወንጀለን አላደረግሁም በማለታቸው ፍርድ ቤቱ የግል ተበዲይን ጨምሮ በተጠሪው በኩል የተቆጠሩትን ስምንት ምስክሮች ከሰማ እና የተጠሪውን የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኃላ አመልካቹ እንዱከላከለ በሰጠው ብይን መሰረት ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ሶስት የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበው ያሰሙ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ሰነድችንም በመከላከያ ማስረጃነት አቅርበዋል።ፍርድ ቤቱም አመልካቹ ባሰሟቸው ምስክሮች እና ባቀረቧቸው ሰነድች በተጠሪ ማስረጃ የተመሰከረባቸውን ማስረጃ ማስተባበል አለመቻላቸውን ገልጾ በሁለቱም ክሶች በተጠቀሱባቸው ድንጋጌዎች ስር የጥፊተኝነት ውሳኔ ከሰጠባቸው በኃላ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብል ወንጀልቹ በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ደረጃ ያልወጣላቸው መሆኑን ገልጾ በሁለቱም ክሶች ወንጀለን በዝቅተኛ ደረጃ መድቦ ለእያንዲንደ ወንጀል መነሻ የሆነውን እንደቅደም ተከተለ ሰባት ዓመት እና አምስት ዓመት ደምሮ የ12 ዓመት ጽኑ እስራት መነሻ አድርጎ በመያዝ፣ይህ የቅጣት መጠን የሚወድቀው በአባሪ አንድ በእርከን 29 ስር መሆኑን በመግለጽ፣ወንጀለ የተደረገው በግብረአበርነት መሆኑን በምክንያትነት ይዞ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 84 (1) (መ) መሰረት ቅጣቱን በአንድ ማክበጃ ወደ እርከን 30 ከፍ በማድረግ እና ቀጥልም የቀድሞ ጸባይ መልካምነትን እና የቤተበሰብ አስተዲዲሪነትን በሁለት የማቅለያ ምክንያትነት ተቀብል ቅጣቱን ወደ እርከን 28 ዝቅ በማድረግ እና ለሁለቱ ወንጀልች የተቀመጠውን መነሻ መቀጮ እንደቅደም ተከተላቸው ብር 5,000 እና ብር 10,000 ደምሮ ተከሳሾቹ እያንዲንዲቸው በዘጠኝ ዓመት ጽኑ እስራት እና በብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) መቀጮ እንዱቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሁለቱ ተከሳሾች በተለያዩ መዝገቦች ያቀረቡትን ይግባኝ አጣምሮ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ በስር 2ኛ ተከሳሽ ላይ በ2ኛ ክስ ተሰጥቶ የነበረውን የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በመሻር እና በ1ኛ ክስ ስር የተሰጠበትን የቅጣት መጠን በማሻሻል በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እና በብር ሁለት ሺህ መቀጮ እንዱቀጡ ሲወስን የአሁኑን አመልካች ይግባኝ ግን ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጎ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማጽናት ውሳኔ ሰጥቷል።የስር 2ኛ ተከሳሽ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ያቀረቡት አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችልት በመዝገብ በ25/10/2006 ዓ.ም. በተሰጠ ትዕዛዝ ውድቅ የተደረገ መሆኑንም መዝገቡን አስቀርበን ተመልክተናል፡ አመልካች ለዚህ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች በ1ኛው ክስ ስር ጥፊተኛ መባላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ 2ኛውን ክስ በተመለከተ ግን ድርጊቱን መፈጸሙ ግምት የሚያስወስድ ነው የመባለን አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም፡-
አመልካቹ በሁለቱም የወንጀል ክሶች ጥፊተኛ የተባለት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም?
ቅጣቱ ሉሻሻል ይገባል ወይስ አይገባም?
የሚለትን ነጥቦች መሰረት በማድረግ ጉዲዩን መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ አመልካቹ ወንጀልቹን አላደረግሁም በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ተጠሪው ያቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ አጠቃላይ ይዘት ሲታይ አመልካቹ ረዲት የጉምሩክ አስተላላፉ ሆነው ይሰሩ የነበረ መሆኑን፣በስራው ደንብ መሰረት እሽጎች ተከፍተው ናሙና ሉወሰድ የሚችለው ባለዕቃውን፣የጉምሩክ ሹምን እና የመጋዘን ኃላፉውን ጨምሮ አግባብነት ያላቸው አካላት በተገኙበት መሆኑን፣አመልካች ሀሰተኛ የናሙና መጠየቂያ ቅጽ ይዘው በመቅረብ እና ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር በመተባበር ለናሙና ነው በሚል እሽጉን ከፍተው ሁለት ቴላቪዥኖችን የወሰደት ከእርሳቸው እና ከመጋዘን ጠባቂው ውጪ ላላ ሰው ባልተገኘበት መሆኑን፣በግል ተበዲይ አስመጪነት ከመጣው ዕቃ ውስጥ ናሙና እንዱወሰድ በባለስልጣኑ የተሰጠ ትዕዛዝ አለመኖሩን፣ ቴላቪዥኖቹ ከተወሰደ በኃላ አመልካች ሞባይል ስልካቸውን አጥፍተው ከግል ተበዲይ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ያቋረጡ መሆኑን እና መሰል ፍሬ ነገሮችን የሚያረጋግጥ ሲሆን ከተሰሙት የተጠሪ ምስክሮች መካከል በተጠሪ ተቋም መጋዘን የገቢ እና የወጪ ዕቃዎች መዝጋቢ መሆናቸውን የገለጹት 8ኛው ምስክር አመልካቹ ሰነደን በማቅረብ የስር 2ኛ ተከሳሽ ከሚጠብቁት መጋዘን ቴላቪዥኖቹን ይዘው ሲወጡ ማየታቸውን በማረጋገጥ የመሰከሩ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካቹ ወንጀልቹን አለማድረጌን ያስረደልኛል በማለት ያቀረቡት የሰው እና የሰነድ ማስረጃ የተጠሪን ማስረጃ ሉያስተባብል ያልቻለ ስለመሆኑ ፍሬ ነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የተሰጣቸው ሁለቱ የስር ፍርድ ቤቶች የተስማሙበት ጉዲይ ሲሆን በ1ኛ ክስ የተሰጠባቸውን የጥፊተኝነት ውሳኔ አስመልክቶ አመልካቹ ያቀረቡት የአቤቱታ ነጥብ በአጣሪው ችልትም ቢሆን ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን ከማስቀረቢያ ጭብጡ ይዘት መገንዘብ ይቻላል።2ኛውን ክስ በተመለከተ አመልካች ድርጊቱን መፈጸሙ ግምት የሚያስወስድ ነው የመባለን አግባብነት ለማጣራት በሚል በአጣሪው ችልት የተያዘውን ነጥብ በተመለከተ በመሰረቱ ይህ አነጋገር የተገለጸው በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ሲሆን የተገለጸውም የአሁኑን አመልካች በሚመለከት ሳይሆን የስር 2ኛ ተከሳሽን በሚመለከት ሆኖ ከድርጊቱ አጠቃላይ አፈጻጸም አንጻር 2ኛ ተከሳሽ በ1ኛው ክስ በተመለከተው ወንጀል ከአሁኑ አመልካች ጋር ወንጀለን በመተባበር ያደረገው ስለመሆኑ ግምት የሚወሰድበት ነው ተብል ነው።በልላ በኩል አመልካች ቴላቪዥኖቹን ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር መሆኑን እሽጉን ከፍቶ የወሰደው ሀሰተኛ የሆነ የናሙና መጠየቂያ ፍርም ለተጠሪ 8ኛ ምስክር በማቅረብ ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።ይህ በሁለተኛ ክስ የተመለከተው የባለስልጣኑ ሰነድችን ወደ ሀሰት የመለወጥ ተግባር ራሱን ችል በአዋጁ በወንጀልነት የተደነገገ በመሆኑ በማስረጃ በተረጋገጠው መሰረት አመልካቹ በ2ኛው ክስ ጭምር ጥፊተኛ መባለን የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም።ከይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ በግልጽ መገንዘብ እንደሚቻለው የስር 2ኛ ተከሳሽ ከ2ኛው ክስ በነጻ እንዱሰናበቱ የተደረገው የሰነደን ሀሰተኛነት ያውቁ የነበረ ወይም ማወቅ ይገባቸው የነበረ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በሚል እንጂ የሰነደ ሀሰተኛነት ጉዲይ ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኖ አይደለም። በመሆኑም አመልካቹን በሁለቱም ወንጀልች ጥፊተኛ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አላገኝንም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች ጥፊተኛ የተባለት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 ድንጋጌዎች ሲሆን ጉዲዩ በስር የመጀመሪያ ደረጃ እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ካገኘ በኃላ በዚህ የሰበር ደረጃ በክርክር ላይ ባለበት ሂደት አመልካቹ ጥፊተኛ ተብለውበት የነበረው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 ከ30/03/2007 ዓ.ም. ጀምሮ ተሽሮ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 ተተክቷል። አመልካች የተከሰሱባቸው ድርጊቶች በአዱሱ አዋጅም ቢሆን እንደቅደም ተከተላቸው በአንቀጽ 170 (1) እና በአንቀጽ 167 (1) ስር በወንጀልነት ተደንግገዋል።ለ2ኛው ክስ በቀድሞውም ሆነ በአዱሱ ሕግ የተደነገገው የእስራት ቅጣት መጠን ተመሳሳይ ሲሆን በ1ኛው ክስ በቀድሞው ሕግ በአንቀጽ 95 (1) (ሐ) ስር ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት ጽኑ እስራት ሉደርስ ይችል የነበረው የቅጣት መጠን ግን በአዱሱ ሕግ ከአምስት ዓመት ወደማያንስ እና ከአስር ዓመት ወደማይበልጥ ጽኑ እስራት ዝቅ የተደረገ መሆኑን ተገንዝበናል።
በአንድ በኩል አዱሱ የወንጀል ሕግ እንዱጸና ከተደረገ በኃላ አድራጊው ሕጉ ከመጽናቱ በፉት ላደረገው ወንጀል ሲፈረድበት ወንጀለን በፈጸመበት ጊዜ በስራ ላይ ከነበረው ሕግ ይልቅ አዱሱ ሕግ ቅጣትን የሚያቃልለት በሆነ ጊዜ ተፈጻሚ መደረግ የሚገባው በአዱሱ የወንጀል ሕግ የተመለከተው ቅጣት ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የወንጀል ሕግ ጠቅላላ ክፍል በአንቀጽ 6 ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን በልላ በኩል ደግሞ በላልች ሕጎች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጅ ቁጥር 859/2006 ከጸናበት ቀን በፉት የተጀመሩ ጉዲዮች ፍጻሜ የሚያገኙት በነበረው ሕግ መሰረት ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 182 ስር ተደንግጎ ይገኛል። በመሰረቱ ደርጊቱ ከተፈጸመ በኃላ የወጣ ሕግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው ጠቃሚ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ተፈጻሚነት ሉኖረው የሚገባው ድርጊቱ ከተፈጸመ በኃላ የወጣው ሕግ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ.
ሕገ መንግስት አንቀጽ 22 (2) ስር የተደነገገ ከመሆኑም በላይ አዋጅ ቁጥር 859/2006 ከጸናበት ቀን በፉት የተጀመሩ ጉዲዮች ፍጻሜ የሚያገኙት በነበረው ሕግ መሰረት ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 182 ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚነት ሉኖረው የሚገባው ክርክር ስላስነሳው ጉዲይ በላልች ሕጎች የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በማይነካ ሁኔታ ስለመሆኑ ከላይ ከተጠቀሰው የአዋጁ አንቀጽ 182 ድንጋጌ አነጋገር መገንዘብ የሚቻል በመሆኑ በተያዘው ጉዲይ በአዋጁ አንቀጽ 182 የተመለከተው ድንጋጌ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የወንጀል ሕግ ጠቅላላ ክፍል በአንቀጽ 6 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተፈጻሚነት የማያስቀር መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም በ1ኛው ክስ በአመልካቹ ላይ ለሚጣለው ቅጣት መሰረት ተደርጎ መያዝ የሚገባው በአዱሱ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 በአንቀጽ 170 (1) ስር የተመለከተው የቅጣት መጠን ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል አመልካቹ ወንጀልቹን ያደረጉት በ17/08/2003 ዓ.ም. ሲሆን የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ የተሰጠባቸው ደግሞ እንደቅደም ተከተለ በ14/02/2006 ዓ.ም. እና በ22/02/2006 ዓ.ም. ነው።ይህንኑ ጊዜ መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች ቅጣቱ የተሰላውም ከጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በስራ ላይ በዋለው የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በማድረግ ነው።የጥፊተኝት እና የቅጣት ውሳኔ በተሰጠበት ጊዜ በስራ ላይ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ይልቅ ለተከሳሽ ወገን ቅጣቱን የሚያቀለው ወንጀለ በተደረገበት ጊዜ በስራ ላይ የነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ከሆነ ለቅጣቱ አወሳሰን መሰረት ተደርጎ መያዝ የሚገባው ይኸው መመሪያ ስለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ እና በላልችም መዝገቦች በሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ለቅጣቱ አወሳሰን መሰረት ተደርጎ መያዝ የሚገባው የቀድሞው መመሪያ መሆኑን ተገንዝበናል።ከላይ በተገለጸው ሁኔታ በሁለቱ ወንጀልች በአመልካቹ ላይ ሉጣል የሚገባው መነሻ ቅጣት የአስር ዓመት ጽኑ እስራት ሲሆን ይህም በአባሪ አንድ በእርከን 27 ስር የሚወድቅ ነው።ይህ የቅጣት መጠን በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ባገኘው አንድ የማክበጃ ምክንያት ወደ እርከን 28 ከፍ ከተደረገ በኃላ በተመሳሳይ ሁኔታ በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ባገኙት ሁለት የማቅለያ ምክንያቶች ወደ እርከን 24 ዝቅ የሚደረግ በመሆኑ በአመልካቹ ላይ ለሚጣለው ቅጣት መነሻ ተደርጎ መያዝ የሚገባው በእርከን 24 ስር የተመለከተው የቅጣት ፍቅድ ስልጣን ነው።በተመሳሳይ ምክንያት በመቀጮው መጠን ላይም ተገቢው ማሻሻያ ላደረግበት የሚገባ መሆኑን ተገንዝበናል።
ሲጠቃለል በአመልካቹ ላይ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ባይሆንም ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች በአመልካቹ ላይ ተጥል የነበረው የቅጣት መጠን ሉሻሻል የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በአመልካቹ ላይ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሁለቱም ክሶች በመዝገብ በ14/02/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ08/07/2006 ዓ.ም. በፍርድ የጸናው የጥፊተኝነት ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 195 (2) (ለ) (2) መሰረት ፀንቷል።
በአመልካቹ ላይ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሁለቱ ክሶች በመዝገብ በ22/02/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ08/07/2006 ዓ.ም. በፍርድ የጸናውን የዘጠኝ ዓመት ጽኑ እስራት የብር አስራ አምስት ሺህ መቀጮ የቅጣት ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 195 (2) (ለ) (2) መሰረት በማሻሻል አመልካቹ በዚህ ጉዲይ የታሰሩበት ጊዜ ሁለ ታስቦላቸው በሰባት ዓመት ጽኑ እስራት እና በብር ስምንት ሺህ መቀጮ እንዱቀጡ ወስነናል።
በተሻሻለው የጽኑ እስራት ቅጣት ውሳኔ መሰረት እንዱያስፈጽም የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ከመሸኛ ትዕዛዝ ጋር አመልካቹ ለሚገኙበት የአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት ይላክ።
ለአመልካቹም በዚያው በኩል ይድረስ።
እንዱያውቁት የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይላክ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.