ከፉል የዲኝነት ሰልጣን ላለው አካል በፍሬ ነገር ደረጃ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ መሆኑ በግልፅ ተቀምጦ እያለ፤ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በሕግ አተረጎጎም ረገድ ብቻ የተሰጠውን ስልጣን በማለፍ ማሰረጃን በመመዘን በፍሬ ነገር ላይ የሚሰጠው ድምዲሜ ሰርዓቱን የተከተለ ስላለመሆኑ ፤ የአ/ብ/ክ/መ/ መገናኛ ብዙሀን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ 200/2005 አንቀፅ 13(2) XIV ክልልች ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ የሚነሱ ይግባኞች መቅረብ ያለባቸው ከፋደራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጋር አቻ ስልጣን ላላቸው በየክልለ ላለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልቶች ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 154 የዑ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/2/ አዋጅ ቁ. 322/95 ( አሥር ሰዎች) እና ኢትዩ ቴላኮም ጉሙሩክ 185
No summary available.
ህዲር 13 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድ የተጀመረ ነው። ክርክሩ የበርሃ አበል ከደመወዝ ጋር ተደምሮ የገቢ ግብር እንዱከፈልበት መደረጉ ያላግባብ ነው በሚለው የአመልካቾች ክስ መነሻ የተጀመረ ነው።
አመልካቾች ለስራ ወደ ጉጂ ዞን ሉበን ወረዲ ነገላ ከተማ አስተዲደር በነገላ ቦረና ሾፕ ስር ተጠሪ መድቧቸው በመስራት ላይ እያለ በዚሁ አካባቢ ለሚሰሩ ሰራኞች 30% የበረሃ አበል ምክንያት እስከ ግንቦት ወር 2004 ዓ/ም ድረስ ሲከፈላቸው መቆየቱንና ከግንቦት ወር 2004 ዓ/ም በኋላ ግን ባልታወቀ ምክንያት ይከፈላቸው የነበረው የ30% የበርሃ አበል ላይ በወር ከሚያገኙት ደመወዝ ጋር በመደመር ያላግባብ ግብር እየተቆረጠባቸው ከፍተኛ የመብት ጉዲት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልፀው ይኼው የተጠሪ እርምጃ ተገቢ ያለመሆኑ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው የመከላከያ መልስ ክርክርም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክርን የሚመለከት ነው። ተጠሪ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያት ያነሳውም ጉዲዩ በቦርደ ስልጣን ስር የሚወድቅ አይደለም የሚል ሲሆን መቃወሚያው የቀረበለት ቦርድም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 147(1(ሀ)) ስር ስልጣኑ በግልጽ መደንገጉንና የአመልካቾች ጥያቄ ደግሞ በዚህ ድንጋጌ ስር የማይወድቅ መሆኑን ገልጾ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት ብይን ሰጥቷል። በዚህ ብይን የአሁኑ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ አመልካቾች ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን ስር እንደሚወድቅ አምነው በቦርደ ላይ ክስ ከአቀረቡና ተጠሪም ይህንኑ በመቃወሙ በተሰጠው ብይን ላይ ይግባኙ መቅረብ ያለበት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 139 (ለ) መሰረት በክልለ ላለው የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሳይሆን በአዋጁ አንቀፅ 154 በተደነገገው መሰረት ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው በማለት ይግባኛቸውን ሰርዞታል። በዚህ ብይን አመልካቾች ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበውም ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ችልቱ የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ሙለ በሙለ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ጉዲዩ የወል የሥራ ክርክር ሁኖ እያለ ቦርደ በስልጣኔ ስር አይወድቅም ማለቱም ሆነ የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙ የሚቀርበው ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው በማለት ብይን ሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት መፅናቱ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ የጹሐፍ መልስ የሰጠ ሲሆን በመልሱ ላይም ጉዲዩ በቋሚ ቦርድ ስልጣን ስር እንደማይወድቅና ጉዲዩን ለማየት የሚችል አካልም በአዋጅ ቁጥር 466/97 አግባብ በክልለ ያለ ቋሚ ቦርድ ያለመሆኑን፣ ተጠሪ እጅግ አስፈላጊ ከሚባለት መንግስታዊ የልማት ድርጅቶች መካከል አንደ በመሆኑ የአመልካቾች ጥያቄው በክስ ላታይ የማይችል መሆኑን ዘርዝሮ በአመልካቾች የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም በማለት ተከራክሯል።
ይህም ችልት በቅድሚያ ምላሽ ሉሰጠው የሚገባው አቢይ የህግ ነጥብ ላይ ብቻ በማተኮር መዝገቡን መርምሯል። በዋነኛነት ሉፈታ የሚገባው የነገሩ ጭብጥ፡- አንድ ጉዲይ የወል የስራ ክርክር ነው በሚል እምነት በቋሚ ቦርደ ከቀረበ በኋላ ቋሚ ቦርደ በስልጣኑ ስር የማይወድቅ መሆኑን ገልፆ መዝገቡን ሲዘጋው ይግባኙ መቅረብ ያለበት ለየትኛው ፍርድ ቤት ነው? የሚለው ጉዲይ ነው።
ለተያዘው ጭብጥ ምላሽ የማግኘቱ ጉዲይ ስለ ስራ ክርክር፣ ስለ ቦርድና ስለ ፍርድ ቤት ሥልጣን የሚገልጹትን የአዋጅ ቁ. 377/96 ድንጋጌዎችን ተመስርቶ ጭብጡን መመርመርን ይጠይቃል።
አዋጅ ቁጥር 377/96 ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 በኋላ የወጣ ሲሆን በአንቀጽ 136(3) ስለ ስራ ክርክር ምንነት ትርጓሜ የሚሰጥ ድንጋጌ ከመያዙም በላይ የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 137 ደግሞ የስራ ክርክር ችልት መቋቋማቸውን በግልፅ ያስቀምጣል። በዚህም መሰረት የአዋጁ አንቀጽ 147 ስለቦርድ ሥልጣን የሚደነግገው ሲሆን የፍ/ቤት ስልጣን ደግሞ የሚደነግገው የአዋጁ አንቀጽ 138/2/ ነው። በአዋጁ አንቀጽ 138/1/ የተዘረዘሩትንና መሰል የግል የሥራ ክርክሮችን የመዲኘት ሥልጣን ለፍርድ ቤት መስጠቱን ከዚህ ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። አዋጁ የስራ ክርክርን የክልልና የፋዳራል ጉዲይ ነው የሚል መለኪያ በመስጠት የስነ-ነገር የዲኝነት ስልጣን መከፊፈለን በግልፅ አያሳይም። በአዋጅ ቁጥር 322/95"ም" ሆነ በሕገ መንግስቱ መሰረት የክልለ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስራ ክርክርን አስመልክቶ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣንን በውክልና ሉመለከት ይችላል የሚባልበት አግባብም የለም። በአዋጁ አንቀፅ 138(1) ድንጋጌ መሰረት ለፍርድ ቤት የተሰጡትን የስራ ክርክሮችን በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት(የወረዲ ፍርድ ቤት) መሆኑ በግልፅ ተቀምጧል። የአዋጁ አንቀጽ 139(1(ሀ)) ደግሞ በክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በስራ ክርክር ችልት የተሰጡ ውሳኔዎች ላይ የክልለ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የስራ ክርክር ችልት የይግባኝ ስልጣን እንዲለው ያሳያል።
በመሆኑም የክልለ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የስራ ክርክር ችልት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 138 መሰረት በክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሚታዩት ጉዲዮች ላይ የይግባኝ ስልጣን ያለው መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 139(1(ሀ)) በግልፅ ያሳያል።
በልላ በኩል በክልል በተቋቋሙ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድች በሚሰጡ ብይኖች እና ውሳኔዎች ይግባኙ የሚቀርበው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 154 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 466/97 ድንጋጌዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መሆኑ ይታወቃል።
በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 154 እንደተመለከተው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ በተሰጠ ብይን ወይም ውሳኔ ላይ ይግባኝ መቅረብ ያለበት ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ ተደንግጓል። በአዋጅ ቁጥር 322/95 ከተደነገገው ውጪ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች በመደበኛነት የተዋቀሩት በአዱስ አበባና በድሬዲዋ ከተማ አስተዲደሮች መሆኑ ይታወቃል።፡ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 78/2/ እንደተደነገገው ክርክር የተነሣበትን ክልል ጨምሮ በአፊር፣ በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በሱማላና በደቡብ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስታትም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለመደራጀቱ በአዋጅ ቁጥር 322/95 አንቀጽ 2 ስር በግልጽ ተደንግጓል።
ይህ ማለት ግን በአዋጅ ቁጥር 377/96 የተዘረጋውን የይግባኝ ስርዓት ቀሪ የሚያደርግ አይደለም። በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። ስለሆነም ሰራተኞች ተጠሪን ከሚመስለ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጋር በክልልች የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድች በሚያቀርቧቸው ክሶች የሚነሱ የይግባኝ ቅሬታዎች ላይ ይግባኝ ማቅረብ ያለባቸው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 154(1) ስር የተቀመጠውን መሰረት በማድረግ በአዋጅ ቁጥር 322/95 የተደነገገውን ስርዓትና በሕገ መንግስቱ በተሰጠው የውክልና ስልጣን አግባብ ሳይሆንን በአዋጀ ቁጥር 377/96 በተዘረጋው የይግባኝ አቀራረብ ስርዓት ነው።
ከዚህ አንጻር ሲታይ በአዋጅ ቁጥር 322/95 አግባብ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸውና ባልተደራጀባቸው ክልልች ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ የሚነሱ ይግባኞች መቅረብ ያለባቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 80(2) ድንጋጌ መሰረት ከፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋር አቻ ስልጣን ላላቸው ለክልለ ላለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልቶች ስለመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 154 መገንዘብ የሚቻል ሁኖ ተገኝቷል።
ስለሆነም አመልካቾች ጉዲዩ የወል የስራ ክርክር ነው የሚል የዲኝነት ጥያቄ መሰረት ባደረገ መልኩ ክስ ያቀረቡ ስለመሆናቸው የክርክሩ ሂደት ስለሚያሳይ እና ይኼው ጥያቄ የቀረበት ቦርድ ደግሞ ተገቢ ነው ያለውን ብይን ከሰጠ በዚሁ ብይን ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ይግባኙን ማቅረብ ያለበት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 154(1) እና ለዚህ ድንጋጌ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ለደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ነው። የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጉዲዩ ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ የተነሳ መሆኑን የተገነዘበና ራሱ ይግባኙን አላይም በማለት ብይን መስጠቱ ተገቢ ቢሆንም ጉዲዩ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት በማለት ብይን መስጠቱ ግን ከላይ የተዘረዘረውን የሕግ ማዕቀፍና ስለሕግ ማዕቀፈ ትክክለኛ አተገባበር ይህ ችልት የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ያላገናዘበ በመሆኑና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም በዚህ ረገድ የተፈጸመውን የሕግ ስህተት ሳያርም ብይኑን ማፅናቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈጸሙን የሚያሳይ ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስናል።
ው ሣ ኔ
በሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሰኔ 01 ቀን 2007 ዓ/ም የጸናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽልአል።
ጉዲዩ በይግባኝ ስልጣን ደረጃ ላታይ የሚገባው በክልለ በተደራጀው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሳይሆን በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ነው ብለናል።
አመልካቾች አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላለ ብለናል።
No topics extracted.