ከፉል የዲኝነት ሰልጣን ላለው አካል በፍሬ ነገር ደረጃ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ መሆኑ በግልፅ ተቀምጦ እያለ፤ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በሕግ አተረጎጎም ረገድ ብቻ የተሰጠውን ስልጣን በማለፍ ማሰረጃን በመመዘን በፍሬ ነገር ላይ የሚሰጠው ድምዲሜ ሰርዓቱን የተከተለ ስላለመሆኑ ፤ የአ/ብ/ክ/መ/ መገናኛ ብዙሀን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ 200/2005 አንቀፅ 13(2) XIV ክልልች ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ የሚነሱ ይግባኞች መቅረብ ያለባቸው ከፋደራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጋር አቻ ስልጣን ላላቸው በየክልለ ላለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልቶች ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 154 የዑ.ፋ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/2/ አዋጅ ቁ. 322/95 ( አሥር ሰዎች) እና ኢትዩ ቴላኮም ጉሙሩክ 185
No summary available.
ሀምላ 22 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት - ነ/ፈ አብርሃም ጌቴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዲንኤል ከፊለ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ወስነናል ።
ጉዲዩ ተጠሪ በስራ ገበታቸው ባለመገኘታቸው የዱሲፕሉን ቅጣት ተቀጥተው እያለ በዚህ ሳይታረሙ ሃሰተኛ የህክምና ፈቃድ ማስረጃ በማቅረብ ከባድ የድሲፕሉን ጥፊት ፈፅመዋል ተብል ከስራ እንዱሰናበቱ በአመልካች ድርጅት የበላይ አካል የተሰጠው ውሳኔ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች ታይቶ ውሳኔው መሻሩን በመቃወም አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ይመለከታል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው የአሁን ተጠሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ እንደማንኛውም ታካሚ ካርድ አውጥቼ የታከምኩ በመሆኑና ማስረጃውን ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል መቀበላ ባልተካደበት ሁኔታ በካርደ ላይ የበሽታው አይነት አልተጠቀሰም በሚል ምክንያት የህክምናው ማስረጃ በሃሰት የቀረበ ነው ተብል ጥፊተኛ ተብየ መቀጣቴ አግባብ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች በሰጡት መልስ የይ/ባይ ቅሬታ የፍሬ ነገር እንጅ የህግ ስህተት ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም፤ ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተም ይ/ባይ በሃሰት የተዘጋጀ የህክምና ፈቃድ ማስረጃ ያቀረበ ለመሆኑ ማስረጃውን ሰጠ የተባለው ሆስፒታል ያረጋገጠና ጥፊቱ ከባድ ከመሆኑም በላይ ከዚህ በፉትም በዱሲፕሉን የተቀጣ በመሆኑ ከስራው እንዱሰናበት መወሰኑ ተገቢ ነው ተብል ውሳኔው እንዱፀና ተከራክረዋል።
የይግባኝ ክርክሩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተሻሻለው የክልለ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 200/2005 አንቀፅ 13(2) መሰረት ቦርደ በፍሬ ነገር ረገድ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ሲሆን ውሳኔው የህግ ስህተት ያለበት ከሆነ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ለማየት ስልጣን እንዲለው መደንገጉን፤ ከዱሲፕሉን መመሪያው አንፃር ከስራ ሉያሰናብተው የሚችል ጥፊት ፈፅሟል/አልፈፀመም የሚለው ጭብጥ የህግ ክርክር በመሆኑ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን እንዲለው፤ ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተም በድርጅቱ የሥነ ምግባር እና የድስፕሉን መመሪያ ቁጥር 002/2006 አንቀፅ 24(3) መሰረት ሃሰተኛ ማስረጃ ማቅረብ ከባድ የዱሲፕሉን ጥፊት መሆኑ መደንገጉን፤ ማስረጃውን ሰጠ የተባለው ሆስፒታል የማስረጃውን ትክክለኛነት እንዱያረጋግጥ ተጠይቆ የህክምና ካርደን አውጥቶ በመመልከት ህመሙን የሚያስረዲ ነገር ካርደ ላይ ያልተገለፀ በመሆኑ የህክምና ማስረጃው ህጋዊ አይደለም የሚል ምላሽ መፃፈን፤ ነገር ግን የህክምና ፈቃድ ማስረጃው ከሆስፒታለ የተሰጠ ለመሆኑ ባልተካደበት ሁኔታ በካርደ ላይ የበሽታው አይነት አልተገለፀም በሚል ምክንያት ተጠሪ ሀሰተኛ ማስረጃ አቅርቧል ተብል ጥፊተኛ መባለ አግባብ አይደለም በማለት የዱሲፕሉን ኮሚቴው እና ዋና ስራ አስኪያጁ እንዱሁም ቦርደ የሰጡትን ውሳኔ በመሻር ተጠሪ ያልተከፈለው ደመወዝ ተከፍልት ወደ ስራው እንዱመለስ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ቅሬታ የቀረበለት የክልለ ሰበር ችልት ቅሬታውን ሳይቀበል ቀርቷል።
አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይህን በመቃወም ነው። ህዲር 3/2008 ዓ.ም ያቀረቡት የሰበር ማመልከቻ ተመርምሮ የፈለገ ህይወት ሆስፒታል ተጠሪ ያቀረበው የሐኪም ማስረጃ ህጋዊ አይደለም በማለት እያረጋገጠ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ሐሰተኛ ሰነድ አላቀረበም በማለት ወደ ስራው እንዱመለስ የመወሰኑን አግባብ ለማጣራት ሲባል መዝገቡ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ እና ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፅሁፍ እንዱለዋወጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከፍ ሲል በተጠቀሰው የድርጅቱ ማቌቌሚያ አዋጅ ፍሬ ነገሩን ለማጣራት እና ማስረጃውን ለመመዘን ስልጣን የተሰጠው የድርጅቱ የበላይ አካል ተጠሪ በተደጋጋሚ በስራ ገበታው የማይገኝ፤ በምክር እና በቅጣትም ሉመለስና ሉማር ያለመቻለን፤ እንዱሁም ከስምሪትና ከተቌሙ ፈቃድ ውጪ ሰቆጣ መሄደ እና እዚያ የታየ ስለሆነ ለዚሁ እንዱረዲው ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል የ10 (አስር) ቀን የህክምና ማስረጃ ማምጣቱን፤ ሆስፒታለም ስለማስረጃው ትክክለኛነት ተጠይቆ የተሰጠው የሀኪም ማስረጃ ትክክለኛ አለመሆኑን ገልጾ መፃፈን ፤ ይህም በተቌሙ የዱሲፕሉን መመሪያ አንቀፅ 23 መሰረት ከስራ የሚያሰናብት ከባድ ጥፊት መሆኑን በማረጋገጥ ከ19/05/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከተቋሙ እንዱሰናበት ወስኗል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህን ውሳኔ የሻረው የህክምና ፈቃድ ማስረጃው ከሆስፒታለ የተሰጠ ለመሆኑ አልተካደም፤ በካርደ ላይ የበሽታው አይነት ሳይገለፅ መገኘቱም ተጠሪ ሀሰተኛ ማስረጃ አቅርቧል አያሰኝም በማለት ነው። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ስልጣን ያለው አካል በፍሬ ነገር ረገድ ያረጋገጠውን ሳይቀበል ማለፈና ማስረጃውን በመመዘን የራሱ መደምደሚያ ላይ መድረሱ በህጉ የተሰጠውን ስልጣን የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም። ፍርድ ቤቱ ማስረጃውን ይመዝን ቢባል እንኳ የህክምና ማስረጃው ወጣ የተባለበት የፈለገ ህይወት ሆስፒታል ሜዱካል ዲይሬክተር በቁጥር 959/2687/06 በ26/12/06 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ ከሆስፒታለ ተወሰደ የተባለው የሀኪም ዕረፍት ማስረጃ በተመለከተ አጣርቶ ህጋዊ አለመሆኑን እያረጋገጠ ፍርድ ቤቱ ማስረጃው ከሆስፒታለ የተሰጠ ለመሆኑ እስካልተካደ ሀሰተኛ ልባል አይችልም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ተገቢ አይደለም። መብት ወይም ጥቅም ለማግኘት ሲባል አንድን ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ የሚያስችለ በማስረጃነት የሚቀርቡ ፅሁፍችን (ሰነድችን) በሃሰት መፍጠርም ሆነ በእነዚህና መሰል ፅሁፍች መገልገል የድሲፕሉን እና የወንጀል ጥፊተኝነትን የሚያስከትል በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የደረሰበት ውሳኔ በህጉ የተደነገገውን መሰረት ያደረገ አይደለም። ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ማስረጃውን በተመለከተ የሰጠው ትርጉምና የደረሰበት መደምደሚያ እንዱሁም ይህን ተከትል ያሳለፈው ውሳኔ ህጋዊ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ የአመልካች ድርጅት የበላይ አካል (ቦርደ) በፍሬ ነገር ረገድ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ ይኸው አካል በፍሬ ነገር ረገድ በደረሰበት መደምደሚያ ላይ ተመስርቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተመልክቶ ውሳኔው የህግ ስህተት ያለበት ከሆነ ማረም ሲገባው ከዚህ አልፍ ፍሬ ጉዲዩን ለማጣራት ማስረጃውን መመዘኑ ህጉን የተከተለ ካለመሆኑም በላይ ፍርድ ቤቱ ማስረጃውን በመመዘን የደረሰበት መደምደሚያም የተሻሻለውን የክልለ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 200/2005 አንቀፅ 13(2) እና አመልካች ያወጣውን የሥነ ምግባር እና የዱስፕሉን መመሪያ ቁጥር 002/2006 አንቀፅ 24(3) ድንጋጌዎች እንዱሁም በሃሰተኛ ማስረጃ ስለመገልገል በህጉ የተደነገገውን የጣሰና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ሰላገኘነው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያሳለፈው ውሳኔ እና የሰበር ችልቱ የሰጠው ትዕዛዝ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአማራ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 40498 ጥቅምት 02 ቀን 2008 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ እንዱሁም የክልለ ሰበር ችልት በሰ/አ/መ/ ጥቅምት 18 ቀን 2008 ዓ/ም ያሳለፈው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ በ7/5/2007 ዓ.ም፤ እንዱሁም ቦርደ በ22/7/2007 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.