የአዱስ አበባ ከተማ ቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የቤት ባለቤትነት ክርክርን አጣርቶ የመወሰን ስልጣን የላለው አቶ ተክለስላሴ ገላን እና ልደታ/ክ/ከ/የመ/ል/ከተማ ልማት ጽ/ቤት
No summary available.
ግንቦት 24 ቀን 2008ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሹ ሺርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ድጋፋ ታደሰ - ጠበቃ ሞገስ ናደው ቀርቧል ተጠሪዎች፡-
ለክርክር መነሻ የሆነው የአሁኑ አመልካች የውርስ ሃብት ይጠራልኝ ሲለ ባቀረቡት አቤቱታ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችልት ነው።
የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ፡- አባታቸው አቶ ታደሰ አበበ ሐምል 11 ቀን 1974 ዓ.ም ከዚህ አለም የተለዩ ሲሆን ወራሽነታቸው የካቲት 11 ቀን 1975 ዓ.ም በመ/ቁ. 830/75 ያረጋገጡ መሆናቸው፤ ተጠሪዎች የወላጅ አባታቸው በጉለላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 8 ውስጥ የሚገኘውን የቤት ቁጥር 092 የሆነውን መኖሪያ ቤት ይዘው ስለሚገኙ የውርስ ሃብት ይጣራልኝ በማለት አመልክተዋል።
የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ የቀረበውን አቤቱታ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የውርስ ሃብት ይጣራልኝ ጥያቄ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1000/1/2/ መሰረት የውርስ ሃብቱ በተጠሪዎች መያዙን ካወቁ ሶስት አመት ካለፈ በኋላ የቀረበ ስለሆነ በይርጋ ይታገዲል። በፍሬ ጉዲዩ ላይም የውርስ ሐብቱ ተመዝግቦ የሚገኘው በተጠሪዎች ስም እንጂ በአባታችን አይደለም። በዚህ ንብረት ላይ ከፍተኛ ንብረት አፍሰውበት ይዘው እንደሚገኙ በመግለፅ አቤቱታው ውድቅ እንዱደረግላቸው መከላካያ መልሳቸውን አቅርበዋል።
በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የአሁን 2ኛ ተጠሪ በክርክሩ ጣልቃ እንዱገባ በመፍቀድ ክርክር ካከሄደ በኋላ አመልካች አባታቸው ከሞቱ በኋላ በ1975 ዓ.ም ወራሽነታቸው ያረጋገጡት በፍ/ብ/ህ/ቁ.1000/1/ የተጠቀሰው የ3 ዓመት ይርጋ ጊዜ ሳያልፍ ስለሆነ የቀረበው መቃወሚያ በብይን ውድቅ በማድረግ፤ የውርስ አጣሪ በመሾም ከዚያም በውርስ አጣሪው የቀረበውን ሪፖርቱ ለህግና ለሞራል ተቃራኒ ስላልሆነ በማለት ተቀብል መዝግቦታል።
ይህ ውሳኔ በመቃወም የአሁኑ ተጠሪዎች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት ፍርድ ቤትም አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1000/1/ መሰረት በ3 ዓመት ይርጋ ይታገዲል በማለት የስር ፍርድ ቤት የተሰጠው ብይንና ውሳኔ በመሻር ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቤቱታው ቢያቀርብም በትእዛዝ ሰርዞታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስሕተት የተፈፀመበት ስለሆነ እንዱታረም በማለት የቀረበ ነው። የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ፡- ያቀረብኩት አቤቱታ ወራሽነቴን አረጋግጫለሁ በማናቸውም ጊዜ ውርስ ሀብቱን ለመካፈል የፍ/ብ/ህ/ቁ.1060 አስከ 1113 ባለው ህግ ስር የተሸፈነ ስለሆነ በይርጋ የማይተገድ እያለ ይታገዲል ተብል የተሰጠ ውሳኔ የተፈፀመው መሰረታዊ የህግ ስህተት በማረም የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ በማፅናት እንዱወሰንለት አቤቱታውን አቅርበዋል።
የቀረበው የሰበር አቤቱታ በመመርመር አመልካች በወቅቱ ወራሽነቱን ማረጋገጡ አልተካደም ተጠሪዎችም የውርስ ንብረቱን በስማቸው በማዞር ካርታ ያሰሩት በ2004 ዓ.ም ከመሆኑ አንፃር የአመልካችን የውርስ ንብረት ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ነው የመባለን አግባብነትና የይርጋ ጊዜው መቆጠር ያለበት ተጠሪዎች ንብረቱን በሰማቸው አድርገው ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ነው ወይስ ሟች ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ ነው የሚለውን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል።
በዚሁ መሰረትም ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት በታዘዘው መሰረት ታህሳስ 14 ቀን 2008 ዓ.ም የተፃፈ 2 ገጽ መልስ አቅርቧል። አመልካች በበኩለ ጥር 26 ቀን 2008 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን በማቅረብ ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመርነውም አመልካች ያቀረብኩት አቤቱታ ወራሽነቴን አረጋግጫለሁ በማናቸውም ጊዜ የውርስ ሀብቱን ለመካፈል የፍ/ብ/ህ/ቁ.1060 አስከ 1113 ባለው ህግ ስር የተሸፈነ ስለሆነ በይርጋ አይታገድም የሚል ነው። በተጠሪዎች በኩል ደግሞ አመልካች በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1060 ተጠቃሚ የሚሆነው በወቅቱ ውርስ አጣርተው የዉርሱ ንብረት በወራሾች የጋራ ስም ተመዝግቦ ወይም ታውቆ የተቀመጠ የውርስ ሀብቱን እንከፊፈል ብል ለሚጠይቅ እንጂ የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄ ለሚያቀርብ አይደለም። በስር ፍርድ ቤት የቀረበው የውርስ ሃብት ይጣራልኝ ስለሆነ አቤቱታና ሪፖርት በይርጋ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው የሚል ነው።
የአመልካች አቤቱታ ተጠሪዎች የውርስ ሀብት ስለያዙ የውርስ ሀብት ይጣራልኝ የሚል መሆኑ በስር መዝገብ ተመልክቷል። ከቀረበው አቤቱታ በመነሳት ነው በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የውርስ ሀብት የሚያጣራ በመሾም ሪፖርት ሉቀበል የቻለው። ስለሆነም አመልካች የውርስ ይጣራልኝ ሳይሆን የውርስ ሀብት ክፍፍል ስለሆነ በይርጋ የሚታገድ አይደለም የሚል ክርክር፤ በስር ያልተነሳና ክርክር ያልተካሄደበት በዚህ ደረጃ መነሳቱ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 83 እና 329/1/ መሰረት ተቀባይነት የላለው ነው።
በልላ በኩል የአመልካች አቤቱታ ይዘት ሲመረመር ለአቤቱታ መነሻ የሆነው የውርስ ሀብት ነው የተባለው ቤት ይዘው የሚኖርበት ወይም በኪራይ በልላ አግባብ ተጠቃሚ መሆናቸው የሚያመለክት ክርክር የለም። አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጥያቄ የወራሽነት እንጂ የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1000/1/ መሰረት በሶስት ዓመት ዋጋ የሚታገድ ነው። ወራሾች ተለይተው የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ግን ደግሞ ክፍፍል ሳይደረግ የቆየውን የውርስ ሀብት በማናቸውም ጊዜ መጠየቅና በይርጋ የሚታገድ እንዲልሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ.
1060 እና ተከታዮቹ ቁጥሮች መረዲት ይቻላል። በተያዘው ጉዲይ ግን ውርስ ማጣራት በመሆኑ ወራሾች መለየት፤ኑዛዜ መኖሩን አለመኖሩን፤ ዕዲ ጠያቂዎች መኖራቸው አለመኖራቸው፤
የእያንዲንደ ወራሽ ድርሻ የሚታወቅበትና የሚጣራበት ነው። በመሆኑም የወራሽነት ጥያቄ አንድ ወራሽ በልላ በወራሽነት የውርስ ሀብት በያዘው ሰው ላይ ክስ ሲያቀርብ ተፈፃሚነት ባላው የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1000/1/ ድንጋጌ ስር በተመለከተው በሶስት አመት ይርጋ የሚገደብ በመሆኑ ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በዚህ ረገድ የፈጸሙት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለ ለማለት አልተቻለም። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.