በኦሮሚያ ከተማ አስተዲደር ውስጥ የሚነሱ የከተማ ቦታን ከማስለቀቅና ምትክ ቦታ እና ካሣን ከመክፈል አንጻር የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችን በመጀመሪያ ደረጃ የማየት ስልጣኑ በከተማው አስተዲደር የተዋቀረው አካል ስለመሆኑ፣ የኦሮሚያ ክልል የመሬት ሉዝ አዋጅ ቁ. 721/2004 አቶ አወል አማን (ሁለት ሰዎች) እና ወ/ሮ አሳለፈች እንዲግቤ /ሦስት ሰዎች/ XIII ቁ. 26፣27፣28፣29 እና 30 አዋጁን ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ቁጥር 155/2005 አንቀጽ 26፣55 እና 56
No summary available.
ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻዉ አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካቾች፡-
ይህ የሰበር ጉዲይ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ክስ መነሻ ያደረገ ነዉ። የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ፡ የአሁን አመልካቾች /የሥር ጣልቃ ገቦች/፣ የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች /የሥር ከሳሾች/፣ የአሁን 3ኛ ተጠሪ /የሥር ተከሳሽ/ ሆኖ ሲከራከሩ እንደነበር መዝገቡ ያመለክታል። የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ለእያንዲንዲችን 200 ካ.ሜ ቦታ እንዱሰጠን ተወስኖ በዚሁ መሰረት ካርታ የተሰጠን ቢሆንም 1ኛ ከሳሽ በእጄ የደረሰዉ ቦታ 90 ካ.ሜ ሲሆን፣ 2ኛ ከሳሽ ደግሞ በእጄ የገባዉ 110 ካ.ሜ ብቻ በመሆኑ ተከሳሽ እና ማዘጋጃ ቤት የተቀነሰዉን ቀሪ ቦታ አሟልቶ እንዱያስረክበን በማለት ከሷል። የሥር ተከሳሽ መጥሪያ ደርሶት ባለመቅረቡ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል። የሥር ፍ/ቤት ጉዲዩን በማየት በሰጠዉ ዉሳኔ ከሳሾች ለእያንዲንዲቸዉ 200 ካ.ሜ እንዱሰጣቸዉ ተወስኖ ካርታ ተሰጥቷቸዉ መሬት ቢሰጣቸዉም በካርታ ላይ የተጠቀሰዉ ሙለ ይዞታ በእጃቸዉ ስላልገባ ተከሳሽ እና ማዘጋጃ ቤት የተቀነሰዉን ቀሪ ቦታ አሟልቶ እንዱያስረክባቸዉ በማለት ወስኗል። ከዚህ በኋላ የአሁን አመልካቾች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.358 መሰረት ባቀረቡት የመቃወሚያ አቤቱታ ከሳሾች እና ተከሳሽ የተስማሙበት ይዞታ ጣልቃ ገቦች ከኃ/ስላሴ ጊዜ ጀምሮ በገጠር መሬት ይዘን የቤት ቁጥር 188 እና ግምቱ 500,000.00 የሚያወጣ ቤት ሰርተንበት እየተጠቀምን ያለን በመሆኑ፣ ተከሳሽ ንብረታችንን ለከሳሾች እንዲያስክረብብን፣ ካልሆነ ካሳ የመጠየቅ መብታችን እንዱጠበቅልን በማለት አመልክተዋል። የሥር ከሳሾች እና የሥር ተከሳሽ ለየብቻ ባቀረቡት መልስ ከሳሾች ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለዉም በማለት ወስኗል።
የወረዲዉ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን የሰዉ ምስክሮች በመስማት በሰጠዉ ዉሳኔ የከተማዉ አስተዲደር በጣልቃ ገቦች ይዞታ ላይ ለከሳሾች ካርታ ሰርቶላቸዉ እንደሆነ ወይም መሬቱን በሕጋዊ መንገድ ወስድ እንደሆነ ከመሬት ጉዲይ ጋር በተያያዘ በሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26፣ 29፣ 30 በደንብ ቁጥር 155/2005 እና የኦሮሚያ ከተማ በሉዝ ለማስተዲደር የወጣ መመሪያ ቁጥር 9/2005 መሰረት በአስተዲደራዊ መንገድ እዛዉ የሚታይ እንጂ በፍ/ቤት የሚቀርብ ጉዲይ አይደለም፣ የካሳ ጥያቄም ከሆነ መጠኑን ለይተዉ ለብቻ ክስ ማቅረብ ስለሚቻል፣ ጣልቃ ገቦች ያቀረቡት ክስ የክስ ምክንያት የለዉም በማለት የቀረበዉን የመቃወሚያ አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ የቀድሞዉን ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን አመልካቾች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ከሳሾች የተጓደለዉ ይዞታ ተሟልቶ እንዱሰጣቸዉ በማለት ያቀረቡት ክስም ሆነ የሥር ጣልቃ ገቦች ያቀረቡት አቤቱታ ፍ/ቤት የማየት ስልጣን የለዉም በማለት ለሥር ፍ/ቤት ቀድሞ እና በኋላ የተሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል። የሥር ከሳሾች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ ፍ/ቤት የሥር ከሳሾች ያቀረቡትን ጥያቄ ለማየት ስልጣን የለዉም የሚያስብል ነገር የለም፣ የወረዲዉ ፍ/ቤት ዉሳኔ ጸንቷል፣ የከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ ተሽሯል በማለት ወስኗል። የሥር ጣልቃ ገቦች ይህን ዉሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታቸዉ ተቀባይነት ሳያገኝ ዉድቅ ተደርጎ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ጸንቷል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካቾች በ11/10/2007 ዓ.ም በተጻፈ ሶስት ገጽ አቤቱታ የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች የጎደለዉን መሬት አሟልቶ 3ኛ ተጠሪ እንዱሰጣቸዉ ያቀረቡት ዲኝነት ፍ/ቤቶች በሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 እና የኦሮሚያ ክልል የከተማ መሬትን አስተዲደር ያወጣ ሉዝ አዋጅ ቁጥር 55/2006 ለመወሰን ያልተፈቀደላቸዉ ሆኖ ሳለ ያለስልጣን የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ። የአሁን አመልካቾች በዋናነት ያቀረብነዉ የዲኝነት ጥያቄ ለረጅም ዓመታት በእጃችን የቆየዉን ይዞታንና ንብረትን 3ኛ ተጠሪ ለ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ማስረከብ አይገባዉም እንዱሁም በአማራጭ ማስረከብ አለበት የሚባል ከሆነ ካሣ የመጠየቅ መብታችን እንዱጠበቅልን በማለት አመልክተን እያለ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጥያቄያችን የመሬት ካሳ ጥያቄ ስለሆነ በፍ/ቤት የሚታይ አይደለም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ተሽሮልን፣ የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ እንዱጸናልን ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት አመልክቷል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በማየት የሚጣራ ነጥብ አለ በማለት አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ በታዘዘዉ መሰረት የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ሐምል 16 ቀን 2007 ዓ.ም የተጻፈ አራት ገጽ መልስ እና የአሁን 3ኛ ተጠሪ በ15/01/2007 ዓ.ም የተጻፈ መልስ ሶስት ገጽ አቅርበዉ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል። የመልሱም ይዘት፡ የአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለዉ ትክክለኛ ዉሳኔ ስለሆነ እንዱጸናልን ወጪና ኪሳራ እንዱወሰንልን በማለት በዝርዝር ተከራክሯል። የአሁን አመልካቾችም የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ያላቸዉን የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ፣ እንዱሁም መደበኛ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ የማየት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉን እንደጭብጥ በመያዝ እንደሚከተለዉ መርምሮታል። መዝገቡን እንደመረመርነዉ ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነዉ የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ሲሆን፣ የዲኝነት ጥያቄአቸዉም በካርታ ላይ ተጠቅሶ ለእያንዲንዲችን የተሰጠዉ ቦታ 200 ካ.ሜ ቢሆንም በእጃችን የገባዉ የቦታ መጠን ከዚህ የሚያንስ በመሆኑ የጎደለዉ ይዞታ ተሟልቶ እንዱሰጠን በማለት 3ኛ ተጠሪን የከሰሱ ሲሆን፣ የወረዲዉ ፍ/ቤት ይህን የዲኝነት ጥያቄ መሰረት በማድረግ ዉሳኔ የሰጠ በመሆኑ፣ የአሁን አመልካች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይዞታችን ማስረከብ የለበትም ካልሆነ ካሳ ላሰጥን ይገባል የሚል መቃወሚያ አቅርቧል። የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ያቀረቡት ጥየቄ የጎደለዉ ይዞታ ተሟልቶ እንዱሰጥን የሚል ሲሆን፣ የአሁን አመልካቾች ደግሞ ያለምንም ምትክ ቦታ ወይም ካሳ ይዞታችን ሉወሰድብን አይገባም የሚል መቃወሚያ ማቅረባቸዉን ማየት ይቻላል። የግራ ቀኙ ክርክር የሚያተኩረዉ በአዲማ ከተማ አስተዲደር ሥር ያለውን የከተማ ቦታን የሚመለከት ነዉ።
የአዲማ ከተማ አስተዲደር በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ዉስጥ የሚገኝ እንደመሆኑ መጠን ይህን የከተማ ቦታ የሚያስተዲድረዉ የከተማ መሬት የሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004፣ ይህን አዋጅ መሰረት በማድረግ ክልለ ያወጠዉ የከተማ መሬትን በሉዝ ለማስተዲደር የወጣ ደንብ ቁጥር 155/2005 እና የከተማ መሬትን በሉዝ ለማስተዲደር የወጣ መመሪያ ቁጥር 9/2005 በተመለከቱ መርሆዎች መሆን እንዲለበት መገንዘብ ያስፈልጋል። ከከተማ ቦታ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች እንዱሁም ቦታን ከማስለቀቅ እና ተያያዥነት ያላቸዉ ጥያቄዎች የሚስተናገደት በዚህ አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ መሆን ይገባል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አግባብነት ያላቸዉ የአዋጁ ድንጋጌዎች አንቀጽ 26፣ 27፣ 28፣ 29፣ እና 30 ሲሆን፣ የከተማ ቦታን ከማስለቀቅና ምትክ ቦታ እና ካሳን ከመክፈል አንጻር ጉዲዩ የሚታይ መጀመሪያ በሕግ አግባብ በከተማዉ አስተዲደር የተዋቀረዉ አካል እንደሆነ ያመለክታል። የደንብ 155/2005 አንቀጽ 26፣ 55 እና 56 እንዱሁም የመመሪያ አንቀጽ 33 እና 36 ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት እንዲለዉ ማየት ይቻላል። በዚህ አግባብ ስልጣን የተሰጠዉ የአስተዲደር አካል የከተማ ቦታ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ የመብት ጥያቄዎች፣ ይዞታን ለማስለቀቅ ትዕዛዝ ከመስጠት፣ ምትክ ቦታ እና የካሳ መጠን ወስኖ ከማሳወቅ አንጻር ስልጣን የተሰጠዉ መሆኑን ያመለክታል። በዚህ አስተዲደራዊ ዉሳኔ ላይ ቅሬታ ያለዉ አካል አቤቱታዉን እዛዉ በሕግ አግባብ በተዋቀረዉ አካል ዘንድ ማቅረብ እንዲለበት ነዉ። ይህ አካል በአቤቱታዉ ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ቅሬታ ያለዉ አካል ይግባኙን በከተማ አስተዲደር ደረጃ በተዋቀረዉ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ማቅረብ መብት እንዲለዉ ከአዋጁ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል።
በዚህ አካሄድ ጉባኤዉ የሚሰጠዉ ዉሳኔ ካሳን በተመለከተ ካልሆነ በስተቀር ላልች ምትክ ቦታን ጨምሮ በላልች በሕግም ሆነ በፍሬ ነገር ክርክሮች ላይ ጉባኤዉ የሚሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ ይሆናል። የካሳ ጥያቄም ቢሆን በይግባኝ ለመደበኛ ከፍተኛ ፍ/ቤት ላቀርብ እንደሚገባ እንጂ ቀጥታ ክስ ላቀርብ እንደማይችል ይደነግጋል። ይህ የሚሆነዉ ግን እነዚህ አካላት በሕጉ አግባብ ተዋቅረዉ ከከተማ መሬት ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ክርክሮች የሚያስተናግደበት ሥርዓት የተዘረጋ እንደሆነ ነዉ። የአሁን አመልካቾችም ሆኑ የአሁን 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ይህ አስተዲደራዊ አካል በህጉ አግባብ ስላልተዋቀረ በመደበኛ ፍ/ቤት ክስ ማቅረባቸዉን አግባብነት ባለዉ ማስረጃ አስደግፈዉ ያቀረቡት ክርክር የለም። ስለዚህ ከዚህ አንጻር ሲታይ በግራ ቀኙ መካከል ያለዉን የጎደለዉ ይዞታ እንዱሟላልን የሚል የዲኝነት ጥያቄ፣ ምትክ ቦታ እና ካሳ ሳይከፈለን ከይዞታችን ልንነቀል እና ማስረከብ የለብንም የሚለዉ የዲኝነት ጥያቄ በተመለከተ በቀጥታ ክስ ለመደበኛ ፍ/ቤት ላቀርብ የሚገባ ጉዲይ አይደለም። ከላይ በተመለከተዉ መሰረት ስልጣን ላለዉ የአስተዲደር አካል የሚቀርብ ጉዲይ ነዉ። ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ አግባብ በማየት ከግራ ቀኙ የቀረበዉን የዲኝነት ጥያቄዎች ለመወሰን ስልጣን ስለላላቸዉ የቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.244 /2፣ ሀ/ እና 245 /2/ መሰረት ዉድቅ ማድረግ ሲገባቸዉ፣ ጥያቄዉን በመቀበል የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለዉ በመሆኑ የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት በመ.ቁ.68317 በ06/12/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.200569 በ13/08/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.204835 በ25/09/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ተሽሯል።
የአዲማ ልዮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.19245 በ04/03/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
መደበኛ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ በቀጥታ ክስ ተቀብል አከራክሮ ዉሳኔ ለመስጠት ስልጣን የለዉም ብለናል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤት ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.