የከተማ ቦታን በሉዝ በመጫረት ጨረታውን በማሸነፍ የሉዝ ውል የተፈጸመ እንደሆነ ይህን የውል ግንኙነት ለመዲኘት የሚችለው ፍርድ ቤት ስለመሆኑ፣ የሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 የፍ/ሓር/ሕ/ቁ. 1731፣1808/2/
No summary available.
መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻዉ አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- በወላይታ ዞን የበላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዓ/ሕግ ኤርገና ቆልቻ - ቀርበዋል ተጠሪ፡- ወ/ሮ ታደለች ዲባራ - ተወካይ ታደለ ወ/ሚካኤል - ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ በዉል ያገኘሁትን የከተማ ይዞታ እንዱያስረክበኝ በማለት የቀረበ ክስን መነሻ ያደረገ ክርክር ነዉ። የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ፡ የአሁን አመልካች የሥር 1ኛ ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ በመሆን ሲከራከሩ እንደነበር መዝገቡ ያመለክታል። የአሁን ተጠሪ በኪንድ ኮይሻ ወረዲ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ 1ኛ ተከሳሽ /የአሁን አመልካች/ በበላ ቀበላ 02 በግብርና ሰፈር በኮድ ቁ.0443፣ 300 ካ.ሜ ይዞታ ለጨረታ አዉጥቶ እኔ ተወዲድሬ አሸንፋ ተገቢዉን ክፍያ ሁለ ፈጽሜ ዉል ተዋዉዬ እያለሁን፣ 2ኛ ተከሳሽ ተወዲድሮ ያሸነፈዉ ኮድ 0024፣ 200 ካ.ሜ ይዞታ ሁኖ እያለ የመጀመሪያዉን ዉል አስቀርድድ በቦታዉ ላይ የተለጠፈዉን ታፔላ በመቀያየር ላላ ክፍያ በመፈጸም ለ2ኛ ተከሳሽ አሳልፍ የሰጠ በመሆኑ፣ 1ኛ ተከሳሽ ይህን ይዞታ ከ2ኛ ተከሳሽ አስለቅቆ ለከሳሽ እንዱያስረክበኝ እንዱወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ መልስ ከሳሽ በተወዲደረችበት ቦታ ላይ ያቀረበችዉን የጨረታ ሰነድ በሰም ያልታሸገ በመሆኑና ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ አሰጣጥን ያልተከለተለ ስለመሆኑ በመረጋገጡ በ1ኛ ተከሳሽ ማኔጅመንት በሕግ አግባብ የከሳሽ ዉል እንዱመክን ተደርጓል፤ ከሳሽ ይህን ክስ ያቀረበችዉ ከቅን ልቦና በመሆኑ ዉድቅ እንዱደረግልን በማለት ተከራክረዋል። የሥር 2ኛ ተከሳሽ /አቶ ማቴዎስ ማያ/ ባቀረበዉ መልስ ይህን ይዞታ በሕጋዊ መንገድ ተወዲድሬ ያገኘሁት በመሆኑ የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክረዋል።
ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ ክርክሩን በማጣራት በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን አመልካችን ክርክር በመቀበል የአሁን ተጠሪን ክስ ዉድቅ በማድረግ፣ የአሁን ተጠሪ ከጨረታዉ ጋር በተያያዘ የከፈለት ገንዘብ ብር 3600 /ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ብር/ የአሁን አመልካች እንዱከፍላቸዉ ወስኗል። የአሁን ተጠሪ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በሰጠዉ ዉሳኔ መደበኛዉ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ አይቶ ለመወሰን ስልጣን የለዉም በማለት የስር ፍ/ቤት ዉሳኔ በመሻር ወስኗል። የአሁን አመልካች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኙን ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ጉዲዩ በአስተዲደር በኩል ታይቶ እልባት እንዱሰጣት አቤቱታዋን በየደረጃዉ ላለት የመንግስት መዋቅር አቅርበዉ ምላሽ በማጣታቸዉ ይህን ክስ ለፍ/ቤት ያቀረቡ በመሆኑ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለዉ፤ የሥር 2ኛ ተከሳሽ ተወዲድረዉ ያሸነፈት በ200 ካ.ሜ ሲሆን፣ ከሳሽ በ300 ካ.ሜ ላይ በጨረታ ተወዲድረዉ አሸነፉዉ ዉልም ተዋዉለዉ ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ የአሁን አመልካች በሰም የታሸገ ኤንቨልፕ አላቀረብሽም በሚል ምክንያት ዉለን ዉድቅ ማድረጉ አግባብነት የለዉም፣ በዉለ በተጠቀሰዉ መሰረት በጨረታ ያሸነፈችዉን ይዞታ 300 ካ.ሜ ለከሳሽ እንዱያስረክባት በማለት ወስኗል። የአሁን አመልካች አሁንም ይህን ዉሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታዉን ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን ችልቱ ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የስር ፍ/ቤት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለዉም በማለት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች ነሐሴ 20 ቀን 2007 ዓ.ም በተጻፈ አራት ገጽ አቤቱታ ተጠሪዋ ያሰነፈችበትን ዉጤት እንዱሰረዝ ዉሳኔ የሰጠዉ የወረዲዉ ማኔጅመንት ኮሚቴ በመሆኑ የሉዝ አዋጁን ለማስፈጸም በወጣዉ መመሪያ መሰረት ቅሬታዋን ለሚመለከተዉ አስተዲደር ማቅረብ ነበራባት እንጂ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለዉም። የአሁን ተጠሪ በጨረታ ሂደት አለአግባብ መብቴ ተነክቷል የምትል ከሆነ የሉዝ ኮሚቴ ወይም የመሬት ማኔጅመንት ኮሚቴ ቅሬታዋን አቅርባ በሚሰጠዉ ዉሳኔ ካልተስማሙ ይግባኝ ለዞን ይግባኝ ሰሚ ወይም ለክልለ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ማቅረብ እንዲለባቸዉ በሉዝ አዋጅ ቁ.721/2004 መሰረት ክልለ ባወጠዉ መመሪያ ቁ/01/2005 አንቀጽ 74 መሰረት መሆን አለበት። የሥር ፍ/ቤት በዚህ መቃወሚያ መሰረት የቀረበዉን ክስ ዉድቅ ማድረግ ሲገባዉ የሰጠዉ ዉሳኔ ተገቢ አይደለም። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች የተጠሪዋን መሬት ለላላ ግለሰብ አሣልፍ ለመስጠት ነዉ ዉጤቱን የሰረዘዉ፣ የተወዲደሩበትን ታፔላ ቀያይሯል የሚል ሲሆን ይህ ስለመሆኑ በተጨባጭ ማስረጃ ያጣራዉ ነገር የለም ወይም ወደ ስር ፍ/ቤት መልሶት እንዱጣራ ያደረገዉ ነገር በላለበት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። ስለዚህ ይህን ጉዲይ የመደበኛዉ ፍ/ቤት ለማየት ስልጣን ስለላለዉ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት እና ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሻርልን፣ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ እንዱጸናልን በማለት አመልክተዋል።
ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን በማየት የሚጣራ ጉዲይ አለ በማለት አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጡ ባዘዘዉ መሰረት በ10/02/2008 ዓ.ም የተጻፈ ሁለት ገጽ መልስ አቅርበዋል። የመልሱም ይዘት፡ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለዉ በመሆኑ እንዱጸናልኝ ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብት እንዱጠበቅልኝ ወይም በቁርጥ እንዱወሰንልኝ በማለት ተከራክረዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ፣ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም? የሚለዉን ጭብጥ በመያዝ እንደሚከተለዉ መርምሮታል። መዝገቡን እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካች በበላ ቀበላ 02 በግብርና ሰፈር በኮድ ቁ.0443፣ 300 ካ.ሜ ይዞታ ለጨረታ ባቀረበዉ መሰረት የአሁን ተጠሪ ተወዲድረዉ አሸንፈዉ ተገቢዉን ክፍያ ፈጽመዉ ዉል ያደረጉ መሆኑን ግራ ቀኙ የሚካካደት ጉዲይ አይደለም። በልላ በኩልም የአመልካች መ/ቤት በዚህ አግባብ ተጠሪ ጨረታዉን አሸንፈዉ ተገቢዉን ሁለ ፈጽመዉ ዉል ከተዋዋለ በኋላ ለጨረታዉ ሲወዲደሩ በሰም የታሸገ ኤንቨልፕ አላቀረቡም የሚል ምክንያት በማንሳት በኮሚቴ በማየት ዉለን የሰረዘ መሆኑ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ። የአሁን ተጠሪ ባቀረቡት ክስ አመልካች ይህን ዉል ያለአግባብ የሰረዘ በመሆኑ በዉለ ላይ በተመለከተዉ መሰረት ይዞታዉን እንዱያስረክበኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁን አመልካች ይህ ጉዲይ በአስተዲደር አካል መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ እንጂ መደበኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለዉም በማለት ተከራክረዋል። በዚህ አግባብ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠዉን ፍሬ ነገር አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማየት መደበኛ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ የማየት ስልጣን አለዉ ወይስ የለዉም የሚለዉን ጭብጥ መመልከቱ ተገቢ ነዉ።
ከዚህ አንጻር ሲታይ የአሁን አመልካች የከተማ ቦታን በሉዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 እንዱሁም ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የወጣ መመሪያ መሰረት ለክርክር ምክንያት የሆነዉን ይዞታ ለጨረታ አቅርቦ፣ የአሁን ተጠሪ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 /1-6/ መሰረት ተወዲድረዉ የጨረታ ሂደቱን አልፈዉ አሸንፈዉ በአንቀጽ 16 መሰረት የሉዝ ዉል የፈጸሙ መሆኑን ያመለክታል። የአሁን ተጠሪ በሕጉ የተመለከተዉን ሂደት ሁለ አልፈዉ ዉል ከፈጸሙ በኋላ አመልካች ወደ ኋላ በመመለስ ለዉድድር ሲቀርቡ ተጠሪ በሰም የታሸገ ፖስታ ወይም ኤንቨልፕ ባለማቅረባቸዉ የጨረታዉን ዉጤት የሆነዉን ዉል መሰረዙን ገልጸዋል። ነገር ግን የአመልካች መ/ቤት ተጠሪዋ በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚያስፈልገዉን መስፈርቶች ሁለ ያሟለ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በጨረታዉ እንዱሳተፈ ያደረጋቸዉ መሆኑ የሚያከራክር አይሆንም።
የአሁን ተጠሪ አስፈላጊዉን መስፈርት ባያሟለ ኖሩ በጨረታዉ ላይ እንዱሳተፈ ያደረጋል ተብል አይገመትም። ስለዚህ የአሁን አመልካች ተጠሪዋ በአግባቡ የጨረታ ሂደቱን አልፈዉ ዉል ከተዋዋለ በኋላ በሰም የታሸገ ኤንቨልፕ አላቀረቡም በማለት ይህን ዉል መሰረዙ ከጨረታ ሂደት አልፍ አስገዲጅ የዉል ግዳታ በተገባበት ጉዲይ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ይህ ከሆነ መታየት ያለበት ከላይ የተመለከተዉ የሕግ ድንጋጌ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የዉል ሕግ ድንጋጌ እንደአግባብነቱ ተፈጻሚነት የሚኖረዉ ይሆናል። ምክንያቱም በግራ ቀኙ መካከል በሕግ ፉት የሚጸና መብት ግዳታ የሚፈጥር ዉል እስከተደረገ ድረስ ይህን ዉል የማፍረሱ ጉዲይ በአመልካች መ/ቤት ብቻ የሚተዉ ጉዲይ አይደለም። ይህ ማለት በግራ ቀኙ መካከል ይህ ዉል በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1731 መሰረት እንደሕግ የሚቆጠር ነዉ። ግራ ቀኙ በዚህ ዉል መሰረት መብትና ግዳታቸዉን መወጣት እንደሚጠበቅባቸዉ ግልጽ ነዉ። ይህ ከሆነ ይህ ዉል የሚፈርስባቸዉ ሕጋዊ ምክንቶች አለ ወይስ የለም የሚለዉን አይቶ ለመወሰን ለተዋዋይ ወገኖች ብቻ የሚተዉ ጉዲይ ሳይሆን ገለልተኛ በሆነ ፍ/ቤት ታይቶ መዲኘት ያለበት ጉዲይ ሁኖ ይታያል። ይህን ዉል ለማፍረስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1808 ሥር የተመለከቱት ዉልን ለማፍረስ ተገቢ የሆኑ ምክንያቶች መሟላት ይጠበቅበታል። ይህ በመሆኑ እነዚህ ምክንያቶች ወይም ሁኔታዎች መሟላታቸዉን አለማሟላታቸዉን በመደበኛ ፍ/ቤት ታይቶ እልባት ላሰጥበት የሚገባ ጉዲይ ነዉ። ስለሆነም ይህ ጉዲይ በህጋዊ መንገድ የተቋቋመዉን ዉል ከማፍረስ ጋር የሚመለከት በመሆኑ መደበኛ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ የማያይበት ምክንያት የለም። የአሁን አመልካች መ/ቤት ማናቸዉንም ምክንያት በመፈለግ በፈለገ ጊዜ እያነሳ ይህን በሕግ አግባብ የተቋቋመዉን ዉል ለመሰረዝ የሚያስችለዉ የሕግ አግባብ የለም።
የአሁን አመልካች ይህን ዉል ለመሰረዝ የጠቀሰዉ ምክንያት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1808 /2/ ሥር የሚወድቅ ሁኖ ስለማይታይ ዉለን ለመሰረዝ በቂ ምክንያት ነዉ ተብል ሉወሰድ የሚችል ጉዲይ አይደለም። ስለዚህ የሥር ፍ/ቤቶች መደበኛ ፍ/ቤት ይህን ጉዲይ ለማየት ስልጣን አላቸዉ በማለት የአሁን አመልካች ያለ በቂ ምክንያት ዉለን መሰረዙ ተቀባይነት የለዉም አመልካች በዉለ ላይ የተጠቀሰዉን ይዞታ ለአሁን ተጠሪ እንዱያስረክብ በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.06872 በ13/09/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ በ29/11/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለዉ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችልት የደረሰባቸዉ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ።
በ29/12/2007 ዓ.ም የተሰጠዉ የእግድ ትዕዛዝ በዚህ ዉሳኔ ተነስቷል። ይጻፍ።
No topics extracted.