የገጠር መሬት የይዞታ ባለመብት የሆነ በሙለ ፍቃድ የሰጦታ ውል አድርጎ እንዱሁም ውለ በሚመለከተው አካል ከተመዘገበ በኃላ ፤በውለ ላይ ያልተመዘገበ ቅድመ ሁኔታ በመዘርዘር ውለ ፈራሽ እንዱሆን በማለት የሚቀርብ ጥያቄ ውልንም ህግንም የሚቃረን መሆኑ የአ/ብ/ክ/መ አዋጅ 133/98 አንቀፅ 15 እና 17 ፤ የአ/ብ/ክ/መ ደንብ ቁጥር 51/99 እና የፍ/ሕ/ቁ 2436 ፣2437 ፣2438 ፣2439 XII ቁጥጥር ይዞታ ሥር ነፃ አድርጎ ፣የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሀብትነት ለማስተላለፍ የሚያስችለ አስፈላጊ ሰነድች ለገዢ የማስረከብና የማይንቀሳቀሰዉን ንብረት የማይነካ የባለሀብትነት መብት ለገዥ ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆነ ተግባራትን የመፈጸም ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2875፣ 2879(1)፣2281 እና እነ ወ/ሮ ሜሪ ታደሰ ( ሦሰት ሰዎች)
No summary available.
ህዲር 29 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ አማረች ማሬ ……………….. ጠበቃ ማስታወል ሀብታሙ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪዎች እየኖሩበት ያለውንና በ 300 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት ለቀው እንዱያስረክቧት የመጠየቅ መብት የላትም ንብረቱን የሸጠችላትን ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ከሳ ትጠይቅ በማለት የሰጡት ውሳኔ አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል ።
ከሳሽ ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የመፈላም ክስ ነው ከሳሽ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቀበላ 03 የቤት ቁጥር 287 የግል ሀብቴ ስለመሆኑ በክፍለ አስተዲደር የባለሀብትነትና ባለይዞታነት ማረጋገጫ ማስረጃ (ካርታ) በእጁ ይገኛል። ተከሳሾች ከቤቴ ውስጥ በጥገኝነት እንዱኖሩ ፈቅጄላቸው ሲኖሩ ቆይተዋል ። አሁን ግን ቤቴን እንዱለቁ ብጠይቃቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ቤቴን እንዱለቁና እንዱያስረክቡ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርባለች ።
ተጠሪዎች በተከሳሽነት ቀርበው እኛ በከሳሽ ቤት በከሳሽ ፈቃድ በጥገኝነት የምንኖር ሰዎች አይደለም ። ተከሳሾች በእጃችን አድርገን ይዘን እየኖርንበት ያለው ቤትና ይዞታ አያታችንና እናታችን ከዛሬ አርባ ዘጠኝ ዓመት ጀምሮ ይዘውት ሲኖሩበት የነበረ ቤት ነው።ተከሳሾች ከአያታችንና ከእናታችን ጋር ክስ ያቀረበበትን ቤት ይዘን ስንኖር ፣ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በአያታችን ባድ የይዞታ ቦታ ላይ በአንድ በኩል ቤት ሰርታ ስትጠቀም ቆይታ ፣ቤቱን ለአሁን ከሳሽ ሸጣለታለች ሆኖም እኛ የምንኖርበት ቤት ወ/ሮ ሂሩት አበራሽ በእጇ አድርጋ ይዛው የማታውቅና የራሱ የሆነ ይዞታና የወሰን አጥር ያለው በመሆኑ ከሳሽ ቤቱን ለከሳሽ የሸጠችውም ሆነ ከሳሽ የእኛን ቤትና ይዞታ በማጠቃለል እንዳት ካርታና ፕላን እንዲወጡ የክፍለ አስተዲደር እንዳት የእኛን ቤትና ይዞታ በማጠቃለል እንዳት ካርታና ፕላን እንደሰጠ ይጠየቅልን በማለት መልስ ሰጥተዋል። የስር ፍርድ ቤት የክፍለ አስተዲደር ተገቢዉን ማጣሪያ በማድረግ መግለጫ እንዱሰጥ ትዕዛዝ የቤቱ ስመ ሀብትና ከወ/ሮ እህተ ገብረማርያም ሂሩት አበራሽ ስም ሂሩት ስም የተዛወረዉ በስር ትዕዛዝ ፊይል ቁጥር 139/84 መስከረም 25 ቀን 1985 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ መሰረት እንደሆነና ከዚያ በኃላ ሂሩት አበራሽ በውልና ማስረጃ ከከሳሽ ጋር በተዋዋለችው የቤት ሽያጭ ውል 1189 ሜትር ካሬ ላይ ያረፈው ቤትና ይዞታ በከሳሽ ስም እንዱዘዋወር ተደርጎ ከሳሽ የባለሀብትነት ማስረጃ የሰጠ መሆኑን ተረጋግጧል ።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ወ/ሮ እህተ ገብረማሪያም ጋር ባደረጉት የቤት ሽያጭ ውል የገዙት ዋናውን ቤት የቤት ቁጥር 287 እንደሆነ የሚገልፅ ቢሆንም ገዥ ይህንን ዋናውን ቤት ተረክበውና በእጃቸው አድርገውት አያውቁም ። ወ/ሮ ሂሩት አበራሽ ገብተውና ከሻጭም ተረክበው ይኖሩ የነበሩት ሰርቪስ ቤትና በባድ ይዞታ ላይ ራሳቸው የሰሩትን ቤት ነው ። ገዥ ገዝቻለሁ የሚለትን የቤት ቁጥር 287 በ 300 ካሬ ሜትር ላይ 1984 ዓ.ም ጀምሮ ተረክበውና በእጃቸው አድርገውት አያውቁም ነገር ግን የሻጭን መሞት ምክንያት በማድረግ ይህንን 1984 ዓ.ም ተረክበውና ይዘው የማያውቁትን ቤት ጨምሮ በሽያጭ ውለ መሰረት ተረክበው የሚኖሩበትን ይዞታ ላይ ያለው ቤት ስመሀብት እንዱዛወርላቸው በማድረግ የባለሀብትነት ማስረጃ ተሰጥቷቸዋል ።
ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በፍርድ ቤት ውሣኔ መነሻ የተሰጣቸውን የባለሀብትነት ሰነድ በማየት ፣ከሟች እህተ ገ/ማሪያም ቤቱን ከገነባች ጀምራ ተረክባና በእጇ አድርጋ የማታውቀውን የቤት ቁጥር 287 ዋናውን ቤት በ 300 ካሬ ሜትር እንዲረፈ ፣በእጇ አድርጋ ስታካብት ከኖረችው ቤት ጋር አንድ ላይ ለከሳሽ ሸጣ ቤቱና ይዞታው በተከሳሾች እጅ ባለበት ከሳሽ በሻጭ ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት እጅ ባልነበረና ሆኖ በማያውቅ ቤትና ይዞታ ላይ ጭምር የባለሀብትነት ማስረጃ አውጥታለች ። ይህም ለከሳሽ ቤቱን የሸጠችው ወ/ሮ ሂሩት አበራሽ ተከሳሾች ይዘው የሚኖሩበትን ቤትና የይዞታ ቦታ በሽያጭ ውለ መሰረት ያላስረከበቻትና ቤቱና ይዞታው በተከሳሽ እጅ ባለበት የሰነድ ርክክብ ብቻ ያደረገች መሆኑን ስለሚያሳይ ከሳሽ ሻጭዋን ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት እንጂ ተከሳሾች ቤቱን እንዱያስረክቧት መክሰስ አትችልም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል ። ይህንን ውሣኔ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ እንዱያየው አመልካች ጠይቃ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አፅንቶታል።
አመልካች ሚያዝያ 27 ቀን 2008 ዓ.ም አመልካች አከራካሪውን ቤት በውል ገዝታ የንብረት ባለሀብት መሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ አላት ይህ ከሆነ ንብረቷ እንዱለቀቅ የመክሰስ መብት የላትም በማለት መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ጭብጦችን አልመሰረቱም ተጠሪዎች ቤቱን በጥገኝነት ስለመያዛቸው ለቀበላ ለአስተዲደር አመልክተዋል በሻጭና በከሳሽ መካከል የተደረገው ውል ተጠሪዎችን የሚመለከት አይደለም ። አመልካች የቤቱ ሻጭ በዋቢነት እንድትቀርብላት ሣትጠራ ፣ንብረቱ ላይ ያገኛቸው የባለሀብትነት መብት ለማስከበርና ለመፊለም የሚከለክላት ህግ በላለበት ሁኔታ የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክታለች ።
ተጠሪዎች በመጀመሪያም ሂሩት አበራሽ ከሟች አያታችን እህተ ገ/ማሪያም ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውል አስመልክቶ ለአውራጃው ፍርድ ቤት ክስ ስታቀርብ ሟች የሸጠችላትን ቤት እጇ አድርጋና ተረክባ እየኖረችበት መሆኑን ገልፃለች። ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት እኛ የምንኖርበትን ቤትና በአዋሳኝ አጥር ታይቶ ያለውን 300 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ተረክባም ሆነ ይዛው አታውቅም ። እኛ በማናውቀው ሁኔታ የእኛን ቤትና ይዞታ ካርታና ፕላን ማውጣቷና ለከሳሽ መሸጧ ከሳሽን የቤቱ ባለመብት አያደርጋትም ። የባለሀብትነት ካርታና ማስረጃውም በክፍለ አስተዲደር የታገደ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት መልስ ሰጥተዋል ።
አመልካቾች የመልስ መልስ አቅርበዋል ። ግራቀኙ የሚያከራክራቸውን ጭብጥ ለመረዲት ችልቱ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ሰምቶ የቃል ክርክሩ ከትራንስክራይበር ማሽን ተገልብጦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል ። የክፍለ አስተዲደር በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የፃፈውን መግለጫ ለማየት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዝገብ እንዱቀርብ በታዘዘው መሰረት መዝገቡ ቀርቦ ተያይዟል ።
ተጠሪዎች የሚከራከሩበት ከሳሽ የቤትና ይዞታውን ባለቤትነት መብት በሽያጭ አስተላልፊልኛለች የሚለት አበራሽ ሂሩት እኛ የያዝነውን ቤትና 300 ካሬ ሜትር ይዞታ ለከሳሽ በሽያጭ ለማስተላለፍ መብት የላትም ። ከሳሽ እኛን ከመጠየቋ በፉት በሽያጭ ውለ መሰረት እኛ የምንኖርበትን ቤትና 300 ካሬ ሜትር የይዞታ ቦታ ሻጭ ነፃ አድርጋ እንድታስረክባትና የሽያጭ ውለን እንድትፈፅምላት ከምትጠይቅ በስተቀር ከሳሽ የሽያጭ ውለ ሙለ በሙለ እንደተፈጸመላትና ንብረቱንም ከሻጭ እንደተረከበች አድርጋ በመቁጠር በቀጥታ እኛን ከቤት እንድንወጣ የመጠየቅና ክስ የማቅረብ መብት የላትም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ተረድተናል።
ግራቀኙ በሥር ፍርድ ቤትና በዚህ ሰበር ችልት ያቀረቡት ክርክር አመልካችና ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት የካቲት 3 ቀን 1997 ዓ.ም የተዋዋለት የቤት ሽያጭ ውል ሻጭ ሙለ ለሙለ ፈፅማለች ወይስ አልፈፀመችም ሻጭ በሽያጭ ውለ መሰረት ግዳታዋን ሙለ በሙለ ካልፈፀመችና ውለን በከፉል የፈፀመች መሆኑ ቢረጋገጥ ገዥዋ ሻጭ ቀሪውን ግዳታዋን እንድትፈፅምላት በሻጭ ላይ ክስ ሣታቀርብ ወይም በተከሳሽነት አጣምራ ሳትከስ የውለ ተዋዋይ ያልሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ላይ በቀጥታ ክስ ለማቅረብ ትችላለች ወይስ አትችልም ?የሚለት ነጥቦች መታየት ያለባቸው ናቸው።
ከላይ ከተገለፁት ነጥቦች አንፃር ስንመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል የገባውን ግዳታ የሚፈፅምባቸው ሁለት መሰረታዊ ኃላፉነቶች አለ። የመጀመሪያው ሻጭ በሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በአንደ ወይም በልላ መልኩ በስፍራው የሚገኙ ሰዎች የተሸጠውን የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዱለቁ በማድረግ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ይዞታ ከላልች ሶስተኛ ወገኖችና ከሻጭ ቁጥጥርና ይዞታ ነፃ በማድረግ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለገዥ ማስረከብ እንደሆነ ከፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2875 እና ከፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 2274 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ለመረዲት ይቻላል ሻጭ ከዚህ በተለየ ሁኔታ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ርዕስ መዝገብ ላይ የተመዘገበና ገዢውንም ሉያስገድደ የሚችለ የሶስተኛ ወገኖች መብት በሰጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ካለ ይህንኑ የሶስተኛ ወገኖች መብት ካለ ሻጭ ለገዥ ማስታወቅ ያለበት መሆኑ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2880 እና በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2881 ተደንግጓል ።
የሻጭ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ከሶስተኛ ወገን ይዞታና ቁጥጥር ነፃ በማድረግ የማስረከብ ግዳታ ገዥ ለሻጭ ከሚሰጠው የመነቀል ዋስትና ግዳታ የተለየ ነው ። ሻጭ በንብረቱ ላይ ያሰፈሩና በንብረቱ መዝገብ የተመዘገበ መብት የላላቸውን ሰዎች የማይንቀሳቀሰውን ንብረት እንዱለቁ በማድረግ ለሻጭ የማስረከብ ግዳታ የማይንቀሳቀስ ንብረት ውል በመፈፀም ሂደት ገዥ ሻጭ ሉያከናውነው የሚገባ የመጀመሪያ ግዳታ ሲሆን በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2882 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት ሻጭ ለገዥ የሸጠለት የማይንቀሳቀስ ንብረት የማይነቀል ስለመሆኑ የሚሰጠው ዋስትና ገዥ የገዛውን የተረከበውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ከላልች ሰዎች ቁጥጥር ነፃ ሆኖ ከተረከበ በኃላ ንብረቱ የእኔ ነው ባይ ቢመጣ ሻጭ በዋቢነት ሉቆምለት የሚገባ መሆኑን የሚያመለክቱ ድንጋጌዎች ናቸው።
የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ ሰው ንብረቱን ከላልች ሰዎች ቁጥጥር ይዞታ ሥር ነፃ አድርጎ ለገዢ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2875 እና በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2274 መሰረት የማስረከብ ግዳታ ያለበት ከመሆኑ በተጨማሪ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሀብትነት ለማስተላለፍ የሚችለ አስፈላጊ ሰነድች ለገዢ የማስረከብና የማይንቀሳቀሰዉን ንብረት የማይነካ የባለሀብትነት መብት ለገዥ ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆነ ተግባራትን የመፈጸም ግዳታ መሆኑ በፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 2875 በፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 2879 ንሁስ አንቀጽ 1 እና የፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 2281 ድንጋጌዎችን በጣምራ በማየት ለመረዲት ይቻላል።
ከላይ በዝርዝር ካየናቸው የህግ ድንጋጌዎች አንጻር ሲታይ 1139 ካሬ ሜትር የይዞታ ቦታ ላይ ያረፈውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ሙለ በሙለ ለአመልካች የሸጠችው ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት፣በሽያጭ ውለ መሰረት የማይንቀሳቀስውን ንብረትና ይዞታውን ከላልች ሰዎች ቁጥጥርና ይዞታ ስር በማስለቀቅ የማይንቀሳቀስ ንብረትና ይዞታውን በፍትሃብሄር ሕግ ቁጥር 2875 በፍትሃብሄር ሕግ ቁጥር 2274 እና በፍትሃብሄር ሕግ ቁጥር 2888 መሰረት ለገዥ(ለአመልካች)የመፈጸም ግዳታውን የተወጣችው ሙለ በሙለ ሳይሆን በከፉል ነው።ሻጭ ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ተጠሪዎች የሚኖሩበትን ቤትና 300 ካሬ ሜትር ይዞታ ከተጠሪዎች አውራሽ ንብረቱን ገዛሁ ከምትልበት 1984 ዓ.ም ጀምሮ ተረክባውና በእጇ አድርጋው የማይታወቅ መሆኑና፣ቤቱን ለአመልካች ከሸጠችላት በኋላ ተጠሪዎች የሚኖሩበትን ቤትና ይዞታ፣ ተጠሪዎች በህግ አግባብ እንዱለቁ በማድረግ ለአመልካች ያላስረከበችበት አመልካችም በሽያጭ ውለ የተገለጸውን ቤትና ይዞታ ሙለ በሙለ ሳይሆን፣ሻጭ(አበራሽ ሂሩት)ይዛው የነበረውን ቤትና ይዞታ ብቻ ከሻጭ የተረከበች መሆኑን ተረድተናል።
ገዥ ሻጭ በሽያጭ ውለ የገለጸችውን የማይንቀሳቀስ ንብረትና ይዞታ፣ ተጠሪዎች የሚኖሩበት ቤትና ይዞታ ሳይጨምር በሻጭ እጅና ይዞታ ስር ያለውን ቤትና ይዞታ የተረከበች ቢሆንም፣ሻጭ የሰጠቻትን ሰነድ በመጠቀም በሽያጭ ውለ ላይ የተመለከተውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለመብት መሆኗን የሚሳይ ማስረጃ ከክፍለ አስተዲደር ተሰጥቷታል።ይህም ገዥዋ(አመልካች)ከላልች ሰዎች ይዞታና ቁጥጥር እንደዚሁም የመብት ጥያቄ ነጻ ሆኖ ከሽያጭ ያልተረከበችውን ተጠሪዎች የሚኖሩበት ቤትና ይዞታ ባለመብት መሆኗን የሚያረጋግጥ የባለህብትነት ማስረጃ የተሰጣት መሆኑን ያሳያል።አመልካች የቤቱ ባለሃብትነት መብት በሽያጭ ውል ከወ/ሮ አበራሽ ሂሩት የተላለፈላት መሆኑን የሚያሳይ የሽያጭ ውል ሰነድና በሽያጭ ውለ መሰረት በማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብትነት የተዛወረላት መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ በማያያዝ በፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 1206 መሰረት ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም አላት።ነገር ግን አመልካች ባቀረበችው የክስ መነሻ አከራካሪ ሆኖ የተገኘው ጭብጥ፤(ሀ) ቤቱን ንብረቴ ነው ካለች ለአመልካች የሸጠችው ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት አከራካሪውንና ተጠሪዎች የሚኖሩበትን ቤትና ይዞታ ባለሃብትነት መብት ለአመልካች የማስተላለፍ እርግጠኛ የሆነ የባለሀብትነት መብት በንብረቱ ላይ አላት ወይስ የላትም?
(ለ)ሻጭ ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ተጠሪዎች የሚኖርበትን ቤትና 300 ካሬ ሜትር ይዞታ ጨምራ የባለሀብትነትን ማስረጃና ካርታ ያሰራችው በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም?አመልካችስ 1139 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትና ባለይዞታ መሆኗን የሚያረጋግጥ የባለህብትነት ማስረጃና ካርታ የተሰጣት በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም?(ሐ)ተጠሪዎች እየኖሩበት ያለውን ቤትና 300 ካሬ ሜትር ይዞታ ቦታ ለአመልካች የመልቀቅና የማስረከብ ግዳታ አለባቸው ወይስ የለባቸውም?የሚለት ለአመልካች 1139 ካሬ ሜትር የይዞታ ቦታ ላይ ያለውን የማይንቀሳቀስ ንብረት በሽያጭ ውል አስተላልፊለች የተባለችው ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በክርክሩ ተሳታፉ ሳትሆን ውሳኔ ላሰጥባቸው የሚችለ ጭብጦች አይደለም።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች የቤቱ ሻጭ የሆነችውን ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ከሚከሱ በስተቀር በቀጥታ ተጠሪዎች ቤቱን እንዱለቁላት ክስ ማቅረብ አትችልም በማለት የሰጠው ውሳኔ ሻጭ በሽያጭ ያስተላለፈው ንብረት ላይ ያለውን መብትና ጥቅም ለማስከበር ገዥው ከውል የመነጨ መብት ያለው መሆኑን ያላገናዘበና የፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 1195 የፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 1206 እና የፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 33(2) ድንጋጌዎች ያላገናዘበ በመሆኑ ስህተት ያለበት ነው።ነገር ግን የበታች ፍርድ ቤቶች ቤቱን ለአመልካች የሸጠችው ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በክርክሩ ተከሳሽ መሆን አለባት በማለት የደረሱበት ድምዲሜ የፍትሃብሄር ህግ አንቀጽ 2875፣ አንቀጽ 2274፣አንቀጽ 2888 እና የፍትሃብሄር ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 40 ንዐስ አንቀጽ 2 ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች ሻጭ ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በጉዲዩ ተከሳሽ መሆን አለባት በማለት የደረሱበት መደምደሚያ በውጤት ደረጃ የሚነቅፍ ሆኖ አላገኘነውም።
የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የቤቱን ሻጭ ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት መክሰስ አለባት ካለ በኋላ፣ይህ ውሳኔአቸው የሚያስከትለውን ህጋዊ ውጤት ሳይመዝኑ ተጠሪዎችን ከክስ ማሰናበታቸው አግባብነት ያላቸውን የስነ-ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም አመልካች ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በሽያጭ ውለ መሰረት ተጠሪዎች የያዙትን ቤት አስለቅቃ ታስረክበኝ የሚል ክስ ስታቀርብ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ በማናቸውም ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን በተከሳሽነት አጣምራ መክሰስ እንዲለባት የፍትሃብሄር ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 36 ንዐስ አንቀጽ 4 አስገዲጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል።ይህም አመልካች ሻጭዋን ወ/ሮ አበራሽ ሂሩትን በምትከስበት ጉዲይ ተጠሪዎች የግድ በተከሳሽነት እንዱሳተፈ ማድረግ የሚገባ መሆኑ በህግ የተደነገገ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ዲኝነት ከፍላ ያቀረበችውን ክስ የቤቱ ሻጭ በጉዲዩ የመጀመሪያ ተከሳሽ መሆን አለባት በሚል ምክንያት ዘግቶ አመልካችን ከሚያሰናብት፣በጉዲዩ የቤቱ ሻጭ በክርክሩ በተከሳሽነት ተሳታፉ እንድትሆን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 40 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ትዕዛዝ መስጠት በዚህ ፍርድ አንቀጽ ተራ ቁጥር 13 በተመለከቱና በላልች ጭብጦች ላይ አመልካች (የቤቱ ገዥ)፣ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት ሻጭና በአከራካሪው ቤትና ይዞታ ይዘው የሚኖሩት ተጠሪዎች የሚያቀርቡትን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ መወሰን ሲገባው፣አመልካች ተጠሪዎችን የመክሰስ መብት የላትም በማለት መዝገቡን መዝጋቱና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ማጽናቱ ከላይ በዝርዝር የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎችና የዲኝነት አካሄድ ስርዓት ያልተከተለና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ የካቲት 29 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዝገብ መጋቢት 2 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሸሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ወ/ሮ አበራሽ ሂሩት በተከሳሽነት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 40 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት በመጨመር፣በዚህ ፍርድ በተራ ቁጥር 13 የተመለከቱትንና ላልች አከራካሪ ጭብጦች ላይ ግራ ቀኙ የሚያቀርቡትን ክርክርና ማስረጃ በማሰማትና ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 343(1) መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.