No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል ቀነአ ቂጣታ ክፍለፅዮን ማሞ ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- አቶ ድጋፋ ክፍላ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ጎሣ ገድል - የቀረበ የለም መዝገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የእርሻ መሬት ስጦታ ውል ክርክር የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በአ/ብ/ክ/መ/ሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ወረዲ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በ22/03/2007 ዓ.ም በመዝገብ 715/07 ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ይዘትም፡- አመልካች ካላቸው የመሬት ይዞታ ለተጠሪ አዋሳኙ በምስራቅ ወንድአፈራሽ ፣በምዕራብ ገደል፣ በደቡብ ጎደና በሰሜን ወንዝ የሚያዋስነው 3 ጥማድ መሬት በሽተኛ በመሆናቸው ተጠሪ መሬቱን፣ በመሬቱ ላይ ያለ ዛፍ እና ድንጋዮች እንዱቆጠርላቸው የመሬት ግብር በየዓመቱ ተከታትል እንዱገብር በቀን 18/07/2005 ዓ.ም በተፃፈ የስጦታ ውል አድርገው በስጦታ ይዞታ መሬቱን አስተላልፈውለት ተጠሪው የመሬት ግብር እንኳ ሳይገብር ለከፍተኛ ጉዲት መዲረጉን፣ በመሬቱ ላይ ያለ ዛፍችም ያልተንከባከባቸው የተቆራረጡ እንዱሁም የመሬቱ አጥርም መፍረሱን፤
አመልካችን ሉጠይቃቸውና ሉያስታምማቸው አለመቻለን በመግለጽ የመሬት ስጦታ ውለ ፈራሽ እንዱሆንላቸውና ወደነበሩበት እንዱመለሱ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁን ተጠሪ በሰጠው መልስም ከአመልካች ጋር የስጋ ዝምድና እንዲላቸው አመልካችን ለረጅም ዓመታት ያለጥቅም እያረሰ ምርት ሲሰጣቸው እንደነበር ውለታውም ማንም ሳያስገድዲቸው በጤናማ አዕምሮ በራሳቸው ፍላጎት የአካባቢ ሰዎች ሰብስበው በ03/07/2005 ዓ.ም በተፃፈ የስጦታ ውል መስጠታቸው፤ የስጦታ ውለ በሚመለከተው አካል ከመመዝገቡ በፉት ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት ወይም የቤተሰብ አባል እንዲለ፣ መሬቱ ለ3ኛ ወገን ተላልፍ ወይም በኮንትራት የተሰጠ ከሆነ ከክትቻ ቀበላ የመሬት አስተዲደር ጽ/ቤት እንዱጣራ ተደርጎ መጋቢት 18 ቀን 2005 ዓ.ም በወረዲው የመሬት አስተዲደር አጠቃቀም ፀድቆ ማስረጃ እንደተሰጠው የስጦታ ውለ ከህግም ከሞራልም ተቃራኒ አለመሆኑን ስጦታው በሚመለከተው አካል ፉት የተደረገና በስጦታ በተላለፈለት መሬት በስሙ መገበሩን በይዞታ መ/ቁ. A/I/83/17/850 በሆነ ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንደወጣለት በመግለፅ አመልካች ያቀረቡት የስጦታ ውል ይፍረስልኝ ክስ ተገቢ ባለመሆኑ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክራል።
የሥር ወረዲ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ እንዱሁም ለክርክሩ መነሻ የሆነው የስጦታ ውል በማስቀረብ ከመረመረ በኋላ ውለ የመሬት አዋጅ በሚያዘው አግባብ ስለመደረጉ፤
ተጠሪ በስጦታ ባገኘው መሬት ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማውጣቱን፣ አመልካች ውለን ለማፍረስ እንደመከራከሪያ ያቀረቡት ምክንያት በማስረጃ ያልተደገፈ፣ ውለ በክልለ የመሬት አዋጅ ቁጥር 133/98 አንቀጽ 17 አግባብ ተደርጎ በሚመለከተው አካል የፀደቀ እና ሕጋዊ እውቅና ያለው በመሆኑ የሚፈርስበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት የአመልካች ክስ ውድቅ አድርጎታል።
አመልካች የሥር ወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የአ/ብ/ክ/መ/ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 133/98 ሆነ ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የወጣው የደንብ ቁጥር 51/99 የእርሻ መሬት ስጦታ የሚፈርስበት ምክንያት ያልደነገገ በመሆኑ አግባብነት ያለውን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2436 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ መመልከቱ ተገቢ እንደሆነ፣ በእነዚህ ድንጋጌዎች የስጦታ ውል የሚጸናው ስጦታ አድራጊው ወድና ፈቅድ ስጦታ በአደረገበትና የስጦታ ተቀባዩም ውለን በተቀበለበት ቅጽበት መሆኑን የፍ/ህ/ቁ. 2436(1) በግልጽ የሚያስነብብ ስለመሆኑ ውለ ሉፈርስ የሚችለው ስጦታ አድራጊው ስጦታው ያደረገው ጤነኛ ባልሆነ አእምሮ ያደረገው መሆኑን ያስረዲ እንደሆነ ወይም ስጦታው የተደረገው በህግ ከተፈቀደው ውጭ የሆነ እንደሆነ ወይም ስጦታ የተደረገበት ነገር ግብረገብ ካልሆነ ወይም ስጦታ አድራጊው የመንፈስ መጫን ደርሶበት እንደሆነ መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2437፣ 2438፣ 2439 ድንጋጌዎች እንደሚያመለክቱ፣ በተያዘው ጉዲይ እነዚህ ተግባራት መከናወናቸው አልተረጋገጠም።
ይልቁንም ስጦታ አድራጊው በጤነኛ አዕምሯቸው ስጦታው ያደረጉ መሆኑን ስልጣን በአለው አካል ህጋዊነት ተረጋግጦ የስጦታ ውለ በጽሐፍ ከተደረገ በኃላ የጸደቀ የተመዘገበ ስለመሆኑ፣ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በአንድ ግቢ ጋር የሚኖሩ መሆኑንና የአመልካች መሬት በነፃ እያረሰ የቆየ መሆኑን የምንጃር ሸንኮራ ወረዲ አካባቢ ጥበቃ መሬት አስተዲደር አጣርቶ ስጦታውን ያጸደቀ ከመሆኑም በላይ በስር ፍ/ቤትም ይህንኑ በሰው ማስረጃ የአረጋገጠ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት የሰጦታ ውለ ሉፈርስ አይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት በማጽናት ወስኗል።
አመልካች የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታው መሰረታዊ ይዘትም የአሁኑ ተጠሪ አመልካችን እየጦረና እየተንከባከበ ስለመሆኑ አላስረዲም፣ የመሬት ይዞታ ስጦታ ውል በፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎች መታየት የለበትም፤ አመልካች አቅመ ደካማና በሽተኛ በመሆናቸው ውለ ፈርሶ ወደነበሩበት እንዱመለሱ መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ለሰበር ችልት ይቅረብ በመባለ ግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። ተጠሪ በሰጠው መልስም አመልካች ካላቸው 20 ጥማድ መሬቱ 3 ብቻ እንደሰጡት፤ ስጦታው ተጠሪ ለረጅም ጊዜ ባበረከተው አገልግልት የተሰጠው ስለመሆኑ ውለም ገደብ እንደላለበት፣ በሚመለከተው አካል ተጣርቶ የተመዘገበ በመሆኑ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል።
ይህ ችልትም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ይረዲ ዘንድ ግራ ቀኙ አደረጉት የተባለው የስጦታ ውል በማስቀረብ ተመልክቶታል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ ‛በዚህ ጉዲይ አመልካች በተጠሪ ለመጦር የሰጡት የመሬት ስጦታ ውለ ይፍረስልኝ ሲለ ያቀረቡት ክስ ውለ አይፈርስም የመባለን አግባብነት ከክልለ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 133/98 አንፃር“ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር የሚል ሆኖ አገኝቶታል።
ከሥር የክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች የስጦታ ውል ማድረጋቸው ሳይክደ የአሁኑ ተጠሪ መሬቱ እንዲልተንከባከበ ሉያስታምማቸው አለመቻለን በመግለጽ የስጦታ ውለ ፈራሽ እንዱሆን መጠየቃቸውን ነው። ተጠሪ በበኩለ የስጦታ ውለ በሕጉ አግባብ የተደረገ በመሆኑ የሚፈርስበት ሕጋዊ ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤቶች የመሬት ስጦታው ፈራሽ የሚሆንበት ምክንያት አልተገኘም በማለት የአመልካች ክስ ውድቅ አድርገውታል። አመልካች የስጦታ ውለ ለማፍረስ እንደምክንያት የጠቀሱዋቸው ነጥቦች በስጦታ ውለ ላይ የተመዘገቡ ቅድመሁኔታዎች /Conditions/ ስለመሆናቸው የግራ ቀኙ ያደረጉት የውል ስምምነት አያሳይም። አመልካች ያደረጉት ስጦታ የክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም መወሰኛ ቁጥር 133/98 አንቀጽ 15 እና 17 መሰረት መደረጉ በትዕዛዝ ከቀረበው ሰነድ መመልከት ይቻላል። አመልካች እንደውል ማፍረሻ የዘረዘሩዋቸው ምክንያቶች በስጦታ ውለ ላይ ያልተመዘገቡ መሆናቸው ግልጽ ነው። የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመሬት ስጦታ ውል ክርክር በቀረበበት ሁኔታ ፈራሽ መሆን ያለመሆኑን ለመወሰን የክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 133/98 ሆነ አዋጁን ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ቁጥር 51/99 ግልጽ ድንጋጌ እንደላላቸው በውሳኔው አስፍሯል። አመልካች ባቀረቡት ክርክር ጉዲዩ ከፍትሐብሕር ሕግ አንፃር መታየት የለበትም ያለ ቢሆንም የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔው እንዲሰፈረው የስጦታ ውል የሚፈርስበት ሁኔታ ካለ አግባብነት ካላቸው የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎች አስተሳስሮ ማየቱ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም። በእርግጥ የገጠር መሬት የክርክር ይዘትና ባሕሪ እንዱሁም ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ በመለየት ረገድ ተገቢ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። ይሁንና አመልካች ያነሱዋቸው የስጦታ ውለ ያፈርሳለ የተባለ ምክንያቶች የሕግና የውል መሰረት ያላቸው መሆን ያለመሆኑን መርምሮ መወሰን ተገቢ ነው።
አመልካች ለተጠሪ ያደረጉት ስጦታ በነፃ ፍላጎት እና በትክክለኛ የአእምሮ ሁኔታ እንደነበር እንዱሁም ውለ አግባብ ባለው አካል መመዝገቡን የተካደ ጉዲይ አይደለም። የስጦታ ውለ ሕገወጥ በሆነ ምክንያት ወይም የመንፈስ መጫን እንደነበረ አመልካች አላስረደም። አመልካች የስጦታ ውለ በገደብ የማድረግ መብት የነበራቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2455(1) ያስገነዝበናል። ይሁንና አመልካች በስጦታ ውለ ላይ ያስቀመጡት ቅድመሁኔታ ስለመኖሩ ውለ አያሳይም፣ ያቀረቡዋቸው ምስክሮችም ስጦታ ውለ በገደብ /ግዳታ/ ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን ፍሬ ነገር በማጣራትና ማስረጃ በመመዘን ሥልጣን ያላቸው የሥር ፍርድ ቤቶች ከድምዲሜ ላይ ደርሷል። በአንፃሩ የአሁኑ ተጠሪ ለረጅም ጊዜ ያገለገላቸው ስለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ግንዛቤ መወሰደን መዝገቡ ያሳያል። በመሆኑም አመልካች በገዛ ፈቃዲቸው 3 ጥማድ መሬት መስጠታቸው እና ውለም ሥልጣን ባለው አካል ተረጋግጦ መመዝገቡን ባለተካደበት አመልካች በውለ ላይ ያልተመዘገበ ቅድመ ሁኔታዎች በመዘርዘር ውለ ፈራሽ እንዱሆን ያቀረቡት ክርክር የሕግም ሆነ የውል መሰረት የላለው ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም አመልካች ለተጠሪ ያደረጉት የእርሻ መሬት ስጦታ ለማፍረስ የሚያስችል የሕግ ድጋፍ ያለው ክርክር አለማቅረባቸው ተረድተናል።
አመልካች ለተጠሪ ከሰጡት 3 ጥማድ መሬት ውጭ ላላ የመሬት ይዞታ ያላቸው ስለመሆኑ በትዕዛዝ ቀርቦ ከታየው የአመልካች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማረጋገጥ ተችሎል። በእርግጥ አመልካች ስጦታ ከሰጡት መሬት ውጭ ላላ መሬት እንደላላቸው ወይም ራሳቸው መቀለብ በማይችለበት ደረጃ የሚኖሩ ከሆነ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2458(1) በሚያዘው አግባብ ቀለብ የመጠየቅ መብት እንዲላቸው ተጠሪም ቀለብ የመስጠት ግዳታ ያለው በመሆኑ መብታቸውን በሕጉ አግባብ ማስከበር የሚችለበት ሁኔታ መኖሩን ችልቱ ይገነዘባል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ውለን ለማፍረስ እንደምክንያት የጠቀሱዋቸው ቀለብ ከመጠየቅ ጋር በቀጥታ ግንኙነት የላላቸው ከመሬቱ እንክብካቤና ግብር መክፈል የተያያዙ ናቸው። ይህ ደግሞ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን 3 ጥማድ መሬት በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የወጣበት በመሆኑ የሚመለከተው አካል ከሚጠይቀው በስተቀር አመልካች ስለግብር መክፈልና መሬቱ ላይ መደረግ ያለበት እንክብካቤ የሚጠይቁበት ሥርዓትና የሕግ ምክንያት አይኖርም። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ ያደረጉት የስጦታ ውል የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት የአመልካች ክስ ውድቅ ማድረጋቸው ሕጉን በአግባቡ ተፈፃሚ አድርጓአል ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸማቸውን የማያሳይ በመሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም። በዚህም ተከታዩን ወስነናል።
የምንጃር ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 01010775/07 በ15/05/2007፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 0116800 በ13/08/2007 የሰጡት ፍርድ፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት 030-6216 በ22/10/2007 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ጸንቷል።
አመልካች ለተጠሪ ያደረጉት የ3 ጥማድ መሬት ስጦታ ውል በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 133/98 ይዘትና መንፈስ የተደረገ በመሆኑ የሚፈርስበት የሕግ አግባብ የለም በማለት ወስነናል።
የዚህ ፍ/ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.