የመሬት የይዞታ መብት ያለው ሰው ፤በይዞታው ላይ የአላባ የመጠቀም መበት መስጠቱ በልላ ጊዜ ይዞታውን በስጦታ የማሰተላለፍ መብቱን የማይገድብ ሰለመሆኑ ፤ የአ/ብ/ክ/መ/መሬት አጠቃቀም አዋጁ 133/98 አንቀፅ 1፣7
No summary available.
ሐምል 19 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ማናለው ተካ - ተወካይ ታዳ ተካ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ እቴነሽ ተካ - ተወካይ አቶ ተስፊው ከቤ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዲዩ የተጀመረው በምስራቅ ጎጃም ዞን እነብሴ ሳር ምድር ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ወላጅ አባቴ አቶ ተካ አንተነህ በስጦታ ያስተላለፈልኝን መሬት አመልካች በጉልበት በመያዝ እየተጠቀመበት ስለሚገኝ እንዱለቅልኝ በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካች የሰጠው መልስ ክስ የቀረበበት መሬት ላይ ለተጠሪ የስጦታ አስተላላፉ ከሆኑት ከአቶ ተካ አንተነህ ጋር አስቀድሞ የካቲት 7 ቀን 2003 ዓ.ም በተደረገ የእርቅ ስምምነት ያለቀ በመሆኑ የተጠሪ ስጦታ አድራጊ በስጦታ ለማስተላለፍ የማይችለ ከመሆኑም በላይ መሬቱ ለአመልካች እናት ጭምር የተሰጠ ስለሆነ የተጠሪ ክስ የአመልካችን መብት የሚነካ ስለሆነ ውድቅ እንዱደረግ በማለት መልሱን በማቅረብ ተከራክሯል።
በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ አቶ ተካ አንተነህ አስቀድሞ ያደረጉት የእርቅ ስምምነት መሬቱን በስጦታ ከማስተላለፍ የሚከለክል ባለመሆኑ አመልካች መሬቱን ለተጠሪ ሉለቅ ይገባል በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ቅሬታ ለምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤቱም አቶ ተካ አንተነህ መሬቱን በተመለከተ አስቀድመው በእርቅ የጨረሱ ስለሆነ መሬቱን ለላላ ሰው የማስተላለፍ መብት የላቸውም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል።
ተጠሪ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአ/ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዱሁም ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበው የክልለ ሰበር ችልት አባ ተካ አንተነህና አመልካች ያደረጉትን ስምምነት ይዘት የአባ ተካ አንተነህ የይዞታ መሬት አመልካች ይዞ እያረሰ ሰብል እንዱሰጥ የተስማሙበት እንጂ የአባ ተካን መሬት ወደ አመልካች የማስተላለፍ ህጋዊ ውጤት ያለው ስምምነት አይደለም፤ የክፍለ መሬት አስተዲዲርም አስቀድሞ የአባ ተካ መሬት ለአመልካች ያለማስተላለፈን በመገንዘብ ለተጠሪ የተሰጠውን ስጦታ መዝግቦታል በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር የወረዲውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አፅንቶታል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የክልለ ሰበር ሰሚ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም በፃፈት አቤቱታ በክልለ ሰበር ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ:- በአባ ተካ አንተነህ እና በአመልካች መካከል የካቲት 7 ቀን 2003 ዓ.ም የተደረገው እርቅና በፍርድ ቤት የፀደቀው ስምምነት ባለበት ሁኔታ እንዱሁም በዚሁ ስምምነት መሰረት እንዱፈፀም የአፈፃፀም ትእዛዝ ባለበት ሁኔታ ያደረጉት ስምምነት መሬቱን ወደ አመልካች የማስተላለፍ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይህ ውሳኔ ተሽሮ የካቲት 7 ቀን 2003 ዓ.ም የተደረገው ስምምነት እንዱፈፀም ለተጠሪ የተደረገው ስጦታ እንዱሻር በማለት አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት በታዘዘው መሰረት የካቲት 2 ቀን 2008 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል።
አመልካችም አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
የአመልካች ጥያቄ ለክርክር መነሻ የሆነው መሬት በእርቅ ስምምነት ያገኘሁት ለተጠሪ ልለቅ አይገባም የሚል ሲሆን በተጠሪ በኩል ደግሞ በስጦታ ያገኘሁትና በአግባቡ በማስረጃ ተረጋግጦ የተሰጠ ውሳኔ ሉፀና ይገባል ሲል ተከራክሯል። የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች ለክርክሩ መነሻ የሆነው የመሬት ይዞታ አመልካች ከስጦታ አድራጊ አባ ተካ የእርቅ ስምምነት የነበራቸው መሆኑ እና ተጠሪም በስጦታ የተሰጣቸው መሆኑ አከራካሪ ነጥብ አይደለም። የሚያከራክረው በአመልካችና በአባ ተካ መካከል የተደረገው የእርቅ ስምምነት ይዘት ላይ ነው። ስለሆነም የእርቁ ስምምነት አመጣጥ መመርመሩ ተገቢ ነው የሚሆነው።
አመልካች ለአባ ተካ የመሬት ይዞታ እያረሰ በአላባ እንዱጠቀም በነበራቸው ስምምነት አለመግባባት በመፈጠሩ ጉዲያቸው ወደ ፍርድ ቤት ደርሶ ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ባደረጉት የእርቅ ስምምነት ሉቋጭ እንደቻለ ነው። ከዚያ በኋላ አባ ተካ የአማራ/ብ/ክ/መ/ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ አንቀጽ 15/1/፣17 ማንኛውም ሰው የይዞታ መብቱን በስጦታ ለማስተላለፍ በሚፈቅደው መሰረት በሚመለከተው አካል ቀርበው ለአሁን ተጠሪ በስጦታ መስጠታቸውን በክፍለ ተመዝግቦ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው መሆኑ የፍሬ ነገር የማጣራትና የማስረጃ የመመዘን ስልጣን በተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች የተረጋጋጠ ነው።
የእርቁ ስምምነት ይዘት አባ ተካ የመሬት ባለይዞታ በመሆን አመልካች ደግሞ በጉልበቱ እያረሰ የአላባ የመጠቀም መብት የሚሰጥ ነው። ይህ የእርቅ ስምምነት ለአባ ተካ የመሬት ይዞታቸው በስጦታ ለፈለጉት ሰው የማስተላለፍ መብታቸውን የሚገድብ አይደለም። በልላ በኩል ስምምነቱ አመልካች የአባ ተካ ይዞታ እስካለ ድረስ የአላባ የመጠቀም መብት የሰጠ ነው። ይዞታው ለላላ ሰው ከተላለፈ ተጠሪ በአላባ የመጠቀም መብቱም የማቋረጥ ውጤት ነው ያለው። አመልካች ላላ መከራከሪያ ነጥብ አባ ተካ ለተጠሪ ያደረጉት ስጦታ የእናቴ ይዞታ ጭምር ነው በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ በተመለከተ በስር ፍርድ ቤት የመሬት ይዞታው ለአባ ተካ ተለክቶ የተሰጣቸው መሆኑን ባደረጉት ማጣራት የተረጋገጠ በመሆኑ ይህ ችልትም በፍሬ ነገር የማጣራትና የመመዘን ስልጣን በህገ መንግስቱ አንቀፅ 80/3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ስልጣን ያልተሰጠው ስለሆነ የአመልካች አቤቱታ ተቀባይነት የለውም።
ሲጠቃለል በተያዘው ጉዲይ ላይ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የአ/ብ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ.03-40156 ጥቅምት 9 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችልት የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.0116362 ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የአ/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ.37155 ሚያዝያ 2 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠ ትእዛዝ በመሻር የእነብሴ ሳርምድር ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.01-012499 ህዲር 30 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ በማፅናት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ከዚህ ፍርድ ቤት የእነብሴ ሳርምድር ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.0112499 የተጀመረው አፈፃፀም ተላልፍ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ተነስተዋል። የሚመለከው አካል ይፃፍ።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጭ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገብ ተዘግተዋል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.