በትግራይ ክልል በገጠር መሬት ላይ የሚደረግ አቶ ተክላ ይይ ተስፊይ XI ሕጋዊ ነው የሚባለው በውልና ማስረጃ ፀድቆ የወረዲው የመሬት ዳስክ አውቆ በቅጽ ተሞልቶ የተለዋወጡ ከሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣ የትግራይ የመሬት አዋጅ ቁጥር 239/06 እና ደንብ ቁጥር 48/2000 እና ወ/ሮ ንግስቲ ገ/መድህን
No summary available.
ሚያዚያ 25 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች- አቶ ተክኤ ፀጋይ ተስፊይ -ቀርበዋል ተጠሪ- ወ/ሮ ንግስቲ ገ/መድህን - ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ የሰበር አቤቱታ መዝገብ ክርክር አመልካች አቶ ተክኤ ፀጋይ ተስፊይ ጥቅምት 11/2007 ዓ/ም. በተጻፈ አቤቱታ ከተጠሪ ጋር ያደረግነው የመሬት ይዞታ ልውጫ በፍላጎታችን ተስማምተን ያደረግነውና ለ3 ዓመት ቆይቶ የሚፈርስበት ምክንያት ሳይኖር መሬቱን ይመላለሱ ተብል መወሰኑ ተገቢ አይደለም። ተጠሪ የመሬት ለውጥ ውል መኖሩን እያመነች በሥር ፍ/ቤት ወደነበሩበት ይመለሱ መባለ አለአግባብ በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ወ/ሮ ንግስቲ ገ/መድህን በትግራይ ብ/ክ/መንግስት በፅምብላ ወረዲ አስተዲደር በደብረአባይ ቀበላ መሬት አስተዲደር ዲኝነት አካል ባቀረቡት ክስ ከሳሽና ተከሳሽ አቶ ተክኤ ፀጋይ መሬት ተለዋውጠን በኔ የመሬት ይዞታ ላይ ቤት ሰርቶበት የራሱን ግን ያላስረከበኝ በመሆኑ መሬቴን ይመልስልኝ ስትል ከሳለች ተከሳሽም በሰጠው መልስ መሬት ተለዋውጠናል ከተለዋወጥን ከ3 ዓመት በኋላ እና ቤት ሰርቼበት ካለማሁ በኋላ ይመልስልኝ ማለቷ ተገቢ ባለመሆኑ ክሷ ውድቅ ይሁንልኝ ብሎል።
የደብረ አባይ ቀበላ መሬት አስተዲደር የዲኝነት አካል አከራክሮ ጥር 14/2006 ዓ/ም.
በሰጠው ውሳኔ ከሳሽና ተከሳሽ መሬት እንዱለዋወጡ የቀበላው የመሬት አስተዲደር ድጋፍ ሰጥቷቸው እና በመሬት አስተዲደር ዳስክ እንድትጨርሱ ተብል የነበረ ቢሆንም ሳይጨርሱ ቀርተዋል። የከሳሽ መሬት በተከሳሽ እጅ ያለው ወሰኑን በመጥቀስ ለከሳሽ ይመለስ በማለት ወስኗል። ተከሳሽ ለፅምብላ ወረዲ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የፅምብላ ወረዲ ፍ/ቤት በመ. /06 አከራክሮ ሚያዚያ 15/2006 ዓ/ም. በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ የግራ ቀኙ ምስክር ተሰምቶ ከሳሽና ተከሳሽ የተለዋወጡት መሬት ተከሳሽ ሁለት ቤት የሰራበት ቢሆንም የመሬት ለውጡ በሚመለከተው አካል አልፀደቀም። በመሆኑም ልውጫው ህጋዊነት የላለው በመሆኑ ወደየራሳቸው ይመለሱ ተከሳሽ የሰራውን ቤት በተመለከተ የቤቱን ዋጋ ተስማምተው ለተከሳሽ ይከፈለው። ካልሆነ ¼(አንድ አራተኛ) ከሳሽ ለተከሳሽ ትክፈለው ሲል ወስኗል።ተከሳሽ ለሰሜን ምዕራብ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የሰሜን ምዕራብ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ./06 አከራክሮ ግንቦት 29/2006 ዓ.ም. በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ ግራ ቀኙ መሬት መለዋወጣቸውን አይካካደም እየተከራከሩ ያለው የመሬት ልውጫው በሚመለከተው አካል አልፀደቀም በሚል ነው። የመሬት መለዋወጡ ከህግ ጋር እስካልተቃረነ ድረስ ውለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም። ከዚህም በላይ ውል ይፍረስ ቢባል እንኳ ወደ ነበሩበት መመለስ የሚችለ አይደለም ተከሳሽ በመሬቱ ላይ የሚገመት ቤት ሰርቶበታል። በመሆኑም የተለዋወጡትን መሬት ይዘው ይቆዩ ሲል የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር ወስኗል። ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ ) ለትግራይ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርባ የጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.
አከራክሮ ጳጉሜ 3/2006 ዓ/ም. በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ በተከራካሪዎቹ መሀከል የመሬት ልውጫ የተባለው ህጉ በሚያዘው በአዋጅ ቁ. 239/06 እና ደንብ ቁ. 48/2000 መሰረት በውልና ማስረጃ ፀድቆ የወረዲው የመሬት ዳስክ አውቆ በቅፅ ተሞልቶ የተለዋወጡ ካልሆነ ህጋዊ ልውጫ አይደለም። ይህ ሆኖ እያለ ከፍ/ፍ/ቤት የወረዲውን ውሳኔ እና የቀበላውን ውሳኔ መሻሩ ስህተት ነው በማለት የከፍ/ቤት ውሳኔ ሽሮ የወረዲውንና የቀበላውን ውሳኔ በማፅናት ወስኗል።
የአሁን አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርበዋል። መዝገቡ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ ግራ ቀኙ ይዞታቸውን ተለዋውጠው ከቆዩ በኋላ ልውውጡ በሚመለከተው አካል አልፀደቀም በሚል ብቻ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ የካቲት 25/2007 ዓ/ም. በተፃፈ መልስ በኔና አመልካች ተደርጎ የነበረውን የመሬት ለውጥ የመሬት ውል አፅዲቂው አካል አመልካች የመሬት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የላለው ስለሆነ አላጸደቀውም። በመሬቱ ላይ የሰራቸው ስራዎች እየተቃወምኩት የሰራው ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር የሚያሰኝ ባለመሆኑ ይጽናልኝ ብለዋል። የአመልካች የመልስ መልስ ባለመቅረቡ ታልፎል።
በዚሁ መሰረት ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መዝገቡን እንደመረመርነው፡ በትግራይ ብ/ክ/መ.
የመሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 239/06 የተመለከተውን አሟልቶ የመሬት ይዞታ መለዋወጥ አልተከለከለም። ይሁንና አመልካች ከተጠሪ ጋር ተለዋወጥን የሚለት የመሬት ይዞታ በአዋጅ ቁ. 239/06 መሰረት በውልና ማስረጃ ጸድቆ የወረዲው የመሬት ዳስክ ያልመዘገበው በመሆኑ የክልለ የመሬት አስተዲደርና እና አጠቃቀም አዋጅና ደንቡ በሚደነግገው መሰረት ያላሟላ በመሆኑ የመሬት ይዞታ ልውጫ በአመልካችና ተጠሪ መሀከል ተፈጽሟል ለማለት አይቻልም። በመሆኑም የትግራይ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም።
የትግራይ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ጳጉሜ 3/2006 ዓ/ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ፣ የፅምብላ ወረዲ ፍ/ቤት በመ. /06 ሚያዚያ 15/2006 ዓ/ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ መዝገብ ወጪና ኪሳራ ተቻቻለ ብለናል።
በዚህ መዝገብ መጋቢት 23/2007 ዓ/ም. በዋለው ችልት የሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ይጻፍ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.