የከተማ ቦታ የሉዝ ይዞታ በሚቋረጥበት ወቅት /ሲቋረጥ / ባለይዞታው እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በቦታው ላይ ያሰረፈውን ንብረት በማንሳት ቦታውን አግባብ ላለው አካል መልሶ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 26(5) እና (6)
No summary available.
መጋቢት 28/2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- የሱለልታ ከተማ አስተዲደር -አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ደባልቄ ደምሴ -ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ የሰበር አቤቱታ መዝገብ ክርክር አመልካች የሱለልታ ከተማ አስተዲደር ታህሳስ 10/2007 ዓ.ም. በተጻፈ አቤቱታ ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) በመሬቱ ላይ የነበረውን የከሳሽ (የአሁን ተጠሪ ) ንብረት በሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 25(5 እና 6) መሰረት ያለምንም ክፍያ ሉወሰድ እንደሚችል ደንግጎ እያለ የስር ፍ/ቤት ንብረቱ ይመለስ ብል መወሰኑ ካለአግባብ ነው። ከሳሽ የንብረቶቹን ትክክለኛ ግምትና አይነት የሚያስረዲ ማስረጃ ባልቀረበበት ንብረቱ ይመለስ መባለ አግባብነት የለውም። ተከሳሽ በጽሁፍ በሰጠው ማስጠንቀቅያ ከሳሽን ያሳወቀው በመሆኑ ለንብረቱ መጥፊትና መበላሸት ሃለፉነት የለበትም።
ተከሳሽ ንብረቶቹን ለማፍረስ ለተጠቀመው የሰው ሀይል ወጪ ታሳቢ ሳይደረግ የትኞቹ ንብረቶች መመለስ እንዲለባቸው ሳይለይ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ባለመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ ) አቶ ደባልቄ ደምሴ በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ በፉንፉኔ ዙርያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍ/ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ተከሳሽ የሱለልታ ከተማ አስተዲደር የከሳሽ ጋራዥ የሆነውን በሱለልታ ከተማ ቀበላ 01 ውስጥ የሚገኝ ስፊቱ 1500 ካ/ሜ በካርታ ቁጥር 05-ስ-01/90 አዋሳኙን ጠቅሶ የካቲት 7/2001 ዓ.ም.
ስላፈረሰብኝ በሁከት ከስሼ ሁከት የለም ተብል ቢወሰንም አፍርሶ የወሰደብኝን ንብረት ግምት ለመጠየቅ ስለምችል ግርግዲው በቆርቆሮ እና በእንጨት የተሰራ 2 ቤቶች፣ የተከልኳቸው ባህር ዛፍች፣ 120 ቢያጆ ድንጋይ፣ በቆርቆሮ የተሰራ አጥር፣ የአየር ኮምፕሬሰር ከነ ዕቃው፣ አንድ የብረት መበየጃ፣ አንድ ግራይንደር፣ ትራንስፍርመር ጨምሮ የተለያዩ መፍቻዎች ሁለት የብረት ሳጥኖች በአጠቃላይ ብር 1,330,100 እንዱከፍለኝ ሲል ከሷል። ተከሳሽም በሰጠው መልስ ከሳሽ በተጠቀሰው መሬት ላይ ለ3 ዓመት ከ1990 ዓ.ም.
እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ ለመጠቀም ከተከሳሸ ላይ በሉዝ ውል ወስድ እያለ ለ7 ዓመት ለመልቀቅ ፍቃደኛ ስላልሆነ በአዋጅ ቁጥር 272/94 አንቀጽ 25(5 እና 6) እና አንቀጽ 16(1እና2) እንዱሁም በሉዝ አዋጅ ቀጥር 721/2004 አንቀጽ 25(5 እና 8 ) መሰረት ንብረቱን የማንሳት ስልጣን ስላለን ቦታውን ለህዝብ አገልግልት እንዱውል ማድረጋችን ህጋዊ በመሆኑ ከሳሽ የጠየቀውን ንብረት ግምት የመክፈል ግዳታ የለብንም። ሃላፉነት አለባቸው ቢባል እንኳ ከመሬቱ ላይ የተወረሰው ንብረት ከጭቃ እና እንጨት የተሰራ 2 ቤት እና 2 ቢያጆ ድንጋይ በአጠቃላይ ብር የማይበልጥ ሆኖ ሳለ በከሳሽ የቀረበው ግምት የተጋነነ በመሆኑ ውድቅ ይሁንልኝ ብሎል። በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ ፉንፉኔ ዙርያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ. አከራክሮ ነሐሴ 15/2005 ዓ.ም.
በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ ከሳሽ ለክርክር ምክንያት የሆነው መሬት ከ1990 ዓ.ም.
እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ ተከራይቶ የክራዩ ዘመን ያበቃ ቢሆንም ለ7 ዓመት ይዞ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ተከሳሽ ከመሬቱ ላይ ንብረቱን ስላነሳ በሁከት ከሶት ሁከት የለም ተብል ተወስኗል። በሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 25(5) መሰረት የኪራይ ውል ከተጠናቀቀ በኋላ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካላነሳ የሚመለከተው አካል መሬቱን በላዩ ላይ ካለው ንብረት ጋር ካለክፍያ መውሰድ እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 25(6) በመደንገጉ የከሳሽ የሉዝ ውል ኪራይ በ1993 ዓ.ም. ካለቀ በኋላ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን አንስቶ መሬቱን ማስረከብ ሲገባው እስከ 7 ዓመት ይዞ በመቆየቱ ተከሳሽ ያለ አንዲች ክፍያ ንብረቱን አንስቶ መሬቱን መውሰድ ስለሚችል ተከሳሽ ለተጠየቀው ክፍያ ሃላፉነት የለበትም ሲል ክሱን ውድቅ አድርጎታል። ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርበው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ታህሳስ 1/2006 ዓ.ም. በዋለው ችልት በሰጠው ትዕዛዝ ለቀረበው የይግባኝ ቅሬታ የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ጉድለት ያለበት ሆኖ አልተገኘም ሲል በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ውድቅ አድርጎታል። የአሁን ተጠሪ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርቦ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. አከራክሮ መስከረም 19/2007 በዋለው ችልት በሰጠው ውሳኔ ከሳሽ ከ1990 ዓ.ም. እስከ 1993 ዓ.ም. በሉዝ ኪራይ የያዘውን መሬት ጊዜው ተጠናቆ የውለ ዘመን የሚታደስ ካልሆነ ንብረቱን አንስቶ ይዞታውን ለተከሳሽ መመለስ እንደሚገባው አያከራክርም። ከሳሽ ውለ ሳይታደስ እስከ 2001 ዓ.ም. ድረስ መቆየቱ ታውቋል ተከሳሽ ታህሳስ 3/2001 ዓ.ም. እስከ የካቲት 26/2001 ዓ.ም. ድረስ ለከሳሽ የማስጠንቀቅያ ደብዲቤ መፃፈ ተረጋግጧል። በአዋጅ ቁጥር 272/94 አንቀጽ 15(5) እና 16(1 እና 2) እንዱሁም በመሬት ሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 25 (5 እና 6) ከመሬቱ ላይ የነበረውን ንብረት ከሳሽ ለማንሳት ፍቃደኛ ባለመሆኑና ተከሳሽ በማንሳቱ ካሳ ለመክፈል የሚገደድ አይደለም። ይሁንና ተከሳሽ በመሬቱ ላይ የነበረውን ንብረት ለመውሰድ የሚፈቅድለት ህግ ባለመኖሩ የወሰደውን ንብረት ለአመልካች መመለስ አለበት ሲል የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አሻሽል ተከሳሽ የወሰደውን ንብረት ይመልስ በማለት ወስኗል።
የአሁን አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርበዋል። መዝገቡ ተመርምሮ አመልካች ለተጠሪ በኪራይ የሰጠውን ቦታ የኪራይ ዘመኑ ካለቀ በኋላ ተጠሪ መሬቱን ለአመልካች ለመመለስ ፉቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ አመልካች በቦታው ላይ የነበረውን ቤት አፍርሶ መውሰደ አያስጠይቀውም በማለት በክልለ የስር ፍ/ቤቶች የተሰጡትን ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ሽሮ አመልካች የወሰደውን ንብረት ይመልስ በማለት የሰጠውን ውሳኔ ከአዋጅ ቁጥር 272/1994 አንቀጽ 25(5) ድንጋጌ አንጻር ለማጣራት ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ ሚያዚያ 15/2007 ዓ.ም.
በተጻፈ መልስ የአመልካች አቤቱታ በተሻረ አዋጅ ቁጥር 272/94 ን በመጥቀስ ከአዋጅ ቁጥር 721/2004 ጋር በመጻረር የቀረበ በመሆኑ ውድቅ ይሁንልኝ። አመልካች ከአዋጁ ድንጋጌ ውጪ ንብረቴን የወሰደብኝ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት ይህንኑ በመጥቀስ የሰጠው ውሳኔ ተገቢና ቅር የማያሰኝ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ሆኖ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ ይጽናልኝ ሲል ተከራክሯል። አመልካችም ግንቦት 9/2007 ዓ.ም. በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
በዚሁ መሰረት ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መዝገቡን እንደመረመርነው፡ የአሁን ተጠሪ የ3 ዓመት የሉዝ ኪራይ ውል ማብቃቱ እና በቦታው ላይ ያከናወነውን ግንባታ በህግ በተቀመጠው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያላነሳና ከዚያም በላይ እስከ 7 ዓመት የቆየ መሆኑ ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ይህ ሲሆን ደግሞ የአሁን አመልካች በአዋጅ ቁጥር 721/2004 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቦታውን ከነንብረቱ ያለምንም ክፍያ ሉወስድ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 25(6) ስር ተደንግጓል። የአሁን ተጠሪ በአዋጁ አንቀጽ 25(5) መሰረት ቦታውን የሉዝ ጊዜው እንዲለቀ በአንድ ዓመት ውስጥ ንብረቱን አንስቶ ቦታውን ለሚመለከተው አካል ያላስረከበ መሆኑ በመረጋገጡ አመልካች በቦታው ላይ የነበሩትን ግንባታ አፍርሶ መውሰደ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 25(6) መሰረት ሃላፉነት የሚያስከትልበት አይደለም። በአዋጁ ቁ. 721/2004 አንቀጽ 25(5 እና 6) መሰረት ተጠሪ በሉዝ የያዘውን መሬት ጊዜው አልቆና ባለመታደሱ በቦታው ላይ ያሰፈረውን ንብረት አንስቶ ቦታውን ለሚመለከተው አካል ባለማስረከቡ አመልካች በቦታው ላይ የሰፈረውን ንብረት አንስቶ መውሰድ ይችላል በማለት ደንግጓል። ይሁንና በቦታው ላይ የሰፈረ ንብረት ሲባል ግን ቦታውን ለተፈለገው ሥራ ጉዲይ እንዲያስቸግሩ ምቹ ለማድረግ በቦታው ላይ የተሰሩ ግንባታዎችንና ከዚሁ ጋር የሚያያዙ የመሳሰለትን ንብረቶች ለማንሳት እንጂ በቀላለ የሚነሱ የሥራ መገልገያዎችን ጨምሮ የሚወረስ መሆኑን አያመለክትም።
በመሆኑም የአሁን አመልካች በቦታው ላይ በተጠሪ የተገነቡ ግንባታዎች ቤቶች፣ ድንጋዮች፣ ባህር ዛፍች እና አጥር አንስቶ መውሰደ በአዋጁ መሰረት ሃላፉነት ያለበት አይደለም። ከዚህ ውጪ ያለትን ግን ተጠሪ በአመልካች ተወስደውብኛል ሲል የከሰሰውና አመልካቸ በመልሱ መውሰደን ያላመነውን የሥራ መገልገያ ንብረቶችን በተመለከተ ለመውረስ በአዋጁ የሚሸፈን ባለመሆኑ ተጣርቶ ለተጠሪ ሉመለስ የሚገባ ነው። የስር የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ የአሁን አመልካች ንብረቱን ከቦታው ላይ ማንሳቱ ተገቢነቱን ተቀብል ንብረቱን ግን ለመውረስ የሚፈቅድለት ህግ የለም የወሰደውን ንብረት ይመልስ ሲል መወሰኑ በአዋጁ በግልጽ ተቀምጦ ባለና የሚመለሱ ንብረቶችንም ሳይለይ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ሉታረም የሚገባ ነው። በአዋጅ ቁ. 721/2004 አንቀጽ 25(6) አመልካች ከቦታው ላይ የሰፈሩ ንብረቶችን አንስቶ መውሰድ እንደሚችል ደንግጎ እያለ ተጠሪ ተወስደውብኛል ሲል የከሰሰውና የአሁን አመልካችም ወስጃለሁ ያላላቸውን ንብረት በማስረጃ ሳይጣራና ሣይለይ በደፈናው አመልካች የወሰደውን ንብረት ይመልስ ብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ቁ. 193036 መስከረም 19/2007 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ. ቁ. 170402 ታህሳስ 1/2006 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ፣ በፉንፉኔ ዙርያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ. ቁ. 09981 ነሐሴ 13/2005 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ ፉንፉኔ ዙርያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች(ተከሳሽ) ተወስደውብኛል ሲል በክሱ እንዱመለሱለት ከጠየቀው ንብረቶች ውስጥ ቤቶቹን፣ ድንጋዮች፣ ባህርዛፍች እና አጥርን ሳይጨምር የተጠሪ ስራ መገልገያ ንብረቶች የማይወረሱ ያልናቸው እንደ የአየር ኮምፕሬሰር፣ የብረት መበየጃ፣ ግራይንደር ትራንስፍርመርን ጨምሮ፣ የተለያዩ መፍቻዎች እና የብረት ሳጥኖች ያላቸውን እና በአመልካች መወሰዲቸው ያልታመኑ በመሆኑ በአመልካች መወሰድ አለመወሰዲቸው በማስረጃ በማጣራት ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 343(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ መዝገብ ወጪና ኪሳራ ተቻቻለ ብለናል።
ለኦ/ብ/ክ/መ/ ፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በዚህ ውሳኔ መሰረት እንዱከወን የዚህ ውሳኔ ቅጂ ይድረሰው ለላልች የስር ፍ/ቤቶች ደግሞ እንዱያውቁት ይድረሳቸው።
No topics extracted.