ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው አካል ፈቃድ ሳያገኝ በህጋዊነት ከያዘው ይዞታ ጎን ያለን የከተማ ቦታ አስፊፍቶ መከለልና መጠቀም የማይቻል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 5(2)
No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዲ 03 የግንባታ ፈቃድ ቁጥጥር ጽ/ቤት - አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ ሲሳይ ተስፊዬ -አልቀረበም መዝገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 7/11/06 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ላይ ያቀረቡትን ይግባኝ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 7/02/07 እንዱሁም የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ሰበር ችልት በመ/ በቀን 02/06/07 ዓ.ም በማጽናታቸው መሰረታዊ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን አይቶ ውሳኔ የሰጠው የአሁን ተጠሪ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዲ 3 ክልል ውስጥ ከሚገኘው የቤት ቁጥር 1/17 የሆነ ቤታቸው ጋር በተያያዘ ከጏረቤት ጋር የወሰን ምልክት ይሆን ዘንድ አጥር ያጠሩበት ይዞታ መኖሩን በይዞታው ላይ ለ10 ዓመት ግብር የገበሩበት መሆኑን፣ አጥሩ በሉዝ ወደ ህጋዊ ይዞታቸው እንዱጠቃለል አመልካችን ጠይቀው ተከሳሽም ካርታ እንዱዘጋጅ በ7/10/2001 ዓ.ም የተጻፈ ደብዲቤ ለክ/ከተማ ፅፍ የነበረ ቢሆንም በ2004 ዓ.ም ካወጣው የሉዝ አዋጅ ሥርዓት ጋር በተገናኘ ጥያቄው መቆሙን፣ ይህ በእንዱሀ እንዲለ የአሁን አመልካች በ20/02/2006 በተፃፈ ደብዲቤ አጥሩ በ3 ቀን እንዱፈርስ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሁከት የፈጠረብኝ በመሆኑ ሁከት እንዱነሳ ይወሰንልኝ በማለት በ20/03/2006 ዓ.ም ያቀረቡትን ክስ መነሻ በማድረግ ነው።
የአሁን አመልካች በሰጠው መልስ ክርክር ያስነሳው አጥር ተጠሪ አስፊፍተው የያዙት ትርፍ ቦታ ላይ የሚገኝ መሆኑን፣ አጥሩን ለመስራት የግንባታ ፈቃድ አለማውጣታቸውን ማስጠንቀቂያው የተጣለብኝን ኃላፉነት የምወጣበት እንጂ ሁከት አለመሆኑን በመገለጽ ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ማስረጃዎችን ከመረመረ በኋላ ከክ/ከተማው የመጡት ምላሾች የአሁን ተጠሪ ያጠሩት ቦታ መንገድ መሆኑንና መንገድ ሆኖ አጏራባቾች ሲገለገለበት ቆይተው በመሀል የተጠሪ መሆኑን የሚያስረደ አይደለም። መንገድ በከሳሽ ይዞታ ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም የአሁን አመልካች በልላ አካሄድ መጠየቅ ከሚችል በቀር በማስጠንቀቂያ መጠየቅ አይችልም።
የከተማ ልማት ጥናቱ /LDP/ ወደ ተግባር ያልተሸጋገረ በመሆኑ እሱን መሰረት በማድረግ ለባለይዞታው ሳይነግሩ ይዞታው እንዱፈርስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ይህም ሁከት በመሆኑ ይወገድ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ይህንኑ ውሳኔ የከተማዋ አስተደደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመደበኛ ይግባኝ እና በሰበር ችልት ተመልክቶ አፅንቶታል።
ይህ የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ሲሆን የአቤቱታው ይዘትም ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤት መመስረት የነበረበትን ጭብጥ ሳይመሰርት፣ የአሁን ተጠሪ በግልፅ አከራካሪው ይዞታ ወደ ይዞታቸው እንዱጠቃለልላቸው የጠየቁ መሆኑን በማለፊ ከከተማው የአስተዲደር አካላት የመጣውን ምላሽ ያለአግባብ በመረዲት፣ በአሁን አመልካች የቀረቡትን ምስክሮች ሳይሰማ በዝምታ በማለፊ፣ በስራ ላይ የዋለውን የኤልዱ.ፒ ጥናት ስራ ላይ ያልዋለ ነው በማለት የመንግስት መሬት አያያዝ አዋጅና መመሪያዎችን ሳይመረምር ወደ ጏን በመተው የአሁን አመልካች ህጏችን ለማስከበር የሰጠውን ግዳታ የሁከት ተግባር ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ እንዱታረም የጠየቁ መሆኑን ያሳያል።
ተጠሪም የአመልካች የሰበር አቤቱታ ደርሷቸው በሰጡት መልስ ክርክር ባስነሳው ይዞታ መሬት ይዞታን አስመልክቶ በወጡ ህጏች መብት ያገኙ መሆናቸውን የስር ፍ/ቤት ከከተማው አስተዲደር አካላት የመጡትን ምላሾች በትክክል ተረድቶ የተገበረ መሆኑንና የኤል.ዱ ፒ ጥናት ከ20 ዓመት በፉት ለተገነባ አጥር ተመልሶ ተግባራዊ መሆን የላለበት መሆኑን በመግለፅ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት በመሆኑ ፀንቶ አመልካች የተጠሪን ወጪና ኪሳራ እንዱሸፍን ይታዘዝልን በማለት ተከራክረዋል። አመልካቹም የመልስ መልስ አቅርቦ ክርክሩን አጠናክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል። እንደመረመረውም በዚህ ችልት ዕልባት ማግኘት ያለበት የአሁን አመልካች ድርጊት የሁከት ተግባር ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው።
በመሰረቱ አንድ ሁከት ተፈጥሮብኛል ይወገድልኝ የሚል ተከራካሪ ወገን ሁከት ተፈጠረበት በተባለው ንብረት ላይ የተሻለ መብት ያለው መሆኑን የመለየት ግዳታ ያለበት መሆኑን ከፍ/ህ/ቁ 1149 ድንጋጌ መረዲት እንችላለን።
በዚህ በያዝነው ጉዲይ ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ አከራካሪ የሆነው አጥር የሚገኝበት ቦታ በሉዝ ሥሪት መሰረትም ወደ ይዞታቸው እንዱገባላቸው የጠየቁ መሆኑን፣ ቦታውን አጥር በማጠር የያዙት በራሳቸው የወሰን ምልክት ይሆነኛል በማለት እንደሆነ ነው።
በመሰረቱ ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው አካል ፈቃድ ሳያገኝ በህጋዊነት ከያዘው ይዞታ ጏን ያለን የከተማ ቦታ አስፊፍቶ መከለልና መጠቀምም ሆነ በሉዝ አዋጁ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ የከተማ ቦታ መያዝ እንደማይችል የሉዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 5/2/ እና /4/ ተቀምጧል።
የአሁን ተጠሪ አከራካሪ የሆነውን ቦታ በሉዝ ወደ ይዞታቸው ለመቀላቀል አቅርበውት የነበረው ጥያቄም ተቀባይነት አግኝቶ ያልተፈፀመ መሆኑን ገልፀው ቦታውን የያዝኩት ከሉዝ አዋጁ መውጣት በፉት ሲሆን ነባር ይዞታን ወደ ሉዝ ስሪት በመቀየር ከቀድሞ ይዞታቸው ጋር እንዱካተትላቸው እየጠየቁ በሂደት ላይ ያለ ሁኔታ መኖሩን፣ የክርክሩ ሂደት ያሳያል።
የሚመለከታቸው የከተማዋ አስተዲደር አካላትም የሰጡት መልስ እንደሚያስረዲው በተጠሪ ካርታ ላይ በተጠናው የኤል.ዱ.ፒ ጥናት መሰረት በቦታው ላይ መንገድ ያለ መሆኑን ይገልጻል።
የከተማ ቦታ አሰጣጥ ስርዓት ደግሞ የህዝቡንና የከተሞችን ጥቅም በቀዲሚነት በማስከበር የከተማ ልማትን በማፊጠንና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የዜጏችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የሀገሪቱን ልማት ቀጣይነት የሚያረጋጋጥ መሆን እንዲለበት የሉዝ አዋጁ አንቀጽ 4/4/ ይደነግጋል። በመሆኑም ተጠሪ በቦታው ላይ የሉዝ ጥያቄ አቅርቤ በመጠየቅ ላይ እገኛለሁ ቢለ እንኳን ቦታው የከተማዋ ልማት እንቅስቃሴ አካል የሆነው መንገድ የሚሰራበት መሆኑን መሰረት በማድረግ አመልካች ለተጠሪ አጥሩን እንዱያፈርሱ የሰጠው ትዕዛዝ በህግ የተጣለበትን ኃላፉነት ለመወጣት የወሰደው እርምጃ ሆኖ እያለ በስር ፍ/ቤቶች ተጠሪ አጥሩን እንዱያነሱ የፃፈው ደብዲቤ የአመልካችን ድርጊት የሁከት ተግባር ነው ያለው ያለአግባብ ስለሆነ ውሳኔውን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህ መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 7/11/06 ዓ.ም ተሰጥቶ በከተማዋ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ በቀን 7/02/07 ዓ.ም እና በከተማዋ አስተዲደር ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 02/06/07 ዓ.ም ያፀናው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ከህጋዊ ይዞታ ውጭ ያለፈቃድ ያጠረውን አጥር እንዱያነሳ አመልካች የፃፈው ደብዲቤ የሁከት ተግባር አይደለም።
ግራ ቀኙ በዚህ ፍ/ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.