በመንግስት የተወረሰን ቤት የባለቤትነት መብት ከላለው ሰው/አካል/ መግዛት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በቅን ልቦና ባለሀብትነትን የሚያጎናጽፍ ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 47/67 X ከገነባ ወይም የጋራ ሕንጻ ቤት ከገዛ ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲን ቤት ካገኘ ወይም በልላ በማናቸውም ምክንያት ቤቱን የለቀቁ ከሆነ ቤቱን ባለበት ሁኔታ ለአስተዲደሩ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑ፣ የአ.አ.ከ.አስተዲደር ባወጣው የመንግስት ቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁ. 3/2007 አንቀጽ 42/ሀ እና በጉ/ክ/ከ/ወ/7/ኮ/ቤ/አ/ል/ፅ/ቤ ት
No summary available.
ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም ዳኞች፡- ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡- ወ/ሮ ትሁኔ አዲነ ጠበቃ አቶ ሙለጌታ ደላ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- በጉለላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 7 ኮንስትራክሽንና ቤቶች አስተዲደር ልማት ፅ/ቤት መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው የአሁን አመልካች አ/አ/መጀ/ደ/ፍ/ቤት ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ሲሆን የክሱ ይዘት ጉለላ ክ/ከ/ወረዲ 7 ቤ.ቁ 673 በሆነው የመንግስት መኖሪያ ቤት ውስጥ ከሟች ባለቤቴ አቶ አረጋ ካሳ ጋር ስንኖርበት ነበር። ባለቤቴ በሞት የተለየኝ በመሆኑ ተከሳሽ የቤቱን ኪራይ ውል ሉያዛውርልኝ ሲገባ ፈቃደኛ ባለመሆን ቤቱን ለቃችሁ እንድታስረክቡኝ በማለት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶኛል ተከሳሽ የቤቱን ኪራይ ውል በስሜ እንዱያዋውለኝ የተሰጠኝ ማስጠንቀቂያም ይነሳልኝ የሚል ነው።፡ ተከሳሽ ለክሱ በሰጠው መልስ በመጀ/ደ/መቃወሚያ ከሳሽ ክስ በቀረበበት ቤት ላይ መብት የላትም ክስ ማቅረብ አትችልም የሚል እና በፍሬ ጉዲይ መልሱ የከሳሽ ባለቤት የቤ.ቁ 734 የሆነ ሕጋዊ የግል መኖሪያ ቤታቸውን በግልፅ ኑዛዜ ከእነ ሙለ ዕቃው የወረሷቸው በመሆኑ በመመሪያ ቁ.
3/07 መሰረት የመንግስት ቤት ከሳሽ ማስረከብ አለባቸው በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱ መቃወሚያውን በብይን በማለፈ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃን መርምሮ ከሳሽ ከላልች ወራሾች ጋር በጋራ የወረሱት የግል ቤት እንዲላቸው የቀረበው ማስረጃ ያረጋግጣል። በመመሪያ ቁ. 3/07 የግል ቤት ያለው ግለሰብ በመንግስት መኖሪያ ቤት ላይ የኪራይ ውል ለመዋዋል አይቻልም በማለት ደንግጓል። የቀረበውን ክስ አልተቀበልነውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ከሳሽ በዚህ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ለአ/አ/ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አቅርበው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት የስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ የፀና ሲሆን ከሳሽ ለሰበር ሰሚው ችልትም አቅርበው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቷል። የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የስር አቤቱታው ተመርምሮ አመልካች ከሟች ባለቤታቸው ጋር የመንግስት ቤ.ቁ 763 ተከራይተው ሲኖሩ በባለቤታቸው ሞት ምክንያት የግል ቤት ቁ. 734 ላይ ከላልች ወራሾች ጋር የኑዛዜ ወራሽ በመሆን ተጠቃሹን የመንግስት ቤት ሉለቁ ይገባል ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥና ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እና አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ አቤቱታው እንዱመረመር ከተያዘው ጭብጥ አንፃር የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምረናል።
በመሰረቱ የመንግስት መኖሪያ ቤት ለኪራይ የሚገባው የመኖሪያ ቤት ለላላቸው ነዋሪዎች ነው።
ማንኛውም የቀበላ መኖሪያ ቤት የተከራየ ሰው የራሱ ቤት ከገነባ ወይም የጋራ ሕንፃ ቤት ከገዙ ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ቤት ካገኘ ወይም በልላ በማናቸውም ምክንያት ቤቱን የለቀቁ ከሆነ ቤቱን ባለበት ሁኔታ ለአስተዲደሩ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑ የአ/አ/ከተማ አስተዲደር በወጣው የመንግስት ቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁ. 3/2007 አንቀፅ 42/ሀ/ ተመልክቷል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ለክርክር ምክንያት በሆነው መኖሪያ ቤት አመልካች ከባለቤታቸው ጋር ሲኖሩበት የነበረ መሆኑ አልተካደም አመልካች ከላልች ወራሾች ጋር በጋራ ሟች ባለቤታቸው ባደረጉት ኑዛዜ የግል ቤት የወረሱ መሆኑ ስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ተመልክቷል።
አመልካች በክሱ መሰማት ወቅት ባለቤታቸው ቁጥሩ 734 የሆነ የግል ቤታቸውን የራሱን ድርሻ ከላልች 4 ልጆች ጋር እንዱወርሱ እንደተናዘዙላቸው ያመኑ መሆኑ ስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ተመልክቷል። በሰበር አቤቱታቸውም ሟች ባደረጉት ኑዛዜ የራሳቸውን ግማሽ ድርሻ አመልካች ከአራት ወራሾች ጋር በመሆን 1/5 ኛ ለአመልካች እንዱሰጥ የተናዘዙ መሆኑን እና የሟች የውርስ ንብረት ተጣርቶ ድርሻዬ አልተለየም። የውርስ ድርሻ አለኝ ማለት ለመኖር የሚያስችለኝ ቤት አለኝ ማለት አይደለም። በኑዛዜው መሰረት ገንዘብ ወይም ቤት ይድረሰኝ አልታወቀም በማለት የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ የአመልካች ባለቤት በኑዛዜ የራሳቸውን ድርሻ እና ሙለ የቤት ዕቃ በቀጥታ ሰጥተዋቸዋል። ቤቱ ከ10 በላይ ሰርቪስ ቤት ያለው 720 ካ.ሜ ነው ለአራት ሰዎች የተላለፈ በመሆኑ አመልካች ከዚህ የመኖሪያ ቤት አይደርሳቸውም ብል ማለት የሚቻል አይደለም ስር ፍ/ቤት ይህን በማጣራት ወስኗል። በማለት ተከራክሯል።
በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ አመልካች ከላልች ወራሾች ጋር በኑዛዜ የወረሱትን ቤት ይዘት እና ከዚህ ቤት ለአመልካች ለመኖሪያ የሚሆን ቤት የሚደርሳቸው ስለመሆኑ መጣራቱን ውሳኔው አያመለከትም። የአመልካች ባለቤት ባደረጉት ኑዛዜ አመልካች ከላልች 4 ወራሾች ጋር የቤ.ቁ 734 የሆነውን የግል መኖሪያ ቤት በጋራ እንዱወርሱ ያለ ቢሆንም ቤቱ ለወራሾች በዓይነት ተካፍል ለአመልካች ለመኖሪያ የሚሆን ቤት በክፍፍለ ሉደርሳቸው የሚችል መሆን አለመሆኑን ስር ፍ/ቤት ሳያጣራ አመልካች ከላልች ወራሾች ጋር የግል ቤት በኑዛዜ አግኝተዋል በሚል ብቻ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን መመሪያ ቁ. 3/2007 ዓላማና መንፈስ የተከተለ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ፈፅሟል። ሰለሆነም ተከታዩን ወስነናል።
የአ/አ/ከ/አስ/መጀ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 10/03/08 በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ፣ የአ/አ/ከ/አ/ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 1/4/08 እና ሰበር ሰሚ ችልቱ በመ/ በቀን 20/5/08 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአ/አ/ከ/አስ/መጀ/ደ/ፍ/ቤት የተዘጋውን መ/ቁ. 04308 የሆነውን መዝገብ በማንቀሳቀስ የአመልካች ባለቤት የነበሩት ሟች አቶ አረጋ ካሳ ቤ.ቁ 734 ላይ ባደረጉት ኑዛዜ መሰረት በኑዛዜ ወራሾች መካከል ክፍፍል ቢደረግ ለአመልካች መኖሪያ ቤት የሚደርሳቸው መሆን አለመሆኑን ተገቢውን ማጣራት በማድረግ እንዱወሰን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1/ መሰረት ጉዲዩን ወደ ስር ፍ/ቤት መልሰናል።
የሰበር ክርክሩ ላስከተለው ወጭ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ። ብለናል። መዝገቡ ተዘጋ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.