በመንግስት የተወረሰን ቤት የባለቤትነት መብት ከላለው ሰው/አካል/ መግዛት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በቅን ልቦና ባለሀብትነትን የሚያጎናጽፍ ስላለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 47/67 X ከገነባ ወይም የጋራ ሕንጻ ቤት ከገዛ ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲን ቤት ካገኘ ወይም በልላ በማናቸውም ምክንያት ቤቱን የለቀቁ ከሆነ ቤቱን ባለበት ሁኔታ ለአስተዲደሩ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑ፣ የአ.አ.ከ.አስተዲደር ባወጣው የመንግስት ቤቶች አስተዲደር መመሪያ ቁ. 3/2007 አንቀጽ 42/ሀ እና በጉ/ክ/ከ/ወ/7/ኮ/ቤ/አ/ል/ፅ/ቤ ት
No summary available.
መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ ፈይሳ ወርቁ አመልካች፡-- አይከል ከተማ አገልግልት ፅ/ቤት ዐ/ህ ዮሃኒስ ተገኘ ቀርበዋል ተጠሪ፡ -ሼክ ሸምሱ መሀመድ ተ/ይ አሚናት ሸምሱ ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ የሰበር አቤቱታ መዝገብ ክርክር አመልካች አይከል ከተማ አገልግልት ጽ/ቤት የካቲት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. በተጻፈ አቤቱታ የአማራ ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.
ታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በዋለው ችልት በሰጠው ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት የቀረበ ሲሆን ቅሬታውም የሥር ፍ/ቤት የማይንቀሳቀስ ንብረት በቅን ልቦና ባለሀብትነት ሉገኝ የማይችል ሆኖ እያለ የአይከል ከተማ አገልግልት ጽ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተወረሰ ቤት በተመለከተ የመወሰን ስልጣን የላለው ሆኖ እያለ የተወረሰን ቤት መብትና ጥቅም የላለው አካል መሸጥ የማይችል በመሆኑ የስር ፍ/ቤት የቤት ቁጥር 140 የተወረሰ መሆኑን አረጋግጦ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ ) በቅን ልቦና ገዝተውታል ሲል የሰጠው ውሳኔ ስህተት በመሆኑ፣ ያከራከረውን ቤት ከ36 ዓመት በላይ ቀበላው ሲያስተዲድር የቆየ ሆኖ እያለ ከሳሽ ገዛሁት የሚለትን ቤት ካርታና ፕላን ያላወጡበትና ገዛሁ ካለት ከ1983 ዓ.ም.
ጀምሮ ቀበላው እንዱያስረክባቸው ጠይቀው በማያውቁበት ሁኔታ በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ስህተት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው።
በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ሼክ ሸምሱ መሀመድ በአማራ ብ/ክ/መ/ ጭልጋ ወረዲ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ ተከሳሽ እሙሃይ ማናለብሽ ጌታሁን ከሳሽ በአይከል 01 በካርታ -92316 የሚታወቅ አዋሳኙን በመጥቀስ 4 ክፍል ቤት ያላቸው ሲሆን ተከሳሽ ባልታወቀ ምክንያት ቤቱ ውስጥ ገብተው የሚኖሩበት ሲሆን ጉዲዩ ለአይከል ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቤትና ቦታ አስለቃቂ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቀርቦ ጉባኤው በቁጥር ደስ/26/2001 በቀን 27-5-2001 ዓ.ም. በተጻፈ ውሳኔ ቤቱ የተወሰነልኝ ቢሆንም ተከሳሽ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ቤቱን ይልቀቁልኝ ሲለ ከሰዋል። ተከሳሽም በሰጡት መልስ ቤቱን ለ35 ዓመት ያህል ለቀበላ ኪራይ እየከፈልኩበት የኖርኩበት በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል። ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተወረሰ በቅጽ ተሞልቶ ከቀበላ ተከራይቼ ለ35 ዓመት የኖርኩበት በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይሁንልኝ ብለዋል። ጣልቃ ገቢ የአይከል ከተማ አገልግልት ጽ/ቤት ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር በአ/ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተወስኖ በመመለሱ ጣልቃ ገብቶ የሰጠው መልስ ከሳሽ ከ1988 ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም.ከፍያለሁ የሚለት ግብር በ2003 ዓ.ም.የከፈለትና ከመመርያ ቁጥር 4/2000 ጋር የሚጻረር ነው። ከሳሽ በዚህ ግብር ብቻ የቤቱ ባለቤት ላሆን አይችልም። ቤቱ ከአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለተከሳሽ የተከራየና ተከሳሽ ከ1968 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1983 ኪራይ ከፍለው የአይከል አውራጃ አስተዲደር በጻፈው ደብዲቤ ተከሳሽ የኪራይ ክፍያ አቋርጠዋል። ቤቱ የከሳሽ ባለመሆኑ ክሱ ውድቅ ይሁንልኝ ብለዋል።
በአማራ ብ/ክ/መ/ ጭልጋ ወረዲ ፍ/ቤት በመ. አከራክሮ ሐምል 16 ቀን 2005 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ ካሁን በፉት በዚህ ጉዲይ ውሳኔ ተሰጥቶ የሰሜን ጎንደር መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ሽሮ ጉዲዩን ከአዋጅ ቁጥር 47/67 ከቅጽ 001፣004 እና 003 ታይቶ ውሳኔ እንዱሰጥ በመለሰው መሰረት አይተነዋል።ከሳሽ ያቀረቧቸው የተለያዩ የአስተዲደር ክፍል ሀላፉዎች የጻፎቸው የሰነድ ማስረጃዎችና የግብር ካሪኒዎች ይህ ክርክር የተነሳበት ቤት በመንግስት ያልተወረስና የከሳሽ ህጋዊ ቦታ እና ቤት መሆኑን እጅግ ሚዛን በደፊ ከፍ ባለ ሁኔታ ያስረዲ በመሆኑ ተከሳሽ ቤቱን ለከሳሽ ይልቀቁለት ሲል ወስኗል።
ጣልቃ ገብ የአይከል ከተማ አገልግልት ጽ/ቤት ለሰሜን ጎንደር መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ የሰሜን ጎንደር መስተዲድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ቁጥር 01-17437 አከራክሮ ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ ከሳሽ የገዙት ቤት አራት ክፍል ሲሆን የተገዛው ቤት ለወፍጮ ቤት የሚውል ነበረ።
የጎንደር አስተዲደር አካባቢ ኢንደስትሪና እደጥበብ ለአይከል ልዩ ከፍተኛ አንድ ጽ/ቤት በጻፈው ደብዲቤ ቤቱ በባንክ ዕዲ ታግድ የነበረና ቤቱ ተሸጦ ከባንክ ዕዲ ነጻ መሆናቸውን ገልጾ የጻፈው ደብዲቤ ማዘጋጃ ቤቱም ሽያጩን በማይንቀሳቀስ ንብረት ማስተላለፍያ ሰነድ ቅጽ 13(1) መዝግቧል። የቦታ እና የይዞታ የምስክር ወረቀት 8991 መዝገብ የያዘው መሆኑ የሚያስረዲ 1 ገጽ ጽሁፍ ቀርቧል። ከሳሽ የተወረሰ ቤት መሆኑን ሳያውቁ ከአራቱ ክፍል አንድ ክፍል ቤት በቅን ልቦና የተወረሰ መሆኑን ሳያውቁ የገዙት መሆኑን ያስገነዝባል። ከሳሽ የአራቱም ቤቶች ባለሀብት እንደሆነ የሚገመትና ይህን ግምት ሉያስተባብል የሚችል ነገር የላለ መሆኑን አረጋግጠናል። ከሳሽ ያከራከረውን አንድ ክፍል ቤት የቅን ልቦና ባለሀብት ሉሆኑ እንደሚገባ የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንተነዋል ሲል ወስኗል። ጣልቃ ገብ (የአሁን አመልካች) ለአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበው የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ ለቀረበው አቤቱታ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አላገኘንበትም አቤቱታውን አያስቀርብም ሲል ውድቅ አድርጎታል።
የአሁን አመልካች በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ቀርበዋል። መዝገቡ ተመርምሮ አመልካች ለክርክር መነሻ የሆነው ቤት ከ36 ዓመት በላይ እያስተዲደረው እንዲለ በተረጋገጠበት ቤቱ ለተጠሪ በላልች ግለሰቦች የተሸጠ ነው ተብል እንዱያስረክብ የመወሰኑን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ቀርቧል። መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል። ተጠሪ ሐምል 28 ቀን 2007 ዓ.ም.በጻፈ መልስ ያከራከረውን ቤት ጥር 3 ቀን 1983 ዓ.ም. 4 ደጃፍ ቤት በሽያጭ ውል ህጋዊነቱ ተረጋግጦ ስመ ንብረቱ ወደ ተጠሪ እንዱዛወር ተወስኖ በአይከል ከተማ ማ/ቤት በኩል ተላልፍልኛል። በአመልካች በኩል የቀረቡት ሰነድች አከራካሪ የሆነው የወፍጮ ድርጅት 1 ክፍል ቤት በአመልካች ይዞታ ስር ሆኖ ለ36 ዓመት በይዞታው አድርጎ እያከራየው የነበረ ስለመሆኑ ሰነድቹ በእርግጠኝነት ስለማያስረደ የበታች ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ስህተት ያለበት ባለመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ይሁንልኝ ሲለ ተከራክረዋል። አመልካችም ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
በዚሁ መሰረት ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መዝገቡን እንደመረመርነው፡ በከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ክስ የቀረበበት ያከራከረው ቤት የስር ፍ/ቤት ተከሳሽ እሙሃይ ማናለብሽ ጌታሁን ከቀበላ መስተዲድር ተከራይተው ከ1968 ዓ.ም. ጀምሮ ሲኖሩበት እንደነበር፣ ቤቱ በቀበላ መስተዲድር ስር ሆኖ የቀበላው መስተዲድር ሲያስተዲድረው የነበረ መሆኑ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠና የተወረሰ ቤት ስለመሆኑ በሥር የአማራ ብ/ክ/መ. ሰሜን ጎንደር መስተዲድር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት አረጋግጦ የአሁን ተጠሪ ቤቱን የገዛው የተወረሰ መሆኑን ሳያውቅ በመሆኑ በቅን ልቦና የቤቱ ባለሀብት ይሆናል በሚል የወሰነ ሲሆን የአሁን ተጠሪ ያከራከረው ቤት ባለሀብት ነኝ ብለው የሚከራከሩት ደግሞ በግዥ ተላልፍልኛል በማለት ነው። ቤቱን ለአሁን ተጠሪ የሸጠለት አካል የቤቱ ባለሀብት አለመሆናቸውና የተወረሰ ቤት መሆኑ፣ ቤቱ በቀበላው መስተዲድር ስር ገብቶ ቀበላው ማስተዲደር ከጀመረና ለስር ተከሳሽ እሙሃይ ማንአለብሽ ጌታሁን ከተከራየ በኋላ የተመለሰለት ስለመሆኑ የሚያሳይ ነገር የላለና የአሁን ተጠሪም ለሸጡለት ግለሰብ ከተመለሰ በኋላ የገዛሁት ነው ብል አይከራከርም። በመሆኑም ያከራከረውን ቤት የሸጠው ሰው የራሱ ያልሆነውን እና የባለቤትነት መብት ሳይኖረው የተወረሰ ቤት ሸጦ ተጠሪም በመንግስት የተወረሰ ቤት ገዝቶት የቤቱ ባለቤት የሚሆንበት የህግ ምክንያት የለም። ተጠሪ ቤቱ መወረሱን ሳያውቅ በቅን ልቦና ንብረቱ ካልሆነው ሰው ላይ ገዝቶም ከሆነ ካለአግባብ የሸጡለትን ሰዎች ከመጠየቅ ውጪ በመንግስት የተወረሰ ቤት መሆኑን ሳያውቅ መግዛቱ የቤቱ ባለቤት የሚያደርገው አይደለም። በመሆኑም የአሁን ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰ ቤት መብቱ ከላለውና ባለቤት ካልሆነው ሰው ገዝቻለሁ በማለት ቤቱ እንዱለቀቅለት ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የላለውና የስር ፍ/ቤትም በመንግስት የተወረሰ ቤት መሆኑን መብቱ ከላለው ግለሰብ ላይ የአሁን ተጠሪ የገዛ መሆኑ አረጋግጠው እያለ በቅን ልቦና ባለቤት የሚሆንበት የህግ መሰረት ሳይኖር የአሁን ተጠሪ ያከራከረው ቤት ባለቤት ስለሆነ ይለቀቅለት ብለው መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው።
የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ቁ. 41846 ታህሳስ 7/2007 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ፣ የሰሜን ጎንደር መስተዲድር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ. ቁ. 01-17437 ግንቦት 18/2006 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔና የአ/ብ/ክ/መ. ጭልጋ ወረዲ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 02912 ሐምል 11/2005 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሸሯል። የአሁን ተጠሪ ክስ ውድቅ በማድረግ ወስነናል።
በዚህ መዝገብ ወጪና ኪሳራ ተቻቻለ ብለናል።
የዚህ ውሳኔ ቅጂ ለስር ፍ/ቤቶች እንዱያውቁት ይድረሳቸው።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.