ተተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤት የሚከራከሩበትን ጉዲይ በእርቅ መጨረስ የሚችለና የእርቅ ውለን ጉዲዩን ለሚያየው ፍርድ ቤት አቅርበው ማፀደቅ እንደሚችለ ፍርድ ቤት ቀርቦ የፀደቀ የእርቅ ውል ሥምምነት በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ያህል አስገዲጅነትና ተፈፃሚነት ያለው ከመሆኑ ባሻገር በዚህ እርቅ ውል ተካፊይ ያልሆነ መብቴ ተነክቷል የሚል ወገን የፍርድ መቃወሚያ ሉያቀርብ የሚችል ሥለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.276፣277(1) እና 358
No summary available.
ቀን 22/06/2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተፈሪ ገብሩ ቀነዓ ቂጣታ አይሸሹም መለሰ ፀሃይ መንክር አመልካችዎች፡- 1. ሀጅ ቢያ አባመጫ 2. አቶ ከሉፊ አባ ቆያስ ጠበቃ ከድር መሐመድ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካችዎች ከሁለተኛ ተጠሪ ጋር የእርቅ ሥምምነት በማድረግ በፍርድ ቤት እንዱመዘገብና እንዱፀድቅ ካደረጉ በኃላ አንደኛ ተጠሪ ያቀረበውን የፍርድ መቃወሚያ በመቀበል የእርቅ ውለ ፈራሽ ነው በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ውሳኔ የሰጠው በህግ አግባብ ነው ወይስ አይደለም ?የሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው ጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
አመልካችዎችና ሁለተኛው ተጠሪ በፈረንጅ ፅድ ሽያጭ ውል በተመለከተ ባለመስማማታቸው አመልካቾች ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። አመልካቾች ከሳሽ፣ሁለተኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመከራከር ላይ እያለ ጥር 5 ቀን 2001ዓ.ም ባደረጉት ዕርቅ ውል አመልካችዎች 1,200,000 /አንድ ሚሉዮን ሁለት መቶ ሺ ብር) ለሁለተኛ ተጠሪ ሉከፍለ ሁለተኛ ተጠሪም የክርክሩ መነሻ የሆነውን የፈረንጅ ፅድ ለአመልካችዎች ሉያስረክቡ ሥምምነት ላይ ደርሰዋል።
አመልካችዎችና ሁለተኛ ተጠሪ የዕርቅ ሥምምነታቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዲር 25 ቀን 2002ዓ.ም በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 277(1) መሰረት የዕርቅ ውላቸውን በመቀበል ግራቀኝ በዕርቅ ውለ መሰረት እንደፈፅሙ ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቶታል ።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲያቸውን በዕርቅ ያዘጉት አመልካችዎችና ሁለተኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ አንደኛ ተጠሪ ፍርደን ለመቃወም የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ የዕርቅ ስምምነቱ የፍርድ መቃወሚያ አመልካችን መብት የሚነካ በመሆኑ የዕርቅ ውለ ፈራሽ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የፍርድ መቃወሚያ አቅርበው የዕርቅ ስምምነት በተደረገበት የፈረንጅ ፅድ ላይ መብት የላለው መሆኑ በወቅቱ በተያዘው ቃለጉባኤ የተረጋገጠ ስለሆነ ፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዕርቅ ውለ ፈራሽ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ አይደለም በማለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ በመሻር ውሣኔ ሰጥቷል። አንደኛ ተጠሪ ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን በመቃወም የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችልት አቅርቧል ። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የዕርቅ ውል የተደረገበት የፈረንጅ ፅድ የመንግስት ደን በመሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዕርቅ ውለ ፈራሽ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካችዎች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ እኛ የገዛነው የመንግስት ደን ሣይሆን የሁለተኛ ተጠሪ ንብረት የሆነ የፈረንጅ ፅድ ነው። አንደኛ ተጠሪ ከሻጭ ጋር ያለንን ልዩነት በዕርቅ ጨርሰን የዕርቅ ውለ በፍርድ ቤት ከፀደቀ በኃላ ማስረጃ እንዱፃፍ በማድረግ የዕርቅ ውለ እንዱፈርስ ማድረጉ የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በሰበር ታይቶ እንደታረምልኝ በማለት አመልክተዋል ። 2ኛ ተጠሪ በበኩለ ንብረቴን ነው የሸጥኩት ከአመልካችዎች ጋር የዕርቅ ውል የፈፀምኩት በንብረቴ ላይ በመሆኑ የሁለተኛ ተጠሪ የፍርድ መቃወሚያ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት የአመልካችዎችን የሰበር አቤቱታ በመደገፍ መልስ ሰጥቷል ። አንደኛ ተጠሪ ግራቀኙ ዕርቅ የፈፀሙበት የመንግስት ደን በመሆኑ የአመልካችዎች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል ። አመልካችዎች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል ። ጉዲዩን እንደመረመርነው ሁለት ተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤት የሚከራከሩበትን ጉዲይ በዕርቅ መጨረስ እንደሚችለና የእርቅ ውለን ጉዲዩን ለሚያየው ፍርድ ቤት አቅርበው ማፅደቅ እንደሚችለ ፍርድ ቤት ቀርቦ የፀደቀ የዕርቅ ውል ሥምምነት በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሣኔ ያህል አስገዲጅነትና ተፈፃሚነት ያለው መሆኑን ከፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀፅ 276 እና አንቀፅ 277(1) ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል።
አመልካችዎችና ሁለተኛው ተጠሪ የፈረንጅ ፅድ ሽያጭ ውል በተመለከተ ጥር 5 ቀን 2001ዓ.ም ያደረጉትና ለጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 277(1) መሰረት ያፀደቁት የዕርቅ ውል የፍርድ ያህል አስገዲጅነትና ተፈፃሚነት ያለው በመሆኑ በዚህ ዕርቅ ውል ተካፊይ ያልሆነ መብቴ ተነክቷል የሚለው አንደኛ ተጠሪ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዕርቅ ውለን በማፅደቅ የሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወም በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 358 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት ፤የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ማቅረቡና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአንደኛ ተጠሪን የፍርድ መቃወሚያና ማመልከቻን ማስረጃ በመቀበል የዕርቅ ውለ የመንግስት ደን የሚያስተዲድረውን የአንደኛ ተጠሪን መብትና ጥቅም የሚነካ በመሆኑ ፈራሽ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሥነ ሥርዓት ሕግ ግድፈት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም ።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አንደኛ ተጠሪ የፍርድ መቃወሚያ ለማቅረብ መሰረትና ማስረጃ የሆነውንና አመልካችዎች ከሁለተኛው ተጠሪ ጋር የዕርቅ ሥምምነት የፈፀሙበት የፈረንጅ ፅድ ጫካ የመንግስት ደን መሆኑን የሚያረጋግጠውን የቴክኒክ ኮሚቴ ሪፓርትና ማስረጃ ያለበቂ ምክንያት ውድቅ በማድረግ አከራካሪው የፈረንጅ ፅድ ዛፍ ጫካ በጨረታ ለአመልካችዎች ከመሸጡ በፉት የተያዘውን ቃለ ጉባኤ ነው መያዝ ያለበት በማለት አከራካሪው የፅድ ዛፍ የሁለተኛ ተጠሪ ሀብት ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ የማስረጃ አመዛዘን መርህን ያልተከተለና መሰረታዊ የማስረጃ ህግ ድንጋጌዎችን የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 250 እና የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 136(1) ያልተከተለና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆኑን በመገንዘብ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም ። በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካችዎች እና አንደኛ ተጠሪ የዕርቅ ሥምምነት ያደረጉት የአንደኛ ተጠሪ መብትና ጥቅም ባለበት የመንግስት ደን ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቀርቦለት እያለ አንደኛ ተጠሪ የዕርቅ ሥምምነቱን መቃወምና ፈራሽ ለማስደረግ የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት የለውም በማለት የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ መጋቢት 14 ቀን 2007ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻቻለ ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.