ማናቸውም ተከራካሪ ወገን በመከላከያ መልሱ ወይም በማናቸውም ላላ መንገድ የተከሰሰበትን ነገር በሙለ ወይም በከፉል የሚያምን መሆኑን የገለጸ እንደሆነ ወይም በሚደረግ ምርመራ የእምነት ቃለን የሰጠ እንደሆነ ፍ/ቤቱ የዲንግላ ወረዲ ውሃ ሀብት ልማት ጽ/ቤት እና አቶ ሙለጌታ ገበየሁ IX ነገር ላይ ብቻ ፍርድ መሰጠት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 83 ፣234/1/ /ሰ/ ፣ 241 እና 242
No summary available.
ህዲር 29 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሀመድ ተኸሉትይመስል ቀነዓ ቀጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- የዲንግላ ወረዲ ውሃ ሃብት ልማት ፅ/ቤት ወኪል የፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ህግ አልቀረበም።
ተጠሪ፡- አቶ ሙለጌታ ገበየሁ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጠ
ጉዲዩ የግንባታ ሥራ ውል የሚመለከት ሲሆን የአሁን ተጠሪ የሥር ከሳሽ ሲሆን በአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ ፅ/ቤት ላይ ለአዊ ብሓረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ተከሳሽ ፅ/ቤት ባለ አራት መቀመጫ ሽታ አልባ መፀዲጃ ቤት ለመስራት ባወጣው ጨረታ ተወዲድሬ በማሸነፍ ተከሳሽ ጋር በገባው ውል መሰረት አምስት ሳይቶችን ሰርቼ በማስረከብ ክፍያ እንዱፈፅሙልኝ ብጠይቅና በፅ/ቤቱ መሀንዱስ ቢታዘዝም የአራት ሳይት ክፍያ ከፍለውኝ የአምስተኛውን ሳይት /የኳንች ኳኩርታን/ ሣይት ብር 68,776.71/ስልሳ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ብር ከሰባ አንድ ሣንቲም/ ያልከፍለኝ ስለሆነ ይህንኑ ክፍያ እንዱከፍለኝ ይኸው ክፍያ በመሀንዱስ ከታዘዘበት ቀን ጀምሮ 379 ቀን ስለሆነ የብር 68,776.71 / ስልሣ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ስደስት ከ ሰባ አንድ ሣንቲም/1% x379 ቀን =ብር 260,663.93/ሁለት መቶ ስልሳ ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ሶስት ብር ከዘጠና ሦስት ሣንቲም/ መቀጫ ግንባታውን አጠናቅቄ ካስረከብኩኝ አንድ ዓመት ስለሞላ ለዋስትና የተያዘ ብር 3,725.38/ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ አምስት ብር ከሰላሳ ስምንት ሣንቲም/ የዲኝነት የጠበቃ አበል 10% እና ኪሣራ እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተከሳሽ ፅ/ቤትም በወኪለ አማካኝነት የመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያ ቢያቀርብም የታለፈበት ሲሆን በአማራጭ ባቀረበው መልስ ከሳሽ በውለ እና በተሰጣቸው የመሀንዱስ የስራ ዝርዝር መሰረት ግንባታውን ሰርተው ያስረከቡና በፅ/ቤት መሀንዱስ ሂሳቡ በትክክል ተሰርቶ በመስሪያ ቤቱ ፀድቆ ለወረዲው ፊ/ኢ/ል/ማ/ ፅ/ቤት ክፍያ እንዱፈፀም በደብዲቤ ብጠይቅም ክፍያ ሉፈፀም አልቻለም እንጂ ተከሳሽ ጽ/ቤት ክፍያ አልከለከላቸውም ካለ በኋላ መልሴን ላሻሸል ብል አሻሽል የሰጠው መልስ ከሳሽ በውለ መሰረት ሽንት ቤቶቹ ሰርተው አስከርበው ክፍያ ያልወሰደ ቢሆንም ክፍያ ያልወሰደት ከሳሽ ከውል ዉጪ በተቆጣጣሪው መሀንዱስ ትእዛዝ የብር 17,358.46 /አስራ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሃምሣ ስምንት ከ አርባ ስድስት ሣንቲም/ሰርቻለሁ እና ይህንን ሂሳብ ካልረከፈለኝ ላላውን አልበቀልም በማለታቸው ነው። የተጨማሪ ሥራ ክፍያ የሚፈፀመው ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤቱ በግዢ አፈፃፀም መመሪያው ተጨማሪ ስራውን ሲያውቀው ነው።
ባላወቀው ስራ ክፍያ ሉጠይቅ አይገባም። ለዋስትና ጉዲይ የተያዘውን ገንዘብ አልተከለከለም ስለሆነም የወሰደት ገንዘብ ተቀንሶ ቀሪ ካላቸው እንዱወስደ ይወሰንልኝ ብሎል።
ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ካዲመጠ በኋላ በግራ ቀኙ ክርክር የሚጠነጥነውን ለተጨማሪ ሥራ ክፍያ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ በግራ ቀኙ ውል ገጽ 3 ተራ ቁጥር 5/3/ ሥር እንደተመለከተው በተመደበ ተቆጣጣሪ ወይም አማካሪ መሀንዱስ ሲደገፍ ተጨማሪ ሥራ ሉሰራ እንደሚችልና ተጨማሪ ክፍያ ሉፈፀም እንደሚገባ ተደንግጓል። በዚህም መሰረት ስራው ተሰርቶ መረከቡን ተከሳሽ ፅ/ቤት አምኗል ስለሆነም ለተጨማሪ ሥራ ክፍያ አልፈፅምም መባለ አይደለም።
በልላ በኩል ክፍያ ለዘገየበት መቀጫን በተመለከተ ፅ/ቤት ክፍያው እንዱፈፀምለት ለፊይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ያስተላለፈ ቢሆንም ክፍያውን ፈፃሚው ፅ/ቤት ከተሰራው ስራ ላይ በላይ ከውል ውጪ የሚታየውን ብር 17,358.46/አስራ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሃምሣ ስምንት ብር ከ አርባ ስድስት ሣንቲም/በስተቀር ላልች ክፍያዎችን አልቀበልም ያለት ከሳሽ መሆናቸው ሲገልፅ ከሳሽ እነዚህ ክፍያዎች በተከሳሽ ፅ/ቤት ምክንያት የዘገዩ ስለመሆናቸው አላስረደም በማለት ከሳሽ የጠየቁትን ክፍያ ለዘገየበት ለ379 ቀን 1 ፏርሰንት ብር 260,663.93/ሁለት መቶ ስልሣ ሺህ ስድስት መቶ ስልሣ ሦሰት ከ ዘጠና ሦስት ሣንቲም/ መቀጫ ተከሳሽ ፅ/ቤት ሉከፍል አይገባም በማለት የተቀሩትን ዋናውን ገንዘብ ብር 68,776.71/ስልሳ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከሰባአንድ ሣንቲም/ ለዋስትና የተያዘ ብር 3,725.38/ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ አምስት ብር ከሰላሳ ስምንት ሣንቲም/ በጠቅላላው ብር 72,502.09/ሰባ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሁለት ብር ከ ዜሮ ዘጠኝ ሣንቲም/ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ዲኝነት እና የጠበቃ አበል10% ተከሳሽ ለከሳሽ ሉከፍል ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የአሁን ተጠሪ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የይግባኝ ቅሬታቸውን ያቀረቡ ሲሆን የቅሬታው ይዘትም በአጭሩ ክፍያ ለዘገየበት ለ379 ቀን መቀጮ ሉከፍል አይገባም ተብል መወሰኑ ተገቢ አይደለም የሚል ነው። ቅሬታው የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሥራው ተሰርቶ የተጠናቀቀ መሆኑንና ክፍያው ያለመፈፀሙ በተከሳሽ የታመነ ጉዲይ ነው ስለሆነም የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ከሳሽ ባቀቡት ክስ መሰረት አላስረደም ማለቱ ተገቢ አይደለም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህግ ቁ. 348/1/ መሰረት ውሣኔውን በመሻር ክፍያ ለዘገየበት ብር 260,663.73 /ሁለት መቶ ስልሣ ሺህ ስድሰት መቶ ስልሣ ሦስት ብር ከ ሰባ ሦስት ሣንቲም /ተከሳሽ ጽ/ቤት ሉከፍል ይገባል በማለት ሲወሰን በአሁን አመልካች በበኩል የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቅሬታው ተጠሪን አያስቀርብም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.337 መሰረት አቤቱታውን ሰርዞታል።
ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታውን ያቀረበው አመልካች ፅ/ቤት ሲሆን አቤቱታው ክፍያ አዘግይተናል ብለን በእምነት የሰጠነው ቃል የለም። ከተጨማሪ ሥራ በስተቀር የተቀሩትን አልወስድም ያለት ተጠሪ ናቸው ስለሆነም ክፍያው ለዘገየበት ልንከፍል አይገባም፤ ክፍያ ለዘገየበት የምንከፍል ቢሆን እንኳን ክፍያ የዘገየበት የገንዘብ መጠን 1 ፏርሰንት ሳይሆን 0.1 ፏርሰንት ከመሆኑም በተጨማሪ በአማራ ክልል የግዢ መመሪያ መሰረት ክፍያው ከዋናዋ ገንዘብ 10% በላይ ላሆን አይገባም የሚል ነው።
አጣሪው ችልትም የቀረበውን አቤቱታና የሥር መዝገብ መርምሮ የመቀጮ ክፍያ ከዋናው ገንዘብ 10%በላይ በስር ፍ/ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ተጠሪ ባለበት ለማጣራት ያመች ዘንድ ተጠሪ ቀርበው መልስ እንዱሰጡ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ተጠሪም በፅሐፍ በሰጡት መልስ የመቀጮ መብዛትንም ይሁን ማነስ የፍሬ ነገር ክርክር ባልሆነበት እና ይህን አስመልክቶ አመልካች ፅ/ቤት ያነሳው መከላከያ ነጥብ በላለበት የሰበር አጣሪው ችልት የያዘው ጭብጥ በሥር ያልተነሳ ክርክር ነውና የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ይፅናልኝ ብለዋል። እኛም የቀረበውን የሰበር አቤቱታ በሥር ፍ/ቤት ከተደረገው ክርክርና ማስረጃ አንፃር የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን ውሣኔ የሰጠው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን ያለመሆኑን ከተገቢው ህግ አንፃር መርምረናል።
እንደመረመርነውም የአሁን ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ፅ/ቤት ላይ ባቀረቡት ክስ ከአመልካች ጋር በነበረን የግንባታ ውል ግንባታውን ከተጨማሪ የመሀንዱስ ትአዛዝ ጋር ሰርቼ ለፅ/ቤቱ ያስረከብኩኝ ቢሆንም አመልካች ፅ/ቤት ክፍያውን አጠናቆ አልከፈለኝምና ያልተከፈለኝ ገንዘብ ከነቅጣቱና ተያያዥ ያላቸውን ክፍያዎች እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ሲሆን፣ የአሁን አመልካች ፅ/ቤት በወኪለ አማካኝነት በሰጠው መልስ ጽህፈት ቤቱ አልከፍልም አላለም የተጨማሪ ስራ ገንዘብ ካልተከፈለ አልቀበልም በማለት ዋናውን ገንዘብ ያልወሰደት ተጠሪ ናቸው ስለሆነም ክፍያ ለዘገየበት ልጠየቅ አይገባም ብለዋል። ምንም እንኳን በሰበር አጣሪው ችልት አቤቱታው ያስቀርባል የተባለበት ምክንያት ክፍያ ለዘገየበት መቀጫ ከዋናው ገንዘብ ከ10%በላይ የመወሰኑን አግባብነት ለማጣራት ቢሆንም ይህ ነጥብ ከታየቱ በፉት ክፍያ ለዘገየበት መቀጮ የአሁን አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ መመርመሩ ተገቢ ሆኖ አግኝተዋል።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 242 ስር እንደተደነገገው ማናቸውም ተከራካሪ ወገን በመከላከያ መልሱ ወይም በማናቸውም ላላ መንገድ የተከሰሰበትን ነገር በሙለ ወይም በከፉል የሚያምን መሆኑን የገለፀው እንደሆነ ወይም በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 241 መሰረት በሚደረግ ምርመራ የእምነት ቃለን የሰጠን እንደሆነ ፍ/ቤቱ በታመነው ነገር ላይ ብቻ ፍርድ መስጠት እንዲለበት ይገልፅና በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 83 እና 234/1/ሰ ሥር እንደተደነገው በግልፅና በዝርዝር ያልተካደ ነገሮች ሁለ እንደታመኑ እንደሚቆጠር ደንግጓል።
በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ከአመልካች ፅ/ቤት በነበረው የግንባታ ውለ ግንባታውን ጨርሼ ያስረከብኩኝ ቢሆንም አመልካች ፅ/ቤት ሉከፍለኝ ከሚገባው ገንዘብ ውስጥ ብር 68,776.71 /ስልሣ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከሰባ አንድ ሳንቲም/ያልከፈለኝ ስለሆነ ይኸው ዋናው ገንዘብና ተያያዠነት ያላቸው ክፍያዎች እንዱከፈለኝ ይወሰንልኝ የሚል ዲኝነት መጠየቃቸውን የአሁኑ አመልካች ጽ/ቤት በግራ ቀኙ መሀከል ውል መኖሩን ተጠሪ በውለ መሰረት ግንባታውን አጠናቀው በተጨማሪም በመሃንዱስ ትአዛዝ ፅ/ቤቱ የማያውቀው የብር 17,358.43 /አስራ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሃምሣ ስምንት ብር ከአርባ ሦስት ሣንቲም/ ተጨማሪ ሥራ መሥራታቸውንና በዚህም ምክንያት አመልካች ጽህፈት ቤት የተጨማሪ ሥራውን ክፍያ አልከፍልም በማለቱ ተጠሪ ሁለንም ክፍያ አልወስድም በማለታቸው ክፍያ መዘግየቱን መልስ በመስጠት መከራከሩን በሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ከተደረገ የግራ ቀኙ ክርክር መረዲት ተችሎል።
በዚህም ክርክር የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ፅ/ቤት በእርግጥም ተጠሪ ዲኝነት የጠየቁበት ገንዘብ ያልተከፈለው መሆኑን አምኗል ነገር ግን ያልተከፈለው በኔ ምክንያት አይደለም እስካለ ድረስ ታምኗል የሚያሰኝ አይደለም፤በተጨማሪም ተጠሪ ክፍያው የዘገየው በአመልካች ምክንያት ስለመሆኑ አላስረደም ስለሆነም ክፍያ ለዘገየበት አመልካች ለተጠሪ ሉከፍል አይገባም በማለት ሲወስን፤ የስር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ጽህፈት ቤት ተጠሪ ስራውን ሰርተው ማስረከባቸውንና ጽ/ቤቱ ክፍያ ያለመፈፀሙን እስካመነ ድረስ ክፍያ የዘገየው በአመልካች ጽ/ቤት ምክንያት መሆኑ ታምኗል በማለት አመልካች ጽ/ቤት ክፍያ ለዘገየበት ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል በማለት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔን በመሻር መወሰኑንና የስር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ይህንኑ የስር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሣኔ በማጽናት መወሰኑ ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ መረዲት ተችሎል።
ነገር ግን ተጠሪ ክፍያ የዘገየው በአመልካች ጽ/ቤት ምክንያት ነው ሲለ አመልካች ጽ/ቤት ክፍያ የዘገየው በተጠሪ ምክነያት ነው እስካለ ድረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.242 መሰረት የታመነ ጉዲይ ነው ወይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.234/1/ ሥር እንደተመለከተው ጉዲዩ በግልፅ ያልተካደ ጉዲይ ነው ልባል የሚቻል አይደለም። በመሆኑም ክፍያ የዘገየው በማን ምክንያት ነው የሚለው ነገር አከራካሪው ነው። በፍትሐብሕር ክርክር አንድ መብት ወይም ግዳታ አለ ብል የሚከራከር ወገን መብቱ ወይም ግዳታው ስለመኖሩ የማስረዲት ሸክም አለበት። የአሁን ተጠሪ ክፍያው የዘገየው በአመልካች ፅ/ቤት ምክንያት መሆኑን ማስረዲት የሚጠበቅባቸው ቢሆንም ያላስረደ መሆኑ ከስር ፍርድ ቤት ክርክር መረዲት ተችሎል።
ከዚህ ሁለ ስንነሳ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ክፍያው የዘገየበት በአመልካች ፅ/ቤት ምክንያት ስለመሆኑ ተጠሪ አላስረዲም በማለት ክፍያ የዘገየበት የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ሲወስን የስር ጠቅላይ ፍ/ቤት ክፍያ የዘገየው አመልካች ጽ/ቤት መሆኑ ታምኗል በሚል የስር ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አንኝተነዋል። በመሆኑም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ውሣኔ
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝገብ ሰኔ 10 ቀን 2006 ዓ.ም ተሰጥቶ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ ጥቅምት 29 ቀን 2007 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በአዊ ብሓረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.07181
No topics extracted.